Administrator

Administrator

ቋሙ በአፍሪካ የአይቲ ማዕከል ለመሆን እየሰራ መሆኑ ተጠቁሟል


       በአፍሪካ የአይቲ ማዕከል ለመሆን ራዕይ ሰንቆ በአዲስ መልክ እየተዋቀረና እየተደራጀ መሆኑ የተነገረለት የአይቲ ፓርክ ኮርፖሬሽን፤ ከሁለት ሳምንት በኋላ በይፋ  ሥራ እንደሚጀምር ተገለጸ፡፡ በአይቲ ፓርኩ፣ በኢትዮጵያ የመጀመሪያ  የሆነው  የግል  የዳታ ማዕከል አገልግሎት መስጠት መጀመሩም ተጠቁሟል፡፡
ይህ ይፋ የተደረገው ባለፈው ረቡዕ ጠዋት በሸራተን አዲስ ሆቴል፣ “የዳታ ማዕከል አገልግሎት ሥነምህዳር ዕድሎችን ለፋይናንስ ዘርፉና ለቴክኖሎጂ ኢንዱስትሪው ማመቻቸት” በሚል ርዕስ፣ ለግማሽ ቀን በተካሄደ ጉባኤ ላይ ሲሆን፤ ጉባኤውን የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር፣ የአይቲ ፓርክ ኮርፖሬሽንና የዊንጉ አፍሪካ ዳታ ማዕከል  በትብብር እንዳዘጋጁት ታውቋል፡፡
የአይቲ ፓርክ ኮርፖሬሽኑን  የሚያስተዳድረው የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትሩ ዶ/ር በለጠ ሞላ በጉባኤው መክፈቻ ላይ እንደገለጹት፤የኢትዮጵያን የዲጂታል ሽግግር እውን በማድረግ ረገድ አይቲ ፓርኩ ጉልህ ሚና የሚጫወት ይሆናል፡፡ ከዚህ አንጻር ጉባኤው ወቅታዊና ተገቢ መሆኑን ሚኒስትሩ አስምረውበታል፡፡
የአይቲ ፓርክ ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ሔኖክ አህመድ በበኩላቸው በሰጡት ማብራሪያ፣ የኮርፖሬሽኑ ትልቁ ዓላማው ቢዝነስ መሥራት የሚያስችል ሥነምህዳር መፍጠር መሆኑን ጠቁመው፤ ለዚህም ሁሉም በጋራ የሚጠቀምበት ሪሶርስ በአንድ ቦታ ያቀርባል ብለዋል፡፡
 ራዕያችን የአፍሪካ የአይቲ ማዕከል መሆን ነው ያሉት ዋና ሥራ አስፈጻሚው፤ ይህን ለማሳካትም  የቴክኖሎጂ ሽግግርን በማምጣትና አቅምን በማሳደግ ዓለማቀፍ ተወዳዳሪነትን ማጎልበት እንደሚያስፈልግ አጽንኦት ሰጥተው ተናግረዋል፡፡
በዛሬው ጉባኤ ላይ  በኢትዮጵያ የመጀመሪያውን የግል የዳታ ማዕከል፣ በአይቲ ፓርክ ገንብቶ አገልግሎት መስጠት መጀመሩን የጠቆመው ዊንጉ አፍሪካ የዳታ ማዕከል ኩባንያ፤ በምሥራቅ አፍሪካ ኢትዮጵያ፣ ጅቡቲ፣ ሶማሊላንድና ታንዛንያን  ጨምሮ በአራት አገራት በዘርፉ አስተማማኝ አገልግሎት እየሰጠ  የሚገኝ ስመ-ጥር ኩባንያ ነው ተብሏል፡፡   
ኩባንያቸው በቀጣናው ተጠቃሽ  የዳታ ማዕከል አገልግሎት አቅራቢ መሆኑን የገለጹት የዊንጉ አፍሪካ ዳታ ማዕከል  ካንትሪ ዳይሬክተር አቶ ተሾመ፤ በኢትዮጵያም ዓለማቀፍ ደረጃውን የጠበቀ አስተማማኝ የዳታ ማዕከል መገንባቱን ጠቁመው፤ በዋናነት  የፋይናንስ ዘርፉና የቴክኖሎጂ ተቋማት የአገልግሎቱ ተጠቃሚ እንደሚሆኑ ተናግረዋል፡፡ዊንጉ አፍሪካ ወደ ኢትዮጵያ ገብቶ ሥራ ከጀመረ 18 ወራት ማስቆጠሩን የጠቆሙት ዳይሬክተሩ፤ የዚህ ጉባኤ አንዱ ዓላማ እነዚህ የፋይናንስና ቴክኖሎጂ ተቋማት ከፍተኛ ወጪ አውጥተው፣ የየራሳቸውን የዳታ ማዕከል ከመገንባት ይልቅ በኛ ማዕከል ቢጠቀሙ፣ የበለጠ እንደሚያዋጣቸው መረጃና ግንዛቤ ለመስጠት ነው ብለዋል፡፡ ጉባኤው አጋርነትና ትብብር የመፍጠሪያ መድረክ እንደሚሆንም ጨምረው አመልክተዋል፡፡
የዳታ ማዕከሉን ከሚመሩት ውስጥ 90 በመቶው ኢትዮጵያውያን መሆናቸው የገለጹት የኩባንያው አመራሮች፤ ማዕከሉ ለወጣት ኢትዮጵያውያን የቴክኖሎጂ ኢንጂነሮች ትልቅ የሥራ ዕድል መፍጠሩን አውስተዋል፡፡የዘርፉ ዓለማቀፍ ተዋናዮች በአጋርነት አብረውን እንዲሰሩ መሳብ ችለናል ያሉት አመራሮቹ፤ የመንግሥት ደንብና መመሪያዎች ወጥተው እንደተጠናቀቁ እኒህ ተዋናዮች ወደ ኢትዮጵያ እንደሚገቡ ገልጸዋል፡፡ ማይክሮሶፍት፣ ቲክቶክና ሜታ (የቀድሞው ፌስቡክ) የመሳሰሉ ግዙፍ ዓለማቀፍ የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች ወደዚህ አገር እንዲመጡም እየሰራን ነው ብለዋል - የዊንጉ አፍሪካ ዳታ ማዕከል ኩባንያ  አመራሮች፡፡ የዊንጉ አፍሪካ ዳታ ማዕከል፣ በ50 ሚሊዮን ዶላር ወጪ መገንባቱ  ይታወቃል፡፡በዚህ ለግማሽ ቀን በሸራተን አዲስ በተካሄደው ጉባኤ ላይ፣ የአይቲ ኢንዱስትሪው መሪዎች፣ የመንግሥት ከፍተኛ ባለሥልጣናትና የፋይናንስ ተቋማት አመራሮች ተሳትፈዋል፡፡


 በኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን የድሬዳዋ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በኩል በህጋዊ ሽፋን ያለ በቂ ቀረጥ እየገባ ያለ  ኮንትሮባንድ ምርት መበራከቱ በአገር ውስጥ አምራቾች እና ህጋዊ ነጋዴዎች ላይ ከፍተኛ ጫና እየፈጠረ ነው ተባለ፡፡
ከጊዜ ወደ ጊዜ በኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን የድሬዳዋ ቅርንጫፍ በኩል ያለበቂ ቀረጥ ከፍተኛ የሆነ ምርት በፍራንኮ ቫሉታ እየገባ ነው የሚሉት አምራቾች እና ነጋዴዎች ይህ ሁኔታ በስራቸው ላይ ከፍተኛ ጫና እየፈጠረና ከስራቸው እያፈናቀለን  ነው ሲሉ ቅሬታ አቅራቢዎቹ  ለአዲስ አድማስ ተናግረዋል፡፡
በጉዳዩ ላይ ለሚመለከተው የመንግስት አካል ተደጋጋሚ አቤቱታ አሰምተናል የሚሉት ቅሬታ አቅራቢዎች ችግሩ ከጊዜ ወደ ጊዜ ሲባባስ እንጂ ምንም የመርገብ ምልክት አልታየበትም ብለዋል፡፡
እንደመረጃ ምንጮች በተለይ ከፍተኛ ዋጋ የሚያወጡ የግንባታ እቃዎች እና መሰል ሌሎች ሸቀጦች መዳረሻቸውን መሃል አገር አድርገው በድሬዳዋ ጉምሩክ በሚወጣ ዲክላራሲዎን ምንም በሚባል ቀረጥ እየገቡ በገበያ ውስጥም ከፍተኛ ጫና ፈጥረዋል ሲሉ አክለዋል፡፡
ይህ ሁኔታ የአገር ውስጥ አምራች እና ህጋዊ ምርት አስገቢዎችን ብቻ ሳይሆን አገሪቷ ከዘርፉ ማግኘት የሚገባትን በቢሊዎን ብሮች የሚቆጠር የመንግስት የቀረጥ ገቢም እንድታጣ ምክንያት ሆኗል ሲሉ ነው ያከሉት፡፡
በማሳያነት የቆርቆሮ እና አርማታ ብረት ህገወጥ እንቅስቃሴን የሚጠቅሱት ቅሬታ አቅራቢዎች የጉምሩክ ኮሚሽን ከሰሞኑ ከኢትዮጵያ መሰረታዊ ብረታ ብረት ኢንዱስትሪዎች ማህበር አመራሮች ጋር ስለችግሩ መምከሩን መግለጹ የችግሩን መኖር አመላካች ነው ብለዋል፡፡
ምንም እንኳን ኮሚሽኑ ስለጉዳዩ መወያየቱን ቢገልፅ የችግሩን መኖር በይፋ አላመነም ያሉት ቅሬታ አቅራቢዎች በጥቅሉ ያሉ ችግሮችን እፈታለው ብሎ መግለጹ ተገቢ አይደለም ብለዋል፡፡
የጉምሩክ ኮሚሽን በማህበራዊ ገጹ ስለውይይቱ ባጋራው መረጃ የኢትዮጵያ መሰረታዊ ብረታ ብረት እና ኢንጂነሪንግ  ኢንዱስትሪዎች ማህበር ዋና ስራአስኪያጅ አቶ ሰለሞን ሙሉጌታ፣ ዘርፉ የውጭ ምንዛሬን በማስገኘትና ለዜጎች የስራ እድል በመፍጠር ረገድ እያበረከተ የሚገኘው አስተዋጽኦ ከፍተኛ ነው ማለታቸውን ጠቅሶ ከጉምሩክ ኮሚሽን አመራሮች ጋር የተደረገው ውይይትም እየገጠሙ የሚገኙ ችግሮችን ለመፍታት እንደሚያግዝ ተናግረዋል ሲል አክሏል፡፡
የጉምሩክ ኮሚሽን ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሙሌ አብዲሳ በበኩላቸው የሐገር ውስጥ የብረት አምራቾች የሚያነሱትን ጥያቄ ለመመለስ ኮሚሽኑ ልዩ ትኩረት ሰጥቶ ይሰራል ብለዋል፡፡
እንደ ቅሬታ አቅራቢዎች ገለፃ ከፍተኛ የሆነ የብረት ምርት በፍራንኮ ቫሉታ እየገባ መሆኑን ጠቅሰው ይህ እጅግ አነስተኛ ቀረጥ እየተከፈለበት የሚገባ ምርት ገበያውንም በማጥለቅለቅ የአገር ውስጥ አምራቾችን በእጅጉ እየጎዳና አንዳንዶቹም ስራ ለማቆም እንዲገደዱ እያደረገ ነው ተብሏል፡፡
አዲስ አድማስም የተለያዩ የጉምሩክ ሰነዶችን ማየት የቻለ ሲሆን፡፡ ሰነዶቹ  የተለያዩ ግለሰቦች የተለያየ መጠን ያለው ብረት ከመደበኛው ማስቀረጫ መጠን እጅጉ ያነሰ ቀረጥ ተከፍሎባቸው የብረት ምርቱ እንደገባ ያሳያል፡፡
እስከ 300 ሺ ቶን ብረት በአንድ የጉምሩክ ሰነድ በአንድ ግለሰብ እንዲገባ መፈቀዱን የጠቀሱት የመረጃ ምንጮች፡፡ በተመሳሳይ 120 ሺ ቶን፣ 150 ቶን በሌላ ግለሰብ እንዱም ሌሎች በርካታ የብረት ጭነቶች በተለያዩ ግለሰቦች ስም በድሬዳዋ ጉምሩክ ቅርንጫፍ በኩል እንዲገቡ ይሁንታ ያገኙበት ሰነዶችምን በመረጃነት ቀርበዋል ።
ባለፉት ጥቂት ወራት የወጡት የጉምሩክ ሰነዶች እንደሚያሳዩት ግለሰቦቹ የከፈሉት የጉምሩክ ቀረጥ መጠንም በኪሎ ግራም ከ92 ሳንቲም፣ 74 ሳንቲም እና 50 ሳንቲም ብቻ መሆኑን የተረዳን ሲሆን፡፡በአንጻሩ በተመሳሳይ ወቅት በህጋዊ መልኩ የገባ ብረት በኪሎ ግራም 35 ብር አካባቢ እንደተከፈለባቸው  ያገኘናቸው የጉምሩክ ሰነዶች ያሳያሉ፡፡ በመሆኑም በህጋዊ የጉምሩክ ሰነድ እጅግ ባነሰ የቀረጥ መጠን እየገቡ የሚገኙት ብረቶች የሁለት አስገቢዎች ብቻ ተሰልቶ እንኳን ለአገሪቱ መግባት የነበረበትን ከ 14 ቢሊየን ብር በላይ ያሳጣ ነው ሲሉ ቅሬታ አቅራቢዎች ያብራራሉ፡፡በጉዳዩ ከትናንት በስቲያ  መግለጫ የሰጠው የመሰረታዊ ብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ  ኢንዱ ስትሪዎች ማህበር ልዩ ልዩ የማጭበርበሪያ ዘዴ እና ህጋዊ ሽፋን በመጠቀም እየገባ የሚገኝ የተለያየ የብረት ምርት በአምራች ኢንደስትሪው ህልውና ላይ አደጋ ጋርጧል ሲል አስታውቋል፡፡
የማህበሩ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ሰለሞን ሙሉጌታ በመግለጫው እንደተናገሩት 76 የሚሆኑ የማህበሩ አባላት አርማት ብረት (Reienforcment bar)፥ ጋልቫናይዝድ ቆርቆሮ (Galvanized sheet)፥ ቱቦላሬና የበርና የመስኮት ዘንጎች( Tubular sections)፥ እንዲሁም ልዩ ልዩ የብረታብረት ኢንጂነሪንግ ምርት ውጤቶች ለመሰረተልማት የጀርባ አጥንት የሆኑ የኮንስትራክሽን ግብአቶችን እንደሚያስመጡ ገልጸዋል። አያይዘውም በአገራችን የሚገኙ ኢንዱስትሪዎች የብረት ማምረት አቅም  10 ሚሊዮን ቶን በአመት መድረሱንና  በአንጻሩ ፍላጎት ደግሞ እስከ 2 ሚሊዮን ቶን በአመት እንደሚሆን ይገመታል ብለዋል።
ይህም ሆኖ ያለቀላቸው ምርቶች ከውጭ አገር በህጋዊ መንገድና ስርአትን ባልተከተል መንገድ የሚገቡ በመሆኑ በገበያው ላይ ኢ-ፍትሃዊ የንግድ ውድድር በመፍጠር ኢንዱስትሪዎች ላይ የህልውና አደጋ  እንዲጋረጥባቸው እያደረጉ ይገኛል ሲሉ ነው ያከሉት።
እነዚህን ምርቶች የሚያመርቱ የአገር ውስጥ አምራቾችን ከገበያ ውጭ ሊያደርጉ የሚችሉ የኮንትሮባንድና ሌሎች ህግን ሽፋን አድርገው የሚፈፀሙ ህገ ወጥና ምንጫቸው ያልታወቁ ምርቶች ከማምረቻ ዋጋ በታች በሆነ ዋጋ የሚሸጡና ከደረጃ በታች የሆኑ ምርቶች ገበያውን እየተቆጣጠሩት በመምጣታቸው በተለያዩ መድረኮች ድምፃችንን በማሰማትና ለሚመለከታቸው ሁሉ አቤቱታችንን በደብዳቤ ጭምር እያሳወቅን ቆይተናል ያሉት የማህበሩ ዋና ስራ አሰስኪያጅ።
በአሁኑ ወቅት ለቆርቆሮ ለቱቦላሬ ምርት የሚያገለግሉ የጥቅል ጥቁር ብረቶችና የአርማታ ብረት ምርቶች በህገ ወጥ መንገድ ወደ አገር ውስጥ ማስገባት  በስፋት እየታየ እንደሚገኝ መረጃዎች እየደረሱን ይገኛሉ ሲሉ ነው ያከሉት።
ማህበራቸው የዘርፉን አጠቃላይ ሁኔታ የመቃኘትና የመከታተል ኃላፊነቱን በመወጣት ሂደት ላይ ሳለ በቀርቡ  ለማመን የሚያስቸግሩ መረጃዎች እየደረሱት መሆኑን አቶ ሰለሞን ጠቅሰው፤  እነዚህ መረጃዎች እንደሚያሳዩት በቢሊዮኖች የመንግስትን ገቢ ሊያስቀሩ የሚችሉና የአገር ውስጥ አምራቾችን ሙሉ ለሙሉ ሊያዘጉ የሚችሉ ችግሮች ሆነው አግኝተናቸዋል ብለዋል። በመሆኑም በዚህ መንገድ ፈፅሞ ሊታመን በማይችልና በየትኛውም ዓለም ሊኖር በማይችል ዋጋ የብረታ ብረት ምርቶች እንደተገዙ ተደርጎ የጉምሩክ ቀረጥ ለማስፈፀም ማቅረብ ምን ያህል የአገሪቱን ኢኮኖሚ እንደሚጎዳ የሚታወቅ ሲሆን በተለይ ደግሞ ከፍተኛ መዋለ ንዋይ አፍስሰው በማምረት ተግባር ላይ የተሰማሩትን የአገረ ውስጥ አንዱስትሪዎች አሽመድምዶ ከገበያ ውጭ ሊያደርጋቸው የሚችል ድርጊት እንደሚሆን ለማንም ግልፅ ነው ሲሉ የችግሩን አሳሳቢነት ገልጸዋል።ኢትዮጵያ ከሜዳዋ ውጪ ማሊን 2ለ0 አሸነፈች

የሴቶች ከ20 ዓመት በታች የዓለም ዋንጫ ማጣርያ ኢትዮጵያ ከሜዳዋ ውጪ ማሊን 2ለ0 አሸንፋለች።

የማሸነፊያ ጎሎቹንም ንግስት በቀለ በ57ኛው፣ እሙሽ ዳንኤል በ68ኛው ደቂቃ ለኢትዮጵያ አስቆጥረዋል።

የመልሱ ጨዋታ እሁድ ህዳር 9 በአዲስ አበባ አበበ ቢቂላ ስታዲየም ይደረጋል።

የቴሌግራም ቻናልችንን በመቀላቀል የአዲስ አድማስን መረጃ ይከታተሉ…
https://t.me/AdissAdmas

በዛሬዉ እለት በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንሰቲትዩት  በመገኘት ለሁለት  ወራት  ስለሰዉሰራሽ አስተዉሎት  ቴክኖሎጅ ምንነት እና ጠቀሜታ ስልጠና ተከታትለዉ የተመረቁ የነገ ሀገር ተረካቢ ወጣቶችን ተመልክቻለሁ፡፡
ልጆቻችን የኢትዮጵያን ችግሮች በሰዉ ሰራሽ አስተዉሎት  በመታገዝ ለመፍታት ቁልፍ የሆነዉን እዉቀት መገብየታቸዉ ተስፋ ሰጭ ነዉ፡፡
በልጆቹ አቅም በመገረም የሃገራችንን እድገት ለማረጋገጥ እንደሚችሉ ሙሉ እምነት አለኝ፡፡

ሉላ ገዙ፣ የሮያል ፎምና ፈርኒቸር ብራንድ አምባሳደር ሆነች

 የኢቢኤስ ፕሮግራም አቅራቢዋና የማስታወቂያ ባለሙያዋ ሉላ ገዙ፤ የሮያል ፎምና ፈርኒቸር ብራንድ አምባሳደር ሆና ተመረጠች፡፡

ሉላ ገዙ፤ ለቀጣዮቹ  4 ዓመታት የሮያል ፎምና ፈርኒቸር ብራንድ አምባሳደር ሆና ለመሥራት በዛሬው ዕለት ከሮያል ግሩፕ አመራሮች ጋር   በይፋ  ተፈራርማለች።

የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን የተኩስ አቁሙ ትክክለኛ እና በቀጣናው የሚፈለገውን መሻሻል ለማምጣት ሚናው ከፍተኛ ነው ሲሉ አወድሰዋል፡፡

የተሰኩስ አቁሙ በዋናነት በሥፍራው የሚገኙ ንጹሃን ዜጎችን ከአካባቢው እንዲሸሱ ለማድረግ ያለመ መሆኑ ነው የተገለጸው፡፡

ከዚህ ባለፈም በቦታው ችግር ውስጥ ለሚገኙ ዜጎች አስፈላጊውን የሰብዓዊ እርዳታ ለማድረሰ እንደሚያስችል ተመላክቷል፡፡

የእስራኤል ጦር ከዚህ በፊት በጋዛ ለሚኖሩ ንጹሃን ዜጎች የሰብዓዊ እርዳታ እንዲደርስ “ታክቲካል የተኩስ አቁም” እንደሚያደርግ ማስታወቁን ቢቢሲ በዘገባው አስታውሷል፡፡


የተለያዩ ሀገራት ወታደራዊ አታሼዎች ታላቁን የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ጎበኙ።
መቀመጫቸውን በአዲስ አበባ ከተማ ላደረጉ የተለያዩ ሀገራት ወታደራዊ አታሼዎች በጉባ ጉብኝታቸው፤ በታላቁ ህዳሴ ግድብ ፕሮጀክት ስራ አስኪያጅ ኢንጂነር ክፍሌ ሆሮ ማብራሪያ ተሰጥቷቸዋል።
ውሃው ተርባይኑን መትቶ ወደ ተፈጥሮአዊ ፍሰቱ የሚመለስና በአባይ ወንዝ ተፋሰስ ሀገራት የሚያመጣው ችግር እንደሌለ መመልከታቸውንም ወታደራዊ አታሼዎቹ በአስተያየታቸው ገልጸዋል።
ከዘጠና ሰባት መቶኛ በላይ የተጠናቀቀው ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ከኢትዮጵያ ባለፈ በከፍተኛ የሀይል እጥረት የምትታወቀውን አፍሪካ ልማት የሚያፋጥንና ለቀጠናዊም ሆነ አህጉራዊ የኢኮኖሚ ትስስር የራሱን በጎ ሚና የሚጫወት አቅም እንደሆነም ነው በጉብኝቱ የተገለጸው።
ኢትዮጵያ ገና በጥቅም ላይ ያልዋሉ እምቅ የተፈጥሮ ሃብት እንዳላት የተናገሩት አስተያየት ሰጪ ወታደራዊ አታሼዎቹ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ሆና ግዙፉን የህዳሴ ግድብ እውን ማድረግ መቻሏ ሙሉ ለሙሉ የተሟላ ሰላም ካሰፈነች በፍጥነት ማደግ የምትችል ስለመሆኗም ነው የተናገሩት።
ጉብኝቱን ያመቻቸው የመከላከያ ውጭ ግንኙነት እና ወታደራዊ ትብብር ዋና ዳይሬክቶሬት ሲሆን ወደ ስልሳ የሚጠጉ ሀገራት ወታደራዊ አታሼዎች ግድቡን ጉብኝተዋል።

የቴሌግራም ቻናልችንን በመቀላቀል የአዲስ አድማስን መረጃ ይከታተሉ…
https://t.me/AdissAdmas

በቢኒያም አቡራ የተዘጋጀውና "ወደ ፍቅር ጉዞ" የተሰኘው፣ የአንጋፋውን ድምጻዊ ቴዎድሮስ ካሣሁን የዘፈን ግጥሞች የሚዳስሰው መጽሐፍ ዛሬ ከ11፡30 ጀምሮ በወመዘክር አዳራሽ እንደሚመረቅ ደራሲው ለአዲስ አድማስ አስታውቋል፡፡

መጽሐፉ በስድስት ምዕራፎች ተከፋፍሎ በ206 ገጾች የተቀነበበ ሲሆን፤ በ320 ብር  ለገበያ ቀርቧል ተብሏል።

ቢኒያም አቡራ፤ ከዚህ ቀደም የተወዳጇን ድምጻዊት እጅጋየሁ ሽባባው የዘፈን  ግጥሞች የሚዳስስ “ባለቅኔዋ ሶሪት” የተሰኘ  መጽሐፍ ማሳተሙ  አይዘነጋም።     

 የቴሌግራም ቻናልችንን  በመቀላቀል የአዲስ አድማስን መረጃ ይከታተሉ…
https://t.me/AdissAdmas                                  

የኢፌዲሪ የትምህርት ሚኒስትር እና የዩኔስኮ ብሄራዊ ኮሚሽን ፕሬዝዳንት ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ከዩኔስኮ አጠቃላይ ኮንፈረንስ ጎን ለጎን ከአለም አቀፍ የትምህርት ቢሮ (UNESCO-IBE) ቦርድ ፕሬዝዳንት ስቪን ኦስትቬት ጋር በፈረንሳይ በሚገኘው የዩኔስኮ ዋና መስሪያቤት የጎንዮሽ ውይይት አካሂደዋል።
በውይይታቸውም ሚኒስትሩ የኢትዮጵያን የትምህርት ሥርዓት ለማሻሻል እና ለማዘመን ያከናወናቸውንና በመተግበር ላይ ያሉ የለውጥ ተግባራትን አቅርበዋል።
ፕሮፌሰር ብርሃኑ ኢትዮጵያ በተለይም በዘርፉ በተለዩ የትምህርት መስኮች ላይ የውጭ ልምድ እንደሚያስፈልጋት በአጽናኦት የተናገሩ ሲሆን የዩኔስኮ-አይቢኢ የቦርድ ፕሬዝዳንቱ በበኩላቸው የትምህርት ስርዓቱን በአዲስ መልክ ለማሻሻልና ለማዘመን ሚኒስቴሩ የሚያደርጉትን ጥረት አድንቀው ቢሮው ጥረታቸውን ለመደገፍ ዝግጁ መሆኑን ገልጸዋል።
H.E. Professor Berhanu Nega discusses with the President of the UNESCO-IBE Board, Svein Osttveit
_______________________
H.E. Professor Berhanu Nega, the Minister of Education of the Federal Democratic Republic of Ethiopia and the President of the National Commission for UNESCO discusses at a sideline meeting with the President of the International Bureau of Education (UNESCO-IBE) Board, Svein Osttveit at the UNESCO headquarters office in Paris, France.
During the conference, Professor Berhanu Nega presented the steps the Ethiopian Ministry of Education has done to improve the curriculum and reform the educational system.
H.E. the Minister emphasized that the country needs foreign experience in the fields under consideration. President Svein Osttveit, for his part commended the Ministry's dedication to restructuring the educational system and stated that the Bureau is prepared to support the Ministry in its efforts to update the curriculum and enhance the educational system.
 ዋና ዋና የጥቁር አዝሙድ የጤና ጥቅሞች
 
1️⃣ ለካንሰር በሽታ
የክሮሺያ ሳይንቲስቶች በጥቁር አዝሙድ ዘይት ውስጥ ስለሚገኙ ሁለት ፋይቶ ኬሚካሎች እንዴት ካንሰርን እንደሚከላከሉ ጥናት አድርገው ነበር።
በጥናታቸውም መሠረት እነዚህ በጥቁር አዝሙድ ዘይት ውስጥ የሚገኙ ሁለት ኬሚካሎች (ታይሞኪውኖን እና ታይሞሃይድሮኪውኖን) ካንሰርን የሚያስከትሉ ቲውመር ሴሎችን በ 52% (በሃምሳ ሁለት ፐርሰንት) መከላከል እንደሚችሉ ማረጋገጥ ችለዋል፡፡
በሁለቱ ኬሚካሎች መበልፀጉ ጥቁር አዝሙድን የተለየ ያደርገዋል ይህም ካንሰርን በተለያዩ መንገዶች ለመከላከል እና ለማከም ይረዳል፡፡
2️⃣ ለጉበት ጤንነት
ጉበት ለሰውነታችን በጣም አስፈላጊ ከሆኑ የሰውነት ክፍሎች ውስጥ አንዱ ነው፡፡
ወደ ሰውነታችን የገባ ማንኛውም መርዛማ ነገር በጉበት አማካይነት ይረክሳል፤ ከጉበት የሚገኘው የሃሞት ፈሳሽ፤ ስብን ወይም ፋትን በመፍጨት እንዲሁም አእምሮና ሰውነታችን ደስተኛና ጤናማ በማድረግ ቁልፍ የሆነ ሚና በመጫወት ይጠቅመናል፡፡
በመድሃኒቶች ምክንያት የሚከሰት የጎንዮሽ ጉዳት፣ በአልኮል መጠጦችና በተለያዩ በሽታዎች ጉበታቸው ለተጎዳ ወይም ስራውን ለቀነሰባቸው ሰዎች፤ የጥቁር አዝሙድ ዘይት ጉበት ለማገገም ወይም ለመዳን የሚያደርገውን ሂደት በሚገርም ሁኔታ ያፋጥናል፡፡
3️⃣ ለስኳር በሽተኞች!
በህንድ የህክምና ቡድን ተጠንቶ ለህትመት የበቃው ጥናት እንደሚሳየው የጥቁር አዝሙድ ዘይት የጣፊያ ቤታ ሴሎች በፍጥነት እንዲያገግሙ ያደርጋል።
በደም ውስጥ በዝቅተኛ መጠን የሚገኘውን የኢንሱሊን መጠን እንዲጨምር እና በደም ውስጥ ጨምሮ የሚገኝውን የስኳር መጠን እንዲጨምር ያደርጋል፡፡
እንደሚታወቀው ኒጌላ ሳቲቫ (Nigella Sativa) በተክሎች ላይ ከሚገኙ ጥቂት ንጥረ ነገሮች ውስጥ አንዱ ሲሆን ዓይነት 1 እና ዓይነት 2 የስኳር በሽታዎችን ለመከላከል ይረዳናል፡፡
4️⃣ የሰውነት ክብደት ለመቀነስ!
ፀረ-ውፍረት ባህሪ ያላቸው ተክሎች የትኞቹ እንደሆኑ ለመለየት የተደረገ አንድ ጥናት እንደሚያሳየው የጥቁር አዝሙድ ዘይት ውጤታማ ተፈጥሮአዊ የውፍረት መከላከያ መሆኑን አረጋግጠዋል፡፡
የጥቁር አዝሙድ ዘይት የሰውነት ክብደትን ሊጨምሩ የሚችሉ ሁኔታዎችን በመግታት ወይም በማስተካከል ይረዳናል። ከእነዚህም መካከል:-
???? የምግብ ፍላጎት
???? ግሉኮስን በአንጀታችን ውስጥ መምጠጥ
???? የደም ስኳር መጠን
???? ኮሌስትሮል እና
???? ትራይግላይሴራይድስ ናቸው።
5️⃣ ለፀጉር መሳሳት!
ከብዙዎቹ ልዩ የሆኑ የጥቁር አዝሙድ ጥቅሞች ውስጥ አንዱ የፀጉር መሳሳትን ወይም መመለጥን መከላከሉና በፍጥነት እንዲያገገም ማድረጉ ነው፡፡
ይህ እንዴት እንደሆነ የሚታወቅ ባይሆንም ለመገመት ግን በጣም ቀላል ነው።
ይህም ጥቁር አዝሙድ ከፍተኛ የሆነ ፀረ-ኦክሲዳንት እና ፀረ-ባክቴሪያ ባህሪ ስላለው ነው፡፡
6️⃣ ሜላኒን እንዳይጎዳ ይከላከላል!
ሜላኒን የቆዳ ቀለም ሲሆን ቆዳችን ጉዳት እንዳይደርስበት በመከላከል ይጠቅመናል፡፡
ለአይናችን፣ ለቆዳችን እንዲሁም የራሳችን ቀለም እንዲኖረን በማድረግ ከፍተኛ የሆነ ሚናን የሚወጣ ኬሚካል ነው፡፡
ከሜላኒን ጋር የተያያዙ የቆዳ በሽታዎች እንዲያገግሙ ይረዳናል፡፡
7️⃣ ኢንፌክሽንን ለመከላከል!
ኢንፌክሽን አለም አቀፍ ስርጭት ያለውንና ሜቲሲሊን ረዚስታንት ወይም በሜቲሲሊን መድሃኒት የማይሞተው ስታፋሎኮከስ አውረስ (Staphylococcus aureus) የተባለውን ባክቴሪያ፤ የጥቁር አዝሙድ ዘይት በመግደልና በማጥፋት ይጠቅመናል፡፡
ጽሑፉን ከወደዱት (Like) በማድረግ ለሌሎችም (share) ያድርጉት፡፡ ቸር እንሰንብት
 
Page 6 of 678