Administrator
Wednesday, 24 September 2025 08:18
"አስገድዶ መድፈር ባለመቆሙ ወላጆች የ12 ዓመት ልጃቸውን እየዳሩ ነው"
በትግራይ ክልል የአስገድዶ መድፈር ሁኔታዎች ባለመቆማቸው፣ ወላጆች በ12 ዓመት ዕድሜ ላይ የምትገኝ ልጃቸውን እየዳሩ እንደሚገኙ ተገልጿል፡፡
ፆታን መሠረት አድርገዉ በሴቶች ላይ የሚፈፀሙ የኃይል ጥቃቶችን ለመከላከል የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥራዎች በተለይም ከአምስት ዓመት ወዲህ ሲሰራ ቢቆይም፣ ከፀጥታዉ ችግር ጋር ተይያዞ ሙሉ ለሙሉ ጥቃቶችን ማስቆም አለመቻሉን ትግራይ ክልልን ጨምሮ በኦሮሚያ ምሥራቅ ሐረርጌ እንዲሁም በአማራ ክልል ደቡብ ጎንደር የተደረገ ጥናት አመላክቷል፡፡
ይህም የተገለፀው የኢትዮጵያ ሴቶች ማህበራት ቅንጅት፣ በትናንትናው እለት "እሷ ትመራለች" በሚል ላለፋት አምስት ዓመታት ሲተገብር የቆየው ፕሮጀክት መጠናቀቁን አስመልክቶ በተዘጋጀው መድረክ ላይ በቀረበው የጥናት ሪፖርት ነው፡፡
በዚህ ወቅት የታዳጊዎችና ስርአተ ጾታ አለም አቀፍ ድርጅት ጥናት የኢትዮጵያ ተወካይና ተመራማሪ ማኔጂንግ ዳይሬክተር ዶክተር ወርቅነህ አበበ፤ በትግራይ ክልል ከጦርነቱ አስቀድሞ የልጅነት እርግዝናን ለመግታት የግንዛቤ ስራዎች ሲሰሩ መቆየታቸውን ተናግረዋል።
አክለውም፤ ከጦርነቱ በፊትና በኋላ እነዚህ ሁኔታዎች በመቆማቸው፣ በክልሉ እንደ አዲስ በልጅነት የሚከሰት እርግዝና መንሰራፋቱን አስረድተዋል፡፡
ወላጆች ጥቃቱን ለመከላከል በሚል ልጆቻቸውን ለ-ያለእድሜ ጋብቻ እየዳረጉ መሆኑን ባቀረቡት የጥናት ሪፖርት አመላክተዋል፡፡
ችግሩ በተመሳሳይ በኦሮሚያ ክልል ምሥራቅ ሃረርጌ፣ በአማራ ክልል ደቡብ ጎንደር ዞን ደብረታቦር፣ በአፋርና ሶማሊያም አሳሳቢ መሆኑን ጠቁመዋል ሲል ሃራምቤ ሬዲዮ ዘግቧል፡፡

Published in
ዜና
Tagged under
Monday, 22 September 2025 15:07
የኢትዮጵያ ምግቦች አምባሳደሯ በስኮትላንድ
በሀገረ ስኮትላንድ የሀበሻ ምግብ ቤት የከፈተችው ወይዘሮ ሙና፤ የኢትጵያን ምግቦች በማስተዋወቅ ዝናን አትርፋለች፡፡
በራሷ ሼፍ ሙና የተመሰረተው ምግብ ቤቱ በሀገራችን በብዛት የተለመደውና የኢትዮጵያውያን መለያ የሆነው በየአይነቱ፣ ጥብስ፣ ክትፎ፣ ዶሮ ወጥ፣ ጥሬ ስጋ፣ ዱለትና ሽሮ የመሳሰሉ ምግቦች የሚገኝበት ሬስቶራንት ነው፡፡
ከኢትዮጵያ ተጉዘው ወደ ስኮትላንድ ጎራ የሚሉ ኢትዮጵያውያንን እንዲሁም የኢትዮጵያን ምግብ የለመዱ የሀገሬው ስኮትላንዳውያንን ሞቅ ባለ መስተንግዶ ለዓመታት አገልግሎት ሲሰጥ ቆይቷል፡፡
ወይዘሮ ሙና ከምግብ ቤትና የንግድ ስራዎቿ ባለፈ የኢትዮጵያን ምግቦች በተመረጡ አደባባዮች ይዛ በመውጣት ማስተዋወቋ ደግሞ ሬስቶራንቷን በውጭ ሀገር ከተከፈቱ የሀበሻ ምግብ ቤቶች የተለየ ያደርገዋል፡፡
አንዳንዴ ምግቦችን በነፃ በማቅረብና በማስተዋወቅ እንዲሁም ምግቦች ላይ ልዩ የዋጋ ቅናሽ በማድረግ የኢትዮጵያውያን ምግቦች በስኮትላንድ እንዲታወቁና እንዲለመዱ ማድረግ ችላለች፡፡
ብዙ ጊዜ ምግቦቿን በዋና ዋና ጎዳናዎች ላይ ይዛ በመውጣት እየተመገበች ሌሎችም እንዲመገቡ የምታደርገው የኢትዮጵያ ምግብ አምባሳደሯ ሼፍ ሙና፤ መንገደኞችን ምግቡን በነፃ በማቅመስ ታለማምዳለች፡፡
በዚህም በርካታ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ አትዮጵያውያን እንዲሁም የስኮትላንድ ዜጎች ኢትዮጵያና ምግቦቿን እንዲያውቁ ማድረግ ችላለች፡፡
በዚህ ብቻ ሳታበቃ የኢትዮጵያውያን ብሔር ብሔረሰቦች ባህል፣ ወግ፣ ቋንቋ፣ ጭፈራና የአለባበስ ዘዴ በማስተዋወቅ ለሀገሯ የአምባሳደርነት ሚናዋን እየተወጣች ትገኛለች፡፡
ግለሰቧ የኢትዮጵያን ምግቦች ለማስተዋወቅ በምታደርገው ጥረትም በስኮትላንድ ባይት በተባለው ጋዜጣ እንዲሁም ኢድንበርግ በተባለው የስነ ምግብ ድረ ገፅ ላይ አርዕስት መሆን ችላለች፡፡
-WMCC-
ቴሌግራም ቻናልችንን በመቀላቀል የአዲስ አድማስን መረጃ ይከታተሉ…



Published in
ህብረተሰብ
Tagged under
Monday, 22 September 2025 15:06
ኬንያ ዜጎቿ የሩሲያ ሠራዊትን ተገድደው እንደሚቀላቀሉ ለማጣራት ምርመራ ጀመረች
ኬንያ ዜጎቿ ወደ ሩሲያ በግዳጅ እየተወሰዱ በዩክሬን ጦርነት ውስጥ እንዲሳተፉ ይደረጋሉ መባሉን ተከትሎ ምርመራ መጀመሯ ተሰምቷል፡፡
ምርመራው ኬንያዊው አትሌት ኢቫንስ ኪቤት፣ የሩሲያ ሰራዊትን እንድቀላቀል ተታልዬ ነበር ማለቱን ተከትሎ የመጣ ነው ተብሏል፡፡
የኬንያ ባለስልጣናት እውነታውን እንዲሁም የተጎጂዎችን ደህንነት ለማረጋገጥ፣ ከሩሲያና ከዩክሬን ባለስልጣናት ጋር እየተነጋገሩ መሆኑ ተዘግቧል፡፡
ይህ ሁኔታ በግጭት ቀጠና ውስጥ የውጭ ሀገር ዜጎችን ኢላማ ያደረገ ቅጥር ላይ ያለውን ስጋት አጉልቶ እንደሚያሳይ ተጠቁሟል፡፡
ኬንያ አንዳንድ ዜጎቿ ወደ ሩሲያ ጦር ሰራዊት በግዳጅ እንደገቡና አሁን በዩክሬን የጦር ምርኮኞች ሆነው እንደሚገኙ የሚገልጽ ዘገባ ከወጣ በኋላ ነው የማጣራት ምርመራውን የከፈተችው፡፡
ቴሌግራም ቻናልችንን በመቀላቀል የአዲስ አድማስን መረጃ ይከታተሉ…
Published in
ከአለም ዙሪያ
Tagged under
Monday, 22 September 2025 15:06
በአዲሱ የብሔራዊ ባንክ ገዢ የተመራ ልዑክ በቻይና የሥራ ጉብኝት እያደረገ ነው
• ጉብኝቱ በእዳ ሽግሽግ ዙሪያ ለመምከርና የኢኮኖሚ
ትብብርን ለማጠናከር ያለመ ነው ተብሏል
በአዲሱ የብሔራዊ ባንክ ገዢ ዶ/ር ኢዮብ ተካልኝ የተመራ ልዑክ በቻይና ቤጂንግ የሥራ ጉብኝት እያደረገ ሲሆን፤
ጉብኝቱ በእዳ ሽግሽግ ዙሪያ ለመምከርና በኢትዮጵያና ቻይና መካከል ያለውን የኢኮኖሚ ትብብር ለማጠናከር ያለመ ነው ተብሏል፡፡
ልዑካኑ በቤጂንግ ቆይታቸው ከቻይና ገንዘብ ሚኒስቴር ከፍተኛ አመራሮች፣ ከቻይና ሕዝብ ባንክ፣ ኤግዚም ባንክ እና ከተለያዩ የንግድ ተቋማት አመራሮች ጋር እንደሚወያዩ ይጠበቃል፡፡
በዚህም በኢትዮጵያ ሀገር በቀል የኢኮኖሚ ሪፎርም የተከናወኑ ሥራዎችንና የተገኙ ውጤቶችን በተመለከተ ገለጻ እንደሚያደርጉ ባንኩ አስታውቋል፡፡
በቀጣይ በኢትዮጵያ የመልማት አቅም ያላቸው የኢንቨስትመንት ፕሮጀክቶችን በተመለከተ ዝርዝር ማብራሪያ እንደሚሰጥ ተጠቁሟል፡፡
Published in
ዜና
Tagged under
Monday, 22 September 2025 15:05
ቢሮው ከባድ የሂሳብ ግድፈቶች የፈጸሙ የ10 የሂሳብ ባለሙያዎች የሙያ ፈቃድ እንዲሰረዝ ጠየቀ
የአዲስ አበባ ከተማ ገቢዎች ቢሮ፣ ከመንግሥት ገቢ ሊቀንሱ የሚችሉ ከባድ የሂሳብ ግድፈቶች የፈጸሙ የ10 የሂሳብ ባለሙያዎችና ኦዲተሮች የሙያ ፈቃድ እንዲሰረዝ ለኢትዮጵያ የሂሳብና ኦዲት ቦርድ ጥያቄ አቀረበ።
ቢሮው እንዳስታወቀው፣ በ2017 በጀት ዓመት ውስጥ 13 የግብር ከፋዮችን የሂሳብ መዝገብ በመመርመር ከባድ ግድፈቶች የተገኙባቸውን 10 ባለሙያዎች ለይቷል። ቢሮው ባደረገው የቅድመ ኦዲት ምርመራ፣ እነዚህ ባለሙያዎች ያዘጋጇቸው የሂሳብ መዝገቦች ከፍተኛ መጠን ያለው የገቢ ልዩነት እንዳለባቸውና በታክስ ስወራ መንግሥት ሊያገኘው የሚገባውን ገቢ ሊያሳጣ እንደነበር ገልጿል።
በዚህም መሰረት፣ ቢሮው ከፍተኛ የገንዘብ መጠን የመንግስትን ጥቅም ሊያሳጣ የሚችል ግድፈት የፈጸሙ 10 የሂሳብ ባለሙያዎችና ኦዲተሮች የሙያ ፈቃዳቸው እንዲሰረዝ ጥያቄ አቅርቧል። የቢሮው ሃላፊዎች እነዚህ ባለሙያዎች በቦርዱ የሙያ ፈቃድ የተሰጣቸው መሆናቸውን አረጋግጠዋል።
ቢሮው በተጨማሪም የከተማው ነዋሪዎችና የግብር ከፋዮች፣ ፈቃዳቸው እንዲሰረዝ የተጠየቀባቸው እነዚህ የሂሳብ ባለሙያዎች የሚያዘጋጁትን የሂሳብ መዝገብ እንደማይቀበል አስጠንቅቋል። የስም ዝርዝራቸውን ከቦርዱ በመጠየቅ የሙያ ስነ ምግባሩን ጠብቀው በሚሰሩ የሂሳብ ባለሙያዎችና ኦዲተሮች የሂሳብ መዝገቡን በማሰራት እንዲያቀርብም አሳስቧል፡፡
የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ ከዚህ ቀደምም በሂሳብ መዝገብ አዘገጃጀት ላይ የሚስተዋሉ ግድፈቶችን ለመቀነስ ከቦርዱና ከሙያ ማህበራት ጋር በመተባበር መፅሄት በማዘጋጀትና በመወያየት ትምህርት ሲሰጥ እንደነበር አስታውሷል።
አስ-
Published in
ዜና
Tagged under
Monday, 22 September 2025 15:03
ትራምፕ አሁንም ታላቁን የህዳሴ ግድብ በክፉ አነሱት
• በአባይ ውሃ ላይ የሚያሳድረውን ተጽእኖ "ትልቅ ችግር" ሲሉ ገልጸውታል
የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ባለፈው ቅዳሜ በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ላይ በሰጡት አስተያየት፤ ግድቡ በአባይ ውሃ ላይ የሚያሳድረው ተጽእኖ ለግብፅ "ትልቅ ችግር" የሚፈጥር ነው ብለዋል፡፡
"ኢትዮጵያ ውስጥ በዓለም ላይ እንደ ትልቅ ግድብ የሚወራለት ትንሽ ግድብ ገንብተዋል፡፡ እናም ወደ አባይ ወንዝ በሚፈሰው ውሃ ላይ ተጽዕኖ ያደርጋል፤ ያ ችግር ነው ትላላችሁ? እኔ ትልቅ ችግር ነው እላለሁ" ሲሉ ተናግረዋል፡፡
ፕሬዚዳንቱ በንግግራቸው፤ ታላቁን የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ፤ በህንድና ፓኪስታን፣ ታይላንድና ካምቦዲያ፣ አርሜኒያና አዘርባጃን፣ ኮሶቮና ሰርቢያ፣ እንዲሁም በእስራኤልና ኢራን መካከል ያለውን ውጥረት ጨምሮ ከሌሎች ዓለም አቀፍ ቀውሶች ጋር አዛምደው አንስተውታል፡፡
ባለፈው ሐምሌ ወር ትራምፕ፣ ታላቁ የህዳሴ ግድብ በአብዛኛው በአሜሪካ የገንዘብ ድጋፍ የተገነባ ነው ሲሉ አወዛጋቢ የሆነ መልዕክት ማስተላለፋቸው አይዘነጋም፡፡
ቴሌግራም ቻናልችንን በመቀላቀል የአዲስ አድማስን መረጃ ይከታተሉ…

Published in
ዜና
Tagged under
Monday, 15 September 2025 09:45
የማይናወጥ የሀገር ፍቅር፣ ሰጥቶ የማይረካ ቅን መንፈስ!
በርካታ ቅን ሰዎች አሉ። መርዳትን፣ መደገፍን፣ ቸርነትን ማዕከል ያደረጉ። ሁለንተናዊ በሆነ መልኩ የሚሳካላቸው ግን ጥቂት ናቸው፡፡
ከ79 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ሰዎች የስራ እድል መፍጠር። በሚሊየኖች የሚቆጠሩ ዜጎችን በቅንነት ማገልገልን ማዕከል ያደረጉ ድርጅቶችን ማቋቋም፣ መምራትና ስኬታማ ማድረግ ብዙዎች የሚታደሉት ጸጋ አይደለም።
የማይናወጥ የሀገር ፍቅር፣ ሰጥቶ የማይረካ ቅን መንፈስ፣ ስለህዝብ በጽናትና ያለመታከት መቆርቆርን እውን ለማድረግ፤ መቻል ብቻ ሳይሆን ሆኖ መገኘትን ይጠይቃል።
ክቡር ዶ/ር ሼህ ሙሐመድ ሁሴን ዓሊ አልአሙዲ በጣም ጥቂት ከሚባሉ የዚህ አይነት ሰብእና ከተጎናጸፉ ሰዎች መካከል አንዱ ናቸው። ማድረግን ስለሚችሉት ብቻ ሳይሆን ከልብ በመነጨ እምነትና ጽናት ማድረግን ሆነው መገኘት ችለዋል።
"ሚድሮኮች" የተጣለባችሁን አደራ በብቃትና በስኬት ተወጥታችሁ በሚቀጥለው ዓመት የሰራተኞችን ቀን ክቡር ዶ/ር ሼህ ሙሐመድ ሁሴን ዓሊ አልአሙዲ በተገኙበት በድምቀት እንደምታከብሩ ሙሉ እምነት አለኝ።
ሙሼ ሰሙ-
የቴሌግራም ቻናልችንን በመቀላቀል የአዲስ አድማስን መረጃ ይከታተሉ…
Published in
ህብረተሰብ
Tagged under
Monday, 15 September 2025 09:41
በኬሚስትሪ ትምሕርት ከፍተኛ ውጤት መመዝገቡ ተገለጸ
• የመንግስት ት/ቤቶች ተማሪዎችን በማሳለፍ ረገድ ዝቅተኛ ውጤት አስመዝግበዋል
በ2017 ዓ.ም. በተሰጠው የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተና፣ በኬሚስትሪ የትምሕርት ዘርፍ ከፍተኛ ውጤት መመዝገቡን የትምሕርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ አስታውቀዋል። በአፕቲትዩድ ትምሕርት ዝቅተኛ ውጤት እንደተመዘገበ ሚኒስትሩ አያይዘው ገልጸዋል።
ፕሮፌሰር ብርሃኑ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ እንዳመለከቱት፣ በሁሉም ክልሎች ካለፈው ዓመት አንጻር ሲመዘን፣ የተሻለ ውጤት ተመዝግቧል። ለአብነት፣ በጋምቤላ ክልል በ2016 ዓ.ም. ከተፈተኑ ተማሪዎች መካከል፣ 1.7 በመቶ ተማሪዎች ብቻ እንዳለፉ አውስተው፣ በ2017 ዓ.ም. ግን 4.5 በመቶ ተማሪዎች ፈተናውን ማለፍ መቻላቸውን ጠቁመዋል።
ከዚህም በተጨማሪ፣ 50 ከመቶ እና በላይ የማለፊያ ውጤት ካስመዘገቡ ተማሪዎች መካከል፣ የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች ቀዳሚውን ደረጃ እንደያዙ ሚኒስትሩ አስታውቀዋል። በዚህም 50 ከመቶ እና በላይ ያመጡ የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች ብዛት 11 ነጥብ 4 በመቶ ሲሆኑ፣ በማሕበራዊ ሳይንስ ደግሞ 5 ነጥብ 2 በመቶ ተማሪዎች እንደሆኑ አስረድተዋል።
ሚኒስትሩ፣ በኬሚስትሪ ትምሕርት ከፍተኛ ውጤት እንደተመዘገበ ጠቅሰው፣ በተቃራኒው በአፕቲትዩድ ፈተና ዝቅተኛ ውጤት መመዝገቡን ተናግረዋል። የአፕቲትዩድ ውጤትን ለማሻሻል፣ ከአጸደ ሕጻናት ጀምሮ የእንግሊዝኛ ትምህርት እንዲሰጥና የትምሕርቱን አሰጣጥ ለማሻሻል የተለያዩ ስራዎች እየተሰሩ እንደሚገኙ አብራርተዋል።
በዚህም ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር በመተባበር፣ ተማሪዎች በቤታቸው ሆነው የሚማሩበት የበይነ መረብ አማራጭ መዘርጋቱን ጠቁመዋል። በይነ መረቡ ስራ በጀመረ ሰሞን፣ ከቤታቸው ሆነው የሚማሩ ተማሪዎች ቁጥር “ከሚፈለገው በታች” እንደነበር ያወሱት ፕሮፌሰሩ፣ በአሁኑ ወቅት ግን “ለውጦች እየታዩ ነው” ብለዋል።
በሌላ በኩል፣ የመንግስት ትምሕርት ቤቶች ተማሪዎችን በማሳለፍ ረገድ ዝቅተኛ ውጤት ማስመዝገባቸውን ሚኒስትሩ አልሸሸጉም። አዳሪ እና በውጭ አገራት የሚገኙ የኢትዮጵያውያን ትምሕርት ቤቶች ተማሪዎችን በማሳለፍ ረገድ ቀዳሚውን ደረጃ ቢይዙም፣ ከመንግስት ትምሕርት ቤቶች በ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተና ተማሪዎችን ያሳለፉት 5 ነጥብ 6 በመቶ “ብቻ ናቸው” ሲሉ ተደምጠዋል።
“የትምሕርት ዘርፍ ማሻሻያ ስራችን ከምንገምተው በላይ ውጤት አስገኝቷል” ያሉት ፕሮፌሰር ብርሃኑ፣ በቀጣይም የመንግስት ትምሕርት ቤቶችን ትኩረት ያደረጉ ለውጦች ተግባራዊ እንደሚደረጉ ገልጸዋል።
የቴሌግራም ቻናልችንን በመቀላቀል የአዲስ አድማስን መረጃ ይከታተሉ…

Published in
ዜና
Tagged under
Monday, 15 September 2025 09:40
""ስለሌላ ነገር ሳስብ የማስበው በአዕምሮዬ ነው፤ ስለኢትዮጵያ ግን የማስበው በልቤ ነው" -ሼህ መሐመድ ሁሴን አሊ ዓልአሙዲ-
ሼህ መሐመድ የምንጊዜም የኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጅ ናቸው! በኢትዮጵያ ታላላቆቹ ሀገራዊ ሥራዎችና የደግነት ምግባራት ውስጥ የእሳቸው ለጋስ እጅ ያላረፈበትን ነገር መጥቀስ ይከብዳል። ሲለግሱና ዕንባ ሲያብሱ፣ ቃል እስኪቸግራቸው ስለኢትዮጵያ የልባቸውን አውጥተው ሲናገሩ፣ ከአጠገባቸው ሆኜ የማድመጥን ብዙ ዕድል አግኝቻለሁ።
ከብዙ አመታት በኋላ በሚድሮክ የቤተሰብ ቀን ላይ በቀረበው ቪዲዮ የተቀረፀውን ድምጻቸውን በመስማቴና ምስላቸውን ማየት በመቻሌ እጅግ በጣም ተደስቻለሁ። ወደሚወዷት፣ በልባቸው በሚያስቡላትና ከአንደበታቸው ወደማትጠፋው ሀገራቸው በጤና ተመልሰው፣ የልጅ ከሚመስለው ፈገግታቸው ጋር በአካለ ሥጋ እናያቸው ዘንድ እንፀልያለን!
ረዥም ዕድሜና ሙሉ ጤናን እመኝልዎታለሁ!
-ከያኒና ጋዜጠኛ ተስፋዬ ማሞ -
Published in
ጥበብ
Tagged under
Monday, 15 September 2025 08:54
የኬንያው ኢኩቲ ባንክ የኢትዮጵያን የባንክ ገበያ ሊቀላቀል ነው
ኢኩቲ ባንክ የኢትዮጵያን የፋይናንስ ኢንዱስትሪ የሚቀላቀል ሁለተኛው የኬንያ ባንክ ሊሆን ነው፡፡
ኢኩቲ ባንክ ወደ ኢትዮጵያ የፋይናንስ ዘርፍ ለመግባት በሚያደርገው እንቅስቃሴ ከኢትዮጵያ ባለስልጣናት ጋር በይፋ ውይይት ጀምሯል፡፡
የኢኩቲ ግሩፕ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ዶ/ር ጀምስ ምዋንጊ በቅርቡ ከኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮሚሽነር ዶ/ር ዘለቀ ተመስገን ጋር ተገናኝተው፣ ባንኩ በኢትዮጵያ ሊንቀሳቀስ በሚችልበት የህግ ማዕቀፍ ዙሪያ መወያየታቸው ተጠቁሟል።
የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽነር በውይይቱ ወቅት እንደገለጹት፤ ባንኩ ኢትዮጵያ ውስጥ በሚያደርገው ኢንቨስትመንት አስፈላጊው ትብብርና ድጋፍ ይደረግለታል።
የኢኩቲ ባንክ ሥራ አስፈጻሚ ዶ/ር ጀምስ ምዋናጊ በበኩላቸው፤ የኢትዮጵያ መንግስት የፋይናንስ ሴክተሩን ለውጪ ባለሀብቶች ክፍት ማድረጉ ምቹ አጋጣሚ ነው ብለዋል።
አክለውም፤ ባንኩ
የኬንያው ኢኩቲ ባንክ የኢትዮጵያን የባንክ ገበያ ሊቀላቀል ነው
ኢኩቲ ባንክ የኢትዮጵያን የፋይናንስ ኢንዱስትሪ የሚቀላቀል ሁለተኛው የኬንያ ባንክ ሊሆን ነው፡፡
ኢኩቲ ባንክ ወደ ኢትዮጵያ የፋይናንስ ዘርፍ ለመግባት በሚያደርገው እንቅስቃሴ ከኢትዮጵያ ባለስልጣናት ጋር በይፋ ውይይት ጀምሯል፡፡
የኢኩቲ ግሩፕ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ዶ/ር ጀምስ ምዋንጊ በቅርቡ ከኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮሚሽነር ዶ/ር ዘለቀ ተመስገን ጋር ተገናኝተው፣ ባንኩ በኢትዮጵያ ሊንቀሳቀስ በሚችልበት የህግ ማዕቀፍ ዙሪያ መወያየታቸው ተጠቁሟል።
የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽነር በውይይቱ ወቅት እንደገለጹት፤ ባንኩ ኢትዮጵያ ውስጥ በሚያደርገው ኢንቨስትመንት አስፈላጊው ትብብርና ድጋፍ ይደረግለታል።
የኢኩቲ ባንክ ሥራ አስፈጻሚ ዶ/ር ጀምስ ምዋናጊ በበኩላቸው፤ የኢትዮጵያ መንግስት የፋይናንስ ሴክተሩን ለውጪ ባለሀብቶች ክፍት ማድረጉ ምቹ አጋጣሚ ነው ብለዋል።
አክለውም፤ ባንኩ ኢትዮጵያ ውስጥ በሚያደርገው ኢንቨስትመንት ለሌሎች ኢትዮጵያ ውስጥ በዘርፉ መሰማራት ለሚፈልጉ የውጭ ኩባንያዎች ምሳሌ መሆን እንደሚፈልግ ገልጸዋል።
ኢኩቲቲ ባንክ በኬንያ፣ ኡጋንዳ፣ ታንዛኒያ፣ ደቡብ ሱዳን፣ ሩዋንዳና ኮንጎ ውስጥ በፋይናንስ ዘርፍ የካበተ ልምድ እንዳለው ይታወቃል፡፡


Published in
ዜና
Tagged under

