Administrator
Tuesday, 02 September 2025 14:10
ለህዳሴው የደስታና የመልካም ምኞት ማስተላለፊያ ቁጥር ይፋ ተደረገ
የታላቁ ህዳሴ ግድብ ማስተባበሪያ ፕሮጀክት ጽህፈት ቤት ኃላፊ ዶ/ር አረጋዊ በርሄ እንደገለፁት፤ የግድቡ መጠናቀቅን ተከትሎ ህብረተሰቡ አጭር የደስታና የመልካም ምኞት መልእክቱን በ8120 በመጠቀም ማስተላለፍ የሚችልበት ፕሮጀክት ይፋ የተደረገ መሆኑን አስታውቀዋል።
«የትውልድ አሻራ - ዲጂታል የብስራት መልዕክትና ገቢ ማስገኛ ፕሮጀክት" የሚል ስያሜ የተሰጠው መሆኑንም ገልፀዋል።
ዓላማውም ህዝቡ ለግድቡ እውን መሆን ሲያደርግ የነበረው ርብርብና ተሳትፎ በተመለከተ ያለውን ስሜት፣ የድል ብስራትና ተስፋ በአጭር መልዕክት እንዲገልጽ የሚያችል መሆኑን ጠቅሰዋል።
መልዕክቱ አሻራውን ለታሪክ መዘክርነት እንዲያስቀመጥ ያለመ መሆኑንም ገልፀዋል።
መርሐግብሩ ከዛሬ ነሀሴ 27 ቀን 2017 ጀምሮ እስከ መስከረም 30 ቀን 2018 የሚተገበር መሆኑም ተነግሯል፡፡
ሁሉም ኢትዮጵያዊ የመልካም ምኞት መልዕክቱን በ8120 ላይ በመላክ፤ 1 ቁጥር "በህብረት ችለናል!" መልዕክት ሲጫን 5 ብር ድጋፍ፤ 2 ቁጥር “ህዳሴ ግድብ የብልጽግናችን አሻራ›› መልዕክት ሲጫን 10 ብር ድጋፍ፤ 3 ቁጥር “ግድባችን የአሸናፊነት ድል አክሊል” መልዕክት ሲጫን 15 ብር ድጋፍ፣ 4 ቁጥር ግድባችን እና የአባይ ዘመን ትውልድ የተጋድሎ ሰንደቅ” መልዕክት ሲጫን 100 ብር ድጋፍ እንዲሁም ላኪው የመረጠውን መልዕክት ሲልክ 20 ብር ብቻ ድጋፍ እንደሚደረግ ተገልጿል፡፡
Published in
ዜና
Tagged under
Tuesday, 02 September 2025 14:09
በሱዳን የመሬት መንሸራተት አደጋ ከ1ሺ በላይ ሰዎች ሞተዋል ተባለ
በሱዳን በደረሰው የመሬት መንሸራተት አደጋ ከ1ሺ በላይ ሰዎች መሞታቸውን ዓለማቀፍ መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል፡፡
ለተከታታይ ሰዓታት የጣለው ከባድ ዝናብ ያስከተለው የመሬት መንሸራተት አደጋ ሙሉ መንደር አጥፍቷል ነው የተባለው፡፡
ከተማይቱን የሚያስተዳድረው ሱዳን ሊበሬሽን ፍሮንት የተባለው ታጣቂ ቡድን ባወጣው መግለጫ፤ ማራ የተሰኘው ተራራ አካባቢ የደረሰው አደጋ በቀዳሚው ቀናት በከተማይቱ በጣለው ከባድ ዝናብ ምክንያት እንደተከሰተ አመልክቷል።
በአደጋው ከተማይቱ ሙሉ ለሙሉ መውደሟንና 1 ሺህ ሰዎች ሕይወታቸው ማለፉን ያመለከተው መግለጫው፤ በሕይወት የተረፈው አንድ ሰው ብቻ እንደሆነም ጠቅሷል።
Published in
ዜና
Tagged under
Tuesday, 02 September 2025 14:08
ሩሲያና ቻይና "ታሪካዊ" የተባለ የኃይል ዘርፍ ጥምረት ፈጠሩ
አዲሱ የሳይቤሪያ 2 የኃይል ማስተላለፊያ መስመር ፕሮጀክት ወደ ሥራ ሊገባ ነው።
ይህን ተከትሎ በሥራ ላይ ካለው የሳይቤሪያ የኃይል ማስተላለፊያ መስመርና እየተገነባ ባለው የሩቅ ምስራቅ መስመር የኃይል አቅርቦቶች ይጨምራሉ።
ሁሉም ፕሮጀክቶች ወደ ሥራ ሲገቡ ከሩሲያ ወደ ቻይና በኃይል ማስተላለፊያ የሚገባው የጋዝ አቅርቦት መጠን 106 ቢሊዮን ኪዩቢክ ሜትር ይደርሳል።
ይህም ሩሲያ እያደገ ላለው የእስያ ኢኮኖሚ ቁልፍ የኃይል አጋርነት ሚናዋን የሚያጠናክርና የወጪ ንግዷን አማራጭ የሚያሰፋው እንደሚሆን ስፑትኒክ ዘግቧል።
Published in
ዜና
Tagged under
Tuesday, 02 September 2025 14:02
የሶማሌላንድ ፕሬዚዳንት ለኢትዮጵያዊያን የተለየ ጥበቃ እንዲደረግ አዘዙ
የሶማሌላንድ ፕሬዚዳንት አብዲራህማን አብዲላሂ፣ የግዛቲቷ ጸጥታ ኃይሎች ለኢትዮጵያዊያን የተለየ ጥበቃ እንዲያደርጉ ትዕዛዝ ማስተላለፋቸውን የግዛቲቷ የዜና ምንጮች ዘግበዋል።
ፕሬዝደንቱ ይህን ትዕዛዝ የሠጡት፣ ሰሞኑን ሐርጌሳ ውስጥ በአንድ ኢትዮጵያዊ ወጣት ላይ የተወሰኑ ግለሰቦች ማስፈራሪያና ዛቻ ሲያደርሱ የሚያሳይ ተንቀሳቃሽ ምስል መሠራጨቱን ተከትሎ ነው።
ፕሬዝዳንቱ፣ ሶማሌላንድ ከኢትዮጵያ ጋር ሥር የሰደደ ግንኙነት እንዳላት መናገራቸውን ዘገባዎቹ ጠቅሰዋል።
የፕሬዝዳንቱን ትዕዛዝ ተከትሎ፣ ጸጥታ ኃይሎች አብዲሪሳቅ ሙሴ የተባለ በቲክቶክ ላይ በተለይ የኦሮሞ ብሄር ተወላጆች የጥቃት ሰለባ እንዲኾኑ ሲቀሰቅስ ነበር የተባለ ግለሰብ በቁጥጥር ስር አውለዋል መባሉን ዋዜማ ዘግባለች።
Published in
ዜና
Tagged under
Tuesday, 02 September 2025 13:56
10 ተጨማሪ ግዙፍ ግድቦች በአባይ ወንዝ ላይ ይገነባሉ
በአባይ ወንዝ ላይ በቀጣይ ዓመታት የሚገነቡ 10 ግድቦች ዲዛይን ተዘጋጅቶ መጠናቀቁን ጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ ተናግረዋል።
የግድቦቹን ዲዛይንና ጥናት በዋናነት አሁን የህዳሴውን ግድብ ከገነባው ሳሊኒ ዊቢውልት ካምፓኒ ጋር የተዘጋጀ መሆኑንና በቀጣይ ከ10 እስከ 15 ዓመታት ውስጥ ሁሉንም ግድቦች ለመገንባት መታሰቡን ጠ/ሚኒስትሩ አስታውቀዋል፡፡
Published in
ዜና
Tagged under
Thursday, 28 August 2025 19:49
አለሽኝ ባወቀ በዳይመንድ ሊግ አሸነፈች!!
በስዊዘርላንድ ዙሪክ የ2025 ዳይመንድ ሊግ የመጨረሻ ዙር ውድድር እየተከናወነ ሲሆን፤ በሴቶች 3000 ሜትር የተወዳደረችው አለሽኝ ባወቀ አሸናፊ ሆናለች፡፡
ወጣቷ አትሌት ርቀቱን ለማጠናቀቅ 8:40.56 ሰዓት ፈጅቶባታል።
የቴሌግራም ቻናልችንን በመቀላቀል የአዲስ አድማስን መረጃ ይከታተሉ…
Published in
ስፖርት አድማስ
Tagged under
Thursday, 28 August 2025 19:04
የ2.5 ቢ. ዶላር ፕሮጀክት ይፋ ተደረገ
• በዓመት 3 ሚ. ሜትሪክ ቶን የአፈር ማዳበሪያ ለማምረት ያስችላል
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ፣ በኢትዮጵያ በዓመት እስከ 3 ሚሊዮን ሜትሪክ ቶን የአፈር ማዳበሪያ ለማምረት የሚያስችል ፕሮጀክት ይፋ አደረጉ፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መረጃ፤ ዛሬ በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግና በዳንጎቴ ግሩፕ መካከል የማዳበሪያ ማምረቻ ኮምፕሌክስ የድርሻ ስምምነት ፈርመናል ብለዋል።
ፕሮጀክቱ 2.5 ቢሊዮን ዶላር ኢንቨስትመንት የሚፈስበት መሆኑን የገለፁት ጠ/ሚኒስትሩ፤ በአመት እስከ ሶስት ሚሊዮን ሜትሪክ ቶን የአፈር ማዳበሪያ የሚያመርት መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡ ይኽም ኢትዮጵያን ከዓለም ግንባር ቀደም አምራቾች አንዷ ያደርጋታል ብለዋል፡፡
ፕሮጀክቱ ለዘመናት ለተፈተኑት ገበሬዎቻችን አስተማማኝ የማዳበሪያ አቅርቦት ያረጋግጣል ሲሉም ጠ/ሚኒስትሩ አክለዋል።
የቴሌግራም ቻናልችንን በመቀላቀል የአዲስ አድማስን መረጃ ይከታተሉ…
Published in
ዜና
Tagged under
Thursday, 28 August 2025 09:28
ከነብር ጋር ታግለው ልጆቻቸውን የታደጉት አባት
ነገሩ የተከሰተው ባለፈው ሳምንት በምስራቅ ሀራርጌ ጉርሱም ወረዳ ጎባ ቀበሌ ነው፡፡ አቶ ሙስጠፋ ረሺድ እንደ ሁልጊዜው በሰርክ ተግባራቸው ላይ ውለው ደክሟቸው ከልጆቻቸውና ባለቤታቸው ጋር ቤታቸው ውስጥ ነበሩ፡፡
የሁለት ታዳጊ ልጆች አባት የሆኑት ሙስጠፋ፣ የገጠማቸውን ለዶይቼ ቬለ እንዲህ ሲሉ ያስረዳሉ፤
“ያጋጠመኝ ነገር ያው ፈጣሪ ኑር ካለ ያኖርሃል ነው እንጂ፣ ህይወትን የሚያስቀጥል ነገር እንኳ አልነበረም፡፡ አስፈሪው የዱር እንስሳ ነብር ከምሽቱ በግምት 1፡30 አካባቢ ከቤተሰቦቼ ጋር ቤት ውስጥ እያለን ነው ከተፍ ብሎ ወደ ቤት ዘልቆ የገባብን፡፡ ምንም ዝግጅት አላደረግንም፡፡ ስታየው የሚስፈራ ቁጡ የዱር እንስሳ ነው፡፡ በዚያ ላይ በእርሻ ማሳ ውስጥ ስለፋ ነው የዋልኩኝ፡፡ ልክ እግሮቼን ታጥቤ አረፍ ስል ነው ይህ የሆነው፡፡ በጀርባዬ የወንድሜ መኖሪያ ቤት አለ፡፡ ነብሩ ዘለል አለና ከፍ ያለች ቤት ውስጥ ባለች አልጋ ነገር ላይ ቁጭ አለ፡፡ ነብር ልጆች ያጠቃል ስለሚባል ልጆቼን እንዳያጠቃብኝ ስጋት ገባኝ፡፡ እናም የሆነ ነገር ማድረግ አለብኝ አልኩ፡፡ ያገኘሁትን ዱላ ነገር አንስቼ ላስወጣው ስል ግን ዘሎ ተከመረብኝ” ብለዋል፡፡
በመኖሪያ ቤታቸው ውስጥ ከገባው ነብር ጋር ትግል የገጠሙት አባት ሕይወታቸው በተዓምር ተርፏል።
ልጆቻቸውንና ባለቤታቸውን ቢያተርፉም፣ ከፍተኛ ጉዳት እንደደረሰባቸው ለዶይቼ ቬለ ተናግረዋል።
Published in
አግራሞት
Tagged under
Thursday, 28 August 2025 09:27
ጋዜጠኛ ሙሉጌታ ጌቱ ሥራዎቹን ከአንጋፋ ፀሐፍት ጋር በማጣመር "መባያ " The Golden Mean በሚል ያስመርቃል።
Published in
ኪነ-ጥበባዊ ዜና
Tagged under
Thursday, 28 August 2025 07:04
የአባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ የዕረፍት መታሰቢያ ለአንድ ዓመት ሊዘከር ነው
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ከፍተኛ ቦታ ከሚሰጣቸው ሊቃውንት አንዱ የሆኑት አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ 600ኛ ዓመት የዕረፍት መታሰቢያ ለአንድ ዓመት ሊዘከር ነው። ይህን ምክንያት በማድረግ ለቀጣይ አንድ ዓመት የሚቆይ ልዩ የፕሮጀክት ማስጀመሪያ መርሐ ግብር በትናንትናው ዕለት ተካሂዷል።
የፕሮጀክቱ ማስጀመሪያ ፕሮግራም በአዲስ አበባ፣ ዮድ አቢሲንያ የባሕል ምግብ አዳራሽ ውስጥ የተካሄደ ሲሆን፣ በዝግጅቱ ላይ የተለያዩ ምሁራንና መምሕራን ተገኝተዋል። መምሕር ዳንኤል ገ/ስላሴ ስለ መጽሐፈ ምስጢር፣ መጋቢ ሐዲስ ሮዳስ ታደሰ (ዶ/ር) ስለ መጽሐፈ ሰዓታት እና መምሕር ዲያቆን ዘላለም ታዬ ደግሞ ስለ ኆኅተ ብርሃን የሊቁ ድርሳናት አጭር የዳሰሳ ጽሑፍ አቅርበዋል።
ይህ ፕሮጀክት የሊቁን ሕይወት፣ ትምሕርቶች እና በቤተ ክርስቲያን ታሪክ ውስጥ ያላቸውን አስተዋጽዖ ዓመቱን በሙሉ በስፋት ለማስታወስ ታስቦ የተዘጋጀ መሆኑን በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን፣ ማኀበረ ጽዮን ጠቅላላ ማሕበር አመራሮች በመርሐግብሩ ላይ ገልጸዋል። እንዲሁም ፕሮጀክቱ የአባ ጊዮርጊስን ማንነት፣ በስማቸው የተሰየመውን የጋስጫ ገዳማቸውን ታሪክ፣ የሊቁን አበርክቶ እና የወደፊት ስትራቴጂያዊ ዕቅዶችን በተለያዩ ዝግጅቶችና ፕሮግራሞች በአገር ውስጥና በውጭ አገራት ከተሞች ዓመቱን በሙሉ ለማስተዋወቅ መታቀዱን ተጠቅሷል።
“ዓምደ ሐይማኖት”፣ “ኢትዮጵያዊው ቄርሎስ” እና “ዳግማዊው ዮሐንስ አፈወርቅ” በሚሉ ስያሜዎች የሚታወቁት አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ፣ በ1357 ዓ.ም. በቀድሞው ወሎ ክፍለ አገር፣ "ሸግላ" በተባለ ቦታ እንደተወለዱ ይነገራል።




See insights and ads
Boost post
All reactions:
99
Published in
ዜና
Tagged under

