Administrator

Administrator

የአትላንቲክ የባርነት ንግድ ሰለባ የሆኑትን አፍሪካውያን አባቶችና እናቶች ለማስታወስ የተሰራው "የአንሴስተር ፕሮጀክት" በጋናዊው ቀራጭ ኳሜ አኮቶ-ባምፎ የተዘጋጀ ሕያው የጥበብ ሥራ ነው። "ንኪይንኪይም" የሚለው ስያሜ የተወሰደው "የሕይወት ጉዞ ጠማማ ነው" ከሚል ምሳሌ ሲሆን፣ ሰዎቹ የተገደዱበትን መራራና አስቸጋሪ የሕይወት ጎዳና ያንጸባርቃል።
እያንዳንዳቸው በእጅ የተቀረጹትና የተለያዩ ስሜቶችን የሚያሳዩት እነዚህ ቅርጻ ቅርጾች፣ ባርነት ከመፈጸሙ በፊት የነበረውን ቅጽበት ያስታውሳሉ።
ይህ ታላቅ መታሰቢያ በጋና በሚገኘው የንኪይንኪይም ሙዚየም እና በአሜሪካ አላባማ በሚገኘው የሰላም እና የፍትህ ብሔራዊ መታሰቢያ ውስጥ ይገኛል። ቅርጻ ቅርጾቹ ያለፈውን ታሪክ ከመዘከር ባለፈ፣ የጠፋውን ማንነታችንን መልሰን የማግኘት ተስፋን የሚሰጡ ትልቅ ታሪካዊ እሴት አላቸው።
የቴሌግራም ቻናልችንን በመቀላቀል የአዲስ አድማስን መረጃ ይከታተሉ…

21ኛው የዓለም ከ20 አመት በታች አትሌቲክስ ሻምፒዮና በዛሬው ዕለት በአሜሪካ ኦሪገን መካሄድ ይጀምራል፡፡

በሻምፒዮናው በ46 የውድድር ዘርፎች ከ147 ሀገራት የተወጣጡ 1 ሺህ 800 አትሌቶች እንደሚሳተፉ ተመላክቷል፡፡

ኢትዮጵያ በሻምፒዮናው በ5 ሺህ ሜትር፣ 3ሺህ ሜትር፣ 1 ሺህ 500 ሜትር እና በ800 ሜትር በሁለቱም ፆታዎች ትሳተፋለች፡፡

በተጨማሪም በ3 ሺህ ሜትር መሰናክል እና በ400 ሜትር በሴቶች እንዲሁም በርምጃ ውድድር ደግሞ በሁለቱም ፆታዎች የምትሳተፍ ይሆናል፡፡

ዛሬ በመክፈቻው ዕለት ኢትዮጵያውያን አትሌቶች የፍጻሜ እና የማጣሪያ ውድድራቸውን ያደርጋሉ።

ምሽት 4 ከ 43 ላይ በ800 ሜትር ወንዶች ማጣሪያ ነጋሄ እያሱ እና የሮሳን ግርማ ሲካፈሉ፤ በሴቶች ደግሞ በዚሁ ርቀት ምሽት 5 ከ 35 ሐብታም ገበየሁ እና ደራርቱ ሽብሩ ማጣሪያቸውን ያከናውናሉ።

ሌሊት 11 ከ 53 በሴቶች 5 ሺህ ሜትር የፍጻሜ ውድድር እመቤት ጥላሁን እና አልማዝ ዮሃንስ የመጀመሪያውን ሜዳሊያ ለማሸነፍ ብርቱ ፉክክር እንደሚያደርጉ ይጠበቃል፡፡

ማለዳ 12 ከ 20 በወንዶች 5 ሺህ ሜትር የፍጻሜ ውድድር ደግሞ ማማሩ ጎዴ እና ዳምጠው ከበደ የሚሳተፉ ይሆናል፡፡

ሻምፒዮናው በአሜሪካ ኦሪገን ግዛት ዩጂን ከተማ ሄይዋርድ ፊልድ ከሐምሌ 29 ቀን እስከ ነሀሴ 3 ቀን 2018 ዓ.ም ይካሄዳል።

በብሔራዊ ሎተሪ አስተዳደር በዋና ሥራ አስኪያጅነት እና በሌሎች መሥሪያ ቤቶች ከ40 ዓመታት በላይ በታማኝነት ያገለገሉት ወ/ሮ መዓዛ ቅጣው ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ። ወ/ሮ መዓዛ የብርሃን ኢንሹራንስ አ.ማ. መሥራችና የቀድሞ የቦርድ ሰብሳቢ የነበሩ ሲሆን፣ ለሥራቸው ትልቅ ራዕይ የነበራቸው አርአያ ሴት ነበሩ።
የብርሃን ኢንሹራንስ አመራሮችና ሠራተኞች በሕልፈታቸው የተሰማቸውን ጥልቅ ሐዘን ገልጸዋል። ወ/ሮ መዓዛ ኩባንያው ለዛሬው ስኬት እንዲበቃ ሌት ተቀን በትጋት በመሥራት፣ መልካም ውሳኔዎችን በማሳለፍና ትልቅ አሻራ በማሳረፍ የማይተካ ድርሻ እንደነበራቸው ተመላክቷል።
ከሥር ከላይ በስተግራ የምታየው ፎቶ 1 የታሪካዊዉ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ትያትር ሕንፃ አሁናዊ ገጽታ ነው ቢባል ማን ያምናል? የሕንፃውን የጥበብ ማዕከልነት ያውጁ የነበሩ እነዚያ ቀለሞች ዛሬ የሉም፤ በግራጫ ቀለም ቁጥጥር ሥር ውለው ደብዛቸው ጠፍቷል።
እናም ቀደም ሲል ማንነቱን በሩቁ ያውጅ የነበረው ይህ ታሪካዊ ሕንፃ ዛሬ አፍሮና ተሸማቅቆ ራሱን በአካባቢው ባሉ ሕንፃዎች ውስጥ ለመደበቅ የሚጥር ይመስላል፤ The historial Ethiopian National Theatre building has totally blended with the surrounding context in the name of homogenization project! ሌላው ቢቀር ቀለሞቹን መልሷቸው። ፈቃደኜነቱ ካለ፣ የቀለሞቹን ሙሉ ወጪና የሠራተኛ ሂሳብ ድርጅታችን ኒታ ከለር ሰንተር ይሸፍናል።
በነገራችን ላይ አርክቴክቱ ሄንሪ ሾሜት የቀለሞቹን ሕብር ያለምክንያት አላስቀመጣቸውም። የቀለማቱ ሕብር ከሥነ ውበታዊ ዓላማ ይልቅ ለ"Functionalism" የቀረቡ ናቸው፤ Just to say that the colors are functional colors!!! እናም በየትኛውም መልኩ ግራጫ ቀለም የጥበብ ማዕከል መገለጫ አይሆንም።
የቴሌግራም ቻናልችንን በመቀላቀል የአዲስ አድማስን መረጃ ይከታተሉ…
በካናዳ ቫንኩቨር የሚኖረው ኢትዮጵያዊ-ካናዳዊ አርቲስት ያሬድ ንጉሱ፤ የካናዳ የስፖርት አፈ ታሪክ የሆነውን ሃሪ ጄሮምን የሚዘክር "Mighty Jerome" የተሰኘ ግዙፍ የሥነ-ጥበብ ሥራ በሰሜን ቫንኩቨር አዲሱ የህብረተሰብ ማዕከል መግቢያ ላይ በቋሚነት አስመረቀ።
ከዚህ ቀደም የቫንኩቨር የሆኪ ቡድን ማልያን በግዕዝ ቁጥሮች በማስዋብ ታዋቂነትን ያተረፈው ያሬድ፣ ይህ አዲስ የህዝብ ጥበብ ፕሮጀክት መመረጡ በካናዳ ያለውን ከፍተኛ ሙያዊ ክብር እና ተዓማኒነት በድጋሚ አሳይቷል።
በ1964 የቶኪዮ ኦሎምፒክ የነሐስ ሜዳሊያ አሸናፊውንና ከከባድ ጉዳት በጽናት ተመልሶ ለወጣቶች ልማት የሠራውን ሃሪ ጄሮምን የሚዘክረው ይህ ሥራ፤ ለኢትዮጵያውያን ካናዳውያን ትልቅ የኩራት ምንጭ ነው። በሺዎች የሚቆጠሩ ጎብኚዎች በሚጎበኙበት ማዕከል ላይ የሚቀመጠው ይህ ሥራ፣ በካናዳ የብዝሃነት፣ የእኩልነት እና የባህል ተሳትፎ ዋጋን በግልጽ የሚያሳይ ታላቅ ምልክት ሆኗል።
የቴሌግራም ቻናልችንን በመቀላቀል የአዲስ አድማስን መረጃ ይከታተሉ…

በ“እናርጅና እናውጋ” መጽሐፉ የሚታወቀውና በ2016 ዓ.ም በክብር አዋርድ “የዓመቱ ምርጥ የግጥም መጽሐፍ” አሸናፊ የነበረው ጌራወርቅ ጥላዬ፣ “የቃል ሊቀ መኳስ” የተሰኘ አዲስ መጽሐፉን ከሕትመት አውጥቷል። 128 ገጾች ያሉትና በ300 ብር የጀርባ ዋጋ በ1,000 ኮፒ ታትሞ የወጣው ይህ መጽሐፍ፣ ለአንባቢያን ይፋ የሚሆንበት ትክክለኛ ቀን ግን ገና አልተወሰነም።

ደራሲው ከመጽሐፍት በተጨማሪ በሙዚቃ ግጥም ድርሰት የሚታወቅ ሲሆን፣ ለአብነትም በአፍሪማ አዋርድ እጩ የነበረውንና በዩጋንዳ በተካሄደው አይኮኒክ አዋርድ “የዓመቱ ምርጥ ዘፈን” ተብሎ የተሸለመውን የሃሌሉያ ተ/ጻዲቅን “የልቤ ቁምነገር” የተሰኘ ተወዳጅ ዘፈን የደረሰው እሱ ነው። ጌራወርቅ ከዚህ ቀደም “ሙሉ አካል ትዝታ” በሚል ርዕስ ልቦለድ መጽሐፍ እንደሚያሳትም መናገሩም ይታወሳል።

ወጣት ሰሎሞን አማረ (በማርኬቲንግ ማኔጅመንት የተመረቀ) አዲስ አበባ ውስጥ የሚያበራራትን ሜትር ታክሲ ወደ "ተንቀሳቃሽ ቤተ-መጽሐፍት" በመቀየር አዲስ ፈጠራን አስተዋውቋል።

  •  ወጣቱ ከስልክና ማህበራዊ ሚዲያ ሱስ ተላቆ ወደ ንባብ ባህል እንዲመለስ ማስቻል፤ የትራፊክ መጨናነቅን ለንባብ አጋጣሚ መጠቀም።

  •  ተሳፋሪዎች በጉዞ ወቅት መጽሐፍትን ያነባሉ፤ ከተመቻቸውም እዚያው ገዝተው ይሄዳሉ።

  •  ከትራንስፖርት አገልግሎት ጎን ለጎን መጽሐፍትን በመሸጥ ድርብ ገቢ ያገኛል፤ በቲክቶክ (Sol Books) ገጹም መጽሐፍትን ያሰተዋውቃል።

  •  ሌሎች የትራንስፖርት አቅራቢዎችም ይህን አርአያነት ያለው ተግባር በመከተል ታክሲዎችን የዕውቀት ማዕከል እንዲያደርጉ ጥሪ ያቀርባል።

የቀድሞው የአርሰናል አሰልጣኝ እና የአሁኑ የፊፋ የዓለም አቀፍ የእግር ኳስ ልማት ኃላፊ አርሴን ቬንገር፣ በፊፋ ፕሬዝዳንት ጂያኒ ኢንፋንቲኖ ቀርቦ ሳይሳካ በቀረው የ'ፊፋ ፉትቦል ኢንተርቴይመንት' (FFE) ስትራቴጂክ ዕቅድ ውስጥ ምንም ዓይነት ተሳትፎ እንዳልነበራቸው አስታወቁ። ቬንገር ስለ ዕቅዱ ለመጀመሪያ ጊዜ የሰሙት ከመገናኛ ብዙኃን እንደነበር ገልጸው፣ አከራካሪው ዕቅድ እንዲሰረዝ የተደረገው ውሳኔም እጅግ አስፈላጊ እና ትክክለኛ እርምጃ መሆኑን አረጋግጠዋል።

በፊፋ ውስጥ ያላቸው በኃላፊነት የሚያከናውኑት ሥራ በጨዋታ መረጃዎች ትንተና፣ በዓለም ዙሪያ በሚገኙ 60 አካዳሚዎች እና በወጣቶች ስልጠና ላይ ብቻ ያተኮረ መሆኑን የገለጹት ቬንገር፣ በተጨማሪም ለIFAB በቴክኒክ አማካሪነት እያገለገሉ ይገኛሉ። አክለውም ፊፋ በገለልተኝነት፣ በግልጽነት እና በታማኝነት ማገልገል እንዳለበት በመግለጽ፣ የእሳቸው ትኩረት አሁንም እግር ኳስን በዓለም አቀፍ ደረጃ ለማሳደግ በሚደረገው ሙያዊ ጉዞ ላይ ብቻ መሆኑን አብራርተዋል።

የቀድሞው የኢዜማ አባል እና ፖለቲከኛ አቶ አበበ አካሉ በፌደራል ፖሊሶች ተይዘው ሜክሲኮ በሚገኘው የፌዴራል ፖሊስ ግቢ እንደሚገኙ ቤተሰቦቻቸው እና የአይን እማኞች አረጋገጡ።
በወቅታዊ ጉዳዮች ትንታኔዎችና በፓርቲ ፖለቲካ እንቅስቃሴያቸው የሚታወቁት አቶ አበበ በምን ምክንያት እንደተያዙ እስካሁን በይፋ የታወቀ ነገር የለም።
የቴሌግራም ቻናልችንን በመቀላቀል የአዲስ አድማስን መረጃ ይከታተሉ…
ሩሲያ "አቫታር 001" የተሰኘ እና በልዩ የምህንድስና አወቃቀሩ የተነሳ "የማይሰጥም" መሆኑ የተነገረለትን አዲስ የባሕር ላይ ድሮን ይፋ አደረገች። በቮልጎግራድ በሀገር ውስጥ ክፍሎች የተመረተው ይህ ዘመናዊ ቴክኖሎጂ፤ እስከ 30 ኪሎ ሜትር የርቀት መቆጣጠሪያ ክልል፣ የ8 ሠዓታት የባትሪ ቆይታ እና እስከ 500 ኪሎ ግራም የጭነት የመሸከም አቅም እንዳለው ተገልጿል።
የአኳ-ቮልጋ ማምረቻ ተቋም ሥራ አስኪያጅ ዲሚትሪ ኮዝሎቭ እንደገለጹት፣ ድሮኑ የባሕር ገጽታ ቅኝት፣ የባሕር ላይ ጥበቃ እና የቁሳቁስ ማጓጓዝን ጨምሮ በርካታ ወሳኝ ተግባራትን የማከናወን አቅም አለው። 90 በመቶ ያህሉ በሀገር ውስጥ ግብአቶች የተመረተው ይህ ፈጠራ በዓለም አቀፍ መድረክ ከፍተኛ መነቃቃትን እየፈጠረ ይገኛል።
Page 2 of 817