የግጥም ጥግ

Saturday, 23 March 2024 20:53

ሣቅሽ እንደ ሀገሬው ...

Written by
Rate this item
(2 votes)
ጥርስሽ የሌላ፥ ፈገግታሽም የተረታ፤በሰው ጉዳይ፥ በሰው መቼት‘ሚበረታ።ትብታቡን ሳይበጥስ፥ ያደደሩበትንሳይቆረጥም፤በአሟሟቱ የሚደመም።ሲንዱት እየሣቀ፥ሲያፈርሱት እየሣቀ፤በቀብሩ ላይ የሚታደም።(የአብፀጋ ተመስገን /maddbn/)
Saturday, 23 March 2024 20:51

ናፍቆቴ ዳርቻው

Written by
Rate this item
(0 votes)
ዥው ብዬወደ ታች እምዘገዘጋለሁበሀይልቁልቁል እወርዳለሁእናም ትንፋሽ አጥሮኝመሬት ርቆኝአለቅሁ ተሳቅቄኧረ ናፍቆኛል መውደቄ፡፡****
Saturday, 23 March 2024 20:49

ዱር ሃገሬ

Written by
Rate this item
(1 Vote)
ልቤን ጫካ አደረግሁትልቤን ዱር አደረግሁትይኸው ዛሬስጎበኘው ተዟዙሬሰፍሮበታል የአገር አውሬ፡፡(ዳዊት ጸጋዬ፤ 2016)
Sunday, 28 January 2024 20:22

ዘመናዊ ብልጦች

Written by
Rate this item
(5 votes)
ዘመናዊ ብልጦችታጋይ እንጂ ትግል አይሞትም እያሉታግለው ሲያታግሉፎክረው የማሉ ታጋይ ሲፈነቸርትግሉም ፍግም ሲልይኸው ይኖራሉ።(ሙሉነህ መንግሥቱ)
Sunday, 28 January 2024 20:20

አይን አዋጅ

Written by
Rate this item
(1 Vote)
ወላድ በድባብ ትሂድ እንጂ ቆንጆ ሞልቶ ባሻገር፣እኔ ዓይን አዋጅ ሆኖብኝእስቲ በምርጫ ልቸገር?(መዓዛ ብሩ
Monday, 08 January 2024 19:51

ሠሚ አልባ ጩኸት !

Written by
Rate this item
(10 votes)
እኛ ስንከፋ ፤ምድሩን ቆርቆርአንገት ደፍተን ቆፈር ቆፈር ...ጌቶች ሲከፋቸው ፤እኛን ኮርከም ኮርከምበ፩ ላይ ወግነው ፥ ከፀሀይ ከሀሩሩ ጋር ።አቤት ብንል ለ “ ማ “ ?አካላችን ቀልጦተስፋችን ተውጦ ፤እንባና ደማችን በ፩ ጅረት ሲፈስስባመንነው መዶሻ አናታችን ሲፈርስ ።ይግባኝ ብንል ለ “ ማ…
Page 1 of 30