Administrator

Administrator

      የአማራ ክልል መንግስት፣ በክልሉ በታጠቁ ኃይሎች እየተፈጸሙ ያሉ ከፍተኛ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶችን  እንዲያስቆም የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባዔ (ኢሰመጉ) ጠየቀ። ኢሰመጉ ባወጣው መግለጫ፤ በአማራ ክልል ያለፍርድ ቤት ትዕዛዝ የሚፈጸመው እስር መቀጠሉንና  የሚያዙ ሰዎች ፍርድ ቤት እንደማይቀርቡ አስታውቋል።
ተቋሙ ባለፈው ረቡዕ ጥቅምት 27 ቀን 2017 ዓ.ም. ባወጣው በዚህ መግለጫ፤ አማራ ክልልን ጨምሮ በሌሎች ክልሎች ተፈጽመዋል ያላቸውን የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች በዝርዝር ያቀረበ ሲሆን፣ በአማራ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች በርካታ ሰዎች መገደላቸውን አመልክቷል። በክልሉ እየተካሄደ ባለው ግጭት ሳቢያ፣ ጥቅምት 17 ቀን 2017 ዓ.ም. በአዊ ዞን፣ አዲስ ቅዳም ከተማ በመንግስትና በተለምዶ ፋኖ በመባል በሚታወቁ የታጠቁ አካላት መካከል ውጊያ ከተደረገ በኋላ፣ የመንግስት የጸጥታ ሃይሎች “የፋኖ ደጋፊ ናችሁ” በሚል በየቦታው ያገኟቸዉን አረጋውያንን ጨምሮ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸውን ሰዎችን ከሕግ አግባብ ዉጭ ግድያ እንደፈጸሙባቸው ኢሰመጉ ጠቅሷል።


ጥቅምት 18 ቀን 2017 ዓ.ም. ምሽት አካባቢ ባሕር ዳር ከተማ፣ ቀበሌ 07 በሚገኘው ሃን ጤና ጣቢያ ተቀጥራ ከ30 ዓመት በላይ ስትሰራ የነበረች ሴት የጤና ባለሙያ፣ ከመንግሥት የጸጥታ ሃይሎች በተተኮሰ ጥይት እንደተገደለች ያመለከተው  ኢሰመጉ፤ “ጥቅምት 21 ቀን 2017 ዓ.ም. በደቡብ ጎንደር ዞን ከጋሳይ ወደ ጉና በጌምድር [ክምር ድንጋይ] ተሳፋሪዎችን ጭኖ ሲጓዝ የነበረ የሕዝብ ማመላለሻ መኪና፣ ከመኪናው ራስ/ፖርቶ መጋላ ላይ ተሳፍረው ሲሄዱ የነበሩ ሰዎች በታጠቁ ሃይሎች በተተኮሰ ጥይት ሁለቱ ተሳፋሪዎች ሲገደሉ፣ አንድ ተሳፋሪ ላይ ደግሞ ከፍተኛ የአካል ጉዳት መድረሱን ለማወቅ መቻሉን ገልጿል፡፡


ከዚህም በተጓዳኝ በክልሉ ያለፍርድ ቤት ትዕዛዝ የሚደረገው እስር እንደቀጠለና የሚያዙ ሰዎች ፍርድ ቤት እየቀረቡ አለመሆኑን ኢሰመጉ አስታውቋል፡፡
ኢሰመጉ በመግለጫው ላይ ለአማራ ክልል መንግስት፣ በመንግስት የጸጥታ ሃይልና በታጠቁ አካላት እየተፈጸመ ያለውን ከፍተኛ የሆነ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶችን በቂ ትኩረት በመስጠት እንዲያስቆምና ዜጎቹን የመጠበቅ ሃላፊነቱን በአግባቡ እንዲወጣ ጥሪ አቅርቧል።
አምነስቲ ኢንተርናሽናል በበኩሉ፣ በመከላከያ ሰራዊትና በአማራ ክልል የጸጥታ ሃይሎች አማካኝነት ከአንድ ወር በላይ ለእስር የተዳረጉ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች በአፋጣኝ እንዲለቀቁ ጠይቋል። የሰብዓዊ መብት ተሟጋቹ ከመስከረም ወር ጀምሮ አደረግሁት ባለው ማጣራት፣ በክልሉ በአራት ጊዜያዊ የማቆያ ስፍራዎች በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች በእስር ላይ እንደሚገኙ ማረጋገጡን ገልጿል።


የሰብዓዊ መብት ተሟጋቹ፣ ከጊዜያዊ የማቆያ ጣቢያዎቹ የወጡ ሁለት ሰዎችን፣ አምስት የታሳሪ ቤተሰቦችንና ዘጠኝ ከጅምላ እስሩ ጋር በተያያዘ በስልጣን ላይ ያሉ ሰዎችን ማነጋገሩን አመልክቷል። በዚህም በዳንግላ፣ ሰራባ (ጭልጋ)፣ ኮሪሳ (ኮምቦልቻ) እና ሸዋሮቢት በተዘጋጁ ጊዜያዊ ጣቢያዎች በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ከአንድ ወር በላይ በእስር ላይ እንደሚገኙ ማረጋገጡን ነው የጠቆመው።
አምነስቲ በሪፖርቱ  በአራት ከተሞች በሚገኙ ጊዜያዊ ካምፖች የታሰሩት በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች የተሃድሶ ስልጠና ወስደው ካጠናቀቁ በኋላ፣ “ይለቀቃሉ” መባሉን ከታሳሪ ቤተሰቦች መስማቱን ገልጿል።

     በትግራይ ክልል ወደ አንድ ሚሊዮን የሚጠጉ ተፈናቃዮች ወደ ቀያቸው አልተመለሱም ሲል የኢትዮጵያ ሕዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋም፣ መቐለ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት አስታወቀ። እነዚህ ተፈናቃዮች ወደ ቀያቸው ያልተመለሱት የፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ ባለመደረጉ ነው ብሏል፡፡
የቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤቱ ሃላፊ የሆኑት አቶ ጸሐዬ እምባዬ ለክልሉ መገናኛ ብዙሃን በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ፤ ከ970 ሺ በላይ በክልሉ ውስጥ የተፈናቀሉ ዜጎች የፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ ባለመደረጉ ወደ ቀያቸው አለመመለሳቸውን አመልክተው፣ በረሃብና በሽታ ምክንያት ሕይወታቸው የሚቀጠፍ ተፈናቃዮች ቁጥር እየጨመረ መጥቷል ብለዋል። አያይዘውም፣ ተቋማቸው ባደረገው ጥናት መሰረት፤ ለተፈናቃዮቹ የሚቀርበው እርዳታ በአግባቡ እየተዳረሰ አለመሆኑን ጠቅሰዋል።


ሃላፊው በሰላም ስምምነቱ “ይመለከታቸዋል” ተብለው ለተጠቀሱት አካላት ባቀረቡት ጥሪ፣ በፕሪቶሪያው ስምምነት መሰረት ተፈናቃዮች ወደ ቀድሞ ቀያቸው እንዲመለሱ ትኩረት ሰጥተው እንዲሰሩ ተማጽነዋል።
የቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤቱ የሴቶችና ሕጻናት ክፍል ሃላፊ አቶ ሃፍታይ አሰፋ በበኩላቸው፤ ከሰብዓዊ ዕርዳታ አቅርቦት እጥረት ባሻገር ተፈናቃዮቹ መሰረታዊ መብቶቻቸውን በመነፈጋቸው ሳቢያ፣ ለሞትና እንግልት እየተዳረጉ መሆናቸውን ገልጸዋል። በሽረ እንዳስላሰ ከተማ ከሚገኙ ተፈናቃዮች መካከል 42 ሺ ያህሉ መሰረታዊ ዕርዳታ ያላገኙ ሲሆኑ፣ ከ78 ሺ በላይ የሚሆኑት ደግሞ፣ ንጹህ ውሃ እንደማያገኙ ሃላፊው ጠቅሰዋል።


በሕዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋም የተሰራው ጥናት እንደሚያመለክተው፣ ከፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነትም በኋላ የእርዳታ አቅርቦት በቂ  አይደለም።
አገልግሎት አሰጣጥ ድክመት አንጻር ለመንግስት ሰራተኞች የ17 ወር ደመወዝ አለመከፈልና ሌሎች ምክንያቶች እንደ መንስዔ እንደሚጠቀሱ ተቋሙ አመልክቷል። የሕዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋም፣ መቐለ ቅርንጫፍ፣ ከፕሪቶሪያው ስምምነት በኋላ የሚቀርቡለት ቅሬታዎች በርካታ መሆናቸውንም ጠቁሟል፡፡  

      በዚህ ዓመት የኢትዮጵያ አማካይ የዋጋ ንረት 25 በመቶ እንደሚሆን ዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት (አይኤምኤፍ) ገልጿል። ድርጅቱ የኢትዮጵያ መንግስት በንግድ ባንኮች ላይ የጣለውን አስገዳጅ የ20 በመቶ የግምጃ ቤት ቦንድ ግዥ “ያነሳል” ሲል አመልክቷል።
አይኤምኤፍ ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር የተራዘመ የብድር አቅርቦትን በተመለከተ ያደረገውን ስምምነት የሚዳስስ የመጀመሪያ ዙር አጠቃላይ ሪፖርት ባለፈው ሰኞ ጥቅምት 25 ቀን 2017 ዓ.ም. ይፋ አድርጓል። ኢትዮጵያ አገር በቀል የምጣኔ ሃብት ፖሊሲ ማሻሻያን ጨምሮ በገበያ ስርዓት ላይ የተመሰረተ የውጭ ምንዛሪ ግብይት ተመንን ተግባራዊ ማድረጓ የሚበረታታ እንደሆነ የድርጅቱ የስራ አመራር ቦርድ በሪፖርቱ አስታውቋል።


የኢትዮጵያ መንግስት የፋይናንስ ስርዓቱን ዋስትና ለማረጋገጥ እየተገበራቸው የሚገኙት የማስተካከያ ጥረቶች ከአይኤምኤፍ የፖሊሲ መስፈርቶችና የፕሮግራም መመዘኛዎች ጋር መጣጣም እንደሚገባቸው ድርጅቱ አሳስቧል፡፡ የአይኤምኤፍ ምክትል ማኔጂንግ ዳይሬክተርና የቦርዱ ሰብሳቢ ቦ ሊ የኢትዮጵያ መንግስት በብሔራዊ ባንክ አማካይነት ሲያደርጋቸው የቆዩትን በውጭ ምንዛሪ ግብይት ላይ የሚደረጉ ጣልቃ ገብነቶች የመቀነስ ተግባራት አጠናክሮ መቀጠል “አለበት” ብለዋል።


“ቀጣይነት ያለው እና ጥብቅ የሆነ የገንዘብ ፖሊሲ፣ እንዲሁም የመንግስት የበጀት ጉድለቶችን ለመሸፈን የሚደረጉ የገንዘብ ድጎማዎች ማስወገድን ጭምሮ ጥንቃቄ የተሞላባቸው የማክሮ ኢኮኖሚ ፖሊሲዎች መተግበራቸው በኢኮኖሚው ላይ የሚከሰቱ የሚዛን መዛባቶችን ለመቀነስ እና የማክሮ ኢኮኖሚ መረጋጋትን ለማምጣት አስፈላጊ ናቸው።” ብለዋል፣ የቦርዱ ሰብሳቢ።
በተጨማሪም የኢትዮጵያ መንግስት በንግድ ባንኮች ላይ የጣለውን አስገዳጅ የ20 በመቶ የግምጃ ቤት ቦንድ ግዥ በሰኔ ወር 2017 ዓ.ም. ሙሉ በሙሉ እንደሚያነሳ አይኤምኤፍ ማረጋገጡን በሪፖርቱ ላይ ጠቅሷል፡፡ በተቃራኒው ደግሞ በ2017 ዓ.ም. ሁሉም ባንኮች ከሚፈጽሙት አስገዳጅ የቦንድ ግዥ በአጠቃላይ 55 ቢሊዮን ብር ለመሰብሰብ ማቀዱን መንግስት ለአይኤምኤፍ መግለጹ ተጠቁሟል፡፡


አይኤምኤፍ ይፋ ባደረገው በዚህ ሪፖርት የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ በዋና ዋና የኢኮኖሚ አመላካቾች ሲታይ የሚኖረው የዕድገት ሁኔታ ምን እንደሚመስል ያመላከተ ሲሆን፣ “ዕውነተኛ የአገራዊ ጥቅል ምርት ዕድገት” በተሰኘው መስፈርት መሰረት ኢትዮጵያ እ.ኤ.አ. በ2024/25 የሚኖራት ዕድገት 6 ነጥብ 5 በመቶ እንደሚሆን ተገምቷል። በተጨማሪም፣ የአገሪቱ አማካይ የዋጋ ንረት 25 በመቶ “ይሆናል” ሲል ድርጅቱ ግምቱን አስቀምጧል፡፡
አይኤምኤፍ በመስከረም ወር 2017 ዓ.ም. መጀመሪያ ላይ ኢትዮጵያ ከኢኮኖሚ ማሻሻያው በኋላ ያለችበትን አጠቃላይ ሁኔታ ከገመገመ በኋላ፣ “ጥብቅ የሆኑ የገንዘብ ፖሊሲዎች እንዲቀጥሉ” የሚል የመጀመሪያ ዙር መግለጫ መስጠቱ ይታወሳል። ይህን ተከትሎ የብሔራዊ ባንክ ገዥ አቶ ማሞ ምሕረቱ ጥብቅ የሆነውን የገንዘብ ፖሊሲ ኢትዮጵያ “ታስቀጥላለች” የሚል መግለጫ ሰጥተው እንደነበር አይዘነጋም።


የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ምክትል ፕሬዚዳንት ጄኔራል ጻድቃን ገብረትንሳዔ “ፕሬዚዳንት እንድሆን በተደጋጋሚ ብጠየቅም ጥያቄውን ግን አልተቀበልኩም” ሲሉ ተናገሩ። ጄኔራል ጻድቃን፤ የትግራይ ሕዝብ በተመረጠለት ሳይሆን በመረጠው መሪ መተዳደር ይገባዋል ብለው እንደሚያምኑ ጠቁመዋል፡፡
ባለፈው እሁድ ጥቅምት 23 ቀን 2017 ዓ.ም. በመላው ዓለም ከሚገኙ የዲያስፖራ ማሕበረሰብ አባላት ጋር በበይነ መረብ ውይይት ያደረጉት ጄኔራል ጻድቃን፣ ለተለያዩ ሃሳቦች  ማብራሪያ የሰጡ ሲሆን፣ ለቀረቡላቸው ጥያቄዎችም ምላሽ ሰጥተዋል።
በዚህ ውይይት ላይ ጄኔራል ጻድቃን፣ የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ዳይሬክተር ጄኔራል አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን በደቡብ አፍሪካ ፕሪቶሪያ፣ የጦር ሃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ በኬንያ ናይሮቢ እንዲሁም በሃላላ ኬላ ተገኝተው በነበሩበት ወቅት የጊዜያዊ አስተዳደሩ ፕሬዚዳንት እንዲሆኑ ጥያቄ እንዳቀረቡላቸው አስታውሰው፤ “‘እኔ ግን የትግራይ ሕዝብ ሲመርጠኝ እንጂ እናንተ በትግራይ ሕዝብ ላይ እንድትሾሙኝ አልፈቅድም። ይህ ለትግራይም፣ ለታሪኬም የሚመጥን አይሆንም’ የሚል መልስ ሰጠኋቸው።” ብለዋል።


በዚህ ጉዳይ ዙሪያ ባለስልጣናቱ ለአቶ ጌታቸው ረዳ በተደጋጋሚ ተመሳሳይ ሃሳብ ያቀርቡላቸው  እንደነበር ያወሱት  ጄኔራሉ፣ በአሜሪካ በኩልም ይኸው ፍላጎት ሲንጸባረቅ መቆየቱንና እርሳቸው ግን ፍላጎቱ እንዳልነበራቸው አስረድተዋል። “ዶክተር ደብረጽዮን ‘በረሃ ሳለን፣ እኔን ከስልጣን ለማንሳት ፈልጎ ነበር’ ሲሉ የተናገሩት ነገር የሚያሳዝን ነው። ሰራዊታችን ከተበታተነ በኋላ ‘እንደገና ተደራጅተን እንዴት ትግሉን እናስተባብር?’ ብለን መከርን። ዶ/ር ደብረጽዮን የውጭ፣ እኔ ደግሞ የአገር ውስጥ ትግሉን ለማስተባበር ተመረጥን። ይህንን ነው ዶ/ር ደብረጽዮን ‘ከስልጣን ለማንሳት ፈልጎ ነበር’ በማለት ሊገልጹ የፈለጉት።” ሲሉ  ያስረዱ ሲሆን፣ አክለውም፤ “እኔ ሕዝቤን ለማገዝ እንጂ የሆነ ስልጣን በአቋራጭ ለመውሰድ ዓላማ የለኝም። ስልጣን ለማግኘት የፕሪቶሪያ፣ የናይሮቢና የሃላላ ኬላ እንዲሁም ሌሎች አጋጣሚዎች ነበሩ። ይህ ግን ከዓላማዬና ከሰብዕናዬ ጋር የሚሄድ ስላልሆነ አላደረግሁትም።” ብለዋል፡፡
“ውስጣዊ ችግራችንን ከፈታን፣ የውጭ ችግሮቻችንን ለመፍታት ብዙም አንቸገርም” ያሉት ጄኔራል ጻድቃን፤ የትግራይ ሕዝብ ከላይ በተመረጠለት ሳይሆን ራሱ በመረጠው መሪ መተዳደር እንደሚገባው በአጽንዖት ተናግረዋል፡፡ ትእምት (EFFORT) የትግራይ ሕዝብ በመሆኑ ድርጅቱ ወደ ዋና ባለቤቱ፣ ወደ ትግራይ ሕዝብ ሊዘዋወር እንደሚገባ በውይይቱ ላይ አንስተዋል።
ከተፈረመ ሁለት ዓመታትን ያስቆጠረው የፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት በውስጡ ያሉትን ዕድሎች በአግባቡ ከተጠቀምንባቸው፣ ከገባንበት  ችግር በፍጥነት እንወጣለን ብለዋል፣ ጄኔራል ጻድቃን።

Friday, 08 November 2024 08:35

ነገረ መጻሕፍት!

ነገ ቅዳሜ ጥቅምት 30  2017 ዓ.ም ከቀኑ 8:00 ጀምሮ ምኒልክ ሆስፒታል አካባቢ በሚገኘው "FSS" አዳራሽ ውስጥ ይካሄዳል።

የፕሮግራሙ አዘጋጅና አቅራቢ ደራሲ እንዳለጌታ ከበደ ነው።

Thursday, 07 November 2024 20:45

ሰባራ ጥላ

ቅዳሜ ጥቅምት 30 አመሻሽ ላይ ከ( 10:00 ) ጀምሮ አብዬ በርሶማ አንጋፋ እና ወጣት የኪነ ጥበብ ባለሞያዎች በክብር እንግድነት በተጋበዙበት መድረክ በብሔራዊ ቤተ መዛግብት እና ቤተ መጽሐፍት አገልግሎት(ወመዘክር) ሥራውን ያቀርባል።

Thursday, 07 November 2024 20:41

መንታ ፍቅር

መንታ ፍቅር:: አዲስ አስገራሚ: ግራ እያገባን እየሳቅን ዋሽንግተን እና እዲስ አበባ የምንመላለስበት ፊልም:: አርብ ፡ ጥቅምት 29:በ 8: በ10: በ1 ሰዓት:: ቅዳሜና እሁድ በ8: 10: 12 ሰአት  ተጋብዘዋልና ይምጡ !

Tuesday, 01 October 2024 00:00

ሂሩት በቀለ ከ1935 - 2015 ዓ.ም.

ሕይወት እንደ ሸክላ (1950 ዓ.ም)
***************************
ዕድሜው ሲገሰግሥ ከንቱ ሰው ዘንግቶት
መች ዐልፎልኝ ይላል ማለፉን ረስቶት
አይቀር መንፈራገጥ ያ! ሆድ እስኪሞላ
ወድቃ እስክትሰበር ሕይወት እንደሸክላ
ጣራና ግድግዳ በወርቅ ቢሠራ
ገንዘብ ተቆልሎ ቢመስል ተራራ
በከፋው ጨለማ በዚያን በሞት መንገድ፣
ተከትሎ አይሄድም ሀብት የሥጋ ዘመድ
ያለው ከሌለው ጋር ተካፍሎ እንደመብላት
ለምን ይሰስታል ዕድሜ አይለውጥም ሃብት
የሌለው ዘመዱን ሸኝቶት በጥርሱ
ችጋር ይዞት ሲሞት ምንድነው ማልቀሱ ?
______________________________
ሂሩት በቀለ ከ1935 - 2015 ዓ.ም. የኖረች ድንቅ ድምፃዊ ነበረች። በሙዚቃው ዓለም ኹሌም ባይኾን የብዙዎችን ስሜት ለዘመናት ገዝተው የሚኖሩ ድምፃውያን ዐልፎ ዐልፎ ያጋጥማሉ:: ከእንደነዚህ ዐይነት ድምፃውያን መካከል አንዷ የኾነችው ሂሩት በቀለ በሙዚቃው ዓለም በቆየችባቸው 30 ዓመታት ውስጥ አይረሴ ዘፈኖችን አበርክታለች፡፡ በመጨረሻው የሕይወት ዘመኗ ከዓለማዊ ዘፈኖች ራሷን ያራቀችው ሂሩት እስከ 1982 ዓ.ም ድረስ ከ150 የማያንሱ ዘፈኖችን ተጫውታለች::

ጥቂት ከማይባሉ፣ ከፍ ያሉ ሀሳቦችን ከያዙ ዘፈኖቹ መካከል፤ “ስድስት” ሲል በለቀቀው አልበም ውስጥ የተካተተና በጥልቅ ፍልስፍና የታሸ ስለ ይቅርታ የሚያትት አንዱ ዘፈን ነው።
ገጸ-ሰቡ በዘፈኑ ውስጥ “ቢሆን...ቦታ ብትሰጪኝ” እያለ፣ “በደልኳት” ካላት ሴት አጥብቆ ይቅርታ ይጠይቃል። ደግሞም “ሰው እምነቱን ሐይማኖቱን፣ ጸሎቱን፣ ምህላውን ቢመስል፣ ‘ቢሆን’ መልካም ነው” የሚል አንድምታም ይደመጥበታል።
 “ተጸጽቶ በይቅርታ ለሚያጎነብስ ‘በዳይ’ ለተባለ ሰው፣ አንድ አማኝ እንዴት ‘ይቅር’ ለማለት ቦታ ያጣል?” በማለት  ይጠይቃል። ተስፋ አንግቦ “እናውጋ...እንወቃቀስ” ይላታል።
ስሚኝ
አጠፋ በደልህ፤ ያልሽኝ ሰው
አታወሪኝ ምነው?
ዛሬም
በተስፋ እጠብቅሻለሁ
እናውጋ እላለሁ።
በድለሃል መባሉን ተቀብሎ በተማጽኖ ለይቅርታ ደጅ እየጠና ነው። “በድለኸኛል” ያለችው ሴት ፊት ብትነሳውም፣ ከነገ ዛሬ እምነቷን፣ ምህላዋን ሆና ይቅር እንደምትለው ተስፋ ሰንቋል። የተመላለሰችበት የአምልኮ ስፍራ ስለ “ይቅርታ እና በዳይን ይቅር ስለማለት” አስተምህሮ እንደማይጠፋው ተስፋ አድርጓል። ያውቃልም።
ጠዋት ማታ ማትቀሪ ደጁ
ነጠላሽ ከልብሽ ንጹህ
ምህረት ከራስ ይጀምራል (ስሚ)
ያን ጊዜ ፈጣሪ ይሰማል።
ለይቅርታ ቸለልተኛ የሆነ ልቧን፤ ቂመኛ ልቧን፣ ከምትለብሰው ነጠላ አነጻጽሮ፤  ከልቧ ነጠላዋ መንጿቱን በ”እንዴት ከጨርቅ አነስሽ” ትዝብት ይወቅሳታል። “ምህረት ስታደርጊ... ይቅር ስትዪ ነው ፈጣሪም የሚሰማው” በማለት “ሳል ይዞ ስርቆት፤ ቂም ይዞ ጸሎት” ይሉትን ብሂል ያስታውሳታል።
በቂም በቆሸሸ ልብ፣ በደልን በሚያመነዥግ ህሊና፣ ከፈጣሪዋ ዘንድ መሄድ ትታ፤ ቅድሚያ ከቤቷ ይቅር እንድትል፣ ነፍሷን በምህረት፣ በመተው እንድታጸዳም እንዲህ እያለ ይወተውታታል። ይሞግታታል።
ከቤቱ መሄድ ይቅርብሽ
ይቅር በይ ቅድሚያ ከቤትሽ
ሁሌ ስትሄጂ አይሻለሁ (ዓለም)
ሰላምሽ ግን በዳይሽ ጋር ነው።
ቢሆን ቦታ ብትሰጪኝ
ለአፍታ ብታዳምጪኝ
ቢሆን ልብሽ ከልቤ
ሰላም ነበርን
አንቺና እኔ
የይቅርታን ጉልበትና ሐይል ከብርሃን እኩል እያስተካከለ፤ ይቅር አለማለት ይቅርታን መንፈግ፣ ከብርሃን እንደሚያርቅም ለማሳሰብ የተዋቡ ስንኞች  ያስከትላል።
ጸሐይ ማልዳ ብትወጣም
ያለ ይቅርታ አልነጋም፤
ምህረትን ነፍጎ ያደረ
በጨለማ ዋለ።
ይቅርታዋን ለማግኘት አይፈነቅለው ድንጋይ፣ አይቧጥጠው ተራራ፣ አይወርደው ቁልቁለት የለምና፤  አንዱን ሀሳብ ከአንዱ እያስተያየ፣ እያመሳከረ መጋፈጡን ይቀጥላል።
በቶ መስቀልሽ
ግንባርሽ ላይ የተነቀሽበት
ምነው አያቅፈኝ
 ከሰው አነስኩበት?
በቃል ብትረቺኝ
ብወድቅለት ያገኘ አጌጠበት
ቅኔ አማርኛሽ
ወርቅ በዝቶበት።
 የእሷ ልብ ቢደነድን እንኳን፣ ለእምነቷ ምስክር አድርጋ በንቅሳት የደመቀችበት የግንባሯ “ቶ” መስቀል ሳይቀር ጨክኖበታል። እሱም ከእሷ ጋር በማበር ሲገፋው፣ “በደሉን” ሲያገዝፍበት እያስተዋለ ግራ ቢያጋባው፣ “ከሰው አነስኩበት ወይ?” ብሎ “ተበደልኩ” ባይን ይጠይቃታል።
 የእሷ በደሉን ማግዘፍያና መፋለምያዋ ደግሞ “ቃል” ነው። “ሰም” የራቀው “ወርቅ” ለበስ ቃል። በእሱ ትፋለመዋለች፤ ከዛ ትረታዋለች። እሱም ይወድቃል። መረታትና መውደቁንም አይክድም። በእሱ መረታትና መውደቅ የተገኘውን “ወርቅ” ደግሞ ሌላው ይደምቅበታል።
ግን ከወደቀበት ተነስቶ፤ እሱም የአቅሙን፣ የሚችለውን የቃል ጦር ያምዘገዝጋል እንጂ በቀላሉ  አይረታም...
ዘንግተን ቃሉን
ማህተቡን ብናስረው ምንድነው
ተይ አፍሮ ይገባል
ፍቅር የሌለው፤
ማውጋት ይበጃል
በአክሱም መስቀል እምልልሻለሁ
ምህላውን ተይ
አጠገብሽ ሳለሁ።
 እጅ አይሰጥም። የቃል ጉልበቷን ተቋቁሞ ሙግቱን ይቀጥላል። የተረታበትን የቃሏን ግዘፍ አትሞግትበትም ብሎ በገመተው ሌላ ቃል ነስቶ ሊረታት ይፍጨረጨራል። የአማኝነቷን ልክ ሲፈታተን የእምነት መጽሐፏ የሚነግራትን ቃል (የይቅርታን ቃል) እየገላለጠ በመጥቀስ፣ ቃል ዘንግተው፣ እምነቱን በወጉ ሳይኖሩት ማህተብ የማሰርን “ከንቱነት” ያስታውሳታል።
 በዚህ መች ያበቃል...
 ልቡ በቁጣ የተንቀለቀለ ጸበኛን፣ ደምን በደም ካልመለስኩኝ ባይ ተበቃይን....ተበዳይን ከበዳይ፣ ቂመኛውን ከተቄመበት አስማምቶ፣ አቀዝቅዞና የጋለ መንፈሱን አርግቦ የሚመልሰውን “አፍሮ አይገባም” መስቀልን ለአማኝ ማንነቷ በገደምዳሜ እያስታወሰ፣ “አፍሮ አይገባም ፍቅር ለሌለው አፍሮ ይገባል” እንደማለት ያለ ሙግት ያነሳል።
 ስለ ቅያሜያቸው ሳያወጉ፣ በደሉን ይቅር ሳትል፣ ትርጉም የለሽ ምህላዋ ላይ የመትጋቷን ከንቱነት በእልህና በግላዊ እምነት ይፈትንባታል። ይሞግትባታል። “ቅኔ የበዛበትን ወርቅ አማርኛዋን” እያገኘ ሳይሆን አይቀርም በሚያሰኝ መልኩ ደፈርና ጠጠር ብሎ መሞገቱን በመቀጠል...
እግር ያደርሳል ከቤቱ ግምብ
ይቅርታ ግን ከልብ
መቅደስ ሰው በእጁ ከሰራው
የእርሱ ጥበብ ገላው።
ሲል ደፈር ባለ ፍልስፍና ለምህላ ጠዋት ማታ የምታቀናበትን ቦታ የእግዜሩ “ግምብ” ብሎ እየጠራ፤ በራሱ በእግዜሩ የተሰራው “ሰው” የተባለ ማንነት፣ ከማንኛውም ሰው ከሰራው ቁስ በላጭ መሆኑን አይነኬ ከተባለ ጉዳይ ጋር (ከመቅደስ) አነጻጽሮ ይገላልጣል።
 በመጨረሻም ባልተሰሰተ ንጽጽራዊ ዘይቤው፣ ከላይ እንደተነሳው “የሸማዋ ከልቧ መንጻት” አሁንም ይከነክነዋልና፤ በውሃ ከሚነጻው ሸማዋ ልቧ ስለምን አንሶ ለይቅርታ እንደሰነፈ፤ ምህረትን ነፍጋ በጨርቅ፣ በሸማ መበለጧን እየነገራት፤ ፈጣሪ በጥበብ የሰው ልጅን ሰላም፣ እፎይታና  በበዳይ ማንነት ውስጥ እንዳስቀመጠልን (ይቅር ስንል የሚገኘውን ሰላም ልብ ይሏል።)፣ ጥቂት የጥበብ ጠብታው ከባህር  ጥልቅ እንደመሆኗ መጠን... አንድ ይቅርታም ለዓለም ማብቃቃቱን  እየነገረና እያጠየቀ ዘፈኑን (ሙግቱን) ይቋጫል። እንዲህ እያለ...
ነጠላሽ የዋህ በውሃ ይነጣል
ልብሽ ግን ይቅርታ እንዴት ያጣል?
ላጠፋ ሰው ምህረት አሻፈረኝ ብለሽ
የለበሽው ሸማ በለጠሽ፤
አምላክ የሰጠውን መች ከሰው ወሰደው
ሰላምን በዳይ ጋር አስቀመጠው
ጥበቡ ጠብ ሲል ከባህር ይጠልቃል
አንድ ይቅርታ ለዓለም ይበቃል።
ነጠላችን፣ ሸማችን...የምንለብሰው ጨርቅ፤ ከልባችን፣ ከእኛነታችን የማይበልጥ ይሁን።
 አጥፍቶ ይቅርታን ለሚማጸን ሰው ምህረት ነፍገን፣ ከበዳይ የምናገኘውን ሰላም በገዛ እጃችን እንዳናጣ ይሁን። የይቅርታ ሰንበት ይሁንልን!



Saturday, 02 November 2024 12:54

የወቅቱ ጥቅስ

“የዘመኑ ጀግንነት ዲሞክራሲያዊነት እንጂ ማናቸውም የኃይል እርምጃ አይደለም፡፡ የሥልጣኔ ቆራጥነት በውይይትና በምክንያታዊ ሙግት መረታታት እንጂ እያደቡ መጠፋፋትና አንዱ ለአንዱ መቃብር መቆፈር አይደለም፡፡”

Page 5 of 739