
Administrator
የህይወት ተፈራ 'ተድባብ' ታሪካዊ ልቦለድ ላይ ውይይትና ዳሰሳ አለ: በዋሊያ መጽሐፍት::
በዘነበች ታደሰ ህይወትና ሥራ ላይ ያተኮረ መፅሀፍ ይመረቃል
ዘነበች ታደሰ ማን ነች? ለምንስ ጭራ ቀረሽ የሚል ስያሜ ተሰጣት? ለጥበብ ምን አበረከተች? የሚሉ ጥያቄዎችን ሊመልስ የሚችል የአርቲስት ዘነበች ታደሰን ህይወት የሚዳስስ በፅሁፍና በምስል የተደራጀ መፅሐፍ በዶ/ር ጌታቸው ተድላ ተዘጋጅቶ ለአንባቢያን ሊቀርብ ነው።
ታህሳስ 12 2017 በሀገር ፍቅር ቴአትር የሚመረቀው ይህ መፅሀፍ 167 ገፆች ያሉት ነው።
ለሀገራዊ ምክክሩ መሳካት የመገናኛ ብዙኃን ሚና የላቀ ነው ተባለ
ለሀገራዊ ምክክሩ መሳካት የመገናኛ ብዙሃን ሚና የላቀ መሆኑን የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ምክር ቤት ገለፀ። ምክር ቤቱ ከተለያዩ የሚዲያ ባለሞያዎችና የዩኒቨርስቲ ምሁራን ጋር “በሀገራዊ ምክክሩ የመገናኛ ብዙኃን ሚና ምን ይመስላል“ በሚለው ጉዳይ ላይ ምክክር አድርጓል።
መገናኛ ብዙሃን ታማኝ፣ ነፃና ገለልተኛ የሆነ ሙያዊ ሃላፊነት የሚስተናገድበት ተቋም መሆኑን ያነሱት የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ምክር ቤት የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ አማረ አረጋዊ፤ ኢትዮጵያ የጀመረችው ሀገራዊ ምክክር የተሳካና ውጤታማ እንዲሆን መገናኛ ብዙኃን ድርሻቸው የጎላ እንደሆነና ለዚህም በትጋት መስራት እንደሚገባ ገልጸል፡፡
ሀገራዊ ምክክሩ ኢትዮጵያ ከገባችበት ችግር የምትወጣበት አይነተኛ መንገድ ነው ያሉት የሀገራዊ ምክክሩ ኮሚሽነር ተገኘ ወርቅ ጌቱ (ዶ/ር) ፤ ምክክሩ በሀገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች እየተሰራ እንዳለና በቀጣይም በአማራና በትግራይ ክልሎች ምክክሩን ለመጀመር የተለያዩ ስራዎች እየተሰሩ ስለመሆኑ ተናግረዋል፡፡
በአማራ ክልል ሀገራዊ ምክክሩን ለመጀመር ከ1 ሺህ 700 በላይ ተባባሪ አካላትን አሰልጥኗልም ብለዋል። በሀገራዊ ምክክሩ ላይ መገናኛ ብዙኃን ላበረከቱት አስተዋፅኦ አመስግነው፣ ምክክሩ የተሳካ እንዲሆን ሁሉም ኢትዮጵያዊ የድርሻውን ማበርከት እንደሚገባም ጥሪ አቅርበዋል።
የቴሌግራም ቻናልችንን በመቀላቀል የአዲስ አድማስን መረጃ ይከታተሉ…
https://t.me/AdissAdmas
ሲንቄ ባንክ ከዴሎይት ጋር የምክር አገልግሎት ስምምነት ተፈራረመ
ድምጻዊት ቬሮኒካ አዳነና ቀላቲ ቢውቲ ለ2 ዓመት ተፈራረሙ
እናት ባንክ፤ ሁለት እናት ተኮር ውድድሮችን ዛሬ በይፋ አስጀመረ
የዘንድሮ የሺህ ጋብቻ አፍሪካውያን ጥንዶችንም ያካትታል
የሺህ ጋብቻ ኹነትን በማዘጋጀት የሚታወቀው ያሜንት ኃ. የተ.የግ.ማ፤ ሦስተኛውን የሺህ ጋብቻ ጥር 18 ቀን 2017 ዓ.ም በአዲስ አበባ ሚሊኒየም አዳራሽ ያካሂዳል፡፡ በዚህ ኹነት ላይ 1ሺ ኢትዮጵያውያን ጥንዶችና 250 የሚደርሱ ከአፍሪካ አገራት የተውጣጡ ጥንዶች የሰርግ በዓላቸውን እንደሚያከብሩ ታውቋል፡፡
የሺህ ጋብቻ ትልቁ ዓላማ፣ የኢትዮጵያን እንዲሁም የአፍሪካ ሀገራት ህዝቦችን የካበተ ባህላዊ የሰርግ ሥነ-ሥርዓት አጉልቶ በማሳየት፣ አዲስ አበባን “የሃኒሙን ማዕከል” ማድረግ እንደሆነ አዘጋጆቹ ገልጸዋል።
የኹነቱ አዘጋጆች ሦስተኛውን የሺህ ጋብቻ አስመልክቶ ባለፈው ቅዳሜ ታህሳስ 6 ቀን 2017 ዓ.ም በሃርመኒ ሆቴል ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡
ዘንድሮ በሚካሄደው የሺህ ጋብቻ በተቻለ መጠን ከሁሉም ብሔርና ብሔረሰቦች የተውጣጡ ጥንዶች የሚሳተፉበት እንዲሆን እየተሰራ መሆኑንና ሙሽሮች ለሠርጋቸው የሚያወጡት ምንም ዓይነት ወጪ እንደማይኖር በመግለጫው ላይ ተጠቁሟል፡፡
የሺህ ጋብቻ የሠርግ ሥነሥርዓትና ባህላዊ ካርኒቫል፤ ከሠርግ ድግስ ጋር የተያያዙ፣ ለዘመናት የቆዩና ሥር የሰደዱ ጎጂ ማኅበራዊ አመለካከቶችን ለማስወገድና ወደ ለውጥ የሚያመራ ማኅበረሰባዊ ውይይት ለማንሳት እንደሚረዳ የተነገረ ሲሆን፤ ቤተሰብ በማህበረሰብ ግንባታ ውስጥ ያለውን ፋይዳ በማጉላት፣ ለበጎ አስተሳሰብ መጎልበት መሠረት መሆኑን ለማሳወቅ እንደሚረዳም ተጠቁሟል፡፡
የሺህ ጋብቻ፤ የውጭ አገር ጎብኚዎችን በመሳብ ከቱሪስት ፍሰት የውጭ ምንዛሪ ግኝትን መፍጠር፣ የባህል ልውውጥ መድረክ በመፍጠር ሃገሪቱ ለህዝቦች አንድነት መጠናከር እንዲሁም ለሰላምና ለባህሎች ዕድገት የምታደርገውን ጥረት መደገፍ አላማው ነው ተብሏል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ ያሜንት ኃ. የተ.የግ.ማህበር ኹነቱን በተሻለ መንገድ ለማስተዋወቅ፣ አርቲስት ተስፋዓለም ታምራትና ባለቤቱን ቃልኪዳን አበራ እንዲሁም አርቲስት ይገረም ደጀኔና ባለቤቱን ፅዮን ዮሴፍን የየሺ ጋብቻ አምባሳደር አድርጎ ሾሟል፡፡
ለዚህ ኹነት ያስፈልጋል ተብሎ የታቀደው አጠቃላይ በጀት ከ68 ሚሊዮን ብር በላይ እንደሆነ ለማወቅ ተችሏል፡፡
”ቤተሰብን መመስረት አገርን መገንባት ነው" የሚል መሪ ቃል ያለው ያሜንት፤ የመጀመሪያውን የሺ ጋብቻ ኹነት በ2005 ዓ.ም 500 ጥንዶችን በመዳር ማከናወኑ ይታወሳል፡፡
ድርጅቱ በመጀመሪያው ዙር ለተጋቡ ጥንድ ሙሽሮች የ10ኛ ዓመት ክብረ በዓላቸውን በሸራተን አዲስ ያከበረላቸው ሲሆን፤ ለሁለተኛው ዙር ሙሽሮች የመልስ ጥሪ በግዮን ሆቴል ሳባ አዳራሽ ተደርጎላቸዋል፡፡
ሁላችሁም በአክብሮት ተጋብዛችኋል! #photographexhibition
የኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ የብላቴን ጌታ ኅሩይ ወ/ሥላሴ የሥነ-ጥበባት ማዕከል ከአዲስ አበባ ፎቶግራፍ ባለሙያዎች ማኅበር ጋር በመተባበር የፎቶግራፍ አውደርዕይ አዘጋጅቷል፡፡
በዚህ አውደርዕይ ታዋቂ ባለሙያዎች አንቶኒዮ ፍዮሬንቴ፣ ሙሉጌታ አየነ፣ ማኅደር ኃይለሥላሴ፣ ናሆም ተስፋዬና ሚካኤል ጸጋዬ ሥራዎቻቸውን ያቀርባሉ፡፡
አውደርዕዩ ቅዳሜ ታህሳስ 12 2017 ዓ.ም 10፡00 ላይ በአካዳሚው ሙዚየም በይፋ ይከፈታል፡፡ መግቢያው በነጻ ሲኾን እንዲታደሙ በአክብሮት ተጋብዘዋል፡፡
የዝግጅቱ ቦታ:- በኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ የብላቴን ጌታ ኅሩይ ወልደ ሥላሴ የሥነ-ጥበባት ማዕከል፡፡
ከፒያሳ ወደ ውንጌት መስመር በሚወስደው ጎዳና - ቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል አካባቢ -
በተለምዶ ወረዳ ስምንት ተብሎ በሚጠራው ቀጭን መንገድ 500 ሜትር ገባ ብሎ
ወይንም ንግድ ባንክ ጉለሌ ቅርንጫፍ በኩል