Administrator

Administrator

በርካታ ቅን ሰዎች አሉ። መርዳትን፣ መደገፍን፣ ቸርነትን ማዕከል ያደረጉ። ሁለንተናዊ በሆነ መልኩ የሚሳካላቸው ግን ጥቂት ናቸው፡፡
ከ79 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ሰዎች የስራ እድል መፍጠር። በሚሊየኖች የሚቆጠሩ ዜጎችን በቅንነት ማገልገልን ማዕከል ያደረጉ ድርጅቶችን ማቋቋም፣ መምራትና ስኬታማ ማድረግ ብዙዎች የሚታደሉት ጸጋ አይደለም።
የማይናወጥ የሀገር ፍቅር፣ ሰጥቶ የማይረካ ቅን መንፈስ፣ ስለህዝብ በጽናትና ያለመታከት መቆርቆርን እውን ለማድረግ፤ መቻል ብቻ ሳይሆን ሆኖ መገኘትን ይጠይቃል።
ክቡር ዶ/ር ሼህ ሙሐመድ ሁሴን ዓሊ አልአሙዲ በጣም ጥቂት ከሚባሉ የዚህ አይነት ሰብእና ከተጎናጸፉ ሰዎች መካከል አንዱ ናቸው። ማድረግን ስለሚችሉት ብቻ ሳይሆን ከልብ በመነጨ እምነትና ጽናት ማድረግን ሆነው መገኘት ችለዋል።
"ሚድሮኮች" የተጣለባችሁን አደራ በብቃትና በስኬት ተወጥታችሁ በሚቀጥለው ዓመት የሰራተኞችን ቀን ክቡር ዶ/ር ሼህ ሙሐመድ ሁሴን ዓሊ አልአሙዲ በተገኙበት በድምቀት እንደምታከብሩ ሙሉ እምነት አለኝ።
ሙሼ ሰሙ-
የቴሌግራም ቻናልችንን በመቀላቀል የአዲስ አድማስን መረጃ ይከታተሉ…
• የመንግስት ት/ቤቶች ተማሪዎችን በማሳለፍ ረገድ ዝቅተኛ ውጤት አስመዝግበዋል
በ2017 ዓ.ም. በተሰጠው የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተና፣ በኬሚስትሪ የትምሕርት ዘርፍ ከፍተኛ ውጤት መመዝገቡን የትምሕርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ አስታውቀዋል። በአፕቲትዩድ ትምሕርት ዝቅተኛ ውጤት እንደተመዘገበ ሚኒስትሩ አያይዘው ገልጸዋል።
ፕሮፌሰር ብርሃኑ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ እንዳመለከቱት፣ በሁሉም ክልሎች ካለፈው ዓመት አንጻር ሲመዘን፣ የተሻለ ውጤት ተመዝግቧል። ለአብነት፣ በጋምቤላ ክልል በ2016 ዓ.ም. ከተፈተኑ ተማሪዎች መካከል፣ 1.7 በመቶ ተማሪዎች ብቻ እንዳለፉ አውስተው፣ በ2017 ዓ.ም. ግን 4.5 በመቶ ተማሪዎች ፈተናውን ማለፍ መቻላቸውን ጠቁመዋል።
ከዚህም በተጨማሪ፣ 50 ከመቶ እና በላይ የማለፊያ ውጤት ካስመዘገቡ ተማሪዎች መካከል፣ የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች ቀዳሚውን ደረጃ እንደያዙ ሚኒስትሩ አስታውቀዋል። በዚህም 50 ከመቶ እና በላይ ያመጡ የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች ብዛት 11 ነጥብ 4 በመቶ ሲሆኑ፣ በማሕበራዊ ሳይንስ ደግሞ 5 ነጥብ 2 በመቶ ተማሪዎች እንደሆኑ አስረድተዋል።
ሚኒስትሩ፣ በኬሚስትሪ ትምሕርት ከፍተኛ ውጤት እንደተመዘገበ ጠቅሰው፣ በተቃራኒው በአፕቲትዩድ ፈተና ዝቅተኛ ውጤት መመዝገቡን ተናግረዋል። የአፕቲትዩድ ውጤትን ለማሻሻል፣ ከአጸደ ሕጻናት ጀምሮ የእንግሊዝኛ ትምህርት እንዲሰጥና የትምሕርቱን አሰጣጥ ለማሻሻል የተለያዩ ስራዎች እየተሰሩ እንደሚገኙ አብራርተዋል።
በዚህም ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር በመተባበር፣ ተማሪዎች በቤታቸው ሆነው የሚማሩበት የበይነ መረብ አማራጭ መዘርጋቱን ጠቁመዋል። በይነ መረቡ ስራ በጀመረ ሰሞን፣ ከቤታቸው ሆነው የሚማሩ ተማሪዎች ቁጥር “ከሚፈለገው በታች” እንደነበር ያወሱት ፕሮፌሰሩ፣ በአሁኑ ወቅት ግን “ለውጦች እየታዩ ነው” ብለዋል።
በሌላ በኩል፣ የመንግስት ትምሕርት ቤቶች ተማሪዎችን በማሳለፍ ረገድ ዝቅተኛ ውጤት ማስመዝገባቸውን ሚኒስትሩ አልሸሸጉም። አዳሪ እና በውጭ አገራት የሚገኙ የኢትዮጵያውያን ትምሕርት ቤቶች ተማሪዎችን በማሳለፍ ረገድ ቀዳሚውን ደረጃ ቢይዙም፣ ከመንግስት ትምሕርት ቤቶች በ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተና ተማሪዎችን ያሳለፉት 5 ነጥብ 6 በመቶ “ብቻ ናቸው” ሲሉ ተደምጠዋል።
“የትምሕርት ዘርፍ ማሻሻያ ስራችን ከምንገምተው በላይ ውጤት አስገኝቷል” ያሉት ፕሮፌሰር ብርሃኑ፣ በቀጣይም የመንግስት ትምሕርት ቤቶችን ትኩረት ያደረጉ ለውጦች ተግባራዊ እንደሚደረጉ ገልጸዋል።
የቴሌግራም ቻናልችንን በመቀላቀል የአዲስ አድማስን መረጃ ይከታተሉ…
May be an image of 2 people, dais, newsroom and text that says 'NBC ETHIOPI'
 
 
 
 
ሼህ መሐመድ የምንጊዜም የኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጅ ናቸው! በኢትዮጵያ ታላላቆቹ ሀገራዊ ሥራዎችና የደግነት ምግባራት ውስጥ የእሳቸው ለጋስ እጅ ያላረፈበትን ነገር መጥቀስ ይከብዳል። ሲለግሱና ዕንባ ሲያብሱ፣ ቃል እስኪቸግራቸው ስለኢትዮጵያ የልባቸውን አውጥተው ሲናገሩ፣ ከአጠገባቸው ሆኜ የማድመጥን ብዙ ዕድል አግኝቻለሁ።
ከብዙ አመታት በኋላ በሚድሮክ የቤተሰብ ቀን ላይ በቀረበው ቪዲዮ የተቀረፀውን ድምጻቸውን በመስማቴና ምስላቸውን ማየት በመቻሌ እጅግ በጣም ተደስቻለሁ። ወደሚወዷት፣ በልባቸው በሚያስቡላትና ከአንደበታቸው ወደማትጠፋው ሀገራቸው በጤና ተመልሰው፣ የልጅ ከሚመስለው ፈገግታቸው ጋር በአካለ ሥጋ እናያቸው ዘንድ እንፀልያለን!
ረዥም ዕድሜና ሙሉ ጤናን እመኝልዎታለሁ!
-ከያኒና ጋዜጠኛ ተስፋዬ ማሞ -
ኢኩቲ ባንክ የኢትዮጵያን የፋይናንስ ኢንዱስትሪ የሚቀላቀል ሁለተኛው የኬንያ ባንክ ሊሆን ነው፡፡
ኢኩቲ ባንክ ወደ ኢትዮጵያ የፋይናንስ ዘርፍ ለመግባት በሚያደርገው እንቅስቃሴ ከኢትዮጵያ ባለስልጣናት ጋር በይፋ ውይይት ጀምሯል፡፡
የኢኩቲ ግሩፕ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ዶ/ር ጀምስ ምዋንጊ በቅርቡ ከኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮሚሽነር ዶ/ር ዘለቀ ተመስገን ጋር ተገናኝተው፣ ባንኩ በኢትዮጵያ ሊንቀሳቀስ በሚችልበት የህግ ማዕቀፍ ዙሪያ መወያየታቸው ተጠቁሟል።
የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽነር በውይይቱ ወቅት እንደገለጹት፤ ባንኩ ኢትዮጵያ ውስጥ በሚያደርገው ኢንቨስትመንት አስፈላጊው ትብብርና ድጋፍ ይደረግለታል።
የኢኩቲ ባንክ ሥራ አስፈጻሚ ዶ/ር ጀምስ ምዋናጊ በበኩላቸው፤ የኢትዮጵያ መንግስት የፋይናንስ ሴክተሩን ለውጪ ባለሀብቶች ክፍት ማድረጉ ምቹ አጋጣሚ ነው ብለዋል።
አክለውም፤ ባንኩ
የኬንያው ኢኩቲ ባንክ የኢትዮጵያን የባንክ ገበያ ሊቀላቀል ነው
ኢኩቲ ባንክ የኢትዮጵያን የፋይናንስ ኢንዱስትሪ የሚቀላቀል ሁለተኛው የኬንያ ባንክ ሊሆን ነው፡፡
ኢኩቲ ባንክ ወደ ኢትዮጵያ የፋይናንስ ዘርፍ ለመግባት በሚያደርገው እንቅስቃሴ ከኢትዮጵያ ባለስልጣናት ጋር በይፋ ውይይት ጀምሯል፡፡
የኢኩቲ ግሩፕ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ዶ/ር ጀምስ ምዋንጊ በቅርቡ ከኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮሚሽነር ዶ/ር ዘለቀ ተመስገን ጋር ተገናኝተው፣ ባንኩ በኢትዮጵያ ሊንቀሳቀስ በሚችልበት የህግ ማዕቀፍ ዙሪያ መወያየታቸው ተጠቁሟል።
የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽነር በውይይቱ ወቅት እንደገለጹት፤ ባንኩ ኢትዮጵያ ውስጥ በሚያደርገው ኢንቨስትመንት አስፈላጊው ትብብርና ድጋፍ ይደረግለታል።
የኢኩቲ ባንክ ሥራ አስፈጻሚ ዶ/ር ጀምስ ምዋናጊ በበኩላቸው፤ የኢትዮጵያ መንግስት የፋይናንስ ሴክተሩን ለውጪ ባለሀብቶች ክፍት ማድረጉ ምቹ አጋጣሚ ነው ብለዋል።
አክለውም፤ ባንኩ ኢትዮጵያ ውስጥ በሚያደርገው ኢንቨስትመንት ለሌሎች ኢትዮጵያ ውስጥ በዘርፉ መሰማራት ለሚፈልጉ የውጭ ኩባንያዎች ምሳሌ መሆን እንደሚፈልግ ገልጸዋል።
ኢኩቲቲ ባንክ በኬንያ፣ ኡጋንዳ፣ ታንዛኒያ፣ ደቡብ ሱዳን፣ ሩዋንዳና ኮንጎ ውስጥ በፋይናንስ ዘርፍ የካበተ ልምድ እንዳለው ይታወቃል፡፡
 
 
 
 
 
 
 
ኢትዮጵያዊው ዲፕሎማት በ95 ዓመታቸው ሕይወታቸው አለፈ
በቀዳማዊ ኃይለሥላሴ ዘመን በማስታወቂያ ሚኒስትርነት፣ እንዲሁም ከአብዮቱ በፊት የመጨረሻው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በመሆን ሀገራቸውን ያገለገሉት አንጋፋው ዲፕሎማት ዶ/ር ምናሴ ኃይሌ በ95 ዓመታቸው ሕይወታቸው ማለፉ ተሰምቷል፡፡
በ1922 ዓ.ም የተወለዱት ዶክተር ምናሴ፤ ከአሜሪካው ዊስኮንሰን ማዲሰን ዩኒቨርሲቲ የመጀመሪያ ዲግሪያቸው ካገኙ በኋላ፣ ከኮሎምቢያ የሕግ ዩኒቨርስቲ ዶክትሬታቸውን አግኝተዋል።
በተለይ የአፍሪካ ሕብረት ዋና መሥሪያ ቤት ከአዲስ አበባ እንዲነሳ በተጠየቀ ወቅት በሠጡት ምላሽ የሚታወቁት አንጋፋው ዲፕሎማት፣ በሚኖሩበት ሰሜን አሜሪካ ሕይወታቸው ማለፉ ተነግሯል፡፡
"የእስራኤል ጄቶች ግብፅን ቢያጠቁ መመለሻ አያገኙም"
የቀድሞ የግብጽ ወታደራዊ አዛዥ ኮሎኔል ሃተም ሳበር፣ የእስራኤል አውሮፕላኖች በግብፅ ላይ ጥቃት ቢሰነዝሩ "መመለሻ ቦታ እንደማያገኙ" በቴሌቪዥን ባደረጉት ቃለመጠይቅ ግልጽ ማስጠንቀቂያ ሰጥተዋል፡፡
"የእስራኤል አየር ሃይል ግብፅን ቢያጠቃ፣ ከእስራኤል ለጥቃት የሚነሱ አውሮፕላኖች የሚመለሱበት መንገድ አያገኙም" ሲሉ ሳበር አስጠንቅቀዋል፡፡
አዛዡ ይህን የተናገሩት በቅርቡ እስራኤል በኳታር ዋና ከተማ ዶሃ ከፍተኛ የሃማስ መሪዎች ላይ ያነጣጠረ የአየር ድብደባ መፈጸሟን ተከትሎ ነው።
በአንድ ወቅት በግብፅ ጦር ውስጥ ካሉት ልዩ የፀረ-ሽብር ክፍሎች አንዱን የመሩት ሳበር፤ ምንም ተጨማሪ ማብራሪያ ባይሰጡም፣ መልዕክታቸው ከወትሮው በተለየ መልኩ ቀጥተኛ እንደነበር ዴይሊ ኒውስ ኢጂፕት ዘግቧል፡፡
ተንታኞች፤ የአዛዡ ማስጠንቀቂያ የእስራኤል ወታደራዊ እንቅስቃሴ ከተለመደው አድማስ እየተስፋፋ መምጣቱ፣ ካይሮ ላይ የፈጠረውን ሰፊ ስጋት እንደሚያንጸባርቅ ጠቁመዋል፡፡
የግብፅ መንግስትና ወታደራዊ ሃይሎች ለሳበር የቴሌቪዥን ማስጠንቀቂያ አዘል አስተያየቶች እስካሁን ምላሽ አልሰጡም ተብሏል።
የቴሌግራም ቻናልችንን በመቀላቀል የአዲስ አድማስን መረጃ ይከታተሉ…
የትምሕርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ፣ በ2017 ዓ.ም. የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተና ስርቆትና ማጭበርበር በአመዛኙ እንዳልተስተዋለ ተናገሩ። ሚኒስትሩ አክለውም፣ መካከለኛ ገቢ የሚያገኘው ዜጋ ልጆቹን ከግል ወደ መንግስት ትምሕርት ቤቶች መልሶ እንዲያስተምር የተለያዩ እርምጃዎች እንደሚወሰዱ ገልጸዋል።
ዛሬ መስከረም 4 ቀን 2017 ዓ.ም. ለመገናኛ ብዙሃን ጋዜጣዊ መግለጫ የሰጡት ፕሮፌሰር ብርሃኑ፣ መሰረታዊ የትምሕርት ዘርፍ ለውጥ የመተግበር ዕንቅስቃሴ ከተጀመረ አራት ዓመት ማስቆጠሩን ጠቅሰው፣ የመጀመሪያው ዙር በ2017 ዓ.ም. መጠናቀቁን አመልክተዋል። የፈተና አሰጣጥ ሂደቱን መለወጥ የዚሁ ዕንቅስቃሴ አንድ አካል መሆኑንና "ተጨባጭ መሻሻሎች" እየተስተዋሉ እንደሚገኙ አንስተዋል።
"በፈተና አሰጣጥ የተጋረጠብን ችግር ከአጠቃላይ የማሕበረሰብ የሞራል ክስረት ጋር የተያያዘ ነው" ያሉት ሚኒስትሩ፣ ስኬትን በአቋራጭ መንገድ የማግኘት አስተሳሰብ በትምሕርት ዘርፉ ላይ ፈተና መጋረጡን ተናግረዋል። ይህን እና መሰል ተግዳሮቶችን ለመቅረፍ እርሳቸው የሚመሩት ሚኒስቴር መስሪያ ቤት የፈተና አሰጣጥ ሂደቱን "በየደረጃው" የመለወጥ ስራዎችን በመስራቱ ሳቢያ፣ የፈተና ስርቆትና ማጭበርበር ተግባራት "በጉልሕ" መቀነሳቸውን አስረድተዋል።
ፕሮፌሰር ብርሃኑ፣ "ስርቆትና ማጭበርበር ከሞላ ጎደል የጠፋበት ዓመት ነው" በማለት ባሳለፍነው ዓመት በመላ አገሪቱ ለሚገኙ 585 ሺሕ 882 ያህል ለሚሆኑ ተማሪዎች በተሰጠው የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተና ላይ የኩረጃ ተግባራት ቀንሰው መታየታቸውን ጠቅሰዋል።
ሚኒስትሩ ከዚሁ ጋር የተገናኙ አሕዛዊ መረጃዎችን ሲያብራሩ፣ ባለፉት ሶስት ዓመታት 29 ሺሕ 100 የማጭበርበር ተግባራት መመዝገባቸውን፤ በ2016 ዓ.ም. 379 ተመሳሳይ ተግባራት ሲስተዋሉ፤ በዘንድሮ ዓመት ግን 120 የኩረጃ እና ማጭበርበር ድርጊቶች መገኘታቸውን አብራርተዋል።
"ተፈታኝ ተማሪዎች በራሳቸው አቅም ብቻ ፈተናውን ማለፍ እንደሚችሉ ያወቁበት ዓመት ነው" ያሉት ፕሮፌሰሩ፤ ለአጠቃላይ የውጤት "መሻሻል" የተማሪ ወላጆች ለትምሕርት የሚሰጡት ትኩረት መጨመር እና በቅርቡ መሰጠት የተጀመረው የመምህራን ስልጠና አስተዋጽዖ ማድረጋቸውን አልሸሸጉም።
ከዚህም ባለፈ፣ በመጪው ጊዜያት መካከለኛ ገቢ የሚያገኙ ኢትዮጵያውያን ልጆቻቸውን ከግል ወደ መንግስት ትምሕርት ቤቶች እንዲመልሱ በትምሕርት ሚኒስቴር በኩል የተለያዩ ዕርምጃዎች እንደሚወሰዱ ተናግረው፣ በተለይ የመንግስት ትምሕርት ቤቶች የመማር ማስተማር ሂደትን የማሻሻል ስራ ቅድሚያ እንደሚሰጠው አስታውቀዋል።
 
 
 
 
 
 
ዳንጎቴ የነዳጅ ማጣሪያ ኩባንያ በመላ ናይጄሪያ ነፃ የነዳጅ ማጓጓዝ አገልግሎት ሊሰጥ መሆኑ ተዘግቧል፡፡
ኩባንያው ከመስከረም 5 ጀምሮ በአቡጃ፣ ኤዶ፣ ሪቨርስ፣ ዴልታ፣ ክዋራ፣ ሌጎስ እና በደቡብ ምዕራብ አካባቢዎች የነዳጅ ችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ላይ ቅናሽ እንደሚያደርግም አስታውቋል፡፡
"በሀገሪቱ ያሉ ሁሉም የነዳጅ ማደያ ጣቢያ ባለቤቶች ለነፃ ማጓጓዣውና ለሌሎችም ጥቅማ ጥቅሞች መመዝገብ ይችላሉ" ሲል ኩባንያው መግለጹን ስፑትኒክ ዘግቧል፡፡
ዛሬ በተደረገው የወንዶች 100 ሜትር ፍጻሜ ጀማይካውያኑ 1ኛ እና 2ኛ ወጥተዋል፡፡
ኦብሊኬ ሴቪሊ በአንደኝነት ሲያጠናቅቅ የገባበት 9 ሰከንድ 77 ማይክሮ ሰከንድ የግል ምርጥ ሰዓቱም ሆኖ ተመዝግቧል፡፡
ለመጨረሻ ጊዜ በ2015 የቤጂንግ ዓለም ሻምፒዮና በአትሌት ዩሲያን ቦልት የወርቅ ሜዳልያ ያገኝችው ጃማይካ፤ ከ10 ዓመት በኋላ ከወርቅ ሜዳልያው ጋር ተገናኝታለች፡፡
ሌላኛው ጃማይካዊ ኪሻኒ ቶምሰን 2ኛ ደረጃን በመያዝ አጠናቋል፡፡ አሜሪካዊው ኖህ ላይስ 3ኛ ደረጃን አግኝቷል፡፡
በሴቶች 100 ሜትር ፍጻሜ ደግሞ አሜሪካዊቷ ጀፈርሰን ውድን አሸንፋለች፡፡
Ebc sport-
የቴሌግራም ቻናልችንን በመቀላቀል የአዲስ አድማስን መረጃ ይከታተሉ…
በጃፓን ቶክዮ እየተካሄደ ባለው 20ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና በሁለተኛ ቀን ዉሎ ኢትዮጵያ ሁለት የብር ሜዳሊያዎች አገኘች።
ዛሬ ከሰዓት በኋላ ላይ በተደረገው የወንዶች የ10 ሺህ ሜትር የሩጫ ውድድር አትሌት ዮሚፍ ቀጄልቻ ሁለተኛ በመሆን የብር ሜዳሊያ አስገኝቷል፡፡
ዮሚፍ ቀጀልቻ 50 ሜትር እስከሚቀር ድረስ ሲመራ ቢቆይም፣ በፈረንሳዊው አትሌት ጂሚ ግሬሰር ተቀድሞ 2ኛ ደረጃን ይዞ አጠናቋል፡፡
አትሌት ሰለሞን ባረጋ 6ኛ ደረጃን ይዞ ሲያጠናቅቅ፣ በሪሁ አረጋዊ 12ኛ ደረጃን ይዞ ውድድሩን አጠናቋል፡፡
የቴሌግራም ቻናልችንን በመቀላቀል የአዲስ አድማስን መረጃ ይከታተሉ…
Page 7 of 790