Administrator

Administrator

አሸናፊዎች በአሜሪካ በሚካሄደው ዓለማቀፍ የሮቦቲክስ ውድድር ላይ ይሳተፋሉ


3ኛው ዙር የአፍሪካን ሮቦቲክስ ሻምፒየንሺፕ ውድድር ከመጋቢት 4 እስከ 6 ቀን 2017 ዓ.ም በአዲስ አበባ ሳይንስ ሙዚየም እንደሚካሄድ ኢትዮ ሮቦቲክስ አስታወቀ፡፡ ከፊታችን ሐሙስ ጀምሮ ለሦስት ተከታታይ ቀናት በሚካሄደው በዚህ ውድድር የመጀመሪያ ደረጃ፤ የሁለተኛ ደረጃ፣ የኮሌጅና የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች እንደሚወዳደሩ የተገለጸ ሲሆን፤ውድድሩ በዲዛይኒንግ፤ በኢንጅነሪንግና በአውቶነመስ ኮዲንግ ላይ እንደሚያተኩር ታውቋል፡፡
በውድድሩ አሸናፊ የሚሆኑ ተማሪዎች የዋንጫ ሽልማቶችን የሚያገኙ ሲሆን፤ በኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር የተፈረመ ሰርተፊኬትም ይበረከትላቸዋል ተብሏል፡፡ በዚህ ውድድር በአዲስ አበባ የሚኖሩ አፍሪካውያንም የሚካፈሉ ሲሆን፤ ለፍጻሜ የሚበቁ ተማሪዎች አገራቸውን ወክለው በአሜሪካ በሚካሄደው ዓለማቀፍ የሮቦቲክስ ውድድር ላይ እንደሚሳተፉ የኢትዮ ሮቦቲክስ ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ሰናይክረም መኮንን ገልጸዋል።
ላለፉት 15 ዓመታት የነገዎቹን ኢንጂነሮችና ፕሮግራመሮች የመፍጠር ራዕይ ሰንቆ ሲሰራ የቆየው ማዕከሉ፤ ኢትዮጵያውያን ታዳጊዎች በዓለማቀፍ የሮቦቲክስ ውድድሮች ላይ እንዲሳተፉና ዓለማቀፍ ልምድና ተሞክሮ እንዲቀምሱ በማድረግ ረገድ ጉልህ አስተዋጽኦ እያበረከተ ይገኛል፡፡ ባለፈው ዓመት በቻይና ሻንጋይ በተካሄደው ኢንጆይ ኤአይ ዓለማቀፍ የሮቦቲክስ ውድድር ላይ 21 ኢትዮጵያውያን ታዳጊዎች ሀገራቸውን ወክለው የተወዳደሩ ሲሆን፤ በውድድሩ ከተሳተፉ 27 የዓለም አገራት 3ኛ ደረጃን ይዘው ማጠናቀቃቸው ይታወሳል፡፡
በተመሳሳይ፣ ዓምና በአሜሪካ በተካሄደ የዓለም ሮቦቲክስ ሻምፒዮን የተሳተፉ ታዳጊዎች አስደማሚ ውጤት ያስመዘገቡ ሲሆን፤ ይህን ተከትሎም የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር “ታዳጊዎቹ ኢትዮጵያን በዓለም መድረክ ማስጠራት ጀምረዋል” ሲል ዕውቅና ሰጥቷል፡፡
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ዕውቅናና አድናቆት በመስጠት ብቻ ግን አልተወሰነም፡፡ ኢትዮ ሮቦቲክስ የጀመረውን ታዳጊዎችን በቴክኖሎጂ የማሰልጠንና የማብቃት ሥራን አጠናክሮ እንዲቀጥል ሙሉ ድጋፍ እያደረገ እንደሚገኝ ለማወቅ ተችሏል፡፡
የኢትዮ ሮቦቲክስ መሥራችና ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ሰናይክረም መኮንን እንደሚሉት፤ ማዕከላቸው ታዳጊዎችን ከማሰልጠንና በዓለማቀፍ ውድድሮች እንዲሳተፉ ዕድሎችን ከማመቻቸት የሚዘልቅ ራዕይን ሰንቋል፡፡ እንደ ቻይናና ሌሎች ያደጉ አገራት ሮቦቲክስ በመደበኛ የትምህርት ሥርዓት ውስጥ እንዲካተት ፍላጎት እንዳላቸው የተናገሩት ዋና ሥራ አስፈጻሚው፤ ለዚያም በትጋት እየሰራን ነው ብለዋል፡፡

 

“ጥራቱ የወረደ ምርት ወደ ገበያ እንዲገባ በጭራሽ አንፈቅድም”


በመዲናችን አዲስ አበባ ህገ-ወጥነትን በዘላቂነት ለመቆጣጠር ስለተቋቋመው የገበያ ማረጋጋትና ህገ ወጥ ንግድ ቁጥጥር ግብረ-ሃይል የከተማዋ ምክትል ከንቲባ እና የአዲስ አበባ ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ጃንጥራር አባይ ሲያስረዱ፤ ግብረ ሀይሉ ሰፋ ያሉ ተቋማትን ያቀፈ ነው ይላሉ - እነዚህም የገበያ ማረጋጋት፣ የገቢ አሰባሰብና የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ መሆናቸውን ይገልጻሉ፡፡
ግብረ ሃይሉ በውስጡ የንግድን፣ የከተማ ገቢን፣ የማህበራትን፣ የሰላምና ፀጥታን፣ የፖሊስን፣ የኢንዱስትሪን እንዲሁም የኮሙኒኬሽንን ተግባራት አቅፎ እንደሚገኝ የሚናገሩት ምክትል ከንቲባው፤ ግብረ ሃይሉ በየጊዜው ያደረጃጀት ለውጥ ቢያደርግም፣ ባለፉት ዓመታት የተለያዩ ሥራዎችን እያከናወነ መዝለቁን ጠቁመዋል፡፡
ግብረ ሃይሉ የተቋቋመው ተቋማቱ የሚሰሩትን ሥራ ለመተካት አለመሆኑን ሲያስረዱም፣ ይልቁንም ችግሮችን በቅንጅት ለመፍታትና ሥራዎችን በጋራ ለመሥራት የሚያስችል አደረጃጀት መሆኑን ይገልጻሉ፡፡
ግብረ ሃይሉ በዋናነት ገበያ ላይ የምርት እጥረት እንዳይፈጠር ሲሰራ መቆየቱን የጠቆሙት ም/ከንቲባ ጃንጥራር፤ ለዚህም ምርት የሚያቀርቡት እነማናቸው፣ እንዴት ይቀርባል የሚሉትን በማጣራትና በማጥናት ሥራ ላይ ማተኮሩን ተናግረዋል፡፡
“በአንድ በኩል የሰብል ምርት በማህበራት በኩል እንዲቀርቡ ማድረግ፣ የከተማ አስተዳደሩ ያቋቋመው የንግድ ስራዎች ድርጅት ምርት በቀላሉ ከአርሶ አደሩ ገዝቶ እንዲያቀርብ የሚያስችል አደረጃጀት መፍጠር፣ በግሉ ዘርፍ የሚቀርብ ምርት ህጋዊ የሆነ የግብይት ስርዓት ማምጣቱን እያረጋገጡ መምራት” ግብረ ሃይሉ የሚያከናውናቸው ሥራዎች ናቸው ብለዋል፡፡

ግብረ ሃይሉ መንግሥት ባቋቋማቸው የግብይት ማዕከላት ውስጥ አርሶ አደሩ በቀጥታ መጥቶ ምርቱን የሚሸጥበት ሁኔታ መመቻቸቱን የማየት፣ የመቆጣጠርና ድጋፍ የማድረግ ሥራ እንደሚሰራም ም/ከንቲባው ገልጸዋል፡፡
በተጨማሪም፣ የእሁድ ገበያዎች በትክክል እየተተገበሩ ነው ወይ፣ ግብይቱ ላይ በቂ ምርት አለ ወይ፣ ማነው ምርቱን የሚያቀርበው፣ የሚሸጡበት ዋጋ ትክክል ነው ወይ፣ የሚሉትን ጉዳዮች የማረጋገጥ ሥራ እንደሚሰራ ጠቁመው፤ እነዚህን ከማረጋገጥ አንፃር ሰፋፊ ስራዎች መከናወናቸውን አመልክተዋል፡፡
“በከተማችን ብዙ ዳቦ አምራች ፋብሪካዎች ተቋቁመዋል፤ ትልልቆቹን የሸገር ዳቦና የብርሃን ዳቦዎች ጨምሮ ሰፋ ያለ ቁጥር ያላቸው ከግል ተቋማት ጋር በትስስር ያቋቋምናቸው ዳቦ ቤቶች አሉ፡፡ በግልም የተቋቋሙ ዳቦ ቤቶች አሉ፡፡” ያሉት ም/ከንቲባው፤ “የዳቦ ምርት በተገቢው በገበያው ላይ እንዲቀርብ ለማድረግ ማህበራት ምርት በቀጥታ ከአርሶ አደሩ አምጥተው ዱቄት ለሚያመርቱ በማቅረብ የዳቦ ምርት ወደ ገበያ እንዲገባ እየተደረገ ነው” ብለዋል፡፡
በመዲናዋ የኮሪደር ልማቱን ጨምሮ በርካታ የልማት ሥራዎች እየተከናወኑ እንደሚገኙ ይታወቃል፡፡ ለእኒህ የልማት ሥራዎች ደግሞ ከተማዋ ገቢ በአግባቡ መሰብሰብ ያስፈልጋታል፡፡ ከዚህ አንጻር ባለፉት 6 ወራት አስተዳደሩ 111 ቢሊዮን ብር ገቢ በመሰብሰብ የተሻለ ውጤት ማሳየቱን ያስታወሱት ም/ከንቲባ ጃንጥራር፤ ይህም ሊሆን የቻለው የገቢ ግብር መሰረቱን በማስፋት በተከናወነ ስራ መሆኑን አብራርተዋል፡፡
ከግብረ ሃይሉ አንድ ንዑስ ኮሚቴ በማቋቋም ደረሰኝ የማይቆርጡ አካላትን መከታተልና መቆጣጠር የሚያስችል ሥራ እየተከናወነ መሆኑን ያመለከቱት ም/ከንቲባው፤ በተለይ መርካቶ አካባቢ የብሎኪንግ ሥራ በመጀመር ከደረሰኝ ጋር ያለውን ችግር ለመፍታት ከንግድ ቢሮ፣ ከገቢዎች፣ ከሰላምና ፀጥታ እንዲሁም ከአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ጋር በቅንጅት በተከናወኑ ስራዎች የተሻለ ውጤት መምጣቱን ይገልጻሉ - ሆኖም በቂ ነው የሚባል አይደለም፤ ብለዋል፡፡
“ይሄ በሌሎችም የገበያ ቦታዎች ሁሉ መቀጠል ያለበት ነው፤ የቄሳርን ለቄሳር እንዲሉ መንግሥት ገቢውን ካልሰበሰበ ልማትን ማረጋገጥ አይችልም፡፡ ስለዚህ ህገወጦችን ወደ ህግ ስርዓቱ በማስገባት ህጋዊ ንግድን ማስቀጠል ይኖርብናል፡፡” ሲሉም አክለዋል፡፡
ባለፉት 6 ወራት ግብረ ሃይሉ የምርት አቅርቦት እጥረት በገበያ እንዳይኖር እንዲሁም በግብይት መካከል ያለውን የደላላ ሰንሰለት ለመበጣጠስ ትኩረት አድርጎ በመሥራቱ ሰፊ ቁጥር ያላቸው በህገ ወጥ መንገድ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ አካላት ወደ ህጋዊነት መምጣታቸውን ም/ከንቲባው ይገልጻሉ፡፡ በዚህም ከ14 ሺ በላይ የሚሆኑ በህገ ወጥ መንገድ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ አካላትን ወደ ህጋዊ መስመር የማስገባት ስራ መሰራቱን ጠቁመው፤ ይሄ ደግሞ የገቢ ግብር መሰረቱን በማስፋት ከፍተኛ ገቢን ለመሰብሰብ አስችሎናል፤ብለዋል፡፡
ግብረ ሃይሉ በህገ ወጥ የንግድ እንቅስቃሴዎች ላይ ብቻ አይደለም አተኩሮ የሚሰራው፡፡ በተለይ በበዓላት ወቅት ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው ማህበረሰቦች ገበያ ወጥተው በቅናሽ ዋጋ የተለያዩ ምርቶች የሚያገኙበት ሁኔታ መመቻቸቱን ያረጋግጣል፡፡
“ለምሳሌ የማህበራት ሱቆች ጤፍ መሸጥ ብቻ ሳይሆን እሴት በመጨመር ዱቄትና እንጀራ ያቀርባሉ፤ በተመሳሳይም ዳቦ የሚያቀርቡ ማህበራትም አሉ፤ በበዓላት ወቅት ለበዓላት የሚሆኑ ምርቶች በስፋት እንዲቀርቡ ማህበራትን እንጠቀማለን፡፡” ይላሉ ም/ከንቲባው፤ በማህበራቱ አማካኝነት የእርድ እንስሳት ሳይቀር ለበዓላት እንደሚቀርቡ በመግለጽ፡፡
በመዲናዋ ለዋጋ መናርና ለገበያ አለመረጋጋት በምክንያትነት ከሚጠቀሱት መካከል ምርት የሚደብቁ ህገ ወጥ አካላት የአንበሳውን ድርሻ ይወስዳሉ፡፡ ይህን ህገ ወጥ ተግባር ለማስቀረት ግብረ ሃይሉ ምን እየሰራ እንደሚገኝ ም/ከንቲባው ሲያብራሩ፤ “የግብረ- ሃይል አደረጃጀቱ በክፍለ ከተማም አለ፤ ይህ ግብረ ሃይል በንዑስ አደረጃጀት በሰላምና ፀጥታ ቢሮ ሰብሳቢነት፣ የንግድንና ገቢን የንዑስ ኮሚቴው አባል በማድረግ ቁጥጥር ያደርጋል፡፡ ቁጥጥር የሚያደርገው በመዲናዋ ብቻ ሳይሆን ወሰን ዘለል ጭምር ነው፡፡ ለዚህም ከሸገር ሲቲና ከኦሮሚያ ክልል ጋር በትብብር ይሰራል፡፡” ብለዋል፡፡
ምክንያቱንም ሲያስረዱ፤ “የምርት መጋዘናቸው ቡራዩ ወይም ገላን አሊያም ዱከም ወይም ለገጣፎ ይሆንና ምርታቸውን እዚህና ሌላ ቦታ ይሸጣሉ፤ እነዚህን የመሳሰሉ ህገ ወጥ የንግድ እንቅስቃሴዎችን በቅንጅት በመሥራት እየተከላከልን እንገኛለን፡፡” ይላሉ፡፡
ቁጥጥሩ በዚህ መንገድ እየተሰራ ቢሆንም፣ ከሁሉም አስቀድሞ ከነጋዴው ማህበረሰብ ጋር ሰፊ ውይይት መደረጉንና የግንዛቤ ማስጨበጫ መርሃ ግብር መካሄዱን ይናገራሉ፡፡
“ህብረተሰባችን ለኑሮ ጫና መጋለጥ የለበትም፤ እናንተም ድርሻ አላችሁ፤ ህጋዊ ንግድን ማንቀሳቀስ ትችላላችሁ፤ደረሰኝ መቁረጥ አለባችሁ፤ምርት በመደበቅ ሸማቹ ላልተፈለገ የዋጋ ጭማሪ መጋለጥ የለበትም፤ በሚሉት ዙሪያ ከንግዱ ማኅበረሰብ ጋር በክፍለ ከተማ፣ በየደረጃው ውይይት ተደርጓል፡፡ ከዚህ ባለፈ ግን ወደ ህጋዊ እርምጃ የማስገባት ሥራ ነው እየተሰራ ያለው፡፡” ብለዋል፡፡
እንዲያም ሆኖ እንደ መርህ አድርገን የወሰድነው ምርትን ወደ ገበያ ማቅረብ እንጂ መከታተል፣መቆጣጠርና ማሸግን አይደለም፤ ይላሉ ም/ከንቲባው፡፡
“የመጀመሪያውና ዋና አጀንዳችን ምርት ወደ ገበያ ይቅረብ፤ ነጋዴውም ይነግድ አምራቹም ያቅርብ፤ ህብረተሰቡም በፈለገው ቦታ ተንቀሳቅሶ ይሸምት፤ ይህን ማድረግ የሚያስችል የግብረ-ሃይል እንቅስቃሴ ይኑረን ነው፤በዚህም መሰረት ነው እስካሁን እየተሰራ የዘለቀው፡፡” ብለዋል፡፡
“በዚህ ሂደት ውስጥ አልፎ አልፎ መንገራገጮች ሊያጋጥሙ ይችላሉ፤የግለሰብ ፍላጎቶችም ይኖራሉ፤ እነዚህን ጥቆማ በደረሰን ቁጥር እናርማቸዋለን፤ እርምጃም እንወስዳለን፤ ለምሳሌ ገቢ ላይ እነዚህ ችግሮች ሲያጋጥሙ ህጋዊ እርምጃ እየተወሰደ ይገኛል፡፡ ሌብነትና ጉቦኝነት በመሳሰሉት ላይ በአመራሩ ውሳኔ እየተሰጠ የማስተካከል ስራ እየተሰራ ነው፡፡” ሲሉም አክለዋል፡፡
የምርት ጥራትን ለማስጠበቅ ግብረ ሃይሉ እያከናወናቸው ያሉ ተግባራትን በተመለከተ ም/ከንቲባው ሲያብራሩ፤ ጥራቱ የወረደ ምርት ወደ ገበያ እንዲገባ በጭራሽ አንፈቅድም፤ በጥራት ጉዳይ አንደራደርም ይላሉ፡፡
“ለዚህም እኛ ብቻ ሳንሆን እንደ ምግብና መድሃኒት ቁጥጥር ባለሥልጣን ያሉ አካላት የሚመረቱ ምርቶች ስታንዳርዳቸውን የጠበቁ ስለመሆናቸው ክትትልና ቁጥጥር ያደርጋሉ፤ ከስታንዳርድ በታች የሆኑ ምርቶችንም ያስቆማሉ፤ እኛም ይህን እንደግፋለን፡፡” ብለዋል፡፡
ነገር ግን ከዚያ በፊት ጥራት ያላቸው ምርቶች እንዲመረቱ ድጋፍ እናደርጋለን የሚሉት ም/ከንቲባ ጃንጥራር፤ ለዚህም ከተማ አስተዳደሩ ማህበራትን በመደጎም አቅማቸውን እያጠናከረ እንደሚገኝ ይገልጻሉ፡፡ ይሄ ሁሉ ተደርጎ የሚመረተው ምርት ከስታንዳርድ በታች ከሆነ ግን እርምጃ እንደሚወሰድና ተቋማት ተገቢውን ክትትልና ቁጥጥር ስለማድረጋቸው በግብረ ሃይሉ እንደሚገመገሙ ጠቁመዋል፡፡
ግብረ ሃይሉ ትኩረት ያደረገባቸው የእሁድ ገበያዎች 210 እንደሚደርሱ የሚናገሩት ም/ከንቲባው፤ ከእነዚህ ውስጥ ስታንዳርዳቸውን ጠብቀው በተሻለ ሁኔታ የሚንቀሳቀሱት 180 ያህሉ ናቸው ይላሉ - በአንድ ወረዳ በአማካይ ሁለት የእሁድ ገበያዎች ሊኖሩ እንደሚችሉ በመጠቆም፡፡
ለመሆኑ ስታንዳርዳቸውን የጠበቁ የገበያ ሥፍራዎች ሲባል ምን ማለት ነው?
“ስታንዳርድ ስንል የገበያ አመቺነት፣ የሚቀርበው የምርት አይነት፣ ምርቱ በወጥነት የሚቀርብ መሆኑ፣ የገበያው ዋጋ በተቀመጠው ስታንዳርድ መሆኑን መነሻ በማድረግ የተቋቋሙ የግብይት ቦታዎች ናቸው፡፡” በማለት አብራርተዋል፡፡
ዋናው ዓላማችን የሰንበት ገበያዎች የህብረተሰባችንን ፍላጎት ባሟላ መልኩ እንዲሰራባቸው ማድረግ ነው የሚሉት ም/ከንቲባ ጃንጥራር አባይ፤ ግባችን በኑሮ ላይ ጫና የሚያሳድሩ የምርት ዋጋዎች ነዋሪዎች በቅናሽ የሚሸምቱበትን እድል መፍጠር ስለሆነ ገበያዎቹ በዚያ ልክ ስታንዳርዳቸውን ጠብቀው እንዲያገለግሉ እየተሰራ ነው፤ ብለዋል፡፡
ም/ከንቲባው የገበያ ማረጋጋትና ህገ ወጥ ንግድ ቁጥጥር ግብረ-ሃይልን አስመልክቶ ከሰጡት ሰፊ ማብራሪያ ተነስተን ግብረ ሃይሉ በመዲናዋ በርካታ ሥራዎችን እያከናወነ እንደሚገኝ መረዳት አዳጋች አይደለም፡፡ በዋናነት ከተለያዩ የአስተዳደሩ ተቋማት ጋር ቅንጅትና ትብብር በመፍጠር የገበያ ማረጋጋትና ህገ ወጥ የንግድ እንቅስቃሴዎችን የመቆጣጠር ሥራዎችን እያከናወነ ቢሆንም፣ በዚህ ብቻ ግን አልተወሰነም፡፡
ግብረ ሃይሉ ህጋዊ የንግድ አሰራርን እያሰፋ ይገኛል፡፡ የገቢ ግብር መሰረትን በማስፋት የአስተዳደሩን ገቢ በማሳደግ ረገድ የድርሻውን እየተወጣ ነው፡፡ የከተማዋን ማህበረሰብ የኑሮ ውድነት ጫና ለመቀነስ ምርቶች በተመጣጣኝ ዋጋ የሚቀርቡበትን ሁኔታ ያመቻቻል፡፡ በዚህም የከተማዋንና የነዋሪዎቿን ችግር በመቅረፍ ረገድ ጉልህ አስተዋጽኦ እያደረገ ነው ቢባል ማጋነን አይሆንም፡፡

በፖርቹጋል ሊዝበን በተካሄደ የሴቶች ግማሽ ማራቶን ኢትዮጵያዊቷ አትሌት ፅጌ ገብረሰላማ የቦታውን ሪከርድ በመስበር አሸናፊ ሆናለች።

አትሌት ፅጌ ርቀቱን 1 ሰዓት 04 ደቂቃ ከ21 ማይክሮ ሰከንድ በሆነ ሰዓት በማጠናቀቅ ነው ቀዳሚ የሆነችው፡፡

አንድ የፈረንጆች ተረት አለ፡፡
በማፍቀር ዕድሜ ላይ ያሉ ጐረምሶች፤ “የት ሄደን ነው ራት የምንገባበዘው?” ሲባባሉ፤ አንደኛው፤
“ኦሽን-ቪው ሆቴል እንሂድ” አለ
“ለምን?” ሲሉት፤
“እዚያ ቆንጆ ቆንጆ፣ የሚታዩ ኮረዶች አሉ!” አለ፡፡
ሁሉም ተስማሙና ሄደው በርቸስቸስ ሲሉና ሴት ሲያጫውቱ አመሹ፡፡
ይህ በሆነ ከአሥር ዓመት በኋላ እንደዚሁ ተገናኙ፡፡ “የት እናምሽ?” የሚል ጥያቄ ተነሳ!
“ኦሽን-ቪው ሆቴል” አለ አንዱ፡፡
“ለምን?” አሉት፡፡
“ጥሩ ራትና ጥሩ መጠጥ አለ” ሲል መለሰ፡፡
ይህ በሆነ ከአሥር ዓመት በኋላ ዳግም ተገናኙ። አሁን ወደ ሰባ ዓመት ተጠግቷቸዋል። እንግዲህ “የት እንብላ ራት?” ተባለ፡፡
“ኦሽን- ቪው ሆቴል” አለ አንደኛው፡፡
“ለምን?” አሉት፡፡
“በጣም ፀጥ ያለ፣ የውቂያኖሱን ሰላምና ነፋሻ አየር የምናገኝበት ቦታ ነዋ!” አላቸው፡፡
ተያይዘው ነፋሻውንና ፀጥ ያለውን አየር ሲኮመኩሙ አመሹና ተለያዩ፡፡
ይሄ በሆነ ከአሥር ዓመት በኋላ እንደገና ተገናኙ፡፡ አሁን ጎብጠዋል፡፡ ከዘራ ይዘዋል። ባርኔጣ አድርገዋል፡፡
በጣም በዝግታ ነው የሚራመዱት፡፡ እየተደጋገፉ እየተቃቀፉ ነው የሚቆሙት፡፡
“ዛሬስ ለእራት የት እንሂድ?” አለ አንደኛው፡፡
“ኦሽን- ቪው ሆቴል” አለ ሌላው፡፡
“ለምን?” ብለው ጠየቁ ሌሎቹ፡፡
ሰውዬውም፤
“እዛ ሆቴል ሄደን አናውቅማ!”
“ብራቮ! አዲስ ሆቴል ማየት በጣም ደስ ይላል” አለ አንዱ፡፡
“ድንቅ ሀሳብ!”
“አስገራሚ ሀሳብ!”
“ጉደኛ ሀሳብ!” እየተባባሉ እየተጓተቱ፣ እየተገፋፉ፣ መሰሰሰስ እያሉ፤ ወደ ኦሽን ቪው ሆቴል አመሩ፡፡
* * *
የተፈጥሮን ሂደት ለማቆም አይቻልም፡፡ ይህን የተፈጥሮና የዕድሜ መሰላል፤ በየዕለቱ ከሚገጥመን አገራዊ ችግርና አፈታቱ ጋር ለማስተያየት ብንሞክር፤ አርጅተን ጃጅተን የሠራነውንና ያልሠራነውን፣ የሄድንበትንና ያልሄድንበትን ለመለየት የማንችልበት የመርሳት ዕድሜ እስከምንደርስ ንቅንቅ አልልም ብለን፤ በያዝነው ሥልጣንና ሹመት ሙጭጭ ካልን፤ በዚያውም ለተተኪው ትውልድ ቦታ ካልለቀቅን፤ የአገር- ለውጥ- ቀን እየራቀ ነው የሚሄደው፡፡ በእርግጥም ይሄ ቦታን በሰላም የመልቀቅ ባህል የዋዛ ነገር አይደለም፡፡ ፖለቲካዊ-ገፅ አለው፡፡ የኢኮኖሚ-ገፅ አለው፡፡ የግል ጥቅም-ገፅ አለው።
ከዚህም ባሻገር ከፓርቲ ጋር፣ ከራስ ጥቅም ጋር፣ ከራስ ህሊና ጋር መሟገትንና መታገልን ይፈልጋል፡፡ ይህን ዋጋ ለመክፈል ፈቃደኛ የሆነ በማይገኝበት ዘመን የአገር ምጧ ብዙ ነው፡፡ ይህ ነው አገራችንን በተደጋጋሚ የገጠማት፡፡ ለዚያም ነው አገራችን ምጧ የሚበዛው፡፡ ለዚያም ነው አገራችን በየጊዜው የለየለት ጦርነት ውስጥ የምትገባው፡፡ ጥቂቶች ከላይ የተጠቀሰውን ዋጋ ለመክፈል አሻፈረኝ በማለታቸው ነው፣ ብዙዎች ያልተገባ የህይወት ዋጋ የሚከፍሉት፡፡ ጥቂቶች ከለመዱት ሥልጣንና ምቾት መነቅነቅ ባለመፈለጋቸው ነው፣ አገር ደግማ ደጋግማ እየታመሰች ያለችው፡፡ በእርግጥም የተፈጥሮን ሂደት ማቆም የማይቻል ነገር ነው፡፡ የተፈጥሮን ሂደት ለማቆም ሙከራ ሲደረግ ግን አገር ምስቅልቅል ውስጥ ትገባለች፡፡
ወጣቱ ላይ ዕምነት ይኑረን፡፡ ያለ ጥርጥር አዲሱ ትውልድ አሸናፊ ነው፡፡ The New is invincible ይሉ ነበር የጥንት ፖለቲከኞች፡፡ ዛሬም ይሄ ዕውነታ አይሻርም፡፡ አዲስ ኃይል መፍጠር፣ የአገር አቅም መፍጠር ነው። ለወጣቱ ትውልድ ቦታ መልቀቅ ያስፈልጋል። የተፈጥሮ ህግ ነውና፡፡
ከፖለቲካ ባህላችን ውስጥ እጅግ ሚዛን የሚደፋ አንድ ባህል አለ፡፡ ብዙ ሊጤን ይገባል! የይቅር መባባል ባህል! ቂም፣ የወንጀለኝነት-ስሜት፣ ብድር-የመመለስ ፍላጎት፤ አጥፊ ናቸው፡፡ ዴቪድ ሀውኪንስ እንዲህ ይለናል፤ “የ2ኛው የዓለም ጦርነት አንጋፋ ተሳታፊዎች አሰቃቂውንና አንገፍጋፊውን ጦርነት ከተወጡ በኋላ አብዛኞቹ የጠላት ተፋላሚዎች በፍጥነት ይቅርታ ተደራረጉ፣ ይቅር ተባባሉ፡፡ ሰላምታ ተሰጣጡ፡፡ የፍልሚያውን ፍፃሜም በዓል አከበሩ፡፡ በአዲስ የመተሳሰብ መንፈስ ተጨባበጡ፡፡ አሜሪካኖች አቶሚክ ቦምብ የጣሉና በሺዎች የሚቆጠሩ ሲቪሎችን የቀጠፉ ነበሩ፡፡ ጦርነቱ ካበቃ በኋላ ግን “በቃ ጦርነትኮ ይሄው ነው” ተባለ! የትላንት ተፋላሚዎች የዛሬ ጓደኛ ሆኑና ይጠያየቁ ጀመር፡፡ ይሄው እስካሁንም የተረፉት ታላቁን የጦርነት ቀን ያከብራሉ”
በአያሌ ሰዎች በተግባር እንደተረጋገጠው፤ አሉታዊ አመለካከትና የወንጀለኛነት ስሜት፤ በአዎንታዊ የመረዳት ስሜት፣ በመረዳዳትና በትውስታ ስሜት፤ ሊተካ ይችላል፡፡ … በዚህ ስሜት ሲታይ ከዚህ ቀደም በጠላትነት ይታዩ የነበሩ ሰዎች ይቅርታን ሊያገኙ ይችላሉ። ከዚህ ቀደም ያስፈሩ የነበሩ ሰዎችም አሁን ሰላማዊ ሆነው ሊታዩ ይችላሉ፡፡ ዋናው ራስን ለማየትና ጥፋትን ለመቀበል ዝግጁ የመሆን ጉዳይ ነው። እርግጥ በአንድ ጀምበር እውን የሚሆን ጉዳይ አይደለም፡፡ ልምምድ ይፈልጋል፡፡ አዕምሮአችንንና ልቡናችንን ክፍት እናድርግ፡፡ ለዚህ ቁልፉ ነገር፤ አንዱ ከሌላው መማሩ ነው፡፡ ችግሩ ግን ያልተማረው የተማረውን ካላስተማርኩ፣ አላዋቂው አዋቂው ካላዳመጠኝ የሚልበት፤ ከሁሉም በላይ ደግሞ በአዕምሮም በአካልም ያልዳበረው ሰው፤ ልምድ ያለውንና የዳበረውን ሰው፤ ዘራፍ ሲልበት፣ ሲፎክርበት፣ ከእኔ ወዲያ ላሣር ሲለው የታየበት አገር መሆኑ ነው!
“አውራ ዶሮ ፈረሱን ረግጦ፤ ‘እርግጫ ከእኔ ተማር!’” አለው፤ የሚለው የኦሮምኛ ተረት የሚነግረን ይሄንኑ ነው!!
***

ዓሲምባ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ዓዴፓ) ከትግራይ ክልል ጊዜያዊ ምክር ቤት ራሱን አግልሏል። ፓርቲው ምክር ቤቱን “የሃይማኖት እኩልነት የሌለበት ነው” ሲል ተችቷል።
ፓርቲው ከትላንት በስቲያ የካቲት 27 ቀን 2017 ዓ.ም. ባወጣው መግለጫ፣ ዓዴፓ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ ምክር ቤት በክልሉ ሕዝብ ላይ “አጋጥሟል” ያለውን ችግር ለመቅረፍ የሚያስችል አቅም እንደሚያዳብር ተስፋ አድርጎ ለመቀላቀል ወስኖ እንደነበር አስታውሷል። አክሎም፤ “ምክር ቤቱ ብዙ ድክመቶች ቢኖሩበትም፣ እኛ ተቀላቅለን ድክመቶቹን እያረምን ለመዝለቅ ተስፋ አድርገን ነበር። ወደ ምክር ቤቱ ከገባን በኋላ፣ የተለያዩ የፖለቲካና ሌሎች ድርጅቶችን በማቀፍ አሳታፊ አሰራር እንዲኖር ታግለናል” ሲል አትቷል።
በተጨማሪም፣ ምክር ቤቱ በወሳኝ አጀንዳዎች ላይ ክርክር የሚካሄድበትና የዴሞክራሲ ስርዓት የሚያድግበት ተቋም እንዲሆን ፓርቲው መታገሉን በመግለጽ፣ ይህ ግን ዕውን ሊሆን አለመቻሉን በመግለጫው አብራርቷል። “ከወረዳ ተወክለው የሚመጡ ሰዎች ቁጥር አነስተኛ ነው። በተለይም የኢሮብ እና ኩናማ ብሔሮች እኩል ውክልና እየተሰጣቸው አይደለም። የሴቶች እኩል ተሳትፎ አልተረጋገጠም” በማለት አመልክቷል።
ከጊዜያዊ ምክር ቤቱ ዕውቅና ውጪ፣ የተመረጡ ሰዎች ብቻ የሚሳተፉበት የውሳኔ አሰጣጥ ሂደት እንዳለ በመግለጫው የጠቀሰው ፓርቲው፤ ምክር ቤቱን “የሃይማኖት ዕኩልነት የሌለበት ነው” በማለት ነቅፎታል። ይሁንና ምክር ቤቱ ባለፈው ሐሙስ ባካሄደው መደበኛ ስብሰባ፣ የትግራይ ክልል ሙስሊም ሕብረተሰብ ተሳታፊ እንዲሆን ውሳኔ አሳልፏል።
ምክር ቤቱ ፍትሐዊ አሰራርና መርሕን እንደማይከተል በመጠቆም፣ በተለይም ቁልፍ የቋሚ ኮሚቴ ሹመቶችን “አሳታፊ እና ፍትሐዊ” ባልሆነ መንገድ በሃሳብ ተመሳሳይ ለሆኑ ድርጅቶች ተላልፎ እየተሰጠ መሆኑን ጠቅሷል። ይህን ተከትሎ “ምክር ቤቱ በጥቅማጥቅም ትስስር አማካይነት የተዋቀረ ነው” ሲል ዓዴፓ በመግለጫው ወቅሷል።
“የተዋቀረው ጊዜያዊ ምክር ቤት የታሰበውን ለውጥ ለማምጣት አይችልም። የትግራይን ሕዝብ የሕልውና አደጋ ለመቅረፍ የሚያስችል ቁመና የለውም” ያለው ፓርቲው፤ በምክር ቤቱ ያለውን ውክልና በማንሳት ራሱን እንዳገለለ አስታውቋል።
ከዚህ ቀደም ጊዜያዊ ምክር ቤቱ ሲቋቋም፣ በዶ/ር ደብረጽዮን ገብረሚካዔል የሚመራው ህወሓት ተሳታፊ አለመሆኑ የሚታወስ ሲሆን፣ ሳልሳይ ወያነ ትግራይ በበኩሉ፣ ምክር ቤቱን እንደማይቀላቀል ገልጾ ነበር። ነገር ግን ከሳምንታት በፊት ሳልሳይ ወያነ ትግራይ ወደ ምክር ቤቱ እንደገባ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ አስታውቋል።
የትግራይ ክልል ጊዜያዊ ምክር ቤት የቀድሞ ስያሜው “የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር አማካሪ ምክር ቤት” የሚል ነበር። ቀደም ሲል ሳልሳይ ወያነ ትግራይ ይህ ስያሜ እንዲቀየር ጥያቄ አቅርቦ፣ የመጀመሪያ አስቸኳይ ጉባዔውን በመቐለ ከተማ ያካሄደው የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር አማካሪ ምክር ቤት፣ የተቋቋመበትን ደንብ ቁጥር 10/2016 አሻሽሎ አጽድቋል፡፡ በዚህም ስያሜ ተቀይሯል።
ዓሲምባ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ ባቀረባቸው ትችቶች ዙሪያ፣ ጊዜያዊ አስተዳደሩም ሆነ ምክር ቤቱ እስካሁን የሰጡት ይፋዊ ምላሽ የለም።

የቤተሰብ ዕቅድ ጉዳይ እንደ ፖለቲካ አጀንዳ እየተቆጠረ ነው የተባለ ሲሆን፤ አገልግሎቱን በስፋት ተደራሽ ለማድረግ የሰላም ዕጦትና የአቅም ውስንነት ዋነኛ ፈተናዎች እንደሆኑ ተጠቁሟል።
የተዋልዶ ጤና አገልግሎት ሰጪ ድርጅቶች ማሕበር ከትላንት በስቲያ የካቲት 27 ቀን 2017 ዓ.ም. በስካይ ላይት ሆቴል ባዘጋጀው አምስተኛ ዓመታዊ ጉባዔ ላይ የመንግስት ሃላፊዎች፣ የውጭ የዕርዳታ ሰጪ ድርጅቶች ተወካዮችና ሌሎች የዘርፉ ተዋናዮች የተገኙ ሲሆን፣ በዘርፉ ላይ ስለሚስተዋሉ ችግሮች በስፋት ተነስቷል፡፡ በጉባዔው ላይ አሜሪካን ጨምሮ አንዳንድ የአውሮጳ አገሮች ለአዳጊ አገራት በጤና ዘርፉ በኩል የሚያደርጓቸውን ድጋፎች መቀነሳቸው ተመልክቷል።
በተጨማሪም፣ የፖሊሲ ለውጦች መከሰታቸውን ተከትሎ፣ በስነ ተዋልዶ ጤና ዘርፍ ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ ማሳደሩን የጉባዔው ተሳታፊዎች አስረድተዋል። በተለይ በጽንስ ማቋረጥ፣ በኤችአይቪ ምርመራና የቤተሰብ ዕቅድ አገልግሎት ላይ የደረሰው ተጽዕኖ ቀላል አለመሆኑን በመጠቆም፣ “ኢትዮጵያ በስነ ተዋልዶ ሕክምና ላይ ጠንካራ ስራዎችን ለመስራት የሚያስችሉ ዕምቅ አቅሞች ያሏት አገር ብትሆንም፣ እንደ ሰላም ዕጦት፣ ድህነትና የበጀት ዕጥረት ያሉ ውስብስብና ተያያዥ ተግዳሮቶች እየፈተኗት ያለች አገር ናት” ተብሏል።
በዚህ ሁኔታ ውስጥ አካል ጉዳተኛና በግጭት ቀጣና ውስጥ የሚገኙ ሴቶች ከስነ ተዋልዶ ጋር የተያያዙ አገልግሎቶችን ማግኘት አለመቻላቸው የተገለጸ ሲሆን፤ በተለይ ባለፉት ጥቂት ሳምንታት በርካታ በስነ ተዋልዶ ላይ የሚሰሩ ድርጅቶች ስራዎቻቸውን ማቋረጣቸው የብዙዎችን የተዋልዶ ጤንነት አደጋ ውስጥ የሚከት እንደሆነ ተመላክቷል። ይህን ተከትሎ፣ ያልታቀደ ዕርግዝና እና ጥንቃቄ የጎደለው የጽንስ ማቋረጥ ባልታሰበ ፍጥነት እንዲጨምር የራሱ የሆነ ጫና እንደሚያስከትል ነው በጉባኤተኞቹ የተነገረው፡፡
ችግሮችን ለይቶ ትክክለኛውን የመፍትሔ አቅጣጫ መከተል ከተቻለ፣ የሚደርሰውን ጉዳት መቆጣጠር እንደሚቻል የገለጹት ተሳታፊዎቹ፤ መንግሥት ከአሜሪካ ተቋማት በሚደረጉ ድጋፎች ብቻ የተሻለ ስራ እንደሚሰራ ማሰብ የለበትም፤ ብለዋል። "የአገር ውስጥ ተቋማትን ማገዝና ማሳደግ፣ በእነርሱ ላይ መንተራስ እንዳለበት መገንዘብ ይኖርበታል።” ሲሉም መክረዋል፡፡
የተዋልዶ ጤና አገልግሎት ሰጪ ድርጅቶች ማሕበር ዋና ዳይሬክተር አቶ አበበ ከበደ ለጋዜጠኞች በሰጡት ማብራሪያ፤ ዓመታዊው የተዋልዶ ጤና ጉባዔ መካሄድ የጀመረው እ.ኤ.አ. ከ2017 አንስቶ መሆኑን አስታውሰው፤ የስነ ተዋልዶ ጤና በየጊዜው አዳዲስ ዕውቀቶችንና ልምዶችን እንደሚፈልግ ጠቅሰዋል። አክለውም፣ በጤናው ዘርፍ የአሜሪካ መንግሥት ለስነ ተዋልዶ ጤና ሰፊ ድጋፍ ሲያደርግ እንደነበርና በአሁኑ ወቅት ግን ይህን ድጋፍ እንደማይቀጥል ይፋ ማድረጉን አውስተዋል።
የተዋልዶ ጤና ስራዎች በውጭ እርዳታ ላይ መንጠልጠላቸውን የጠቁሙት አቶ አበበ፤ “ከመንግሥት ጋር ተጋግዘን የተሻለ ስራ ለመስራት እነዚህን ተግዳሮቶች መቋቋም ያስፈልጋል። ከዚህ ቀደም የአገር ውስጥ ሃብት ከማሰባሰብ ይልቅ ውጭው ላይ በብዛት ትኩረት ይደረግ ነበር። አሁን ግን የአገር ውስጥ ሃብትን ለማሰባሰብና ስራዎችን ለማስቀጠል ከዚህ ቀደም በነጻ የሚሰጡትን አገልግሎቶች በተወሰነ መጠን ክፍያ ማስከፈል በሚያስፈልግበት ወይም እንዲሁ በነበሩበት በሚቀጥሉበት ሁኔታ ላይ ምክክር ተካሂዷል” ብለዋል።
አያይዘውም፤ “በመንግሥት በኩል በትምባሆና የአልኮል መጠጦች ላይ ተጥሎ የሚሰበሰበውን ታክስ ለጤናው ዘርፍ ገቢ ለማድረግ እንቅስቃሴዎች አየተደረጉ ነው። ነገር ግን ገቢ የማድረጉ ሂደት ወደ ስራ አልገባም” ሲሉ አስረድተዋል።
የአሜሪካ ድጋፍ መቋረጥ በዘርፉ የሚያስከትለውን ክፍተት ለመቅረፍ ተጨማሪ በጀት ከመንግሥት መመደብ ይኖርበታል የሚሉት አቶ አበበ፣ “ለስነ ተዋልዶ ጤና ዘርፍ የሚደረገው ድጋፍ ሲቀንስ፣ የእናቶችና ሕጻናት ሞት በከፍተኛ ቁጥር እንዲጨምር ያደርጋል” ብለዋል። ዋና ዳይሬክተሩ መንግስት ያለውን አቅም በመፈተሽና በማስተባበር ከሲቪል ድርጅቶች ጋር በቅንጅት በመስራት ሁኔታው ወደ ከፋ ደረጃ ሳይደርስ መቆጣጠር እንደሚቻል ጠቁመዋል።
በግጭት ምክንያትም ሆነ በሌሎች አደጋዎች ከቀያቸው የተፈናቀሉ ዜጎች በሚገኙባቸው መጠለያዎች የስነ ተዋልዶ ጤና አገልግሎት መስጠት ቢያስፈልግም፣ ፈታኝ ሁኔታዎች መኖራቸውን አንስተው፣ “አገልግሎቱን የሚሰጡ ባለሞያዎች ስነ ልቦናቸው የተጎዳ ነው። በመሆኑም የስነ ልቦና ሕክምና ያስፈልጋቸዋል።” ሲሉ ተናግረዋል።
“የቤተሰብ ዕቅድ ጉዳይ እንደ ፖለቲካ አጀንዳ እየተቆጠረ ነው።” ያሉት አቶ አበበ፤ የአንድን አካባቢ የህዝብ ቁጥር ከሚገባው በላይ ጨምሮ ማቅረብና የበለጠ ድጋፍ ማግኘት በክልሎች መካከል ፉክክር መፍጠሩን ገልጸዋል።
የተዋልዶ ጤና አገልግሎት ሰጪ ድርጅቶች ማሕበር፣ በስነ ተዋልዶ ጤና ላይ የሚሰሩ ከ85 በላይ የአገር ውስጥ እና የውጭ ድርጅቶችን በአባልነት ያቀፈ ድርጅት ነው።

የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ (ኦፌኮ) እና የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) ከሌሎች ሃይሎች ጋር በመሆን በኦሮሚያ ክልል የሽግግር መንግስት ለማቋቋም ያወጡትን መግለጫ አራት ተቃዋሚ ፓርቲዎች የተቃወሙት ሲሆን፤ ፓርቲዎቹ መግለጫውን “እሳት ላይ ቤንዚን እንደ ማርከፍከፍ የሚቆጠርና ቀን አይቶ የመጣል አዝማሚያ ያለው ነው” ሲሉ ነቅፈውታል።
ኢሕአፓ፣ መኢአድ፣ አማራ ጊዮናዊ ንቅናቄ እና እናት ፓርቲ ሐሙስ የካቲት 27 ቀን 2017 ዓ.ም. ባወጡት የጋራ መግለጫ፤ "ኦፌኮ እና ኦነግ ያወጡት መግለጫ፣ በአመዛኙ እሳት ላይ ቤንዚን እንደ ማርከፍከፍ የሚቆጠርና ቀን አይቶ የመጣል አዝማሚያ ያለው ሆኖ አግኝተነዋል” ብለዋል፡፡
ሁለቱ ፓርቲዎች የተስማሙባቸውንና በመግለጫቸው ያወጧቸውን ጉዳዮች ያወሱት አራቱ ፓርቲዎች፤ “እኛ የትብብር ፓርቲዎች በኦሮሚያ ክልል ብቻ አይደለም፤ በመላ አገራችን ሰላም እንዲሰፍን ለዚህም መንግሥት ግንባር ቀደም ሚና እንዲጫወት ያለመታከት ስንወተውት ቆይተናል” ብለዋል። አክለውም፣ አሁን ለአገሪቱ ሰላም በጋራ መታገል የሚያስፈልግበት ወቅት መሆኑን አስምረውበታል፡፡
“በተናጠል ያውም በክልል ደረጃ ወርደን የሚመጣ ሰላም አይኖርም፣ የአገራችንን አንድነትም ማስጠበቅ አይቻልም” ያሉት አራቱ ፓርቲዎች፤ “በአንድ ክልል ሊቋቋም የታሰበው የሽግግር መንግሥት አገራችንን አሁን ከምትገኝበት ሁኔታ የበለጠ ያመሰቃቅላታል፣ ችግሮችንም ያባብሳል እንጂ መፍትሄ ሊሆን እንደማይችል መገንዘብ ያስፈልጋል” ሲሉ አስረድተዋል።
በሁሉም የአገሪቱ አካባቢዎች ሰላም ካልሰፈነ “ማንም ወገን ብቻውን ነጻ እንደማይወጣ” ጠቅሰውም፤ የተናጠል ሰላም እንደማይሰፍን አብራርተዋል።
በመሆኑም፣ በኦፌኮ እና ኦነግ መግለጫ አማካይነት ይፋ የተደረገው የሽግግር መንግሥት የማቋቋም እንቅስቃሴን አጥብቀው እንደሚቃወሙ ፓርቲዎቹ አስታውቀዋል። እንቅስቃሴው ኦሮሚያ ክልልን “ጥቂት ፖለቲከኞችና የፖለቲካ ፓርቲዎች በሞኖፖል የያዙት ደሴት በማድረግና ራስን ብቸኛ ወኪል አድርጎ በማስቀመጥ አሁንም የተጠቂ ፖለቲካና የመጡብህ ዓይነት ቅስቀሳ የማራመድ” አካሄድ መሆኑን ጠቁመዋል።
“ይህን አካሄድ በአገር ፍርስራሽ ላይ የራስን ጎጆ ለመቀለስ ያለመ ቅርብ አዳሪ፣ ፍትሕ አልባ፣ ኢ-ሕገ መንግስታዊና ኢ-ሞራላዊ ሆኖ አግኝተነዋል” ሲሉ የተቹት ተቃዋሚ ፓርቲዎቹ፤ በኦፌኮ እና ኦነግ መካከል “ተደርጓል” ያሉት ስምምነት አገሪቱን በበርካታ አስርት ዓመታት “ወደ ኋላ የሚመልስ” ነው ብለውታል፡፡
በቅርቡ ኦፌኮ እና ኦነግ ባወጡት መግለጫ፣ በጋራ ይፋ ያደረጉት አቋማቸው፣ ለሕብረተሰቡ እንቅፋት የሆነውን በኦሮሚያ ክልል ያለውን የሰላም ችግር በትብብር ለመፍታት ያለመ ብቻ መሆኑን ጠቁመው፣ ከመንግሥት ጋር ለመወያየት አስፈላጊውን ዝግጅት ማድረጋቸውንም ገልጸው ነበር፡፡

እግዚአብሔር ከሁሉም ፍጡራን አብልጦ ለሰዎች እውቀትና ፍቅር ሰጥቶናል፡፡ እውቀት ነገር ለመለየት ይጠቅማል፡፡ ፍቅር ተግባብቶ ለመኖር ይረዳል፡፡ የዘመኑ ስልጣኔ የሰረፀውም በእነዚህ ፀጋዎች እንደሆነ ይታሰባል፡፡ ተፈጥሮ ሚስጥር ነች፤ ተለዋዋጭ ነች፣ ዘላለማዊም ነች ይባላል፡፡ የለውጥ ምንጩ ፀሐይና ኮከቦች ውስጥ ያለው ሀይድሮጅን በከፍተኛ ሙቀት ሲቃጠል የሚሰርፀው ጨረር (ኢነርጂ) እንደሆነ ይታመናል፡፡ አንዳንድ ሰዎች ግን ለውጥ የሚመጣው በጊዜ ተፅእኖ ይመስላቸዋል፡፡ እናም “አወይ ጊዜ” እያሉ ያንጐራጉራሉ፡፡ ጨረር ቁስ አካልን እየወዘወዘ ይቀያይረዋል፡፡ ውሁዶች ይፈጥራል ያፈርሳል፣ ሕይወትም ይገነባል፡፡
እኛ ሰዎች ስንሞት ገነት ለመግባት እንመኛለን፡፡ ከሞት በፊት ግን የሕይወትን ፀጋ በደንብ ብናጣጥመው ተገቢ ይመስለኛል፡፡ ሕይወት ልዩ የተፈጥሮ ፀጋ ናት፡፡ ራሷን በራሷ ታውቃለች፣ ነገር ትለያለች፣ ምግብ እየበላች፣ ቆሻሻ እያስወገደች፣ እየተዋለደች ትዘልቃለች፣ ትንሽ ቆይታም ትከስማለች፡፡ ከሞት በኋላ ስለ ጽድቅ ወይም ኩነኔ ከማሰባችን በፊት ግን “በእጅ የያዙትን ወርቅ ላለመጣል” ብለን ሕልውናን ለማዝለቅ ብንጥር ትክክል ይመስለኛል:: ብቃቱም አለን፤ ከእግዜር ተሰጥቶናል፡፡ በዚች ምድር ብዙ ዓይነት ፍጡር አለ፡፡ አንዱ የሚለያዩበት ነገር እድሜ ነው፡፡ ዝንብ አንድ ቀን ትኖራለች፣ ውሻ 25 ዓመት፣ ኤሊ 200፣ ሰኮያ ዛፍ 4600 (አሜሪካ)፣ ሌላ ዓይነት ዛፍ (ደ/አፍሪካ) 6000 ዓመት ይኖራሉ ይባላል፡፡ ይህ የሕይወት ፀጋ ነው፡፡ በሰው ዘንድ ፀጋውን ብናዳብረው የበለጠ ተጠቃሚ እንሆናለን፡፡ ከዚያ በኋላ ብንፀድቅ ደግሞ ድርብ ፀጋ ይሆናል ማለት ነው፡፡ አምላክ መቼም ዝም ብላችሁ ሙቱ የሚል አይመስለኝም፡፡ ፍጡራን እድሜያችን የተለያየው እንደ ብቃታችን ሊሆን ይችላል፡፡
በዚች ተፈጥሮ አምላክ ራሱ ለዘላለም እንዴት እንደሚኖር ግራ ይገባል፡፡ እኛ ሰዎች አንድ ነገር ደጋግመን ስናደርግ ይሰለቸናል:: ማር እንኳን ሲደጋገም “ቋቅ ይላል” ይባላል:: እኛ ይህን ስሜት የምናንፀባርቀው በውዴታ ሳይሆን ተፈጥሯዊ ስለሆነ ነው፡፡ አምላክ ኑሮው “ቋቅ” እንዳይለው ምን ይሆን የሚያደርገው? ምናልባት በእለታዊው ለውጥ ውስጥ አብሮ ይለዋወጥ ይሆን?
የኛ እድሜ ምጥን ነው፡፡ በጊዜ ሒደት ነገር ስለሚቀያየር ደግሞ ፍጡርም ይቀያየራል ይባላል፡፡ በአለፈው 4½ ቢሊየን የሕይወት ዓመት ብዙ ዓይነት ፍጡራን ሰርፀዋል፣ አብዛኛው ግን ከስመዋል ይባላል፡፡ ጨረር ሲጠፋ ሕይወት ራሱ እንደሚከስም ይታሰባል፡፡ እውቀት ካለንና እስከዚያም ድረስ ከዘለቅን ሒደቱን መከታተል ይቻል ይሆናል፡፡ በእውቀት ግን ውሱን ነን፡፡ ስለ ውሱንነታችን ለማወቅ ለምሳሌ አንዱን ተራ ዜጋ ድንጋይ ከመሬት አንስተን፣ ይህ ምንድነው? ብንለው ድንጋይ ነው ይለናል፡፡ ድንጋይ ምንድነው? ካልነው ደግሞ “ድንጋይ ነዋ” ነው የሚለን፡፡ ስለ ድንጋይ ያለን እውቀት እዚህ ላይ አበቃ ማለት ነው፡፡ ስለ አምላክም ያለን እውቀት ተመሳሳይ ሊሆን ይችላል፡፡
ስለ ፍቅር ያለን ግንዛቤ ፈሩን ሳይለቅ አይቀርም፡፡ ፍቅር በሰው ዘንድ የሰረፀው በሴትና ወንድ ግንኙነት እንደሆነ ይታሰባል፡፡ ዓላማውም ረጅም እንክብካቤ የሚፈልገውን ሕፃን ልጃችንን ለአቅመ - መዋለድ ለማድረስ እንደሆነ ይነገራል:: አንዳንድ ሰዎች ለልጆች ፍቅር ስጧቸው ሲሉ ይደመጣሉ፡፡ ፍቅር እንደ ብር ለሰው አይሰጥም:: በፍቅር ያደገ ልጅ ግን ከቤተሰቡ ይወርሳል፡፡ ሰው ይወዳል፣ ከሰው ይግባባል፣ የጋራ ችግርን ለመወጣትም ይተባበራል፡፡ በአንፃሩ ፍቅር ያጣ ልጅ ሰው አይወድም፤ ከሰው አይግባባም፣ አይተባበርም፡፡ እንዲያውም ማሕበረሰቡን ለመጉዳት በቀል ያደርጋል ይባላል፡፡ እናም ሰላማዊ ኑሮ ለመቋደስ በፍቅር መጋባትና ልጅን ተንከባክቦ ማሳደግ ያስፈልጋል ማለት ነው፡፡
የፍቅር ዓላማው ቢገባን ኖሮ የክርስቶስን ትምህርት ተከትለን፣ ሴትና ወንድ በፍቅር አንድ ለአንድ ተወስነን እንኖር ነበር፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ደግሞ የልጅ ብዛትንና የምርት መጠንን ማጣጣም ያስፈልጋል፡፡ እንደሚታወቀው መዋለድና ማምረት እኩል አይሄዱም፡፡ መዋለድ ፈጣን፣ ማምረት ግን ዘገምተኛ ነው:: ሕዝብ ሲበዛ ደግሞ ትርፉ ድህነት፣ የተፈጥሮ ሀብት ብክነትና የእርስ በርስ ግጭት እንደሆነ ይታወቃል:: ይህን ሒደት ባለማወቃችን አለገደብ እየተባዛን ድህነትን ተከናንበን፣ እርስ በርስ እየተጋጨን እንኖራለን፡፡ የችግሩ መፍትሔ (ከ1-2 ልጅ በቤተሰብ መውለድ) በሰለጠኑ ሀገሮች ቢታወቅም፣ እኛ ግን በአጉል ባህል ተተብትበን መኮረጅ እንኳን ተቸግረናል:: መሪዎቻችንም ስለ ሕዝብ ብዛት ትንፍሽ አይሉም፡፡ ይህን የግጭት ምንጭ ካልፈቱልን እንዴት ሰላምና መረጋጋት ያመጡልናል? ከድሮ መሪዎቻችንስ በምንድነው የሚለዩት?
እኛ ኢትዮጵያውያን በረጅም የአብሮነት ታሪካችን፣ እርስ በርስ በእጅጉ ተካሰናል፡፡ የግራኝ አህመድ ወረራ፣ የኦሮሞ ፍልሰት፣ የአፄ ምኒልክ ግዛት ማስፋፋትና የአድዋ ጦርነት ድል እንዲሁም የአፄ ኃይለስላሴና የደርግ የአንድነት አስተዳደር፤ በዚህ አቅጣጫ ጥሩ አስተዋጽኦ እንዳደረጉ ይታወቃል፡፡ ሆኖም ግን በሕወሓት ከፋፋይነት እንዲሁም በጊዜ ሒደት፣ የሕዝብ ብዛትና የኑሮ ፍላጐት ባለመጣጣሙ፣ እውቀትና ፍቅር የጐደላቸው “እንግዴ ልጆች” በሚቀሰቅሱት ነገር ግንኙነታችን እየሻከረ መጥቷል፡፡
እንደ ማሕብረተሰብ ስንኖር ማወቅ ያለብን ጉዳይ፣ በፍጡራን መካከል ስለሚከሰተው ሽሚያ ነው፡፡ የባዮሎጂ ሊቆች እንደሚሉን፤ ፍጡር ሁሉ ለምግብና ውሃ፣ ለፍቅርና ለቦታ ወዘተ… እርስ በርሱ ይሻማል ይሻኮታል፡፡ ሽሚያው ደግሞ በቅርብ ዘመዳሞች መካከል ይግላል ይባላል፡፡ ይህም ማለት በሰው ዘንድ ወንድም ከወንድሙ፣ እህት ከእህቷ፤ የበለጠ ይሻኮታሉ ማለት ነው፡፡ እኛ ሰዎች በዚች ምድር ስንኖር ደግሞ ዋና ፀጋ ብለን የምናስበው ተወልደንና አድገን፣ ልጆች ወልደንና አሳድገን ማለፍን ነው፡፡ ታድያ ይህን ምኞት እንዴት ልናሳካው እንችላለን? ለዚህ ችግር ግልጽ መፍትሔው ዲሞክራሲ ወይም የእኩልነትና የነፃነት ስርዓት ነው፡፡ እኩልነት አንድነትን ያጠናክራል፣ ምርታማነትንና ራስ መቻልን ያበለፅጋል፡፡ ነፃነት፤ ግልፅ ያልሆነችውን ተፈጥሮ በአግባቡ እየዳሰስን እንድናውቃትና እንድንጠቀምባት፣ የእርስ በርስ ግንኙነታችንንም በእውነተኛ መንገድ እንድናሰርፅ ይጠቅመናል:: በጥቅም ምክንያት የሚደርስ ግጭትን ደግሞ የፍትሕ አካሉ (ፍርድ ቤት) ይፈታዋል፡፡ ቂም በቀል ግን አይኖርም፡፡
እኛ በባህላችን የለመድነው ስርዓት የበላይነት ወይም ሌሎችን መግዛት ነው፡፡ ገዢው አካል የኑሮ ፍላጐቱን በሌሎች ጉልበትና ልፋት ያሳካል:: በዚህ ስርዓት ለረጅም ጊዜ ስለቆየን በግልጽ ያካበትናቸው ባህሪዎች ውሸት፣ ማታለል፣ ማስመሰል፣ መስረቅ፣ መንጠቅ፣ መክላትና ቂም በቀል ናቸው፡፡ ባህሪዎቹ በማንኛውም ዓይነት ግንኙነታችን (ለምሳሌ፡- በምርት፣ በንግድ፣ በፍቅር፣ በሀዘን፣ በጦርነት ወዘተ…) በግልጽ ይንፀባረቃሉ፡፡ ችግሮቹ በተለይ በፍቅር፣ በጦርነት፣ በሀዘን ወዘተ-- ላይ ሲንፀባረቁ የበለጠ ይመርራሉ፡፡ በዚህ ዓይነት ጉዞ ለረጅም ጊዜ ስንገጫገጭ በመቆየታችን ከስልጣኔ ጎዳና ከሞላ ጎደል ወጥተናል። ምክንያቱም ስልጣኔ የሚሰርፀው እውነትና መልካም ግንኙነት ሲኖር ነው፡፡
እንስት እንደ አንዳንድ ወንድ ‹‹እውነትን ተናግሮ እመሸበት ማደር›› እምብዛም አትልም ይባላል፡፡ እንደ ሁኔታው ግን ታድራለች:: ልጅ ወልዳ ተንከባክባ በማሳደግ ደግሞ ስኬታማ እንደሆነች ይታወቃል፡፡ ዘመኑ ለነጋዴ ይመቻል፤ ከሰለጠኑ አገሮች የኢንዱስትሪ ውጤቶች ይጎርፍለታል፡፡ ነጋዴው ግን ጥሩ ያልሆነውን እቃ ጥሩ ነው እያለ፣ ከዋጋው በላይ እያስከፈለ ይበዘብዘናል፡፡ በእንቡጥ ሴቶችም እያማለለ ያታልለናል፡፡ ጥሩ ሰው ለመምሰል ግን የማያደርገው  የለም፡፡ በአለባበሱና በአነጋገሩ ቅዱስ ይመስላል፡፡ ለድሆች ይመፀውታል። በእምነት ቤት ዙሪያም ሽር ጉድ ሲል ይታያል:: ድርጊቱ ግን እኛን ብቻ ሳይሆን ራሱ አምላክንም ጭምር እንደ ማታለል ይቆጠራል:: በድንቁርናችን በተዘፈቅንበት የበላይነት ሥርዓት እነሆ በፍሬቢስ ግንኙነት ዘወትር እንታመሳለን፡፡ ስርዓቱ ልዩ የተፈጥሮ ፀጋ የሆነችውን ሕይወታችንን ከእነ ጭራሹ እንዳያሳጣን ያሳስባል፡፡
ኢትዮጵያዊነት የሰፈነው በጥቂት አርቆ አሳቢ ገዢዎቻችንና የአንድነቱ ጥቅም በገባቸው ንቁ ብሔር ብሔረሰቦች ትብብር ይመስለኛል፡፡ በቅድሚያ አፄ ቴዎድሮስ ተበታትኖ የቆየውን የመሳፍንት ግዛት በወቅቱ አሰባሰቡት፡፡ ብልሁ አፄ ምኒልክ የአንድነት በትሩን ከአፄ ቴዎድሮስ ወርሰው ግዛቶችን አስፋፍተውና ሕዝቡን አስተባብረው፣ የኢጣሊያን የቅኝ ግዛት ጦርነት አድዋ ላይ መክተን፣ ከባርነት እንድንድን በቆራጥነት መርተውናል፡፡ በአሁኑ ዘመን ደግሞ ተመሳሳይ ችግር እየመጣ ሳይሆን አይቀርም፡፡ በአለም ደረጃ በካርቦን ልቀት ምክንያት የአየር ሙቀት እየጨመረ መጥቷል፡፡
ዝናብ በዝቷል፣ በየዋልታው ያለው በረዶ ይቀልጣል፤ የባህር ወለልም እያደገ ነው፡፡ ችግሩ እየተባባሰ ከሄደ የአንዳንድ የሰለጠኑ አገሮች መሬት በውሃ ስለሚሸረሸር፣ ውድ አገራችንን እናት ኢትዮጵያን በከፍታ ቦታነቷ ምናልባት ለቅኝ ግዛት ያጯት ይሆን? ማን ያውቃል? ለማንኛውም ጊዜው አሳሳቢ ነው:: ሕብረታችንን እንደ ልማዳችን አጠናክረን፣ የአድዋን ድል እንደገና መድገም ያስፈልገን ይሆናል፡፡
አሁን ‹‹ተረኛ›› መጥቷል ይባላል፡፡ ተረኛ የመጣው ለመግዛት ይሆን? መግዛት ረሀብንና ጥማትን ለጊዜው ያስታግስ እንደሆነ እንጂ ለዘለቄታው አያዋጣም:: በታሪካችን ገዢዎቻችን ሁሉ (ንጉሶች፣ ወታደሮች፣ ታጋዮች) ለጊዜው አለሁ አለሁ ቢሉም በስተመጨረሻ ግን ፈርሰዋል:: እኛንም ረግጠውናል፡፡ ተረኛው፤ አፍራሽነትን ትቶ ‹‹ኢትዮጵያዊነት›› ላይ ቢያተኩርና የራሱን የለውጥ አሻራ ቢያሳርፍ ለሁላችንም ይጠቅመናል፡፡ በቅድሚያ ማወቅ ያለበት ሐቅ ግን በዙሪያው ቆራጥና ጀግና አብሮ አደሮች እንዳሉ ነው፡፡ ከእነርሱ ጋር በመተባበር ዲሞክራሲን ማስረጽ ይጠበቅብናል። ዲሞክራሲ ከተዘፈቅንበት መሻኮትና መቆራቆዝ ያላቅቀናል::
ተረጋግቶ በመኖር ስልጣኔ ይሰርጻል:: በሒደቱም 1/ ለኑሮ አስፈላጊ የሆኑትን ምግብ፣ ውሃ፣ እቃና ልብስ ማምረት ወይም ማቅረብ 2/ ከሰውነት ከቤትና ከስራ ቦታ የሚወጣውን ቆሻሻ በአግባቡ ማስወገድ 3/ በጀርም የሚመጡ በሽታዎችን እንዲሁም ተውሳኮችን መከላከል 4/ የኑሮ ተቀናቃኝን በዘመናዊ ዘዴ መመከት ያስችላል:: በአንድ በኩል፣ ስልጣኔ ሊሰርጽ በሌላ በኩል ደግሞ ችግርም ይከማች ይሆናል:: ችግር ሲበዛም ስልጣኔው ይሰናከላል:: ታሪክ እንደሚናገረው፤ ብዙ ስልጣኔዎች ከስመዋል፡፡ አሁን ከተረኛው የምንፈልገው ቁም ነገር፣ ስልጣኔን ተንቀሳቅሶ ከመኖር ጋር እንዲያዛምድልን ነው፡፡ እንደሚታወቀው፤ በተፈጥሮ ሁሉም ነገር ይንቀሳቀሳል ይባላል:: በሰው ዘንድ ደግሞ ከቦታ ቦታ መንቀሳቀስ ሰውነትን ያፍታታል፤ ሕሊናንም ያድሳል:: በመንቀሳቀስ የሕዝቦች ግንኙነት ይሻሻላል፣ ስልጣኔውም እያደር ይታደሳል፡፡ ዘዴው አዲስ ነው፤ እንሞክረው፡፡ በእንቅስቃሴ ባሕላችን ሕልውናችንን እናድስ!!
እናት ኢትዮጵያ በስኬት ትገስግስ!!  

 ከአድማስ ትውስታ

Wednesday, 05 March 2025 00:00

ምዕራፍ 7

እስካርሌት በሁለት ሳምንቶች ውስጥ ሚስት ሆነች፡፡ ከዚያ በቀጠሉት ሁለት ወራት ውስጥ ደግሞ የሙት ሚስት ሆነች፡፡ በእርግጥ ምንም ሳታስብበትና በጥድፊያ ባለትዳር ብትሆንም ወዲያው ከዚህ ከትዳር ሰንሰለት እፎይ ብላ ለመገላል ችላለች፡፡ ዳሩ ግን እነዚያን ከትዳር በፊት የነበሩ የመዝናናትና እንደልብ የመጨፈር የምንግዴ ሕይወት መብትና ነፃነቷን፤ መልሳ ለማግኘት አልቻለችም፡፡ ከሰርጓ ማግስት ቀጥሎ በነበሩት ወራት የባሏ መሞት ሐዘን ተከተለባት፡፡ በልቧ እፎይ አለች እንጂ በሌላ ወገን የከፋት ነገር ተፈጥሯል- የልጅ እናት መሆን ተክሎባታል፡፡ ባንድ ጀምበር ሚስት፣ በሌላ ጀምበር የሙት ሚስት፣ ደሞ በሌላ ጀምበር እናት፡፡


ዓመታት ካለፉ በኋላ እስካርሌት የእነዚያን 1861 የሚያዚያ ቀናት ከነዝርዝር ውሎ- አመሻሻቸው ለማስታወስ በጭራሽ አትችልም፡፡ ጊዜና ክንውኖቹ ሁሉ እንደህልም፣ እንደቅዠት እየተደራረቡ ያላንዳች እውንነት ወይም ተጨባጭ ምክንያት ብዥ እንዳለ ፊልም አልፈዋል፡፡ መቼም እስክትሞት ድረስ እነዚያ ቀናት በትዝታዋ መዝገብ ውስጥ ባዶ ገጽ ሆነው ይቀራሉ፡፡ በተለይ ቻርለስ ለጋብቻ ሲጠይቃት እሺ ባለችበት ቀንና በሠርጋቸው ቀን ማህል ያለው ትውስታ ጭራሽ ጭልምልም ያለ ነው፡፡ ሁለት ሳምንት፣ መቼም በሰላሙ ጊዜ እንኳን ጋብቻ ፍጥምጥም የማይደረግበት ጊዜ ነው፡፡ ከፍጥምጥም ወዲያ ደግሞ የአንድ ዓመት ወይም ቢያንስ ቢያንስ የስድስት ወር ሞቅ ያሉ ቀናት ተጠብቆ ነበር ጋብቻ የሚፈጸም፡፡ ዳሩ ግን ደቡብ በእሳት በተያያዘበት ጊዜ በመሆኑ ድርጊቶቹ ሁሉ ንፋስ ተሸክሟቸው እንደሚነጉድ ሁሉ በከፍተኛ ፍጥነት ስለሚበሩ የጥንቶቹ ቀናት የእርጋታ ጉዞ ውበት፤ ለዛው ሙጥጥ ብሎ ጠፍቷል፡፡ ያኔ፣ ኤለን እጆቿን አጣጥፋ የረጋ ወተት ቅቤ ይወጣዋል እያለች እስካርሌትን በመምከር፣ ደግማ ደጋግማ ነገሯን ሁሉ እንድታስብበት ሞክራ ነበር፡፡ ሆኖም እስካርሌት የእናቷን ልመና ሁሉ ጆሮ ዳባ ልበስ ብላ ሜዳ አፈሰሰችው፡፡ ማግባቱን አገባች፡፡ ያውም ባንዳፍታ- በሁለት ሳምንት ውስጥ፡፡


አሽሌይ ከሰራዊቱ ጋር በተጠራ ጊዜ ለመሄድ እንዲያመቸው የሠርጉን ቀን ከበጋው መጀመሪያ ወደ ግንቦት መግቢያ ሲያዟዙረው እስካርሌት የሠርጓን ቀን ከሱ ሰርግ በፊት አደረገችወ፡፡ ኤለን እምቢ ብላ ነበር፡፡ ነገር ግን ከዋድ ሐምፕተን ሻለቃ ጦር ጋር ወደ ደቡብ ካሮላይና ለመሄድ ቻርለስ በጣም በመጣደፉ፣ በአዲስ ፍቅሩም ግፊት በመወትወቱ፣ ጄራልድም ሁለቱን ወጣቶች በመደገፉ፣ የተባለው ሠርግ እሷ በፈለገችው ቀን ለመሠረግ በቃ፡፡ ጄራልድ፣ አንድም በጦርነቱ ትኩሳት ምክንያት፤ አንድም እስካርሌት ጥሩ አቻ፣ አልፋም እኩያ ለመምረጥ በመቻሏ ተደስቶ የሠርጉን መፋጠን ይሁን አለ፡፡ ለዛውስ ጦርነቱ መጣሁ መጣሁ እያለ በሚፎክርበት ሰዓት በሁለት ፍቅረኛሞች ማህል ጣልቃ ገብቶ-አርጉ አታርጉ የሚለው፤ እሱ ማን ነውና ነው? ኤለን ሌሎች የደቡብ ሴቶች እንደሚያደርጉት ሁሉ ተሟግታ ተሟግታ በመጨረሻው እጇን ሰጠች፡፡ በእርጋታና በትርፍ ጊዜ የመዝናናት ወግ የተሞላው ዓላማቸው፤ ግርግር በበዛበት ዝባዝንኬ ሕይወት በመተካቱ፤ ልመናቸው፣ ፀሎታቸውና ምክራቸው ሁሉ ከንቱ ቀርቶ፤ እንደ ጎርፍ እየጠራረገ ከሚወስዳቸው ጠንካራ ንፋስ ጋር አብረው እንዲነፍሱ ተገደዱ፡፡
ደቡብ በጉጉትና በጦርነት ስሜት ተሳክሯል፡፡ መቼም ጦርነቱን በአንድ ውጊያ ከፍፃሜ እንደሚያደርሱት ማንም ያውቃል፡፡ በዚህ ምክንያት እያንዳንዱ ወጣት በጥድፊያ ለጦርነቱ ይመዘገባል፡፡ ስለዚህ ለፍቅረኛው በጥድፊያ ቀለበት ያስራል፡፡ ቀለበት ያሰረው ደግሞ በአጭር ጊዜ ሠርጉን ይደግሳል፡፡ እንዲህ በቶሎ አቀለጣጥፎ ጋብቻውን ውል እያስያዘ ወደ ቨርጂኒያ ሄዶ ያንኪዎችን ድባቅ ለመምታት ልቡ ተነሳስቷል፡፡ በደርዘን የሚቆጠሩ ከጦርነቱ በፊት የሚፈጸሙ የጋብቻ ሥነ-ስርዓቶች ስላሉ፣ ሰው ሁሉ ለመለያያ ለቅሶና ለሀዘን ምንም ጊዜ የለውም፡፡ ሴት ሴቶቹ ዩኒፎርም ይሰፋሉ፣ ካልሲዎች ይጠልፋሉ፣ የሚጠቀለሉ ፋሻዎችን ያዘጋጃሉ፡፡ ወንድ ወንዱ የሰልፍ ልምምዱንና ተኩሱን ተያይዞታል፡፡ ከአትላንታ በስተሰሜን ወደምትገኘው ወደ ቨርጂኒያ የሚሄዱ በሠራዊት የተሞሉ ባቡሮች በጆንስቦሮ እያቋረጡ እንደጉድ ይግተለተላሉ፡፡ ለሚሊሺያው ዩኒፎርም ለማዘጋጀት በተመረጡ ሕዝባዊ ኩባንያዎች የተሰፉትን፤ ደማቅ ቀይ፣ ውሃ ሰማያዊና አረንጓዴ ዩኒፎርሞች የለበሱ የተለያዩ ክፍሎች በደስታ ይተምማሉ፡፡ አንዳንድ ትናንሽ ቡድኖች ደግሞ እቤት የተሰፉ ባርኔጣዎችን አድርገዋል፡፡ ሌሎች ከናካቴው ዩኒፎርም ያልለበሱም አሉባቸው፡፡ ሁሉም ቢሆኑ በግማሽ ሥልጠናና በግማሽ ትጥቅ የሚጓዙ ናቸው፡፡ ነገር ግን በስሜት ተሞልተው ሊፈነዱ ከመድረሳቸው የተነሳ እየጮኹ ወደ ሽርሽር የሚሄዱ ይመስላሉ፡፡ እነዚህን ዘማቾች የሚመለከቱት ገና በዝግጅት ላይ ያሉት ወጣቶች ልምምዱን አገባደው ቨርጂኒያ ከመድረሳቸው በፊት ጦርነቱ አልቆ ጉድ እንዳይሆኑ ሰግተዋል፡፡ በዚህም ምክንያት ሠራዊቱን ቶሎ የማዝመት ተግባር በጣም በጥድፊያ እየተሠራ ነው፡፡


በዚህ የጦርነት ጥድፊያ ማህል የእስካርሌት ሠርግ ድግስ ደግሞ እየተጧጧፈ ነው፡፡ በዚህ ተብሎ በዚያ እሷ ራሷ እንኳ መቼ ተገባደደ ብላ ባላሰበችበት ሰዓት የኤለንን የሙሽራ ልብስ ከነቩዋሉ ለብሳ፣ የአባቷን ክንድ ይዛ፣ የታራን ደረጃ በከፍተኛ አጀብ ወርዳ በእንግዶች ጢም ብሎ ወደተሞላው አዳራሽ ገባች፡፡ ሁሉ ነገር ካለፈ በኋላ እንደህልም ውል ውል የሚላት- ግድግዳው ላይ የተሰቀሉት በመቶ የሚቆጠሩ የሚንቦገቦጉ ሻማዎች፣ የእናቷ በፍቅር የተሞላ ፊትና በመጠኑ ደንገጥ ያለ አኳኋን፣ እንዲሁም ጋብቻዋ የአብርሃም የሣራ እንዲሆን ስትጸልይላት በዝግታ ይንቀሳቀሱ የነበሩ ከንፈሮቿ፣ ጄራልድ በብራንዲና በኩራት ፊቱ በላብ ቸፍ ብሎ፣ ሴት ልጁ ገንዘብም፣ መልካም ስምም፣ ደህና ዘርም ያገባች መሆኗ ሲያስፈነድቀው፣ አሽሌይ ደግሞ ከደረጃዎቹ ግርጌ ክንዱን ከሜላኒ ክንድ ጋር እንዳቆላለፈ ቆሞ፣ የሚታየው ትርዒት ነው፡፡ በአሸሌይ ፊት ላይ የሚነበበውን ሁኔታ ስታይ የሚከተለው ሀሳብ መጣባት- “ይሄ እውን ሊሆን አይችልም፡፡ ሊሆን አይችልም፡፡ ቅዠት ነው፡፡ ሕልም ነው፡፡ አሁን ባላስበው ይሻላል እንጂ በዚህ ሁሉ ሰው ፊት ጩኸቴን እለቀዋለሁ፡፡ አሁን በጭራሽ ለማሰብ አልችልም፡፡ ሌላ ጊዜ፣ ዓይኖቹን ለማየት በማልችልበት ጊዜ አስብበታለሁ፡፡”
ፈገግ ባሉትና በተሰበሰቡት እንግዶች ማህል ማለፉም ቢሆን ህልም የመሰለ ነገር ነው፡፡ የቻርለስ ሳምባ የመሰለ ፊትና የሚንቀጠቀጥ ድምጽ፣ የሷም ቀዝቃዛና ግራ የተጋባ መልክ ይታያል፡፡ በመጨረሻ እንኳን ደስ ያለሽ የመባሏ፣ የመሳሟ፣ የጥብስ ግብዣው፤ ዳንሱ ሁሉ እንደህልም ያለፈ ነገር ነበር፡፡ አሽሌይ ጉንጯን ሲስማት የተሰማት ስሜት፣ የሜላኒ “አሁን በእርግጥ እውነተኛ እህትማማቾች ሆንን” የሚል ለስላሳ ድምፅ-ይሄ ሁሉ እውን ያልሆነ ቅዠት ነበር፡፡ የቻርለስን አክስት ወይዘሮ ፒቲፓት ሐሚልተንን ከመቀመጫቸው ያስነሳቸው የስሜት ግንፋሎት እንኳን ሳይቀር፤ የሰመመን መንፈስ እንደዋጠው ባለ ሕልም ነው የሚታያት፡፡
ሊነጋጋ ሲል ዳንሱም ግብዣውም ሲገባደድ፤ ታራንና የምስለኔውን ቤት አጨናንቀውት የነበሩት ከአትላንታ የመጡት እንግዶች፤ በየአልጋው፣ በየሶፋውና በየምንጣፉ ላይ ሲተኙ፤የጎረቤቶችም ሰዎች ሁሉ በሚቀጥለው ቀን በ”አሥራ ሁለቱ ዋርካዎች” መናፈሻ ቦታ ለሚደረገው ሰርግ ለመዘጋጀት ወደየቤታቸው ሲሄዱና አካባቢው ሁሉ እርጭ ሲል፤ ያ ሁሉ እንደህልም እንደ ቅዠት የታየ ነገር ከገሃዱ ዓለም ጋር ተጋጨና እንደ መኪና መስታወት እንክትክቱ ወጥቶ ዱቄት ሆነ፡፡ ገሃዱ ዓለም፤ አንገቷ ድረስ አንሶላውን ስባ የማይጥም መልኳን ስታሳየው እንኳ ከምንም ሳይቆጥራት በደስታ የሚፈነድቀውን ቻርለስን አሳያት፡፡
እስካርሌት ባልና ሚስት በአንድ አልጋ ውስጥ እንደሚያድሩ በደንብ ታውቃለች፡፡ ነገር ግን እስከዚህም ከጉዳይ ጽፋ አስባበት አታውቅም፡፡ ከእናቷና ከአባቷ አንፃር ስታየው ነገሩ ትክክል ነው፡፡ በራሷ ላይ ደርሶ ስታየው ግን በጭራሽ አልዋጥ አላት፡፡ አሁን ለመጀመሪያ ጊዜ ከዛ ከ”አሥራ ሁለቱ ዋርካዎች” ግብዣ በኋላ በራሷ ላይ ምን ዓይነት መዘዝ እንዳመጣች ተገነዘበች፡፡ ለራሷ በችኮላ የማይሆን ውሳኔ በመወሰኗ የፀፀት ምጥ በሚያሰቃያትና አሽሌይን ለዘለዓለም የማጣቷ ነገር እንደ እግር እሳት በሚለበልባት ሰዓት፤ የዚህ ልታገባው ፈጽሞ እቅድ ያልነበራት ልጅ አብሯት አንድ አልጋ ውስጥ ማደር፤ በጭራሽ ልትሸከመው ከምትችለው በላይ ሆኖባታል፡፡ እሱ እያመነታ ወደ አልጋው ሲጠጋ በጎረነነ ድምጿ አንሾካሾከችለት፡፡
“እንዲች ብለህ ብትጠጋኝ እሪ ብዬ ነው የምጮኸው! ላንቃዬ እስከሚሰነጠቅ አገሩን አደባልቀዋለሁ! በል ካጠገቤ ጥፋ! ጫፌን ንካኝና ወዮልህ!”
ቻርለስ ሐሚልተን በዚህ ዓይነት የሠርጉ ዕለት ማታ በመኝታ ቤቱ ጥግ ባለ፣ ባለመደገፊያ ወንበር ላይ ጉልበቱን ታቅፎ አደረ፡፡ ይህን ያህልም አልከፋውም፡፡ ምክንያቱም የሙሽራይቱን ትህትናና ልስላሴ ስለተረዳው ወይም የተረዳው ስለመሰለው ነው፡፡ ፍራቻዋ ሁሉ ሟሙቶ እስኪጠፋና እሱን ለመቀበል ዝግጁ እስክትሆን ድረስ ለመጠበቅ ፈቃደኛ ሆነ፡፡ ብቻ…ብቻ እየተገላበጠ፣ ለመመቻቸት እየሞከረ በጣም በቅርቡ ወደ ጦርነት እንደሚሄድ አሰበና አንዴ በኃይል ተነፈሰ፡፡


የእስካርሌት ሠርግ እንደሕልም እንደቅዠት እንዳለፈ ሁሉ የአሽሌይ ደግሞ ከሷ በባሰ የሕልም ጭጋግ ውስጥ እንደተሸፈነ አለፈ፡፡ እስካርሌት በ”አሥራ ሁለቱ ዋርካዎች” መናፈሻ እልፍኝ፣ ውሃ አረንጓዴውን “የሠርግ ማግስት ቀሚሷን” እንደለበሰች ከትላንት ማታ ጀምሮ እየበሩ ባሉት በመቶ በሚቆጠሩ ሻማዎች ማህል ቆማ፤ የሜላኒ ሐሚልተን ትንሿ ፊት የውበት ፀዳል ስትጎናፀፍ ተመለከተች፡፡ ወ/ት ሜላኒ ሐሚልተን ወ/ሮ ሜላኒ ዊክስ በምትሆንባት በዚህች ቅፅበት ፊቷ ላይ የሚበራው ቁንጅና እጅግ አስደንጋጭ ነው፡፡ እንግዲህ አሽሌይ ለአንዴም ለሁሌም መሄዱ ነው፡፡ ከጭብጧ ተፈልቅቆ ወጥቶ ማምለጡ ነው፡፡ የሷው አሽሌይ፡፡ አዬ! ምኑን የሷው ሆነው፣ አሁንማ የሰው አሽሌይ ሆኗል፡፡ ለመሆኑ የሷ ሆኖስ ያውቃል እንዴ? እስካርሌት በጭንቅላቷ ውስጥ መዓት ነገሮች እየተርመሰመሱ የምታስብ የምታልመውን ሁሉ አሳጧት፡፡ ጭንቅላቷም ለማሰብ ከሚችለው በላይ ስለበዛበት ደከመው፡፡ ተረባበሸ፡፡ አሽሌይ አፈቅርሻለሁ ሲላት አልነበረም እንዴ? ታዲያ ምን ለያያቸው? ይሄን ለማስታወስ ብትችል በጣም ጥሩ ነበር፡፡ ቻርለስን በማግባቷ የመንደሩን ሰዎች ሐሜተኛ ምላስ እንዲታጠፍ አድርጋ፣ አፋቸውን አስዘግታ ነበር፡፡ ዳሩ ያ አሁን ለሷ ምን ረባት? በዚያን ጊዜ በጣም ትልቅ ጉዳይ ነበር፡፡ አሁን ግን ከቁጥር የሚጣፍ ነገር አይደለም፡፡ ያም ቢሆን ለሷ ትልቁና አስፈላጊው ጉዳይዋ አሽሌይ ብቻ ነበር፡፡ አሁን እሱም አመለጣት፡፡ እሷም ብትሆን፤ አለማፍቀር ብቻ ሳይሆን በጣም ከምትጠላው ሰው ጋር ተጋብታ አርፋለች፡፡
(ከነቢይ መኮንን “ነገም ሌላ ቀን ነው” መጽሐፍ የተቀነጨበ)

 

ኢትዮጵያን በቅኝ ግዛት ለመያዝ ለሁለት ሺ ዓመታት ያህል የተደጋገመ ሙከራ ተደርጓል፡፡ ኢትዮጵያውያን ግን አገራቸውን በሌላ ባዕድ ሳያሲዙ ባላቸው ኃይል ሲከላከሉ ቆይተዋል። በኤሮፓም ሆነ በአሲያ ወይም በአፍሪካ የሚነሱ ታላላቅ መንግሥታት ጉልበት እያገኙ ግዛታቸውን በሚያሰፉበት ጊዜ ኢትዮጵያንም ለመደረብ ብዙ ጊዜ ሞክረዋል = ኢትዮጵያውያን ግን ለማንም ሳይበገሩና ሳይገብሩ እስካ ሁን አገራችንን አስከብረው ቆይተዋል።
መለስ ብለን ከታሪካችን ውስጥ በመጠኑ ብንመለከት፣ የሚያኮራንንና የሚያስመካንን ታሪክ ማግኘት እንችላለን። ከክርስቶስ በፊት በ336 በግሪክ ላይ ነግሶ የነበረው ታላቁ አሌክሳንደር ግዛቱን እያሰፋ ከመቆዶንያ’ ግብጽ ድረስ ተሻገረ። ብዙ አገሮችም በጦር ሳይሆን ገና በዝናው እየፈሩ ገበሩለት። ኩዌንቱስ ኩርቲውስ የተባለው የዘመኑ ታሪክ ፀሐፊ የአሌክሳንደርን ግዛት ማስፋፋትና ለጦርነት መነሳት ሲገልጽ፤ “…ወጣቱ ንጉሥ ለጦርነት ሲነሳ የምወረው ግብጽን ብቻ አይደለም። ኢትዮጵያንም ጭምር ነው።…” ማለቱን ጽፏል። አሌክሳንደር ዝቶ እንደተነሳው ከግብጽ ጀምሮ እስከ ህንድ ድረስ አስገበረ። በመሀል ግን ኢትዮጵያ ከገባሪዎች ተነጥላ ቀረች። አሌክሳንደር ስለ ኢትዮጵያውያን ጀግንነት ሰምቶ ነበርና ከኢትዮጵያውያን ጋር ጦርነት ለመግጠም ፈራ። ስለኢትዮጵያውያን የሚነገረው ጀግንነትም እውነት ስላልመሰለው ራሱ አሌክሳንደር ኢትዮጵያ ውስጥ ገብቶ ለመሰለል ተነሳ። ክሮኒክልስ ኦፍ ጆን ፣ ቢሾፕ ኦፍ ኒኩ በሚባለው መጽሐፍ ላይ እንደሚተርከው፤ “አሌክሳንደር ከምርጥ የጦር አለቆቹ ጋር ሆኖ ሁሉም ተራ ሰው መስለው ለመሰለል ወደ ኢትዮጵያ ገቡ። ኢትዮጵያዊቷ ንግሥት ህንደኬም አሌክሳንደር ተራ ሰው መስሎ ወደ ኢትዮጵያ ለመሰለል መግባቱን ሰማች። ንግሥቲቱ እነኚያን እንግዳ ተራ ሰዎች ወደ ቤተ መንግሥትዋ አስጠርታ እንዲህ አለች፤ ‘ዓለምን አንቀጥቅጠህ የገዛህ ታላቁ እስክንድር ሆይ ፧ ዛሬ በሴት እጅ ተይዘሃል’ ስትለው ንጉሡ በመታወቁ ደንግጦ ጥበቧን አደነቀ። የኢትዮጵያን ወታደር ብዛትና የሰላዮቿን ጥበብ አድንቆ “ንግሥት ሆይ፤ የተነገረኝ ሁሉ እውነት ነው = ይህ በጦር የማይፈታ ሕዝብ ነውና እኔና አንቺ ተጋብተን ዓለምን እንግዛ አላት” ይላል።
ኢትዮጵያን ለማስገበር ከተነሱት ታላላቅ የኤሮፓ ነገሥታት መሀል አንዱ አወጉስቶስ ቄሳር ነው። የሮማው አግውስቶስ ቄሣር ኤሮፓንና አፍሪካን፣ ኤስያንም ጭምር አስገብሮ በሥልጣኑ ሥር ካደረገ በኋላ ከክርስቶስ ልደት በፊት በ29 ዓመት ላይ አይሎስ ጋሎስ በሚባል ጦር አዛዥ የሚመራ 10,000 እግረኛና 8,000 ፈረሰኛ ጦር ወደ ኢትዮጵያ ላከ። በዚያን ዘመን የአክሱም መንግሥት ገንኖ ስለነበር፣ የኢትዮጵያ የባህር ኃይል ፈጽሞ የማይበገር መሆኑን ያወቀው አይሎስ ጋሎስ፤ ጦሩን በግብጽና በዛሬው ሱዳን በኩል አሻግሮ የአክሱምን መንግሥት ለመውጋት ገሠገሠ = ይህን የሰሙ ኢትዮጵያውያን ጦራቸውን ከትተው የአውግስቶስ ቄሣርን ጦር ከወሰናቸው ማዶ አቆሙት። ለብዙ ዓመታት ውጊያው ተካሂዶ ኢትዮጵያውያን አልበገር በማለታቸውና ከሮማ የመጣው ጦርም እየመነመነ በመሄዱ፣ የሮማው ጦር አዛዥ አይሎስ ጋሎስ ከሮማው ንጉሥ በታዘዘው መሠረት፣ ጦርነቱ በእርቅ አልቆ የተረፈው የሮማ ጦር ወደ አገሩ ተመለሰ።
በቅርቡ የአድዋን ጦርነት ብድር ለመመለስ ፋሺስቶች በኢትዮጵያ ላይ ጦርነት እንዳወጁት ሁሉ በአውግስቶስ ቄሣር የደረሰውን ሽንፈት ብድር ለመመለስ፣ በ54 ዓ.ም በሮማ የነገሰው ኔሮ ፎክሮ ተነሳ- የኔሮ አማካሪዎችም፣ ኢትዮጵያውያን አገራቸውን የማያስነኩና በጦርነትም የማይሸነፉ ሕዝቦች መሆናቸውን ነግረው፣ ያሁኑ ወደ ኢትዮጵያ ጦር መላክ የባሰ ውርደት ይሆናል በማለት አስጠነቀቁት፡፡
ኔሮ የአማካሪዎቹን ምክር ቢሰማም የዘመኑን የኢትዮጵያን ጦር የሚሰልል የስለላ ቡድን ወደ ኢትዮጵያ ላከ። እዚህ ላይ ሮማዊው የዘመኑ ታሪክ ፀሐፊ ሴኔካ ከፃፈው ታሪክ በጥቂቱ እንጥቀስ፤ “ኔሮ የአባቶቹን ምኞት ለመፈፀም የአባይን ምንጭ የሚፈልጉ ናቸው ብሎ ለኢትዮጵያው ንጉሥ ደብዳቤ ጽፎ ሰላዮቹን ወደ ኢትዮጵያ ላከን = የተላክነው ሰላዮች ኢትዮጵያ ውስጥ ከርመን ስንመለስ ሕዝቡ ጦረኛ መሆኑንና በአሁኑ ጊዜ ወደ ኢትዮጵያ ጦር መላክ እንደማያዋጣ ነገርነው፡፡ አገሪቱ ግን እጅግ በጣም ለም ናት አልነው” ሲል ከስለላ ቡድኑ ጋር አብሮ የነበረው ሴኔካ ጽፏል።
ይህ ሁሉ ቢሆንም ኔሮ አባቶቹ ያልቻሉትን ኢትዮጵያን የማስገበር ምኞት እሱ እንደሚችል ተማምኖ ካምቤይስ በሚባል ጦር መሪ የሚመራ ጦር፣ ወደ ኢትዮጵያ ልኮ ጦሩ ድል ሆኖ መመለሱን ታሪክ ፀሐፊዎቹ ዲዩ ካሲዮ እና ፕሊኒ ጽፈዋል።
ዛሬ በዓለም ላይ አሉ እንደሚባሉት አራቱ ኃያላን መንግሥታት ሁሉ፤ ኢትዮጵያም በሦስተኛው መቶ ዓመት በዓለም ላይ አሉ ከሚባሉት አራቱ ኃያላን መንግሥታት አንዲቱ ነበረች፡፡ ሂስቶሪካ አውጉስታ በሚባለው የታሪክ መጽሐፉ ማኒ በ275 ዓ.ም እንደፃፈው፤ “…… በዓለም ካሉት አራቱ ታላላቅ መንግሥታት አንዷ ኢትዮጵያ ናት = የኢትዮጵያው የአክሱም መንግሥት በወታደርና በጦር መሣሪያ የበለፀገ በመሆኑ ለወዳጁ አገሮች ርዳታ በመስጠት የታወቀ ነው….” ብሏል፡፡ እነ ኮንቲ ሮስኒም ይህን አረጋግጠዋል።
ኢትዮጵያን አስገብሮ ለመያዝ የተደጋገመ የውጭ ጦር ቢመጣም ኢትዮጵያውያን ባላቸው ኃይል የማይበገሩ ሆነው የሚመጣውን የውጭ ጦር ሁሉ መልሰዋል። ኢትዮጵያውያን የራሳቸውን የማይለቁና የሌላ አገር የማይፈልጉ በመሆናቸው እንጂ እንደ ታሪክ ፀሐፊዎች መስካሪነት ከሆነ፣ ኤሮፕንም ሆነ እስያን እያለፉ የሚይዙበት ብዙ ዘመን ነበር = በ1298 የባህር ላይ ጉዞውን የጀመረው ማርኮ ፖሎ በፃፈው ታሪክ ስለ ኢትዮጵያውያን ሲገልጽ እንዲህ ይላል፤ “…ልታውቁት የሚገባ - ነገር አለ = በአበሻ ምድር ምርጥ የሆኑ ወታደሮች አሉ፡፡ አብዛኛዎቹ ወታደሮችም ፈረሰኞች ናቸው። ፈረስም በብዛት አላቸው። በዚህም ምክንያት ተዋጊዎችና ኃይለኞች ናቸው። በህንድ አገር ስላሉትና ከምናደንቃቸው እውቅ የሕንድ ወታደሮችም የሚበልጡ ናቸው ……” ብሏል = ባጭሩ በዚሁ ይብቃን።
(“የኢትዮጵያና የኢጣሊያ ጦርነት” ከተሰኘው የጳውሎስ ኞኞ መጽሐፍ መግቢያ የተወሰደ)

 

 

 

Page 3 of 759