Administrator

Administrator

እናት ፓርቲ ትናንት ህዳር 24 ቀን 2017 ዓ.ም. ባወጣው መግለጫ፣ በኦሮሚያ ክልል፣ ምሥራቅ ወለጋ ዞን፣ የአንዶዴ ዲቾ እና ደጋ ጂጊ ቀበሌዎች ነዋሪዎች “መከላከያ ሰራዊት ነን” ያሉ ሃይሎች ሰኞ ህዳር 23 ቀን 2017 ዓ.ም. ከንጋት 12 ሰዓት እስከ ጠዋት 3 ሰዓት በድንገት ከበባ በማድረግ ከ80 የማያንሱ የጦር መሳሪያዎቻቸውን እንደገፈፏቸው መናገራቸውን ገልጿል። ፓርቲው “በአሁኑ ወቅት ሕዝቡ በራስ ተነሳሽነት ራሱን ለመጠበቅ እያደረገ ያለው ጥረት ሊደገፍና ሊበረታታ እንጂ እንደወንጀል ሊቆጠር አይገባም” ሲልም አመልክቷል።

ፓርቲው በርካታ አርሶ አደሮች “መሳሪያችንን አንሰጥም” በማለት ጫካ እንደገቡና መሳሪያዎቹን ነጥቀው “የራሳችን” ለሚሉት ሰው “ሰጥተውታል” በማለት እንዳማረሩ “ሰምቼአለሁ” ያለው ፓርቲው፣ “የዞንና ወረዳ ካድሬዎችም ጫካ የገባውን ቤተሰቡን ‘እናስራለን፣ እንቀጣለን’ እያሉ እንደሚዝቱ ነዋሪዎቹ ተናግረዋል” በማለት አስረድቷል። “በአካባቢው ከፍተኛ ዘር ተኮር ጭፍጨፋ የተከሰተበት በመሆኑ ራስን መከላከል በሕግና በሥርዓት እንዲመራ ማድረግ የተሻለ አማራጭ እንደኾነ መታወቅ አለበት” ብሏል፣ እናት ፓርቲ በመግለጫው።

እናት ፓርቲ “የጸጥታ ሃይሉ ትርጉም ያለው ጥበቃ ለዜጎች በማያደርግበት ሁኔታ ነዋሪው ራሱን የሚከላከልበትን መሳሪያ መቀማት በቅርቡ በአርሲ የተከሰተው ዓይነት ጥፋት ለማድረስ ካልሆነ፣ ሌላ ትርጉም ሊሰጠው እንደማይችል ታውቆ የእርምት እርምጃ በአስቸኳይ እንዲወሰድ” ሲል ጥሪ ያቀረበ ሲሆን፣ “በአሁኑ ወቅት ሕዝቡ በራስ ተነሳሽነት ራሱን ለመጠበቅ እያደረገ ያለው ጥረት ሊደገፍና ሊበረታታ እንጂ እንደወንጀል ሊቆጠር አይገባም” በማለት አጽንዖት ሰጥቶ ነው ያመለከተው።

የክሪስታል ፓላስ አምባል ማርክ ጉዬ ባለፈው ቅዳሜ ከኒውካስል ጋር በነረበው ግጥሚያ የአምበልነት መለያው ላይ ‘አይ ላቭ ጂሰስ’ (እየሱስን እወደዋለሁ) ብሎ መፃፉ አነጋጋሪ ሆኗል።

የእንግሊዝ ፕሪሚዬር ሊግ አስተዳዳሪ የሆነው ኤፍኤ አምበሉ ላይ እርምጃ ከመውሰድ ቢቆጠብም ለክለቡ እና ተጫዋቹ መለያ ላይ ኃይማኖታዊ ፅሑፎችን መፃፍ ክልክል ነው የሚል ማስጠንቀቂያ ሰጥቷል።

ማክሰኞ ምሽት ፓላስ ከኢፕስዊች ታውን ጋር በነበረው ጨዋታ ማርክ ጉዬ የኤፍኤውን ማስጠንቀቂያ ችላ ብሎ ‘ጂሰስ ላቭስ ዩ’ አሊያም ‘እየሱስ ይወዳችኋል’ የሚል መልዕክት ፅፎበት ገብቷል።

የፕሪሚዬር ሊጉ ክለቦች ለኤልጂቢቲኪው+ ማኅበረሰብ ያላቸውን ድጋፍ ለማሳየት አምበሎቻቸው የቀስተ ደመና ኅብረ ቀለማት ያሉትን መለያ ክንዳቸው ላይ አጥልቀው እንዲገቡ ያደርጋሉ።

ፉትቦል አሶሲዬሽን የተባለው የሊጉ አስተዳዳሪ ኃይማኖታዊ ምልክቶች የእግር ኳስ ማሊያ እና ሌሎች ቁሳቁሶች ላይ መፃፍ ክልክል ነው ሲል ለክለቡ እና ለአምበሉ ማስጠንቀቂያ የላከው ባለፈው ቅዳሜ ነበር።

በተመሳሳይ የኢፕስዊች አምበል የሆነው ግብፃዊው አማካይ ሳም ሞርሲ ባለፈው ቅዳሜም ሆነ ማክሰኞ ምሽት በነበረው ጨዋታ የቀስተ ደመና ቀለማት ያሉትን የአምበሎች መለያ ሳያጠልቅ ነው የገባው።

 

ኢፕስዊች ታውን በለቀቀው መግለጫ ሞርሲ “በኃይማኖቱ ምክንያት” መለያውን ማድረግ እንደማይፈቅድ ማሳወቁ ይታወሳል።

ማክሰኞ ምሽት ከነበረው ጨዋታ በኋላ የፓላስ አሰልጣኝ ኦሊቨር ግላስነር ስለጉዳዩ ተጠይቀው “ማርክ የራሱ አተያይ አለው። የሁሉን ሰው አመለካከት እንቀበላለን፤ እናከብራለንም” ብለዋል።

ጉዬ ማስጠንቀቂያ ቢሰጠውም ጉዳዩን በመድገሙ ኤፍኤው ሊቀጣው እንደሚችል ይጠበቃል።

ይህ ዘመቻ ከአውሮፓውያኑ ኅዳር 29 እስከ ረቡዕ ታኅሣሥ 5 የሚዘልቅ ነው። የእንግሊዝ ፕሪሚዬር ሊግ ስቶንዎል ከተሰኘው የእርዳታ ድርጅት ጋር በመጣመር ነው አምበሎች ይህን ባንዲራ እንዲያጠልቁ የሚያደርገው።

የእስልምና እምነት ተከታይ የሆነው የኢፕስዊቹ አምበል ግብፃዊው ሳም ሞርሲ ይህን ባንዲራ አላጠልቅም ያለ የመጀመሪያው ተጫዋች አይደለም።

ከዚህ ቀደም በተመሳሳይ የእስልምና እምነት ተከታይ የሆነው የሼፊልድ ዩናይትዱ ተከላካይ አኔል አህመድሆድዚች ባንዲራውን አላጠልቅም ማለቱ ይታወሳል።

አሁን ለኤቨርተን የሚጫወተው ሴኔጋላዊው አማካይ ኢድሪሳ ጋና ጉየ ለፓሪ ሳን ዠርማ በሚጫወትበት ወቅት በተመሳሳይ የቀስተ ደመና ቀለማት ያሉትን ማሊያ አልለብስም ማለቱ አይዘነጋም።

19ኛው የብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በዓልን ምክንያት በማድረግ የ5 ኪሎ ሜትር ታላቅ ሩጫ በአርባምንጭ ከተማ ተካሂዷል፡፡

ሩጫው በህዝብ ተሳትፎና በክልሉ መንግሥት ድጋፍ እየተገነባ ለሚገኘው የአርባ ምንጭ ዓለም ዓቀፍ ስታዲየም ግንባታ ገቢ ለማሰባሰብ እንዲሁም በከተማው የሚከበረውን የብሔር፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን በዓልን አስመልክቶ የተዘጋጀ መሆኑ ተጠቅሷል፡፡

በጎዳና ላይ ሩጫው የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደን ጨምሮ ከፍተኛ የክልልና የዞን የሥራ ሃላፊዎች፣ ታዋቂው አትሌት ሙክታር ኢድሪስ፣ የ12ቱም ዞኖች ተወካዮች እንዲሁም ከ10 ሺህ በላይ የህብረተሰብ ክፍሎች መሳተፋቸውን የጋሞ ዞን ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡

መነሻውንና መድረሻውን ጋሞ አደባባይ ባደረገው የጎዳና ላይ ሩጫ በወንዶች አትሌት መክሊት መኮንን አሸናፊ ሲሆን፤ አትሌት ሙሉቀን ታደለ 2ኛ፣ አትሌት ሳሙዔል አብርሃም 3ኛ በመሆን አጠናቀዋል።

በሴቶች አትሌት ህሊና ሚልኪያስ 1ኛ በመውጣት ስታሸንፍ አትሌት በፀሎት አረጋ 2ኛ፣ አትሌት ሀገር ምንአለ 3ኛ በመውጣት የተዘጋጀላቸውን ሽልማት ተቀብለዋል።

ተናጋሪ፡- ረ/ፕ በቀለ መኮንን (ሠዓሊ፣ ቀራፂ እና ገጣሚ)
ርዕስ፡- ሐተታ ፅንሰ ሐሳባዊነት
ቦታ፡- በኢትዮጵያ ቤተ መዛግብት እና ቤተ መጻሕፍት (ወመዘክር) ግቢ
ብላቴን ጌታ ኅሩይ ወልደ ሥላሴ አዳራሽ
ሠዓት፡- ከ10፡00-12፡00
በዝግጅቱ ላይ የሚገኙ ከሆነ ይህንን ቅፅ በመሙላት ይመዝገቡ፡፡ ????
• ገቢው ሠዓሊ ብሩክ የሺጥላ በስዊድን ለሚያደርገው ህክምና ይውላል
ሠዓሊ ብሩክ የሺጥላ በቅርቡ በስዊድን ለሚያደርገው ህክምና ወጪን ለመሸፈን "ነጻነት" የተሰኘ የሥዕል ኤግዚቢሽን ማዘጋጀቱን በዛሬው እለት በጎልደን ቱሊፕ ሆቴል በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ አስታውቋል።
ጋዜጠኛ ኤደን ገብረህይወትና ራኬብ ሐብቴ በጋራ ባሰናዱትና የፊታችን ሐሙስ ሕዳር 26 ቀን 2017 ዓ.ም በሸራተን አዲስ፣ ላሊበላ አዳራሽ፣ ከምሽቱ 12 ሰዓት ጀምሮ በሚካሄደው የሥእል አውደ- ርዕይና የሥዕል ጨረታ ፕሮግራም ላይ ጥሪ የተደረገላቸው ሠዓሊዎችና የጥበብ ሰዎች እንደሚገኙ ታውቋል።
ሠዓሊ ብሩክ የሺጥላ ከ17 ዓመት ዕድሜው ጀምሮ አንኪሉዚንግ ስፖንዳላይተስ የተሰኘ አጥንት ውስጥ ያለ ፈሳሽን የሚያደርቅ ህመም አጋጥሞት ሙሉ በሙሉ ሰውነቱ እንዳይንቀሳቀስ ያደረገው ሲሆን፤ በቅርቡ በስዊድን ሀገር ለሚያደርገው የጉልበት ንቅለ ህክምና ወጪን ለመሸፈን "ነጻነት" የተሰኘ የስዕል ኤግዚቢሽን ተዘጋጅቷል።
ከዚህ የአንድ ቀን የሥእል አውደ ርዕይና የሥእል ጨረታ የሚገኘው ገቢ ሠዓሊ ብሩክ በቅርቡ በስዊድን ሀገር ለሚያደርገው የጉልበት ንቅለተከላ የሚውል ሲሆን፤ አጠቃላይ የህክምና ወጪው 3 ሚሊዮን ብር እንደሆነ ተነግሯል፡፡
 
 
የቴሌግራም ቻናልችንን  በመቀላቀል የአዲስ አድማስን መረጃ ይከታተሉ…
https://t.me/AdissAdmas
Monday, 02 December 2024 20:17

የዱር አበባ

የገጣሚ ቴዎድሮስ ካሳ የግጥም መፅሐፍ የፊታችን ቅዳሜ ሕዳር 28 ከ ቀኑ 11 ፡ 00 ጀምሮ መገናኛ በሚገኘው ሞሰብ የሙዚቃ ማዕከል ቅጥር ግቢ ውስጥ በድምቀት ይመረቃል ።
በእለቱ ሁላችሁም ተጋብዛችኋል።
የካሊንጋሊንጋገርልስ የሴቶች መንግሥታዊ ያልሆነ ድርጅት ባለአደራ በሆነት በያኒና ዱቤኮቭስካያ የተመሰረተውና ከናይጄሪያ፣ ዛምቢያ፣ ዚምባብዌ፣ ሩሲያ፣ ቤልጂየም እና ጀርመን የተውጣጡ ዓለም አቀፍ ዳኞችን ያካተተው ውድድር "እናት አፍሪካ" በሚል መሪ ቃል የተዘጋጀ ነው።
ሽልማቱ የ "ታዳጊ አርቲስቶች" እና "የታዋቂ ማስተሮች" በሚል ለሁለት የተከፈለ ሲሆን፤ ሁለቱም በሥዕል፣ ቅይጥ ሚዲያ እና ቅርፃ ቅርፅ እጩዎችን ሲቀበሉ፣ የታዳጊ አርቲስቶች ምድብ በስዕልና በዲጂታል ጥበብ ተጨማሪ እጩዎችን ያቅፋል።
በ "ታዳጊ አርቲስቶች" ምድብ የመጨረሻ እጩዎች ከናይጄሪያ፣ ሴራሊዮንና ዛምቢያ የተውጣጡ ሴቶች ሲሆን፤ በ "የታዋቂ ማስተሮች" ምድብ የተካተቱት የኢትዮጵያ፣ ናይጄሪያ፣ ናሚቢያና ዛምቢያ ተሳታፊዎች ናቸው።
(ስፑትኒክ ኢትዮጰያ)
የቴሌግራም ቻናልችንን በመቀላቀል የአዲስ አድማስን መረጃ ይከታተሉ…

“AI ENJOY” ውድድር ላይ ያሸነፉ የወርቅ ሜዳልያ ተሸለሙ
የኢትዮ-ሮቦቲክስ መስራችና ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ሰናይ መኮንን፤ በቅርቡ በቻይና በሚካሄደው ዓለማቀፍ የ”ኮዲንግ ስኪል ቻሌንጅ” ላይ 24 ተማሪዎች ኢትዮጵያን ወክለው እንደሚሳተፉ ተናገሩ።
ውድድሩ በየዓመቱ በቻይና እንደሚካሄድ ለአዲስ አድማስ የገለጹት አቶ ሰናይ፤ ዘንድሮም በሻንጋይ ከተማ ከዲሴምበር 14-16 ቀን 2024 ዓ.ም ለሦስት ቀናት እንደሚደረግ አመልክተዋል።
ለዚህም ኢትዮ ሮቦቲክስ ባለፈው ቅዳሜ የኢንጆይ ኤአይ አገር አቀፍ የመጨረሻ ውድድር አካሂዷል። በውድድሩ ላይም ቲም ናይል፣ ቲም አልፋ፣ ቲም ዊነርስ፣ ቲም ላየንስ፣ ቲም ኤግል፣ ቲም አቢሲኒያና ሌሎች ስያሳች የተሰጣቸው የታዳጊ ቡድኖች ተሳትፈዋል፡፡
አሸናፊዎችን ለመለየት በታዳጊ ቡድኖቹ መካከል እልህ አስጨራሽ ፍልሚያ የተካሄደ ሲሆን፤ የማታ ማታ የላቀ ብቃት ያሳዩ ተማሪዎች አሸንፈዋል። ታዳጊዎቹ ስፔስ ትራቭሊንግ፣ ጋላክቲክ ዲፌንስ ባትል እና ክሎዚንግ ሰረሞኒ ኦቭ ስፖርትስ በተሰኙ ዘርፎች ለሦስት ዙር ተወዳድረዋል፡፡
በመጨረሻም፣ ከየዘርፉ ከ1ኛ እስከ 3ኛ የወጡ አሸናፊዎች የወርቅ፣ የብርና የነሐስ ሜዳልያ እንዲሁም የምስክር ወረቀት ተሸልመዋል፡፡ የወርቅ ተሸላሚ የሆኑት ሦስት ቡድኖች የሚከተሉት ናቸው።
ቲም ኤግል -በ120 ነጥብ በክሎዚንግ ሰረሞኒ ኦቭ ስፖርትስ
ቲም ስፓርታ - በ630 ነጥብ በስፔስ ትራቭሊንግ ዘርፍ
ቲም ናይል - በ100 ነጥብ በጋላክቲክ ዲፌንስ ዘርፍ
ለአሸናፊዎቹ የወርቅ ሜዳልያ የሸለሙት የቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ሚኒስትሩ ተወካይ አቶ ሰላምይሁን አደፍርስ ባደረጉት ንግግር፤ ኢትዮ ሮቦቲክስ ከወትሮው ውድድር በተለየ የኤአይ እና ዲጂታል ስኪል አቀላቅሎ መምጣቱን አድንቀው፤ የድርጅቱ መሥራች አቶ ሰናይ ዘርፉን ለማሳደግ በየጊዜው እያደረገ ስላለው ጥረት አመስግነዋል፡፡
አክለውም፤ ውድድሩ ሰፋ ብሎ እንዲካሄድና ተደራሽ ይሆን ዘንድ የሚኒስቴር መ/ቤታቸው ለኢትዮ ሮቦቲክስ የሚያደርገውን እገዛና ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥል ቃል ገብተዋል፡፡
የኢትዮ ሮቦቲክስ መሥራች አቶ ሰናይ፤ በቅርቡ በቻይና የሚደረገውን የኮዲንግ ስኬል ቻሌንጅ አስመልክቶ በሰጡት ማብራሪያ፤ በእስካሁኑ ተሞክሮአችን ቻይናውያኑ ታዳጊዎች የተሻለ ልምድ ያላቸው በመሆኑ፤ በየዓመቱ ውድድሩን በአንደኝነት ነው የሚያጠናቅቁት ብለዋል፡፡
እንዲያም ሆኖ ታዳጊ ኢትዮያውያን ከዓመት ዓመት ቁጥራቸውን በመጨመርና ደረጃቸውን በማሻሻል በዓለማቀፍ ውድድሮች ላይ ኢትዮጵያን እያስጠሩ ነው- ብለዋል። የዲጂታል ኢትዮጵያ ተስፋዎችም እንደዚህ ዓይነቶቹ ታዳጊዎች መሆናቸውን ጨምረው ገልፀዋል።

7ኛው ዓመታዊ የሪል እስቴትና የቤት ኤክስፖ ታህሳስ 18 ቀን 2017 ዓ.ም በሸራተን አዲስ ሆቴል ይከፈታል፡፡ ለሦስት ቀናት የሚቆየው ኤክስፖው ከፍተኛ አልሚዎችን፣ ባለሀብቶችን፣ የፋይናንስ ተቋማትን፣ የቤት ገንቢዎችንና የቤተ ውበት ባለሙያዎችን ጨምሮ፣ የሪል እስቴትና የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪውን ከፍተኛ ባለድርሻ አካላት በአንድ ላይ እንደሚያሰባስብ ተነግሯል፡፡
የ251 ኮሙዩኒኬሽንና ማርኬቲንግ መሥራች አቶ አዲስ አለማየሁ እንደተናገሩት፤ የዘንድሮው ኤክስፖ በኢትዮጵያ ሪል እስቴት ዘርፍ ትልቅ ፋይዳ ያለው ክስተት ሲሆን፤ በኢንዱስትሪው ውስጥ ከፍተኛ ተደማጭነት ያላቸውን ተዋናዮች ያሰባስባል። አቶ አዲስ አክለውም፤ “ዘላቂ ልማትን፣ ፈጠራንና ኢንቨስትመንትን የሚያበረታታ መስተጋብራዊ መድረክ በመፍጠር የዘርፉን እድገት ለመደገፍ ቁርጠኛ ነን።” ብለዋል፡፡
ኤክስፖው በሪል እስቴት ዘርፍ ውስጥ ያሉ አዳዲስ እድገቶችን፣ ፈጠራዎችንና የኢንቨስትመንት እድሎችን ለማሳየት ያለመ ሲሆን፤ በኢንዱስትሪ መሪዎች መካከል ትስስርና ትብብርን ይፈጥራል ተብሏል።
በ7ኛው አመታዊ ሪል እስቴትና የቤት ኤክስፖ ላይ ከኤግዚቢሽኑ በተጨማሪ በኢንዱስትሪው ላይ ከሚገኙ ዋና ባለድርሻ አካላትና ከመንግስት ተወካዮች ጋር የመገናኘት እድል የሚፈጠር ሲሆን፤ የፓናል ውይይትም እንደሚደረግ ተጠቁሟል፡፡

 

10 ታዋቂ የቡና አምራች ኩባንያዎች ይሳተፋሉ
ለኢትዮጵያ የመጀመሪያው ነው የተባለለት የቡና ፌስቲቫል (ኮፊ ፌስት) ዛሬና ነገ እሁድ በሸራተን አዲስ ሆቴል ፋውንቴይኑ አካባቢ እንደሚካሄድ ተገለጸ፡፡ በፌስቲቫሉ ላይ አሥር የሚደርሱ ታዋቂ የቡና አምራችና ላኪ ኩባንያዎች ይሳተፉሉ፡፡
የቡና አምራች ኩባንያዎቹ የተለያዩ ዓይነት የቡና ምርቶቻቸውን የሚያቀርቡ ሲሆን፤ ለኤክስፖርት የተዘጋጁ የቡና ምርቶችን ጨምሮ ለሸያጭ ይቀርባሉ ተብሏል፡፡ የቡና ቀመሳ ሥነስርዓትም ይካሄዳል፡፡
ለሁለት ቀናት የሚካሄደውን የመጀመሪያውን የቡና ፌስቲቫል አስመልክቶ የኹነቱ ጠንሳሾችና አዘጋጆች ከትላንት በስቲያ ሐሙስ በሸራተን አዲስ ሆቴል ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡ ከፌስቲቫሉ ግንባር ቀደም ስፖንሰሮች አንዱ የሖነው የሸራተን አዲስ ዋና ሥራ አስኪያጅ - በመግለጫው ላይ የተገኙ ሲሆን፤ በኢትዮጵያ የመጀመሪያው የቡና ፌስቲቫል በሆቴሉ መዘጋጀቱ ልዩ ደስታና ጉጉት እንደፈጠረባቸው ገልጸዋል፡፡
የኢትዮጵያ ቡና ፌስቲቫል አስፈላጊነትን ያብራሩት አዘጋጆቹ፤የኢትዮጵያን ቡና በሚገባው ልክ ለማክበርና ለማጉላት ነው ብለዋል፡፡ ”እኛ ኮፊ ፌስትን እንደ በዓል ነው የምንቆጥረው፤ቡናችንን የምናከብርበትና የምናጎላበት ታላቅ በዓል ነው፡፡” ሲሉም አስረድተዋል፡፡
እንደ ጀርመን ያሉ አገራት በኦክቶበር ፌስት (ዓመታዊ የቢራ ፌስቲቫል) እንደሚታወቁ የጠቀሱት አዘጋጆቹ፤ ኢትዮጵያም በቡና ፌስቲቫል (ኮፊ ፌስት) መታወቅ አለባት ብለው እንደሚያምኑ ተናግረዋል፡፡

Page 1 of 739