Administrator

Administrator

Saturday, 22 August 2026 11:18

የዕድሜ ደመራ”

በአንጋፋዋ ደራሲና ጋዜጠኛ ውድአላት ገዳሙ ተሻለ የተሰናዳው መጽሐፍ ለንባብ በቃ :: መጽሐፉ ካለፉት 21 ዓመታት (ከ1997 እስከ 2018 ዓ.ም.) በላይ የተሰበሰቡ ትውስታዎችንና የሕይወት ጉዞዎችን የያዘ ማራኪ የሕይወት ታሪክ (Memoir) መጽሐፍ ነው።

ይህ መጽሐፍ ደራሲዋ ያሳለፏቸውን የልጅነት ትዝታዎች፣ ማኅበራዊ ገጠመኞችና የዘመን ውጣ ውረዶችን በጥልቀት የሚተርክ ሲሆን፣ አንባቢዎች የራሳቸውን ያለፈ ታሪክና ልጅነት መልሰው እንዲያስታውሱና እንዲያገኙ የሚያስችል ልዩ የማንጸባረቅ አቅም አለው።

ደራሲት ውድአላት ገዳሙ ተሻለ በኢትዮጵያ የማኅበራዊና ባህላዊ ሕይወት ውስጥ ጉልህ አሻራ ያረፉ ታዋቂ ግለሰብ ናቸው። ሀገራቸውን በመምህርነት፣ በጋዜጠኝነት እንዲሁም በፌዴራል ተቋማት ከፍተኛ አመራርነት ከ40 ዓመታት በላይ በቅንነት ያገለገሉ ሲሆን፣ ለሕፃናትና ለአዋቂዎች የሚሆኑ ከ14 በላይ ጠቃሚ መጻሕፍትን ለንባብ በማብቃት በሥነ-ጽሑፉ ዘርፍ ትልቅ አስተዋጽኦ አበርክተዋል።

የ“የዕድሜ ደመራ”*መጽሐፍ ዋና ዋና መረጃዎች

ደራሲ፡ ውድአላት ገዳሙ ተሻለ (አንጋፋ ጋዜጠኛ፣ መምህር )

ዘውግ፡ የሕይወት ታሪክ እና ትውስታ (Memoir)

የተጻፈበት ጊዜ፡ ከ1997 እስከ 2018 ዓ.ም. (ለ21 ዓመታት የተሰበሰበ)

የሕይወት ጉዞና ትዝታ፡ የደራሲዋን የልጅነት ጊዜ፣ ያደጉበትን ማኅበረሰብ ባህልና የአኗኗር ዘይቤ በግልጽ ያሳያል።

ታሪካዊና ማኅበራዊ ክስተቶች፡ ባለፉት 21 ዓመታት በሀገሪቱ የነበሩትን ማኅበራዊ፣ ባህላዊና ይፋዊ ለውጦች በዓይን እማኝነት ይተርካል።

የማንጸባረቅ አቅም፡ አንባቢዎች ታሪኩን በሚያነቡበት ጊዜ የራሳቸውን ያለፈ ሕይወት፣ ስኬትና ፈተናዎች መለስ ብለው እንዲያስተውሉ ያደርጋል።

ኢትዮጵያ በአጠቃላይ 180 ሺህ ኪሎ ሜትር የመንገድ ሽፋን በመያዝ በአፍሪካ 3ኛ እና በዓለም 30ኛ ደረጃ ላይ መቀመጧን የግሎባል ፋየር ፓወር የ2026 መረጃ አመልክቷል። በዚህም ኬንያን በ18,548 ኪሎ ሜትር ብልጫ በመውሰድ ትልቅ አህጉራዊ ስኬት አስመዝግበች። በሰፊው የመንገድ መሠረተ ልማት ዝርጋታቸው ከቀዳሚዎቹ አሥር አፍሪካውያን ሀገራት መካከል ደቡብ አፍሪካ 750 ሺህ ኪ.ሜ. ይዛ 1ኛ ሲትሆን፣ ናይጄሪያ (195 ሺህ ኪ.ሜ.) 2ኛ፣ እና ኢትዮጵያ (180 ሺህ ኪ.ሜ.) 3ኛ ደረጃን ይዘዋል።
ቀጥሎ ያሉት ሰባቱ ሀገራት ዝርዝር ሲታይ ኬንያ (161,452 ኪ.ሜ.) 4ኛ፣ አልጄሪያ (145,203 ኪ.ሜ.) 5ኛ፣ ሱዳን (139,107 ኪ.ሜ.) 6ኛ፣ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ (129,418 ኪ.ሜ.) 7ኛ፣ አንጎላ (76,000 ኪ.ሜ. አካባቢ) 8ኛ፣ ዛምቢያ እና ታንዛኒያ በቅደም ተከተል የአህጉሪቱን ቀዳሚ የመንገድ መሠረተ ልማት ባለቤቶች ሆነው ተቀምጠዋል።
የቴሌግራም ቻናልችንን በመቀላቀል የአዲስ አድማስን መረጃ ይከታተሉ…
በአማራ ክልል የገጠር አካባቢዎች ከብት ከሀብት በላይ የሕይወት ምሰሶ እና የማንነት መገለጫ ነው። ይህንን ውድ ሀብት ለማቆየት ከሚከፈሉት መስዋዕትነቶች ሁሉ ግንባር ቀደሙ "ቅራት" የተባለው ጥልቅ ባሕላዊ እሴት ነው። ፀሐይ ስትጠልቅ እና ድቅድቅ ጨለማ ምድርን ሲያለብሳት የሚጀመረው የቅራት ሰዓት፤ ከብቶችን ከሌባ እና ከአውሬ ለመጠበቅ፣ የሰው እና የእንስሳት ማደሪያን በመለየት ጤናን ለመንከባከብ እንዲሁም ማሳውን በተፈጥሮ ማዳበሪያ ለማልማት የሚደረግ የትግል መድረክ ነው።
በዚህ ፈታኝ የሌሊት ሰዓት የቤቱ አባወራ ወይም ደፋር ጎልማሳ ወፍራም ጋቢውን ደርቦ፣ ጦር እና ዱላ ጨብጦ፣ ታማኝ ውሾቹን አስከትሎ ወደ ከብቶች ማደሪያ ጊዜያዊ ጎጆ ያመራል። በቅራት ሌሊት እንቅልፍ የለም፤ ቆፈን የሚያስይዘው ብርድ፣ ካፊያ እና የሚመላለሰው ጅብ የሌሊቱ ቋሚ ፈተናዎች ናቸው። ጠባቂው እሳት አንድዶ ብርዱን ሲታገል፣ በዙሪያው ላለ አዳኝ አካል "አልተኛሁም፣ አለሁ!" ለማለት ኃይለኛ ፉጨቶችን፣ ሽለላዎችን እና ቀረርቶዎችን ያሰማል፤ ከጉያው በሚያወጣት ዋሽንት የልቡን ትርታ ከሌሊቱ ጸጥታ ጋር ያዋህዳል።
ጎህ ሲቀድ እና የንጋት ጮራ ጨለማውን ሲገፍፈው የቅራቱ ሌሊት በድል ይጠናቀቃል። ጠባቂው አርሶ አደር ከብቶቹ በሰላም ማደራቸውን ሲያይ የሌሊቱ ድካም ሁሉ በፈገግታ ይታጠባል፤ በማሳው ላይ የተረፈው የከብቶች ጽዳጅም የነገውን አዝመራ ማማር እያሳየው ልቡ በተስፋ ይሞላል። ቅራት በቀላሉ የሚታይ የግብርና ልማድ ሳይሆን፤ አርሶ አደሩ ለሀብቱ የሚከፍለውን የሕይወት ዋጋ፣ ከተፈጥሮ ጋር የሚያደርገውን ግብ ግብ እና የማይናወጥ ጽናቱን የሚያሳይ ደማቅ የማንነት አሻራ ነው።
AMICO-
የቴሌግራም ቻናልችንን በመቀላቀል የአዲስ አድማስን መረጃ ይከታተሉ…

መሰረታዊ የበዓል ፍጆታዎችን ከ15 እስከ 30 በመቶ ቅናሽ አድርጎ ለማቅረብ ያለመው «አደይ አዲስ ዓመት ታላቅ ኤክስፖና ፌስቲቫል» የፊታችን ሐሙስ ነሐሴ 21 ቀን በአዲስ ኢንተርናሽናል ኮንቬንሽን ሴንተር ይከፈታል። ከ250 በላይ ነጋዴዎች የሚሳተፉበት ይህ ፌስቲቫል፤ ሸማቾች በፍጆታዎች ዋጋ ጭማሪ ሳይማረሩ ጥራጥሬዎችን፣ ፍራፍሬዎችን፣ አትክልቶችን እና የወተት ተዋጽኦዎችን በተመጣጣኝ ዋጋ እንዲገበዩ የሚያስችል ሲሆን፣ በ15ቱ ቀናት ቆይታው ከ200 ሺህ በላይ ጎብኝዎችን ይስባል ተብሎ ይጠበቃል።

በኤክስፖው መርሃ ግብር ከግዢ በተጨማሪ የተለያዩ መዝናኛዎች የተካተቱ ሲሆን፤ 15 ልዩ የሙዚቃ ኮንሰርቶች፣ የፋሽን ትርኢቶች፣ የመጽሐፍ አውደ-ርዕይ፣ የልጆች ኮርነር፣ የሳቅ ምሽቶች እና የባህል ቀናት ይቀርባሉ። እንደ ጸጋዬ እሸቱ፣ ለምለም ሃይለሚካኤል፣ ክብሮም (ኬቢ) እና ሚኪ ጎንደርኛን የመሳሰሉ እውቅ ድምፃውያን የሚሳተፉበት ይህ ታላቅ የንግድና የባህል ድግስ ሕብረተሰቡ እየሸመተ የሚዝናናበት ሁነታ እንደሚሆን ተገልጿል።

«የቅን ልቦች የበጎ ሥራ ድርጅት» በሀገር፣ በትውልድ እና በህዝብ ላይ አዎንታዊ ተጽዕኖ ላሳደሩ የማህበራዊ ሚዲያ ተጽዕኖ ፈጣሪዎች እና አርአያ ዜጎች የሚሆን የ15 ሚሊዮን ብር ግምት ያለው 280 ግራም ንጹህ ወርቅ ሽልማት ይፋ አደረገ።

በስካይ ላይት ሆቴል በተሰጠው መግለጫ መሠረት፤ ሽልማቱ ለሰላም ግንባታ፣ ለአንድነት እና ለሀገራዊ እሴቶች ጥበቃ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ላበረከቱ አካላት የሚሰጥ ሲሆን፤ የመጀመሪያው ዘርፍ ለተሻሉ የማህበራዊ ሚዲያ አርአያዎች ከ100 እስከ 30 ግራም ወርቅ (በድምሩ 180 ግራም) ያስረክባል።

«ሀገር ተስፋ የምታደርጋቸው» በሚል መሪ ቃል በተዘጋጀው ሁለተኛው መርሃ ግብር ደግሞ ከዕይታ የተሰወሩ መምህራን፣ ምሁራን፣ ሥራ ፈጣሪዎች እና ባለሙያዎች ተጨማሪ 100 ግራም ወርቅ የሚጋሩ ሲሆን፤ ከ4ኛ እስከ 20ኛ ደረጃ ለሚወጡትም እውቅና ይሰጣል። በመጪው መስከረም በሚካሄደው በዚህ ታላቅ መድረክ ከ10 በላይ አንጋፋ የሀገር ባለውለታዎች እንደሚከበሩ ተገልጿል፤ ሕዝቡም በ yekinlibochaward.org ድረ-ገጽ በመግባት የዓመቱን ተወዳዳሪዎች መምረጥ እንደሚችል ተመላክቷል።

የዩጋንዳ መከላከያ ሰራዊት ጠቅላይ ኤታማዞር ሹም ጄኔራል ሙሆዚ ካይነሩጋባ «ቅዱስ ምድር» ብለው የሚጠሯትን እስራኤልን ለመጠበቅ 100,000 የዩጋንዳ ወታደሮችን ወደ እስራኤል ለመላክ ዝግጁ መሆናቸውን ገለጹ።
ጄኔራሉ ይህንን ውሳኔ የወሰኑት እስራኤል ከዚህ ቀደም ለዩጋንዳ ላደረገችው ድጋፍ ምላሽ ለመስጠት ታስቦ እንደሆነ እና ኃይሉን በራሳቸው መምራት እንደሚፈልጉ ተናግረዋል። ሆኖም እስካሁን ድረስ ምንም አይነት ይፋዊ የወታደር ማሰማራት ስራ ያልተከናወነ ሲሆን፣ የተሰጡት መግለጫዎች በጄኔራሉ የግል አቋም ደረጃ ላይ የተመሰረቱ መሆናቸው ተመልክቷል።
ፊፋ በዓለም ዋንጫው ፍጻሜ ወቅት በተፈጠሩ የሥነ-ምግባር ችግሮች ሳቢያ በአርጀንቲና እግር ኳስ ፌዴሬሽን ላይ የ321 ሺህ ዶላር ቅጣት የጣለ ሲሆን፣ ብሔራዊ ቡድኑም ቀጣይ ሁለት የሜዳው ጨዋታዎችን በግማሽ ተመልካች ብቻ እንዲጫወት አዟል።
በተጨማሪ በተጫዋቾችም ላይ ከባድ እገዳ የተጣለ ሲሆን፣ ሊሀንድሮ ፓሬዴስ የ10 ጨዋታዎች እገዳና የ90,000 ዶላር ቅጣት፣ ናኤል ሞሊና ደግሞ የ7 ጨዋታዎች እገዳና የ90,000 ዶላር ቅጣት ተላልፎባቸዋል።
በተመሳሳይ ቲያጎ አልማዳ እና ፓብሎ ማርቲን አንድ ጨዋታ ሲታገዱ፣ የአሰልጣኝ ቡድኑ አባል የሆኑት ሮቤርቶ አያላ ደግሞ የሦስት ጨዋታዎች እገዳ ተጥሎባቸዋል
የቴሌግራም ቻናልችንን በመቀላቀል የአዲስ አድማስን መረጃ ይከታተሉ…
ታዋቂው የአፍሪካ ፖለቲካ ተንታኝ ዶ/ር ዴቪድ ማትሳንጋ ግብጽ በኢትዮጵያ የውሃ ልማት ፕሮጀክቶች ላይ የምታሳየውን ኃይለኛ ተቃውሞና ዛቻ አጥብቀው አወገዙ። ግብጽ የናይልን ጉዳይ እንደ ፖለቲካ መሣሪያ እየተጠቀመችበት መሆኑን የገለጹት ተንታኙ፣ ሀገሪቱ ዛቻውን በመተው ስጋቶቿን ይዛ ወደ ድርድር ጠረጴዛ መምጣት እንዳለባት አሳስበዋል።
ኢትዮጵያ ፋብሪካዎችን ለማንቀሳቀስ እና የኢኮኖሚ እድገቷን ለማፋጠን ኤሌክትሪክ እንደሚያስፈልጋት የገለጹት ዶ/ር ማትሳንጋ፣ ወንዞቿ ወደ ውጭ ስለሚፈሱ ብቻ ልማቷን ልታቆም እንደማይገባ ተናግረዋል። የኢትዮጵያ ዓላማ ጎረቤት ሀገራትን መጎዳት ሳይሆን የውሃ ሀብቷን በፍትሃዊነት መጠቀም መሆኑንም ገልጸዋል።
በመጨረሻም ግብጽ ወታደራዊ ዛቻዎችን እና የጦርነት ንግግሮችን እንድታቆም አሳስበዋል። ጉዳዩን ወደ ዓለም አቀፍ ተቋማት ከመውሰድ ይልቅ፣ ሁለቱ ሀገራት ወደ አፍሪካ ህብረት በመመለስ በውይይት እንዲፈቱት ጥሪ አቅርበዋል።
FMC English-
የቴሌግራም ቻናልችንን በመቀላቀል የአዲስ አድማስን መረጃ ይከታተሉ…
Saturday, 22 August 2026 10:42

አለማየሁ ገላጋይ አመነ!

አለማየሁ ገላጋይ በፍቅር ስም፣ በእውነት ስም እያለ በፃፋቸው "ቴማቲክ ሲሪየስ" መፅሐፎቹ ውስጥ ማኀበረሰቡን ራቁቱን ነው ያስቀረው...
የመጀመሪያውን "በፍቅር ስም" ሳነብ፣ ፍቅርን፣ እንዴት እንዳመቸን ስንተረጉመው እንደነበረ፣ በፍቅር ስም ስንት ጥላቻ ዘርተን እንዳበቀልን ሲገባኝ፣ ስገረም ሰንብቼ ፣ አለማየሁ ገላጋይ "በእውነት ስም"ን ይዞ መጣ። ነባሩን፣ ተከልለን የኖርንበትን ግንብ ለመናድ መዶሻውን ስሎ እንደወጣ እና ፍርስርሱን ሳያወጣ እንደማይመለስ ወገግ አለልኝ። ብዙ አልቆየም "በእምነት ስም"ን ይዞ ወጣ። ምን ቀረን ታዲያ? ፍቅራችንን፣ እውነታችንን፣ እምነታችንን እንደጥጥ እያባዘተ መሬት ዘረገፈልን።
ፈሪ ነኝ። "በእምነት ስም"ን መጨረስ አልቻልኩም። አለማየሁ የጨከነብን መሰለኝ። እኔና እግዜሬን ለሙግት ጠረጴዛ ዙሪያ አስቀመጠን... መፅሐፉን ገፅ ሀምሳ ሰባት ላይ እንዳጠፍኩ አስቀመጥኩት... አልተመለስኩበትም።
ያኔ፣ አለማየሁ ግን በዚህ ማኀበረሰብ ይሄን ያህል አቂሟል? ይሄን ያህል? ልብሱን ገልቦ ከአንገቱ ላይ ማተቡን የመበጠስ ያህል? አልኩ...አለማየሁ ማኀበረሰቡን እንዳኮረፈ እኔም አለማየሁን አኮረፍኩት።
በቀደም አንድ ቁራጭ ቪዲዮ ስልኬን በጣቴ ስገልጥ አገኘሁ...
አለማየሁ ያወራል። ቃል በቃል አይደለም፤ እንዲህ አለ። "ይሄ ማኀበረሰብ በእምነት ስም ብዙ ሰርቷል... ለግፉ፣ እግዜሩን፣ አለኝ የሚለውን አንድ እምነቱን ሊነጠቅ ይገባል፤ ቅጣቱ ነው። 'አምናለሁ፤ ፈጣሪ አለኝ' የሚል ማኀበረሰብ ሰው ዘቅዝቆ ሰቀለ፤ ህፃናትን ፈጀ፤ ከእናት ማህፀን ልጅ አወጣ... እግዜር አለኝ ብሎ ይሄን ካደረገ፣ እግዜሩን መነጠቅ አለበት፤ ይሄንን ነው በመፅሐፌ ያደረግሁት" አለ።
በፈጣሪ ስር ተከልለን የምንሰራውን ነውር ፈጣሪያችንን በመንጠቅ ሊቀጣን ሞከረ። አለማየሁ ገላጋይ አመነ። ይሄን ጠርጥሬ ነበር መፅሐፉን ያቋረጥኩት፤ አለማየሁን በሌለበት ያኮረፍኩት።
አሌክስዬ እንታረቅ ...
አንተ እግዜራችንን ባትነጥቀንም በዚህ መካከል እግዜር አይኖርም። ቪዲዮ እየቀረፁ በሚተራረዱ ሰዎች መካከል ፈጣሪ እንዴት ይኖራል? ለመገዳደል ቀጠሮ በሚያያዙ ሰዎች መካከል እሱ ምን ይሰራል? አንተ ባትወስድብንም ቅሉ እግዜር ቀድሞ ተሰዷል።
Etsegenet Kebede-
Page 4 of 823