Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62

ኪነ-ጥበባዊ ዜና

Saturday, 14 April 2012 12:56

የኦፕራ ቲቪ አልተሳካለትም

Written by
Rate this item
(0 votes)
ኦፕራ ዊንፍሬይ “ኦውን ኔትዎርክን ማቋቋም ኪሊማንጃሮን መውጣት ነው” ስትል አማረረች፡፡ ስርጭቱን ከጀመረ 16 ወራት ያስቆጠረው የኦፕራ ቴሌቪዥን ጣቢያ ከጅምሩ ከ200 ሚ.ዶላር በላይ ኪሳራ ማድረሱን አንዳንድ መረጃዎች ይጠቅሳሉ፡፡ ዋናው ችግር በቂ ተመልካች አለማግኘቱ ሲሆን ይህ ሁኔታም ከማስታወቂያ የሚገኘውን ገቢ አሳንሶታል ተብሏል፡፡
Rate this item
(0 votes)
በገነነ ግርማ የተዘጋጁ ግጥሞች እና አጭር ልቦለዶች የተካተቱበት መፅሐፍ ለንባብ በቃ፡፡ በፊት ለፊት በኩል “ፊትለፊት ስንኞች” በሚል ርእስ 58 ግጥሞች በጀርባ በኩል “ስልክሽን ልያዘው? እና ሌሎች” ስድስት ታሪኮች የተካተቱበት መፅሐፍ ዋጋ 29 ብር ነው፡፡ በሌላም በኩል “ማጎርሚሳቢብ” ልቦለድ መፅሐፍ ከትናንት…
Saturday, 14 April 2012 12:53

“ጎተ” 50ኛ ዓመቱን እያከበረ ነው

Written by
Rate this item
(0 votes)
አዲስ አበባ የሚገኘው “ጎተ የጀርመን የባህል ማዕከል የተመሠረተበትን 50ኛ ዓመት በተለያዩ ዝግጅቶች ማክበር ጀመረ፡፡ ረቡዕ ምሽት በተጀመረው የክብረ በአሉ መክፈቻ በብሉናይል ፊልምና ቴሌቪዥን አካዳሚ የተዘጋጀ የ15 ደቂቃ ዶክመንታሪ ፊልም ለእይታ በቅቷል፡፡ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ባህልና ቱሪዝም ሚኒስትር እንዲሁም የጠቅላይ ሚኒስትር መለስ የከፍተኛ…
Rate this item
(0 votes)
በሩስያ ሳይንስ እና ባህል ማእከል በሚደረግ ሳምንታዊ የፊልም ውይይት “ዘመናዊ የፊልም ንቅናቄ” ለውይይት እንደሚቀርብ አላቲኖስ የፊልም ሰሪዎች ማህበር አስታወቀ፡፡ በመጪው ሳምንት ሐሙስ ከቀኑ 11 ሰዓት የሚደረገውን ውይይት በርእሱ የዩኒቨርሲቲ መመረቂያ ፅሑፉን እያዘጋጀ ያለው የፊልም ባለሙያ ምኒሊክ መርእድ እንደሚመራው ማወቅ ተችሏል፡፡…
Rate this item
(0 votes)
በሊባኖስ በደረሰባት ጥቃት ሕይወቷ ላለፈው ኢትዮጵያዊት ዓለም ደቻሳ ቤተሰቦች እና ልጆች መደጎሚያ የሥነፅሑፍ ምሽት መዘጋጀቱን “ደጉ ኢትዮጵያዊ” የበጎ ፈቃደኛ ኢትዮጵያውያን ቡድን እና አሲምባ ኮሙኒኬሽን አስታወቀ፡፡ በመጪው ሐሙስ ከቀኑ 11 ሰዓት በዋቢ ሸበሌ ሆቴል በሚቀርበው ዝግጅት ገጣሚያን ኤፍሬም ስዩም፣ ሰለሞን ሳህለ፣…
Rate this item
(0 votes)
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ትያትር “በኢትዮጵያ ሕዳሴ ሕዝባዊ ንቅናቄ የኪነጥበብ ፌስቲቫል” በሚል ርእስ ዝግጅት እንደሚያቀርብ አስታወቀ፡፡ ዛሬ በሚጀመረው ዝግጅት ከጤና ጥበቃ ሚኒስቴር፣ የሴቶች ሕፃናትና ወጣቶች ሚኒስትር እና ባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር በመተባበር አሰናድተውታል፡፡ ዝግጅቱ እስከ መጪው ሰኞ ሳምንት ለሕዝብ ክፍት ሆኖ ይቆያል፡፡