Administrator

Administrator

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ በ2018 በጀት ዓመት ስትራቴጂክ ዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ ላይ እንደገለጹት፣ በተቋማት መካከል ተመሳሳይ መዋቅር፣ በጀትና የሰው ኃይል ተመድቦ ሳለ በአፈጻጸም ሰፊ ልዩነት መታየቱ የሚያስጠይቅ ነው።
በአመራሩ ዘንድ በሚታዩ የሪፖርት ግድፈቶችና የመረጃ አያያዝ ክፍተቶች ላይ ጠንከር ያለ ትችት የሰነዘሩት ከንቲባዋ፣ ትክክለኛ ያልሆነ መረጃ ማቅረብ ከሌብነት ጋር በተመሳሳይ ደረጃ የሚያስጠይቅ እንደሆነ በማስጠንቀቅ ወደፊት የሚቀርቡ ሪፖርቶች በሕዝቡ ሕይወት ላይ ያመጡትን ሁለንተናዊ ለውጥና ጥቅም በግልጽ ማሳየት እንዳለባቸው አሳስበዋል።
በተጨማሪም የኮሪደር ልማትን በማስመልከት የፅዳት ሥራ የእያንዳንዱ ነዋሪ የዕለት ተዕለት ባህል ሊሆን እንደሚገባና ነዋሪው ደጃፉን በባለቤትነት ማጽዳት እንዳለበት አስገንዝበዋል። የኑሮ ውድነትን ለመከላከል፣ የሥራ ዕድል ፈጠራን ለማሳደግና በቤት ልማት ያረጁ የከተማ ክፍሎችን የማደስ ተግባራት ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ የተናገሩት ከንቲባዋ፤ ለመሠረተ ልማቶች ከፍተኛ በጀት መመደቡን ገልጸው፣ ለተመዘገቡት ስኬቶች የሕዝብና የልማት አጋሮች ተሳትፎ ከፍተኛ እንደነበር በመጠቆም፣ በቀጣይም ይህ ትስስር ይበልጥ እንዲጠናከር ጥሪ አቅርበዋል።
የቴሌግራም ቻናልችንን በመቀላቀል የአዲስ አድማስን መረጃ ይከታተሉ…
በዓለም ዙሪያ የሚገኙ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ተመልካቾች የ2026 የፊፋ ዓለም ዋንጫ ፍጻሜ ጨዋታ የዕረፍት ሰዓት ትርኢት በተከታተሉበት ወቅት፣ የኡጋንዳውያኑ "ጌቶ ኪድስ" የዳንስ ቡድን ታሪክ ሰርተዋል።
እነዚህ ወጣት የዳንስ ከዋክብት ከዓለም አቀፏ የፖፕ ንግሥት ሻኪራ እና ከታዋቂው የአፍሮቢትስ ኮከብ በርና ቦይ ጋር በመሆን በዓለም እጅግ ከፍተኛ ቁጥር ያለው የቴሌቪዥን ተመልካች በተከታተለው መድረክ ላይ የሚያስደምምና መንፈስን የሚያነቃቃ የዳንስ ትርኢታቸውን አቅርበዋል።
በኢትዮጵያ ስሜን ተራራዎች ብሔራዊ ፓርክ ብቻ የሚገኘውና የዩኔስኮ የዓለም ቅርስ መለያ የሆነው ብርቅዬው ዋልያ፣ በቅርብ ዓመታት በነበረው ግጭትና የሕግ መላላት ምክንያት ቁጥሩ ከ638 ወደ 306 ዝቅ ብሏል። በዚህም ሳቢያ አካባቢው ለሕገ-ወጥ አደን በመጋለጡ፣ ዓለም አቀፍ የተፈጥሮ ሀብት ጥበቃ ኅብረት (IUCN) ዋልያን «ከፍተኛ የመጥፋት አደጋ የተደቀነበት» ሲል በአደጋ መዝገቡ ውስጥ አካትቶታል። ሆኖም ይህ ምዝገባ ለእንስሳው ዓለም አቀፍ ትኩረት፣ ምርምርና የገንዘብ ድጋፍ ለማሰባሰብ ትልቅ ዕድል የሚፈጥር በመሆኑ እንደ መልካም አጋጣሚ ተወስዷል።
ችግሩን ዘላቂ በሆነ መንገድ ለመፍታት የኢትዮጵያ የዱር እንሰሳት ጥበቃ ባለሥልጣንና የፓርኩ ጽሕፈት ቤት የ10 ዓመት ስትራቴጂ በማዘጋጀት ወደ ሥራ ገብተዋል። በዚሁ መሠረት «የዋልያ አምባሳደሮች» የተሰኙ 12 ባለሙያዎችን በማሰማራት፣ ከኅብረተሰቡ ጋር በመተባበር ሌት ተቀን ቅኝት በማድረግ ሕገ-ወጥ አደንን ሙሉ በሙሉ ማስቆም ተችሏል። ቀደም ሲልም በ1983 ዓ.ም በተደረገ ጥበቃ እንስሳቱን ከአደጋ ቀጠና ማውጣት የተቻለ ሲሆን፣ አሁንም በአንዳንድ አካባቢዎች እስከ 15 የሚደርሱ አዳዲስ ግልገሎች መታየታቸው የዋልያ ቁጥር በፍጥነት እንደሚያገግም ትልቅ ተስፋ ፈጥሯል።
AMECO-
የቴሌግራም ቻናልችንን በመቀላቀል የአዲስ አድማስን መረጃ ይከታተሉ…
በኢትዮጵያ የሙዚቃ አድናቂዎች ዘንድ ከፍተኛ ተወዳጅነትን ያተረፈው ድምጻዊ ጎሳዬ ተስፋዬ በለንደን ያቀረበውን ስኬታማ ኮንሰርት አጠናቆ ወደ አዲስ አበባ ከተመለሰ በኋላ የጤና መታወክ እንዳጋጠመው በይፋዊ የማህበራዊ ትስስር ገጹ ገለጸ።
ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ባልደረባ ጋር የተነሳውን ፎቶግራፍ በማያያዝ «ታምሜ ገባሁ :: ስለሁሉ ግን እግዚአብሔር ይመስገን !!» ሲል ያሰፈረው መልዕክት በበርካታ አድናቂዎቹ ዘንድ ስጋትን የፈጠረ ሲሆን፣ ህመሙ ምን እንደሆነ በዝርዝር ባይታወቅም በርካታ ወዳጆቹ አብሮነታቸውን እየገለጹለት ይገኛሉ።
የቴሌግራም ቻናልችንን በመቀላቀል የአዲስ አድማስን መረጃ ይከታተሉ…
የናይጄሪያ ዓላማ ስማርት ስልኮችን በብዛት መጠቀም ብቻ ሳይሆን፣ እዚያው በሀገሯ መገጣጠምና ማምረት መጀመር ነው። በኢሞ ግዛት የሚገኘውና በ15 ሚሊዮን ዶላር የተገነባው "ዲጂታል ሲቲ" በቀን እስከ 1,000 የሚደርሱ ስማርትፎኖችንና ራውተሮችን የመገጣጠም አቅም ባለው ፋብሪካው ይህንን ራዕይ እውን በማድረግ ላይ ይገኛል።
ፋብሪካው ከማምረት ባለፈ ወጣት ናይጄሪያውያንን በኤአይ፣ በሮቦቲክስ፣ በሳይበር ደህንነት እና በሌሎች የዲጂታል ክህሎቶች በማሰልጠን ላይ ያተኩራል።
ለዓመታት ናይጄሪያ ከውጭ በሚገቡ ስማርት ስልኮች ላይ ጥገኛ በመሆኗ፣ በምንዛሬ ተመን፣ በኢምፖርት ቀረጥና በሎጂስቲክስ ወጪዎች ምክንያት የስልኮች ዋጋ ውድ ሆኖ ቆይቷል። አካባቢያዊ የመገጣጠም ስራዎችን ማስፋፋት የስልኮች ዋጋ ለመቀነስ፣ የክህሎት ስራዎችን ለመፍጠርና የሀገሪቱን ዲጂታል ኢኮኖሚ ለማጠናከር ይረዳል። በተጨማሪም ይህ እንቅስቃሴ የናይጄሪያ የቴክኖሎጂ ማዕከል ከሌጎስ ከተማ ወጥቶ ወደ ሌሎች ግዛቶች እየተስፋፋ መሆኑን ያሳያል።
እንደ ኢሞ ዲጂታል ሲቲ ባሉ ፕሮጀክቶች፣ የተለያዩ የናይጄሪያ ግዛቶች ራሳቸውን የፈጠራ፣ የማኑፋክቸሪንግ እና የታላንት ልማት ማዕከል አድርገው ማዘጋጀት ጀምረዋል። አሁን ያለው ዋናው ፈተና ግን ይህንን ስራ ማስፋፋት እና ማሳደግ ነው።
የቴሌግራም ቻናልችንን በመቀላቀል የአዲስ አድማስን መረጃ ይከታተሉ…
"አፍሪካ በዓለም ላይ ሀብታሟ አህጉር ሆና ሳለ፣ እንዴት ወርቃችን በነጮች ይቆፈራል?
እንዴትስ አፍሪካ የአልማዝ መገኛ ሆና—ከደቡብ አፍሪካ፣ ቦትስዋና፣ ናሚቢያ፣ ሴራሊዮንና ላይቤሪያ አልማዝ እየወጣ—ዋጋውን ግን በቤልጂየም የሚገኙ ሰዎች ይወስኑታል?
ቶጎ፣ ኮትዲቯር እና ጋና ኮኮዋ ያመርታሉ፤ ነገር ግን ቸኮሌት የሚሰሩት አንድም የኮኮዋ ዛፍ የሌላቸው ስዊዘርላንድና ቤልጂየም ናቸው። ይህ እንዴት ሊሆን ይችላል?
ሻይ ቅጠል በኢትዮጵያ፣ በኬንያና በኡጋንዳ ተመርቶ ወደ እንግሊዝ ሲሄድ "የእንግሊዝ ሻይ" ይባላል። ይህ እንዴት ይሆናል?
ለስልክ መስሪያ የሚያገለግለው ኮልታን የተባለው ማዕድን ከኮንጎ እየወጣ፣ አንድም የአፍሪካ ሀገር ግን ሞባይል ስልክ አያመርትም።
ይህ ሁሉ ሊሆን የቻለው አእምሮአችን እንዲማረክ በመፍቀዳችንና ማንነታችንን በመዘንጋታችን ብቻ ነው።"
(PLO Lumumba)
የቴሌግራም ቻናልችንን በመቀላቀል የአዲስ አድማስን መረጃ ይከታተሉ…

በሳዑዲ ዓረቢያ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ይገኙ የነበሩ ከ1 ሺህ 400 በላይ ኢትዮጵያውያን በሳምንቱ ውስጥ በተደረጉ 6 ዙር በረራዎች ወደ ሀገራቸው በሰላም ተመልሰዋል። እንደ ሴቶች እና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ከተመላሾቹ መካከል 879 ወንዶች፣ 554 ሴቶች፣ 48 ጨቅላ ሕፃናት እና 82 ዕድሜያቸው ከ18 ዓመት በታች የሆኑ ታዳጊዎች ይገኙበታል። መስከረም 5/2018 ዓ.ም በተጀመረው በዚህ ዜጎችን የማመለስ አገራዊ ዘመቻ እስካሁን ከ87 ሺህ በላይ ኢትዮጵያውያንን ወደ እናት ሀገራቸው መመለስ ተችሏል።

ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከሚመለከታቸው ባለድርሻና አጋር አካላት ጋር በመተባበር ለተመላሽ ዜጎች በአየር ማረፊያና በማቆያ ማዕከላት አስፈላጊውን እንክብካቤና ድጋፍ በማድረግ ላይ ይገኛል። ከዚህም በተጨማሪ ተመላሾችን ከቤተሰቦቻቸው ጋር የማቀላቀል፣ የመልሶ ማቋቋም እና በስነ-ልቦና የታገዘ ድጋፍ የማድረግ ተግባራት በትኩረት እየተከናወኑ እንደሆነ ተገልጻል።

ወደፊትም መደበኛ ያልሆነ ፍልሰትና ሕገ-ወጥ የሰዎች ዝውውር የሚያስከትለውን አስከፊ አደጋ ለኅብረተሰቡ የማስገንዘብ ሥራዎች ተጠናክረው ይቀጥላሉ። መንግሥት ሕገ-ወጥ ጉዞዎችን ለመከላከልና ደኅንነቱ የተጠበቀ ሕጋዊ ፍልሰትን ለማበረታታት የጀመራቸውን አሰራሮች አጠናክሮ እንደሚቀጥልም ሚኒስቴሩ አረጋግጧል።

ትውልደ ኢትዮጵያዊው የካናዳ ብሔራዊ ቡድን እና የእንግሊዙ ኖርዊች ሲቲ ክለብ ተጫዋች ዓሊ አህመድ በኢትዮጵያ ይፋዊ ጉብኝት ለማድረግ አዲስ አበባ ገብቷል። ቦሌ ዓለም አቀፍ አየር መንገድ ሲደርስም የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ባሕሩ ጥላሁን፣ የባሕል እና ስፖርት ሚኒስቴር ተወካዮች እንዲሁም የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የፕሮቶኮል ዲፓርትመንት ኃላፊዎች አቀባበል አድርገውለታል።

የተጫዋቹ ወደ ሀገር ቤት መምጣት በካናዳ የኢትዮጵያ ኤምባሲ የቀረበለትን ጥያቄ ተቀብሎ የተደረገ ሲሆን፣ ዓላማውም በሀገሪቱ የስፖርት ልማት ላይ አዎንታዊ አሻራ ለማሳረፍና ወጣቶችን ለማበረታታት ነው። የውጭ ጉዳይ፣ የባህልና ስፖርት፣ የቱሪዝም ሚኒስቴሮች እና የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በጋራ በመሆን በኢትዮጵያ የሚያደርገው ቆይታ የተሳካ እንዲሆን እየሰሩ ይገኛሉ።

ዓሊ አህመድ ለካናዳ ብሔራዊ ቡድን 28 ጨዋታዎችን ያደረገ ሲሆን፣ በ2026ቱ የፊፋ ዓለም ዋንጫም በአራት ጨዋታዎች ላይ በመሰለፍ ታሪካዊ ጉዞ አድርጓል። በሜጀር ሊግ ሶከር ባሳየው የላቀ ብቃት በጥር 2026 ወደ እንግሊዙ ኖርዊች ሲቲ ያመራው ዓሊ፣ የደረሰበት የስኬት ደረጃ ለበርካታ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ወጣቶች ትልቅ ተነሳሽነት የሚፈጥር ነው።

አንድ ንጉሥ አንድ ብልህ አጫዋች ነበራቸው። በየጊዜው ከሚመክራቸው ምክር መካከል ሰሞኑን የነገራቸውን ለመቀበል ከብዷቸዋል። ሰሞኑን የመከራቸው “ከወዳጆችዎ ይልቅ፣ ስለርስዎ ድክመት ዕውነቱን የሚነግሩዎ ጠላቶችዎ ናቸውና አዳምጧቸው” የሚል ነበር። ንጉሡ አላመኑበትም። ስለዚህ ለማረጋገጥ መዘዋወር ጀመሩ።
ንጉሡ በጣም የሚፈሩና አይበገሬ ነኝ የሚሉ ናቸው። በሄዱበት ቦታ ሁሉ የሚያገኟቸውን መኳንንቶች “እስቲ ስለ እኔ ጉድለት ንገሩኝ?” ይሉና ይጠይቃሉ።
“ንጉሥ ሆይ! እርስዎ ላይ እንዴት አይነት ሰው ነው ጉድለት ሊያገኝ የሚችለው። ደግሞ እርስዎ ምን ይወጣልዎታል!” ይሏቸዋል።
ቀጥለው ወደ ሠራዊታቸው ይሄዱና፤
“ምን እንከን አለብኝ? እስቲ ስለራሴ ንገሩኝ?” ይላሉ።
ከሠራዊታቸው ታማኙ ባለሟል ብድግ ብሎ፣
“ንጉሥ ሆይ! እርስዎ ከቁመናዎ ጀምሮ፣ ለጀግንነትዎ፣ ለዕውቀትዎ፣ ለዓለም ተደማጭነትዎ ምን የሚቀነስ የሚወጣልዎ ነገር አለብዎ!” ይላቸዋል። እንዲህ ከርመው አንድ ቀን በአጋጣሚ ከጠላቶቻቸው ጋር በሚሲዮን ይቀመጣሉ። አጠገባቸው የተቀመጠው ቀንደኛው ባላንጣቸው ቀስ ብሎ፤
“ስሙ ንጉሥ፤ ሲናገሩ አፍዎት መጥፎ ጠረን ያመጣል” ይላቸዋል።
ንጉሱ ይናደዳሉ። “እንዴት እስከዛሬ አንድ ወዳጄ ይሄን አልነገረኝም? እንዲህ በአደባባይ እንድጋለጥ ያደረጉኝ ወዳጆቼ ናቸው! ቆይ ግድ የለም! ባልሰራላቸው!” ይላሉ በሆዳቸው። ስብሰባውን እንደጨረሱ ሲገሰግሱ ወደ ቤተ-መንግስታቸው ይሄዱና ንግስቲቱን አስጠርተው፤
“አፌ ጠረን እንዳለው እስከዛሬ ያልነገርሽኝ ለምንድን ነው?” ሲሉ በቁጣ ጠየቁ። ንግስቲቱም፤ በንፁህ ልቦናና በቀናነት፤
“ንጉሥ ሆይ! የሁሉም ንጉስ አፍ እንደ እርስዎ አፍ አይነት ሽታ ያለው መስሎኝ ነው” ሲሉ መለሱ።
ንጉሡም እጅግ የቅርባቸው የሆነችው የገዛ ባለቤታቸው ጉድለታቸውን ሳትነግራቸው፤ ሩቅ የሚኖሩት ጠላቶቻቸው ማወቃቸውን ልብ ሲሉ፤ ያ አስተዋይ አጫዋቻቸው የነገራቸው ቁም ነገር እውነት መሆኑን ተገነዘቡ።
***
ማንኛውም መሪ፣ በማንኛውም ደረጃ ያለ ቢሆን፤ አንድ ሀቅ ልብ ማለት አለበት። ራሱን ብቻ የሚያዳምጥ መሪ፤ ከወዳጆቹ የሚጠብቀው ምንጊዜም ምስጋናን ስለሆነ ጉድለቶቹን የማየትም የመስማትም እድል አያገኝም። ወገኖቹም አይደፍሩትም። እሱም ራሱን አይደፍርም። ይህ ሁሉ የሚሆነው ሁሌ በሰላም ጊዜ በሆነ ባልከፋ። ሁኔታዎች በውጥረትና በችግር በሚሞሉበት ሰዓት ሲመጣ ነው አደጋው። ምክንያቱም የሁኔታዎች መወሳሰብን ተከትለው ሰዎችም ይለወጣሉና ነው። ችግሩ ግን በዚህ ብቻ አያቆምም። መሪውን መስለውና አክለው ማደግ ሲመኙ የቆዩ ባለሟሎቹና ተከታዮቹ አለማዳመጥ ሰናይ ስነምግባር እየመሰላቸው እነሱም እኩዮቻቸው የሚሉትን አልሰማ ይላሉ። በዚህ ምክንያት ካለመደማመጥ አልፎ፣ የሚፈጠረውን ጩኸት ለመገደብ ካለመቻል ደረጃ ይደረሳል። በየመንበራቸው እንደተቀመጡ በየራሳቸው ደሴት ውስጥ ይዋጣሉ። ውለው አድረውም የታችኞቹ በላይኞቹ ላይ ቅያሜን ያጠነክራሉ። ቀስ በቀስ በተለይ የመረረ የመከፋት ስሜት ውስጥ በገቡ ጊዜ፤ እንደ ሮማው ካሽየስ፣ ባለቃው ላይ ማሴርን፣ ራስን እንደማዳን ሲቆጥሩ፤ ከላይ ወደ ታች ይወርዱ የነበሩ ትእዛዛት ወደ ጎንም፣ ወደ ይም እንዲያመሩ ሲፈለግ፣ ለወትሮው የአለቃውን ድክመት ሁሉ የእኔ ነው እያለ አሜን ይል የነበረው ሁሉ፣ ድርሻ ድርሻችንን እንውሰድ በሚል፤ ሌላውን ማነሳሳትና ብሶቱን ሌላው ላይ ማጋበቱን ይያያዘዋል። ይሄኔ እንደ ሮማው ብሩተስ ያለው በትዕግስት የሚያገኘውን ስልጣን ቄሳርን በማስወገድ ሊፈጽመው እንዲሻ ሲተነኮስ፣ ወይም ሲወነባበድ፣ ነገር የተገላቢጦሽ ይሆናል። ቄሳር በመሞቻው “አንተም ብሩተስ?” ያለበት ሰዓት የሚመጣ እንግዲህ ያኔ ነው።በተለይ ስልጣንን በዲሞክራሲያዊ መንገድ የመጋራት ልምድ በሌለበት እንደ እኛ ባለው አገር ብርቱ ጥንቃቄ የሚጠይቀው፣ በወንበሩ ዙሪያ አስፈላጊ ትዕግስትና መቻቻል አለመኖር ነው። መተማመን እንዲኖር ሀሳብን መግለጽ ያስፈልጋል። ለዚህ ደግሞ ነጻነቱ አስፈላጊ ነው። ሀሳብን የመግለጽ ነጻነት በሀቅና ከልብ ካልታመነበት፤ “ለብ ለብ ዲሞክራሲ” “ገባ ያለው ዲሞክራሲ” እና “ስፔሻል ዲሞክራሲ” እያልን እንድንከፋፍል ልንገደድ ነው። “አካሄዱ ፍጻሜውን ያሳያል” እንዳንል፤ አባይን ጭብጦዬን ከቀማኝ ወዲህ አላምነውም፤ የሚሉ ወገኖች ይሟገቱናል። የለም “ግቡ አካሄድን ያሳያል” - የትም ፍጪው ዱቄቱን አምጭው ነው ነገሩ- ለሚሉት ደግሞ ካልታዘልኩ አላምንም፣ ስንቱ ሥልጣን ላይ ከወጣ በኋላ አይደል ወይ መላው የጠፋው የሚሉ ይኖራሉ። ሁኔታዎችን አጣጥመን መጓዝ የሚያስፈልገን ለዚህ ነው። የሚያግባባንን መንገድ ከንፍቀ-ክበባችን ውጭም ቢሆን ማዳመጥ፣ ከባላንጣዎቻችንም ቢሆን መማር፣ ሁሌ ከመተላለፍ አንዳንዴ “ምን ይሆን?” ብሎ ለሌሎች ሀሳብ ትንሽ እድሜ መለገስ፤ ቀስ በቀስ ግትርነታችንን ሊያረግበው ይችላል።
አለንልህ ያልነውንና በእርሱም ትከሻ ለስልጣን የበቃንለትን፣ ከቀን በኋላ ከእርሱ እጅ የማንወጣውን ህዝብ ማዳመጥ እንደሚኖርብን እንድናስብም ፋታ ይኖረናል።
ስለሌላው ውሸት እንጂ እውነት በተናገርን ቁጥር፣ ስለሌላው ድክመት እንጂ አንድ አንኳር ጥንካሬ እንኳን ባነሳን ቁጥር፣ እኛ ብቻ ሀቀኛ፣ እኛ ብቻ ጠንካራ እያልን እንገበዛለን። ይህ ደግሞ ስለራሳችን እውነተኛ ገጽታ እናዳናውቅ ያደርገናል። የእኛኑ ቅኝት የሚያዳምጡ ወገኖቻችንና ደጋፊዎቻችን እውነተኛ ይዘትና ቅርጻችንን አይነግሩንም።
ስለዚህ ከእኛ ውጭ የማዳመጥ ባህል ማዳበር ደግ ነገር ነው- ከ”ጥላትም” ሰፈር ቢሆን። አበው “ክፋትህና ውሸትህ ሲጠፋብህ፤ ጠላትህን አስታውሰኝ በለው” የሚሉት ይሄንኑ ሊያስገነዝቡን ነው፡፡

የኢትዮጵያ ሕዝባዊ አብዮታዊ ፓርቲ (ኢሕአፓ) የቀድሞ ሊቀመንበር ፕሮፌሰር ዝናቡ አበራ ከማንኛውም የፓርቲ ፖለቲካ እራሳቸውን በይፋ ማግለላቸውን አስታውቀዋል። ፕሮፌሰሩ ውሳኔያቸውን በይፋ በላኩት ልዩ ደብዳቤ የገለጹ ሲሆን፥ ይህ ከፖለቲካ የመውጣት ውሳኔያቸውም ከሐምሌ 10 ቀን 2018 ዓ.ም. ጀምሮ የጸና እንደሚሆን አረጋግጠዋል።

ላለፉት በርካታ ዓመታት በሀገሪቱ ሰላማዊ የፖለቲካ ትግል ውስጥ በንቃት ሲሳተፉ የቆዩት ፕሮፌሰር ዝናቡ፥ ይህንን ውሳኔ ለማሳለፍ የተገደዱት በአሁኑ ወቅት የፖለቲካ ትግሉ «ውጤት አልባ» ሆኖ ስላገኙት መሆኑን ገልጸዋል።

የቴሌግራም ቻናልችንን በመቀላቀል የአዲስ አድማስን መረጃ ይከታተሉ…
https://t.me/AdissAdmas

Page 6 of 817