Administrator

Administrator

ሁሉም ነገር አንጻራዊ ነው። የ "ሪፖርተር" ጋዜጣ ለ30 ዓመት የታመነ የመረጃ ምንጭነትም እንዲሁ አንጻራዊ ይሆናል። እና በበኩሌ ላለፉት 30 ዓመታት በሪፖርተር ጋዜጣ ልክ መሐል ቆሞ መረጃን በታማኝነት የሚያከፋፍል የሚዲያ ተቋም አላውቅም። በመሐል ታይተው የጠፉ እንደ " አዲስ ነገር " ያሉ ጋዜጦች ይኖራሉ። እነሱ ቢኖሩም ቁጥራቸው ጥቂት ፣ እድሜያቸውም አጭር ነው።
የሪፖርተር መስራችና ማኔጂንግ ኤዲተር አቶ አማረ አረጋዊ ከሕወሓት ነባር ታጋዮች መሐል አንዱ የነበረ ነው። ያም ሆኖ ስለ ሕወሓት የጓዳ ምሥጢሮች ሳይቀር የምንሰማው ከሪፖርተር ነበር ፤ ነው። በቂ አልሆነ ይሆናል። አንጻራዊ ነው ብለናል። በሀገሪቱም ሆነ አቶ አማረ በታገለለት ሕወሓት አንኳር ጉዳዮች ላይ " በሚዛናዊነት " ሪፖርተር የሰጠንን ማንም አልሰጠንም።
ሕይወታችን ስላደረግነው አይታወቀን ይሆናል እንጂ እጅግ የምንበዛው በፖለቲካ፣ በብሔር ፣ በሀይማኖት ፣ በአስተሳሰብ ጽንፈኞች ነን። እንደ ሕዝብም የዴሞክራሲ ልምምድ የለንም። ከለመድነው መውጣት ፣ ከምንፈልገው በተቃራኒ የሆነን መስማት ልምምዱ የለንም። እኛ የሪፖርተር ጋዜጣ ወሳኝ ሰው ብንሆን ከምናደርገው አቶ አማረ አረጋዊ ብዙ ርቆ ሄዷል።
አቶ አማረ አረጋዊ ጣፋጩን የወጣትነት ክሬሙን ጊዜ የሰጠው ሕወሓት ለሚመራው ትግል ነው። ይሁንና በሕወሓት ክፍፍል ጊዜ ( አሁንም በአንጻራዊ መልኩ ) የሁለቱንም ጎራ ሀሳቦች በእኩልነት የምናነበው ከሪፖርተር ነበረ። አምነን የምናነበው ሪፖርተርን ነበረ። በምርጫ 97 ወቅት ሁሉም ብዙሀን መገናኛ ለሁለት የተከፈለበትና እንደ ዘመነ ቀይ/ነጭ ሽብር " ከኢሕአዴግ ወይም ከተቃዋሚዎች " የተባለበት ጊዜ ነበረ። መሐል ለመሆን የሚሞክር " ወያኔ " የሚባል ታፔላ የሚለጠፍበት ጊዜ ነበረ። ዜና ሲሰራም ትንሽ ተቃዋሚዎችን ከነካ ወይም መንግሥትን ( ሕግን ) የደገፈ ከመሰለ " የመንግሥት ዜና " የሚባልበትና በራሱ በፕሬሱ የሚዘመትበት ጊዜ ነበረ። ዋንኛው የቀድሞ " ወያኔ " አቶ አማረ የሚያሳትመው ሪፖርተር ጋዜጣ ነበረ የግራውንም ፣ የቀኙንም በእኩልነት (በመጠኑ ለተቃዋሚዎች ድምጽ እየሆነ ) ያቀርብ የነበረው።
የመንግሥትን አይነኬ ቦታዎች በመረጃና በማስረጃ ላይ ተመስርቶ የሚነካው ሪፖርተር ነው። ሪፖርተር ትላልቅ መረጃዎችንና ማስረጃዎችን ከ " ትላልቅ " ሰዎች ጭምር ማግኘቱ ብቻ ሳይሆን ያገኘውንም በአግባቡ የሚጠቀምበት ኃላፊነት የሚሰማው ጋዜጣ ነው። በወቅቱ በግሉ ፕሬስና በተቃዋሚዎች " ለወያኔ ያደላል " ሲባል በሕወሓት ሰዎች ደግሞ " እንደ ሌላው ፕሬስ ሁሉ ለተቃዋሚዎች ያደረና ኢሕአዴግን ለመጣል ከተባበሩት ጋር የወገነ " ተደርጎ ነበረ የሚቆጠረው። ይሁንና በኢሕአዴግም ሆነ በተቃዋሚዎቹ " ታምኖ " የሚነበበውም ሪፖርተር ጋዜጣ ነበረ። " ሪፖርተር ምን አለ ? " የሚባል ነው። ይሄ ጋዜጣ ነው በህትመት ላይ እያለ 30 ዓመት የደፈነው።
አቶ አማረ አረጋዊ በአንድ በኩል በሌላው ዘንድ " ወያኔ " እየተባለ፣ በ " ወያኔዎቹ " ዘንድ ደግሞ በተቃዋሚነት ተፈርጆ እስከማውቀው ድረስ " ትግራይ አይረግጥም " የተባለ ( እንደሰማሁት ) ሰው ነበር። በሕወሓት ሰዎች ዘንድ " የእኛ " የማይባል ሰው እንደነበረ አውቃለሁ። ከአቶ መለስ ዜናዊም ፣ ከደህንነት ሹሙ ክንፈ ገ/መድህንም ጋር ግንኙነት ያለው ሆኖም በአቶ አማረ አረጋዊ ቦታ ላይ መገኘት ትልቅ የሞራል ድፍረትን የሚጠይቅ ነው። በባለስልጣን መጨበጥ ስንቱን አቅልጦ እንዳስቀረው አይተናል። የአቶ አማረ የለውጥ ሰውነት በሪፖርተር ጋዜጣ ላይ የመጣ ሳይሆን ከዚያ ቀደም ብሎም የነበረ ነው።
ጋዜጠኛ ዘካሪያስ ኃ/ማርያም ( ነፍስ ይማር ) በአንድ ወቅት የነገረኝን ላስታውስ። አቶ መለስ ዜናዊ በለውጡ ዓመታት አካባቢ የዘመን መለወጫ ለመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ የእንኳን አደረሳችሁ ንግግር ያደርጋሉ። በወቅቱ የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን የዋዜማ የመዝናኛ ዝግጅቶች በርከት ያሉ ነበርና የፕሮግራም መጣበብ ያጋጥማል። ከፕሮግራሞቹ አንዱ ደግሞ ምሽቱን የሚተላለፈው የአቶ መለስ ዜናዊ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት ነው። ይህን ያየው የቴሌቪዥን ጣቢያው ስራ አስኪያጅ አቶ አማረ የወሰነው የአቶ መለስን ንግግር ቀንሶ በማግስቱ እንዲተላለፍ ማድረግ ነበር። " ' ይሄ ነገም ቢተላለፍ ችግር አያመጣም ፤ዛሬ በዓል ስለሆነ ሕዝቡ ይዝናናበት ' አለን" ነው ያለኝ።
ሪፖርተር " እንከን የለሽ " ጋዜጣ ነው እያልኩ አይደለም። የሰውም ፣ የአሰራርም ፣ የአመራርም ስህተቶች ይኖሩበታል። ይህ ያለና የሚጠበቅ ነው። የምናወራው ስለ ፍጽምና አይደለም። ፍጽምናም የለም። በእኔ እምነት ከ1984 በኋላ በዚህ ሀገር ከመጡ የግል ይሁን የመንግሥት ብዙሀን መገናኛዎች በሪፖርተር ልክ ለፕሬስ ነጻነት የቆመ ፣ የመንግሥትን እንከን ያሳየ ፣ ቱባ ባለስልጣናትን በመረጃ የደፈረ ፣ ብልሹ አሰራሮችን በድፍረትና በመረጃ የተጋፈጠ አለ ማለት አልደፍርም። ይህን ሀሳብ ብዙዎች ላይቀበሉት እንደሚችሉ አስባለሁ። ይሁንና እነዚያ ሰዎች ይህን ሁሉ ከሪፖርተር በተሻለ ያደረገ ማንንም አይጠሩም። የታመነ የዜና ምንጭ የሆነ ፣ ለበርካታ ዜጎች የስራ ዕድል የፈጠረ ፣ ራሱ አቶ አማረ መርካቶ ወስዶ በነጻ ጭምር ይሰጠው ከነበረው የጳጉሜ 6/1987 ዕትም ጀምሮ እስከ ዛሬ ጳጉሜ 2/2017 በጽናት የዘለቀው አንጋፋውና ብቸኛው የግል ጋዜጣ "ሪፖርተር" እንኳን ለ30ኛ ዓመትህ አደረሰህ።
-ቴዎድሮስ ተ/አረጋይ-
የቴሌግራም ቻናልችንን በመቀላቀል የአዲስ አድማስን መረጃ ይከታተሉ…
 
 
 
 
 
 
 
 
ለአገልግሎት ዝግጁ የሆነችው ጣና ነሸ ፪ ጀልባ ጣና ሐይቅ ላይ መንሳፈፍ ጀመረች።
ጣና ነሸ ፪ ጀልባ በጣና ሐይቅ የትራንስፖርት አገልግሎት ከመስጠት በተጨማሪም የቱሪዝሙን ዘርፍ የበለጠ ታጠናክራለች ተብሎ ይጠበቃል።
የቴሌግራም ቻናልችንን በመቀላቀል የአዲስ አድማስን መረጃ ይከታተሉ…
 
 
 
 
 
 
 
 
በህብር ቀን የአዲስ አመት መባቻን ምክንያት በማድረግ፣ የባህልና ስፖርት ሚኒስትር ሸዊት ሻንካ፣ አንጋፋው ድምጻዊ መሀሙድ አህመድ መኖሪያ ቤት በመገኘት እንኳን አደረሳችሁ ብለዋል።
"ታላላቆችን ማክበር፣ መጠየቅ፣ መርዳትና መንከባከብ ነባር ባህላዊ ዕሴቶቻችን ናቸው። በዓላትን ማብሰርና ማክበር አንዱ ተልዕኮው የሆነው ሚኒስቴሩ፣ ይህንን ማስቀጠልና ከትውልድ ወደ ትውልድ ማስተላለፍ የሚቀጥል ስራ ነው" ያሉት ሚኒስትሯ፤ ጋሽ መሀሙድ ቤት በአካል ተገኝተው እንኳን አደረሳችሁ ማለታቸውና ያላቸውን ክብር መግለፃቸው እንዳስደሰታቸው ገልፀዋል።
የባህልና ስፖርት ሚኒስትር ደኤታ ረ/ፕ ነብዩ ባዬ በበኩላቸው፤ "ጋሼ ለዛውና ቃናው የማይጠገብ ለሰላም የቆመ አርበኛ፤ለሀገርና ለህዝብ መቆምንና ሀገር መውደድን ኖሮ ያሳየ ድንቅ የጥበብ ንጉስ ነው" ሲሉ ተናግረዋል፡፡
አንጋፋው ድምጻዊ መሀሙድ አህመድ፤ "በዛሬው ቀን ሰለተሰጠኝ ክብር የተሰማኝ ደስታ ይህ ነው አልለውም ፤እድሜ ነው የጨመርኩት። ወጣቶች፣ አድናቂዎቼና አዲሱ ትውልድ ለህዝብ ምን ባቀርብ ነው የሚቀበለኝ በማለት ሊሰራ ይገባዋል" ብለዋል።
ድምጻዊው፤ አዲሱ ትውልድ ሀገሩንና ህዝቡን የሚያስቀድም ሰላም ወዳድ እንዲሆን መልዕክት በማስተላለፍ፤ አዲሱ ዓመት የሰላም፣ የፍቅር፣ የአንድነትና የፍሰሀ ዘመን እንዲሆን መልካም ምኞቱን አስተላልፏል፡፡
የቴሌግራም ቻናልችንን በመቀላቀል የአዲስ አድማስን መረጃ ይከታተሉ…
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 

የአፍሪካ መዲና አዲስ አበባ ከ20 ሺህ እስከ 25 ሺህ ሰዎች ይሳተፉበታል ተብሎ የሚጠበቀዉን 2ኛዉን የአፍሪካ አየር ንብረት ጉባኤ ከጳጉሜን 3 እስከ 5 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ ታስተናግዳለች

"ህዳሴው የአፍሪካ ራስን የመቻል ተምሳሌት ነው"
የኬንያው ፕሬዚዳንት ዊልያም ሩቶ፣ "የአፍሪካ ራስን የመቻል ተምሳሌትና የኢትዮጵያ ወሳኝ ምዕራፍ" ሲሉ የገለፁት የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የምረቃ ሥነስርዓት ዋና እንግዳ እንደሚሆኑ ተጠቆመ፡፡
የፕሬዚዳንቱ ጽህፈት ቤት ቃል አቀባይ ዛሬ እሁድ ባወጣው መግለጫ፣ ፕሬዚዳንቱ በምርቃት ሥነስርዓቱ ላይ እንደሚገኙ አረጋግጧል።
ፕሬዚዳንት ሩቶ እና ልዑካቸው ዛሬ ረፋድ ላይ አዲስ አበባ የገቡ ሲሆን፤ ታላቁ ህዳሴ ግድብ ማክሰኞ ጳጉሜ 4 ቀን 2017 ዓ.ም እንደሚመረቅ የኢትዮጵያ መንግሥት አስታውቋል፡፡
የኬንያ ፕሬዚዳንት ጽ/ቤት፣ የህዳሴ ግድቡን ክልላዊ ፋይዳ አጉልቶ ሲገልጽ፤ የኢትዮጵያና የኬንያ የሃይል ማስተላለፊያ መስመር "ንፁህና ተመጣጣኝ የኤሌክትሪክ ሃይል የሚያቀርብና የሃይል ደህንነትን የሚያጠናክር፣ በድርቅ ወቅት አቅርቦትን የሚያረጋጋና የኢንዱስትሪ እድገትን የሚደግፍ ነው" ብሏል።
መግለጫው አክሎም፤ የሩቶ የአዲስ አበባ ጉብኝት በሁለተኛው የአፍሪካ የአየር ንብረት ጉባኤ ላይ መሳተፍን እንደሚያካትት ጠቁሞ፤ ፕሬዚዳንቱ "ከናይሮቢ ወደ አዲስ አበባ፡ የአፍሪካ የአየር ንብረት ለውጥ እርምጃና አጋርነት ጉዞ" በሚል ርዕስ ሪፖርት እንደሚያቀርቡ አመልክቷል፡፡
ሪፖርቱ "በናይሮቢ ከተካሄደው የመጀመሪያው የአፍሪካ የአየር ንብረት ጉባኤ በኋላ ያለውን እድገት የሚገመግም ሲሆን፤የአሁኑን እውነታ በመዳሰስ የወደፊት መንገዶችን ያስቃኛል" ሲል መግለጫው ጠቅሷል።
 
 
 
 
 
 
"ወታደሮቻችሁ በዩክሬን ከተሰማሩ ዒላማ ይሆናሉ"
የሩሲያ ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን፣ ምዕራባውያን በፓሪስ ባካሄዱት ጉባዔ በዩክሬን የተኩስ አቁም ስምምነት ከተደረሰ በኋላ "የደኅንነት መተማመኛ ኃይል" በማለት ወታደሮች ለማሰማራት ያቀረቡትን ምክረ ሃሳብ ውድቅ ማድረጋቸውን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡
የፈረንሳዩ ፕሬዝዳንት ኢማኑዔል ማክሮን 26 የዩክሬን አጋር አገራት ጦርነቱ ከቆመ በኋላ፣ የአገሪቱን ፀጥታ ለማረጋገጥ "በምድር፣በባሕር ወይም በአየር" ጦራቸውን ለማሰማራት በይፋ ቃል መግባታቸውን ተናግረዋል።
ፑቲን የዩክሬን አጋሮች ገቡት የተባለውን ቃል ውድቅ በማድረግ፣ ማንኛውም ዩክሬን ውስጥ የሚሰማራ ወታደር "ዒላማ" ይሆናል ሲሉ አስጠንቅቀዋል።
ፕሬዝዳንቱ አክለውም፤ ምንም እንኳ ወታደሮቹን አሁን የማሰማራት ፍላጎት ባይኖርም፣ ይህ የሚሆን ከሆነ ግን ዒላማ ከመሆን እንደማያመልጡ ዝተዋል።
በአዲስ አበባ የሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ፣ ከሰሞኑ ከኃላፊነታቸው በፈቃዳቸው የለቀቁትን የቀድሞ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ አቶ ማሞ ምህረቱ በይፋ አመሰገነ፡፡
ኤምባሲው በማህበራዊ ትስስር ገጹ ባሰፈረው መልዕክት፤ አቶ ማሞ ለሰጡት አገልግሎትና ለራዕያቸው ምስጋና አቅርቧል፡፡
"የአቶ ማሞ ድፍረት የተመላበት አመራር፣ የኢትዮጵያን ኢኮኖሚና ህዝቧን ወደ ኋላ ይጎትቱ የነበሩ የማክሮ ኢኮኖሚ መዛባቶችን ለማረም ረድቷል" ብሏል፤ ኤምባሲው።
ኢትዮጵያ እሳቸው መንገድ የጠረጉለትን የኢኮኖሚ ማሻሻያ እንድትቀጥልም አሳስቧል።
ኤምባሲው አክሎም፤ "በተለይ ከባድ ተግዳሮቶች ባሉበት ሁኔታ ውስጥ ለውጥ በጭራሽ ቀላል አይደለም" ሲልም ለሪፎርሙ ዕውቅና በመስጠት የቀድሞውን የብሔራዊ ባንክ ገዢ አመስግኗል፡፡
ለመጪዎቹ ዓለም አቀፍ ጉባኤዎች በመዲናዋ የሚገኙ የሆቴሎችና ጤና ተቋማትን ብቃት ማረጋገጥ መጀመሩን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የምግብና መድኃኒት ባለስልጣን አስታውቋል፡፡
በአህጉር አቀፉ የአፍሪካ የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ፣ የአፍሪካና የካረቢያን ሀገሮች ጉባኤ እንዲሁም የታላቁ ህዳሴ ግድብ ምርቃት ላይ የሚሳተፉ ዓለማቀፍና ሀገር አቀፍ ተሳታፊዎች የሚያርፉቧቸውም ሆነ አገልግሎት የሚያገኙባቸው ሆቴሎች፣ ትልልቅ ባርና ሬስቶራንቶች፣ መዝናኛ ቦታዎች፣ ፔንሲዮኖች እንዲሁም ሆስፒታሎች ደረጃቸውን የጠበቁ መሆናቸውንና አገልግሎት አሰጣጣቸው ኢትዮጵያዊ ጨዋነት የተላበሰ ስለመሆኑ ፍተሻና ቁጥጥር እያደረገ መሆኑንም ገልጿል፡፡
እስካሁን ባለው የክትትል ሂደትም የስምንት ሆስፒታሎችና አምስት የሕክምና ማዕከሎች ብቃት መረጋገጡን ያስታወቀው ባለሥልጣኑ፤ በተጨማሪም፣ 160 ሆቴሎችና 308 የምግብና መጠጥ አቅራቢ ተቋማት ብቃታቸው ተረጋግጦ ለአገልግሎት ዝግጁ መሆናቸውን ጠቁሟል፡፡
በሆቴል ዘርፉ በተደረጉ የቁጥጥር ሥራዎች ጉድለት የታየባቸው 2 ሆቴሎች ላይ እርምጃ መወሰዱንና እንግዶች የሚያርፉባቸውን ሆቴሎች፣ ሬስቶራንቶችና የመዝናኛ ስፍራዎች የንጽህናና የደህንነት ደረጃዎች የማረጋገጥ ሥራው መቀጠሉን ባለሥልጣን መ/ቤቱ አስታውቋል፡፡
ጳጉሜ 4 በሚመረቀው የታላቁ ህዳሴ ግድብ ላይ የአገራት መሪዎችን ጨምሮ በርካታ ተጋባዥ እንግዶች እንደሚመጡ የሚጠበቅ ሲሆን፤ በአህጉር አቀፉ የአፍሪካ የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ ላይ 25 ሺ ሰዎች እንደሚሳተፉ ይታወቃል፡፡
May be an image of skyscraper, twilight and road
 
 
 
 
 
አሜሪካ የኢትዮጵያ ጽኑ አጋር ሆና ትቀጥላለች ሲሉ በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ኤርቪን ማሲንጋ ገለጹ፡፡
አምባሳደሩ ይህን የገለጹት ለኢትዮጵያውያን የአዲስ ዓመት መልካም ምኞታቸውን ባስተላለፉበት መልዕክት ነው፡፡
አምባሳደር ማሲንጋ፣ የአገሪቱን የጥንት ታሪክና ባህላዊ ቅርሶች እንዲሁም ለዓለም ያበረከተችውን ታላቅ አስተዋጽኦም አድንቀዋል።
አዲሱ ዓመት ለኢትዮጵያ ሕዝብ ብሩህ ተስፋን የሚያመጣና በሁለቱ አገሮች መካከል ያለውን ወዳጅነት የበለጠ የሚያጠናክር ይሆናል የሚል እምነት እንዳላቸውም በመልካም ምኞት መልዕክታቸው ጠቁመዋል፡፡
May be an image of 1 person
 
 
 
 
የሩሲያው ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን፣ ዘለንስኪን ወደ ሞስኮ የጋበዙት ለውይይት እንጂ እጅ እንዲሰጥ አይደለም ሲል ክሬምሊን ባወጣው መግለጫ አመለከተ፡፡
“ይህ ነው የፑቲን ሀሳብ ነው” ያሉት ዲሚትሪ ፔስኮቭ፤ ዘለንስኪ ሃሳቡን ውድቅ እንዳደረገ ተመልክተናል ብለዋል።
ዘለንስኪ የሰላም ድርድር ለማድረግ ወደ ሞስኮ መምጣት እንደሚችሉ ፑቲን በቤጂንግ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ መናገራቸው ይታወሳል፡፡
የፑቲንን ግብዣ ተከትሎ ዩክሬን ፤“በሞስኮ የሚደረግ ስብሰባ ተቀባይነት የለውም” ስትል ጥሪውን ውድቅ አድርጋለች፡፡
"ፑቲን ዘለንስኪን ወደ ሞስኮ የጋበዙት እጅ እንዲሰጥ አይደለም" ብሏል ክሬምሊን በመግለጫው፡፡
May be an image of 2 people and text that says 'SPUTNIK'
 
 
 
 
Page 10 of 790