Administrator

Administrator

ኦነግ ዛሬ ባወጣው መግለጫ የመንግሥትን የባሕር በር የማግኘት ጥረት በቅንነት እንደሚደግፍ አስታውቋል። የኢትዮጵያ ህዝብ ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረና ኢኮኖሚዋም እያደገ መሄዱን የገለጠው ኦነግ፣ ለዚህ ደሞ የባሕር በር ማግኘት አማራጭ የለውም ብሏል።
ሁሉም የኦሮሞ የፖለቲካ ኃይሎች የሀሳብ ልዩነታቸውን ወደ ጎን በመተው ለኦሮሞ ሕዝብ ጥቅምና ደኅንነት በጋር የሚሠሩበት ጊዜው አሁን ነው ሲል ኦነግ ጥሪ አቅርቧል።
በሌላ በኩል በሰሜን ኢትዮጵያ የሚደረጉ ጦርነቶች የኦሮሚያን ሀብት ለመበዝበዝ ያለሙ ናቸው ያለው ድርጅቱ፤ "በዚያ አካባቢ የሚደረጉ ወታደራዊ ጥምረቶች ኦሮሞንና ኦሮሞነትን ለማጥፋት ያለሙ ናቸው" ሲል አቋሙን ገልጿል።
የቴሌግራም ቻናልችንን በመቀላቀል የአዲስ አድማስን መረጃ ይከታተሉ…
ሶማሊላንድ ኢትዮጵያ የቀይ ባሕር ዳርቻዎችን እና የበርበራ ወደብን እንድትጠቀም ሁኔታዎችን ለማመቻቸት አሁንም ዝግጁ መሆኗን ገለጸች። የሶማሊላንድ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር አብዲራህማን ዳሂር ባካል እንደተናገሩት፣ ኢትዮጵያ ልትጠቀምበት የምትችል ረጅም የባሕር ዳርቻ አለን፤ በተጨማሪም የበርበራ ወደብ ከ30 እስከ 40 በመቶ የሚደርሰው አቅሙ እስካሁን ጥቅም ላይ አልዋለም ብለዋል።
ሚንስትሩ አክለውም ኢትዮጵያ ሉዓላዊነቷን ከሚጥስ ማንኛውም ኃይል ራሷን የመከላከል መብት እንዳላት ገልጸዋል። አያይዘውም በኢትዮጵያ እና በኤርትራ መካከል ያለው ውዝግብ በንግግር እንዲፈታ ጥሪ ማድረጋቸውን ስካይ ኒውስ ዓረቢያ ዘግቧል።
የቴሌግራም ቻናልችንን በመቀላቀል የአዲስ አድማስን መረጃ ይከታተሉ…
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከእስራኤሉ አቻቸው ከጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ጋር በሁለትዮሽ ግንኙነት እና በቀጣናዊ ጉዳዮች ዙሪያ በስልክ ውይይት አድርገዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በማህበራዊ ሚዲያ ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት፣ ውይይታቸው ፍሬያማና ገንቢ መሆኑን ገልጸው፤ ሁለቱ መሪዎች በኢትዮጵያና በእስራኤል ግንኙነት እንዲሁም በዋና ዋና ቀጣናዊ ሁነቶች ላይ መክረዋል።
በውይይታቸውም ሁለቱ ሀገራት በጋራ ጉዳዮች ላይ ያላቸውን የትብብር ቁርጠኝነት በድጋሚ ማረጋገጣቸውን ጠቅላይ ሚኒስትሩ አብራርተዋል።
የቴሌግራም ቻናልችንን በመቀላቀል የአዲስ አድማስን መረጃ ይከታተሉ…
የኢትዮጵያ ከ17 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን የሴካፋ ማጣሪያ ጨዋታውን ከቡሩንዲ ጋር አድርጎ 3 ለ 0 በሆነ ውጤት አሸንፏል፡፡
በኪጋሊ ፔሌ ስታዲየም በተደረገው በዚህ ጨዋታ የኢትዮጵያን የማሸነፊያ ግቦች ዘሚካኤል ምንያህል፣ አክረም አብዱሰላም እና አብዲሳ ጉተማ ከመረብ አሳርፈዋል፡፡
በሴካፋ ከ17 ዓመት በታች አፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ውድድር ላይ ተሳታፊ የሆነው የኢትዮጵያ ከ17 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን ዛሬ ያደረገው ጨዋታ የምድቡ የመጀመርያው መርኃ ግብር ነው፡፡
በአሰልጣኝ ቤንጃሚን ዚመር የሚመራው የኢትዮጵያ ከ17 ዓመት በታች በሔራዊ ቡድን ከሁለት ቀናት በኋላ ከዩጋንዳ አቻው ጋር ሁለተኛ የምድብ ጨዋታውን ያከናውናል።
ጄነራል ታደሰ ወረደ እና ሌሎች የቀድሞ የሕወሃት መኮንኖች ከእስር መለቀቃቸውን ምንጮች አስታወቁ። በአሁኑ ጊዜ መኮንኖቹ በሀገር መከላከያ ሰራዊት እጅ የሚገኙ ሲሆን፣ በደህና ሁኔታ ላይ መሆናቸውም ታውቋል።
እነዚህ መኮንኖች በህወሓት ከታሰሩበት ከመቀሌ ወደ ሰሜን ድንበር ተወስደው እንደነበር ይታወሳል። ይህም ለኤርትራ መንግሥት ይሰጣሉ የሚል ትልቅ ስጋት ፈጥሮ እንደነበር አይዘነጋም።
ጄነራል ታደሰ ወረደ በፌዴራሉ መንግሥት የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዚዳንት ሆነው ዳግም መመረጣቸውን ተከትሎ፣ የህወሃት አመራሮች በሃይል ከሥልጣናቸው በማውረድ ለአጭር ጊዜም ቢሆን የራሳቸውን አስተዳደር መሥርተው እንደነበር ይታወቃል፡፡
የቴሌግራም ቻናልችንን በመቀላቀል የአዲስ አድማስን መረጃ ይከታተሉ…
ታዋቂዋ ድምፃዊት ቬሮኒካ አዳነ «ቢሮኒካ» በተሰኘው ዘፈኗ በአፍሪካው የዚኮሞ አዋርድስ (Zikomo Awards) በ5 ዘርፎች እጩ ሆና መመረጧን ገለጸች። ባለፈው ዓመትም በ4 ዘርፎች ታጭታ የ2 ዘርፎች አሸናፊ በመሆን ሀገሯን ኢትዮጵያን ማስጠራቷ ይታወሳል።
ድምፃዊቷ አሁን ድምፅ መስጠት ስለተጀመረ አድናቂዎቿ ድጋፋቸውን እንዲሰጧት ጠይቃለች። ወደ ታንዛኒያ በመሄድ አምስቱንም ሽልማቶች ይዛ ለመመለስ ትልቅ ተስፋ እንዳላት ጠቁማ፣ ለመላው አድናቂዎቿና ቤተሰቦቿ ያላትን ፍቅር ገልጻለች።
የቴሌግራም ቻናልችንን በመቀላቀል የአዲስ አድማስን መረጃ ይከታተሉ…
FACE OF ETHIOPIA
National Cultural Ambassador Program ????????
ኢትዮጵያ የምትገለጸው በታሪኳ፣ በባህሏ፣ በብዝሃነቷ እና በሕዝቦቿ ውበት ነው።
ይህንን ውበት በእውቀት፣ በማንነት፣ በባህል እና በስራ ለዓለም የምታስተዋውቅ የብሔራዊ ባህል አምባሳደር ለመሆን የምትወዳደረው ሩት ቴዎድሮስ ናት።
ሩት የውበት ተወዳዳሪ ብቻ አይደለችም።
???? የCivil & Environmental Engineering ባለሙያ
???? በManagement የተማረች
???? በProject Management የማስተርስ ዲግሪ ያገኘች
???? የPhD ትምህርቷን በመከታተል ላይ የምትገኝ
????️ ሲቪል ኢንጂነሪንግ ዘርፍ ላይ እየሰራች የምትገኝ
???? ለአካባቢና ለአረንጓዴ ልማት ልዩ አስተዋፅኦ የማድረግ ፍላጎት ያላት
???? በሰብአዊ አገልግሎት የምትሳተፍ
እናም ዛሬ እኛ የምንሰጠው ድምፅ ለአንዲት ተወዳዳሪ ብቻ ሳይሆን
ለኢትዮጵያ ውበት ነው።
ለባህላችን ነው።
ለማንነታችን ነው።
ለአዲሱ ትውልድ ነው።
???????? ከታች ያለውን ሊንክ በመጠቀም ሩት ቴዎድሮስን እንምረጥ!
❤️ ድምፅ እንስጥ።
???? መልዕክቱን እናጋራ።
???? ቤተሰብና ጓደኞቻችንን እናሳትፍ።
???? ሩት ቴዎድሮስ — የኢትዮጵያ የባህል አምባሳደር ለመሆን የእኛ ምርጫ!

* 20ሺ እስረኞችን ነጻ አውጥቷል

«አብዛኞቹ እዚያ የታሰሩት ወንጀል ሠርተው አይደለም» የሚለው የዱባዩ ነጋዴ ፊሮዝ መርቻንት፤ «የታሰሩት ሊከፍሉት ያልቻሉት ዕዳ ስላለባቸው ብቻ ነው» ሲል ያስረዳል፡፡

ፊሮዝ መርቻንት እነዚህን ዕዳዎች እየከፈለ ሰዎችን ከእስር ነጻ ያወጣል፡፡ ነጋዴው ይህንን በጎ ተግባር ላለፉት 18 ዓመታት በኤምሬቶች ውስጥ እያከናወነ የቆየ ሲሆን፣ እስከ ባለፈው የካቲት ወር ድረስ ከ20,000 በላይ ሰዎችን ከእስር ታድጓል።

በአንድ ዓመት ውስጥ ብቻ ከ50 በላይ አገራት የመጡ 2,972 ሰዎችን ዕዳ ከፍሎ ከእስር ያስፈታ ሲሆን፤ በዚህ ዓመት የካቲት መጨረሻ ደግሞ ተጨማሪ 497 ሰዎች በነፃነት ወደ ቤታቸው እንዲመለሱ አድርጓል።

ፊሮዝ መርቻንት ስለነዚህ ሰዎች ሲናገር፡ «እነዚህ ሰዎች ጨካኝ ወንጀለኞች አይደሉም፤ አብዛኞቹ የሁኔታዎች ሰለባ የሆኑ ምስኪኖች ናቸው» ይላል።

በዚያ አንድ ዓመት ውስጥ ብቻ የከፈለው ዕዳ 2.4 ሚሊዮን ዲርሃም (653,506 ዶላር ገደማ) ይደርሳል። በተጨማሪም ለ11 ታካሚዎች የኩላሊት እጥበትና የሕክምና ወጪ የሚሆን 1 ሚሊዮን ዲርሃም አውጥቷል።

የእርሱ መልካምነት ከእስር ቤት በማስወጣት ብቻ ግን አያበቃም፡፡ ከእስር የተፈቱት ሰዎች ወደ አገራቸው የሚመለሱበት የቪዛና የአየር መንገድ ትኬት ወጪም ይሸፈንላቸዋል።

ነጋዴው ይህን በጎ ተግባሩን የሚከውነው በጁሜራ ሌክስ ታወርስ ሕንፃ 39ኛ ፎቅ ላይ በሚገኘው ቢሮው ውስጥ ሆኖ ነው።

«አንድ ሰው ዕዳው ተከፍሎለት ወደ ቤተሰቡና ወደ አገሩ ከተመለሰ፣ ለእኔ ያ ትልቅ ነገር ነው» ይላል ፊሮዝ።

ለካስ ደግነትም መሰጠትን ይጠይቃል፡፡

የቴሌግራም ቻናልችንን በመቀላቀል የአዲስ አድማስን መረጃ ይከታተሉ…
https://t.me/AdissAdmas

የዓለም የጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ቴዎድሮስ አድሃኖም ዓለም አቀፉን የሴት ልጆች ቀን በማስመልከት በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት፣ የዓለም ማህበረሰብ ለሴት ልጆች ጤና፣ ደህንነትና መብት መከበር ቁርጠኝነቱን እንዲያድስ ጥሪ አቀረቡ።

ዶክተር ቴዎድሮስ ባስተላለፉት መልዕክት፡

“እንደ አባትና እንደ አያት፣ ለገዛ ሴት ልጆቼ እና የልጅ ልጆቼ የምመኘውን መልካም ነገር ሁሉ ለእያንዳንዷ ሴት ልጅ እመኛለሁ፤ ይኸውም በጤና፣ በደህንነትና ህልሞቻቸውን በነጻነት የመከተል መብታቸው ተከብሮ እንዲያድጉ ነው።

ነገር ግን የብዙ ሚሊዮን ሴት ልጆች እውነታ ከዚህ እጅግ የተለየ ነው።

በየዓመቱ ዝቅተኛና መካከለኛ ገቢ ባላቸው ሀገራት ውስጥ የሚገኙ ወደ 21 ሚሊዮን የሚጠጉ ታዳጊ ሴት ልጆች ለእርግዝና ይጋለጣሉ። የፍቅር አጋር ካላቸው አራት ሴት ልጆች መካከል አንዷ የአካል ወይም የፆታዊ ጥቃት ይደርስባታል። በተጨማሪም በርካታ ሴት ልጆች በኋለኛ ዕድሜአቸው ከማህፀን በር ካንሰር ሊጠብቃቸው የሚችለውን ክትባት አሁንም አያገኙም።

እነዚህ ቁጥሮች ብቻ አይደሉም። ከእያንዳንዱ ቁጥር ጀርባ ጤናዋ፣ ምርጫዋና የወደፊት ዕጣ ፈንታዋ አደጋ ላይ የወደቀ ሴት ልጅ አለች።

የሴቶች ልጆች ቀንን ስናከብር፣ እያንዳንዷ ሴት ልጅ ጤናማ ህይወት እንድትኖርና አቅሟን ሙሉ በሙሉ እንድታወጣ እድል ለመስጠት ቃል እንግባ። ምንም አይነት ልዩነት ሳይደረግ!”

የኤርትራ ወታደሮች ከዚህ ቀደም በምስራቃዊና ምዕራባዊ የትግራይ ዞኖች ይዘዋቸው ከነበሩት የኢትዮጵያ ግዛቶች እየለቀቁ መሆናቸውን የዓይን እማኞች ለዶይቼ ቬለ ተናገሩ። የኤርትራ ወታደሮች ዛግር፣ ሽመልባ እና ዓዲሃገራይን ጨምሮ ከተለያዩ አካባቢዎች የወጡት፣ የመከላከያ ሠራዊቱና የትግራይ የሰላም ኃይል አካባቢዎቹን በመቆጣጠራቸውና በተፈጸሙ ጠንካራ የድሮን ጥቃቶች መሆኑ ተገልጿል። ሆኖም አሁንም በጓል ባድመና ሸራሮ አካባቢዎች መኖራቸው ተሰምቷል።
በሌላ በኩል በዓዲግራት አቅራቢያ ፋጺ ተሰባስበው የነበሩት የኤርትራ ወታደሮች ትላንት ማምሻውን ከአካባቢው ለቀው መውጣታቸው ታውቋል። ባለፉት ሦስት ቀናት ከፋጺ እስከ ዛላምበሳ ባለው መስመር በሰፈሩ የኤርትራ ወታደሮች ላይ ከፍተኛ የድሮን ድብደባ የተፈጸመ ሲሆን፤ በተለይ በዛላምበሳ መሣሪያ የጫኑ መኪኖች በመመታታቸው ከባድ ፍንዳታዎች ሲሰሙ እንደነበር ተነግሯል።
የቴሌግራም ቻናልችንን በመቀላቀል የአዲስ አድማስን መረጃ ይከታተሉ…
Page 12 of 845