Administrator
Thursday, 31 July 2025 11:32
የኢፊዴሪ ባሕር ኃይል አባላትና የመከላከያ የክብር አባላት ቢሾፍቱ በሚገኘው የመርከበኞች ማሰልጠኛ ማዕከል ግቢ ውስጥ በአንድ ጀምበር የችግኝ ተከላ ላይ፦
Published in
ዜና
Tagged under
Thursday, 31 July 2025 11:31
ባለ 20 የክብር ዶክትሬቶች ንጉሥ!!
• በአፍሪካ ብቸኛው ተወዳዳሪያቸው፣ ኔልሰን ማንዴላ ናቸው
1- ግንቦት 20 ቀን 1946 ዓ.ም ከሐዋርድ ዩኒቨርሲቲ በሕግ የክብር ዶክተሬት ድግሪ
2- ግንቦት 25 ቀን 1946 ዓ.ም ከኮሎምቢያ ዩኒቨርሲቲ በሕግ
3- ግንቦት 28 ቀን 1946 ዓ.ም ከሞንትሪያል ዩኒቨርሲቲ የክብር ዶክተሬት
4- ግንቦት 30 ቀን 1946 ዓ.ም ከሚቺጋን ዩኒቨርሲቲ የሕግ የክብር ዶክተሬት ድግሪ
5- ግንቦት 1946 ዓ.ም ከመክጊል ዩኒቨርሲቲ የሕግ የክብር ዶክተሬት ድግሪ
6- ሐምሌ 16 ቀን 1946 ዓ.ም ከኬምብሪጅ ዩኒቨርሲቲ የሕግ የክብር ዶክተሬት ድግሪ
7- ሐምሌ 29 ቀን 1946 ዓ.ም ከአቴና ብሔራዊና ካፓዲስትሪን ዩኒቨርሲቲ በፍልስፍና የክብር ዶክተሬት ድግሪ
8- 1946 ዓ.ም አትላንታ ጆርጂያ ከሚገኘው ሞርሐውስ ኮሌጅ የሕግ የክብር ዶክተሬት ድግሪ
9- ጥቅምት 10 ቀን 1947 ዓ.ም ከኦክስፎርድ ዩኒቨርሲቲ የሕግ የክብር ዶክተሬት ድግሪ
10- ከቦን ዩኒቨርሲቲ በእርሻ የክብር ዶክተሬት ድግሪ
11- ሕዳር 4 ቀን 19 49 ዓ.ም ከባናራስ ሂንዱ ዩኒቨርሲቲ የሥነ-ጽሑፍ ዶክተሬት ድግሪ
12- ሐምሌ 5 ቀን 1951 ዓ.ም ከሞስኮ ዩኒቨርሲቲ በሕግ የክብር ዶክተሬት ድግሪ
13- ሐምሌ 8 ቀን 1951 ዓ.ም ከፕራግ ከቻርልስ ዩኒቨርሲቲ በሕግ የዶክተሬት ድግሪ
14- ህዳር 27 ቀን 1952 ዓም ከላይቤሪያ ዩኒቨርሲቲ በሕግ የክብር ዶክተሬት ድግሪ
15- መስከረም 22 ቀን 1956 ዓ.ም ከጆርጅ ታውን ዩኒቨርሲቲ በሥነ-ጽሑፍ የክብር ዶክተሬት ድግሪ
16- መስከረም 18 ቀን 1957 ዓ.ም ከሩማኒያ ከቡካሬስት ዩኒቨርሲቲ የሕግ የክብር ዶክተሬት ድግሪ
17- መስከረም 30 ቀን 1959 ዓ.ም ከሊባኖስ ዩኒቨርሲቲ የሀገሪቱ ፕሬዘዳንት ቻርልስ ሄሉ ባሉበት ክብር ዶክትሬት
18- ሚያዚያ 24 ቀን 1960 ዓ.ም ከታይላንድ ከተማስት ዩኒቨርሲቲ የህግ የክብር ዶክተሬት ድግሪ
19- ግንቦት 9 ቀን 1960 ዓም ከምዕራብ አውስትራሊያ ዩኒቨርሲቲ በሕግ የክብር ዶክተሬት ድግሪ
20- ግንቦት 13 ቀን 1960 ዓም ከደቡብ ኮሪያ ዩኒቨርሲቲ የህግ ዶክሬት ድግሪ
***********
[ በአፍሪካ ብቸኛው ተወዳዳሪያቸው፣ ኔልሰን ማንዴላ ናቸው። አልበርት ኤነስታይን በአጠቃላይ 17 የክብር ዶክትሬቶች ያገኘ ሲሆን፣ ከፍተኛው ቁጥር 32 በዴቪድ አቴንበርግ የተያዘ ነው። ]
( የመረጃ ምንጭ ስብስብ፤ ከአጼ ኃ/ሥላሴ የታሪክ መጻሕፍት )
ጥንቅር ፦ ጥበቡ በለጠ
Published in
ህብረተሰብ
Tagged under
Wednesday, 30 July 2025 00:00
በመቀሌ ህዝባዊ እምቢተኝነት እንዲቀጣጠል ጥሪ ቀረበ
ወጣቶችና ሰራዊቱ ትግሉን እንዲቀላቀሉ ተጠይቀዋል
ራሱን "የትግራይ የሰላም ሃይል - ነፃ መሬት ትግራይ (T.P.F)" ብሎ የሚጠራውና በመቀሌ ከተማ ውስጥ ህቡእ እንቅስቃሴ እያደረገ መሆኑን የገለጸው ቡድን፣ ለመላው የመቀሌ ወጣቶችና ለትግራይ ሰራዊት አባላት አስቸኳይ ጥሪ አቅርቧል።
ቡድኑ ያወጣው መግለጫ ሙሉ ቃል ምን ይላል ?
እኛ በመቀሌ ከተማ ደጀን አካባቢ የምንገኝ የትግራይ የሰላም ሃይል - ነፃ መሬት ትግራይ (T.P.F) የውስጥ ህቡእ መዋቅር አባላት ነን። የትግራይ የሰላም ሃይል በቅርብ ጊዜ ወደ ወሳኝ ከተሞች እንቅስቃሴ ለመጀመር ዝግጅቱንና አቋሙን አስተካክሎ ያጠናቀቀ በመሆኑ፣ የመቀሌ ከተማ ሲቪል ወጣት በሙሉ ከከተማው የውስጥ ህቡእ መዋቅር ጋር በመናበብ በሚደረገው (ህዝባዊ እምቢተኝነት) ጥሪ ላይ ዋና ተዋናይ በመሆን አካባቢህን ረመጥ አድርገው።
በቅርቡ ከሻዕቢያ ጋር በመተባበር ጦርነት ለመጫርና ሰላማዊ የሆኑትን የደቡብ ምስራቅና የደቡብ ዞኖችን እንደምክንያት በመጠቀም ሊጀምረው ያሰበው ወታደራዊ ዘመቻ እንዳይፈጸም፣ ንብረት እንዳይዘርፍና ግፋ (ግዳጅ ውትድርና) እንዳይጀምር፣ ተደራጅተህ ከህዝብህ ጋር በመሆን እምቢተኝነትህን አሳይ። ከተማህን አድን!
በሰራዊት ውስጥ ያለህ፣ ከሰራዊት የወጣህ እንዲሁም አሁን በትግራይ ሰራዊት ውስጥ ያለህ ሁሉ፣ ከኮር በላይ ያለው አመራር ገፍቶ ወደማትፈልገው ጦርነት እንዳያስገባህና ወደ ሳዋ ሊወስድህ ዝግጅቱን ስላጠናቀቀ፣ በፍጥነት ባሉ አማራጭ መንገዶች ሁሉ ውሳኔ ወስደህ ጀግናውን የነፃ መሬት ሰራዊት ተቀላቀል።
ድል ለህዝባዊው የትግራይ ነፃ መሬት ሰራዊት!
22/11/2017 ዓ.ም
‛‛ከትግራይ የሰላም ሃይል (T.P.F) የከተማ ውስጥ ህቡእ መዋቅር የተሰጠ መግለጫ


Published in
ዜና
Tagged under
Thursday, 31 July 2025 06:20
የለውዝ (ኦቾሎኒ) የጤና በረከቶች !!
ለውዝ ወይም ኦቾሎኒ ከ1,6ዐዐ ዓመት በፊት በፔሩ የተገኘ እንደሆነ ይነገራል፡፡ ከዛም በአሜሪካና በአውሮፓ ሀገራት ላይ ተሠራጭቶ በዓለም ታዋቂ ሆኗል፡፡ ለውዝ ከምግብነት ባሻገር ለጤናም ሰፊ ጠቀሜታዎች እንዳሉት ይነገራል፡፡ እነዚህን ጠቀሜታዎች በዝርዝር አስቀምጠናል:: እነሆ፡-
1. በተለምዶ ከሚባለው ጋር በተዛመደ መልኩ በዕርግጥም ለውዝ ለተዋልዶ ስርዓት ጤንነት ተመራጭ ነው፡፡ በተለይም ከእርግዝና በፊትና በዕርግዝና ወቅት ለውዝ መመገብ በውስጡ የሚገኘው ፎሊክ አሲድ በእርግዝና ወቅት በጽንሱ ዕድገት ላይ ሊያጋጥም የሚችለውን ችግር 70 በመቶ ያህል ያስወግዳል፡፡
2. በደም ውስጥ ያለውን የስኳር መጠን ያስተካክላል፤ በለውዝ ውስጥ በከፍተኛ መጠን የሚገኘው ማንጋኒዝ ለስብና ለካርቦሀይድሬት መፈጨት፣ ለካልሲየም በሰውነታችን ህዋሳት መዋሀድና በደም ውስጥ ያለው የስኳር መጠን የተስተካከለ እንዲሆን ያስችላል፡፡
3. በሰውነታችን ውስጥ የሚገኘው ጥሩው ኮሌስትሮል እንዲጨምርና መጥፎው የኮሌስትሮል ዓይነት ደግሞ እንዲቀንስ ያደርጋል፡፡ በለውዝ ውስጥ የሚገኘው የመዳብ ማዕድን ሰውነታችን በልብ ህመም እንዳይጠቃ ይከላከላል፡፡
4. የሐሞት ጠጠር እንዳይከሰትና የሐሞት ከረጢት ጤናን ያስጠብቃል፡፡
5. ድብርትን ይከላከላል፡፡
6. የማስታወስ ችሎታን ይጨምራል፡፡
7. የልብ ህመም፣ ካንሰር፣ የነርቭ ህመሞች እንዲሁም ከቫይረስና ከፈንገስ ጋር ተያያዥነት ያላቸው በሽታዎችን ይከላከላል፡፡
8. የአእምሮ ብቃትን ከመጨመርም በተጨማሪ እንደ ፓርኪንሰንና አልዛይመር ዓይነት በሽታዎች እንዳይከሰቱ ይረዳል፡፡
9. በካንሰር መጠቃትን ይቀንሳል፡፡
10. ሐይል ሰጪ ከመሆኑም በላይ ጥቂት በልተው ለረጅም ሰዓታት እንዳይርቦት ስለሚያደርግ የሰውነት ክብደትን ለመቀነስ ይረዳል፡፡
11. በእርግዝና ወቅት ለውዝ መመገብ የሚወለዱ ህጻናት እንደ አስም በመሳሰሉት በሽታዎች እንዳይጠቁ ያደርጋል፡፡
12. ለታዳጊዎች የአካል ግንባታ ለውዝ እጅጉን ተመራጭ ነው፡፡
13. በሰውነታችን ውስጥ ያሉ የተለያዩ መርዛማ ንጥረ ነገሮችን ያስወግዳል፡፡
14. የጸጉር ስሮችን በማጠንከር ለጸጉር ጤንነት ተመራጭ ነው፡፡
15. ስትሮክ የሚሰኘውን ወደ አንጎል በሚሄደው የደም ፍሰት መዛባት ሳቢያ የሚከሰተውን የአንጎል ላይ አደጋ ይከላከላል።
16. ፍሪ ራዲካል በተሰኙት ሞሎክዩሎች ሳቢያ በሰውነት ላይ ሊደርስ የሚችለውን አደጋ ይቀንሳል።
17. እብጠትና ሌሎችን ከቆዳ ጋር የተያያዙ ህመሞችን ይከላከላል። ቆዳን ከውስጥ በማለስለስ የተለያዩ የቆዳ ችግሮችን ይከላከላል።
18. ለውዝ በተለያዩ የቫይታሚን ዓይነቶች የበለጸገ ነው።
19. ለውዝ በፖታሲየም፣ ማንጋኒዝ፣ መዳብ፣ ካልሲየም፣ ማግኒዚየም፣ ብረት፣ ሴሬኒየም እና ዚንክ በመሳሰሉት ማዕድናት የበለጸገ ነው።
(Tigray Tribune)
የቴሌግራም ቻናልችንን በመቀላቀል የአዲስ አድማስን መረጃ ይከታተሉ…
Published in
ዋናው ጤና
Tagged under
Thursday, 31 July 2025 05:22
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በአንድ ጀምበር 700 ሚሊዮን ችግኞችን የመትከል መርሐ-ግብር በይፋ አስጀመሩ
Published in
ዜና
Tagged under
Thursday, 31 July 2025 05:17
"የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ተሟጋቾች ማዕከል" ዋና ዳይሬክተር ከኃላፊነታቸው ለቀቁ
"ዛቻዎች፣ ማስፈራሪያዎችና ትንኮሳዎች ሳስተናግድ ቆይቻለሁ"
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ተሟጋቾች ማዕከል ዋና ዳይሬክተር አቶ ያሬድ ኃይለማርያም ከሀላፊነታቸው መልቀቃቸውን በዛሬው ዕለት ባወጡት መግለጫ አስታውቀዋል፡፡
ላለፉት አራት ዓመታት ማዕከሉን በሀላፊነት የመሩት አቶ ያሬድ፤ በገጠማቸው አስገዳጅ ሁኔታ ከሐምሌ 25 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ ከሃላፊነታቸውና ከድርጅቱ መልቀቃቸውን አሳውቀዋል፡፡
ማዕከሉ አገሪቱ ውስጥ የሚፈጸሙ የመብት ጥሰቶችን፤ በተለይም በጋዜጠኞች፣ በሲቪል ማህበረሰብ አባላትና በሰብአዊ መብት ተሟጋቾች ላይ የሚፈጸሙ የመብት ጥሰቶችን በማጋለጥና መብታቸው እንዲከበር በአደባባይ በመሟገት ግንባር ቀደም ተቋም መሆኑን በመግለጫቸው ጠቁመዋል፡፡
ለዚህም ከድርጅቱ ጠንካራ ሠራተኞችና የቦርድ አባላት ጋር በመሆን ቁልፍ ሚና ሲጫወቱ መቆየታቸውን ገልፀዋል።
"ይሁን እንጅ ከአንድ አመት ወዲህ በሚዲያዎች ላይ እየቀረብኩ በሀገሪቱ ውስጥ ስለሚታዩ የሰብአዊ መብት ጥሰቶች በምሰጣቸው መግለጫዎችና ማብራሪያዎች፤ እንዲሁም በማህበራዊ ድረ ገጾች ላይ የሰብአዊ መብቶች አያያዝን አስመልክቶ የማካፍላቸው ሃሳቦችና የምሰነዝራቸው የሰሉ ትችቶች፣ በአገዛዝ ሥርአቱ ዘንድ በጥሩ ሁኔታ እየታዩ ባለመምጣታቸው፣ በተለያዩ አቅጣጫዎች የተለያዩ አይነት ጫናዎችን ሳስተናግድ ቆይቻለሁ፡፡» ብለዋል፤ በመግለጫቸው።
አቶ ያሬድ አያይዘውም፤ «የተለያዩ ዛቻዎች፣ ማስፈራሪያዎችና ትንኮሳዎች በጸጥታ አካላት በኩል ሲፈጸሙ እንዲሁም በተንቀሳቃሽ ስልኮቼ ያልተለመዱ ጥሪዎችን ሳስተናግድ ያለውን ግልፅ ስጋት ችላ በማለት በሥራዬ ላይ አተኩሬ ቆይቻለሁ፡፡» ሲሉ አብራርተዋል።
«ሆኖም በዚህ ሁኔታ ውስጥ በነጻነት ለመንቀሳቀስም ሆነ የተቀበልኩትን የሥራ ሃላፊነት በብቃት ለማከናወን የማልችልበት ደረጃ ላይ መድረሴን ስላረጋገጥኩ፣ በተጓዳኝም በሥራ ጫና ሳቢያ ችላ ያልኳቸው የግል የጤና ጉዳዮችም ስለነበሩ እነዚህን ምክንያቶች በመጥቀስ ከወራት በፊት ለድርጅቱ ቦርድ የመልቀቂያ ጥያቄዬ አቅርቤ በምትኬ ሰው እንዲፈልጉ አሳውቄያለሁ፡» በማለት ገልፀዋል።
ስለሆነም ይህ መግለጫ ከወጣበት ከሀምሌ 23 ቀን 2017 ጀምሮ በማናቸውም መንገድ የሚያካፍሉት ሀሳብ የግላቸው እንጂ የማዕከሉ አለመሆኑን አቶ ያሬድ ኃይለማርያም በመግለጫቸው አስታውቀዋል፡፡
የቴሌግራም ቻናልችንን በመቀላቀል የአዲስ አድማስን መረጃ ይከታተሉ…
Published in
ዜና
Tagged under
Thursday, 31 July 2025 05:14
የስምረት ፓርቲ ፅ/ቤት በታጣቂዎች ተዘረፈ - ምንጮች
በአቶ ጌታቸው ረዳ የሚመራው ስምረት ፓርቲ፣ ባለፈው ሳምንት በመቀሌ ከተማ የከፈተው ዋና ጽ/ቤቱ በታጣቂዎች መዘረፉ ተሰማ፡፡
ትናንት ማታ 4:45 ገደማ ማንታቸው ያልታወቀ ታጣቂዎች ዘበኞችን አስፈራርተው ወደ ጽ/ቤቱ በመግባት የፓርቲውን ንብረቶች መዝረፋቸውን የጠቆሙት ምንጮች፤ የቀሩትን ሰባብረውና ወረቀቶችን ቀዳደው ከስራ ውጪ ማድረጋቸውን አመልክተዋል፡፡፡
ፓርቲው በቅርቡ በመቀሌ በከፈተው ዋና ጽ/ቤቱ ሊሰጥ የነበረውን ጋዜጣዊ መግለጫ ባልታወቀ ምክንያት ላልተወሰነ ጊዜ ማራዘሙ የሚታወስ ነው።
የቴሌግራም ቻናልችንን በመቀላቀል የአዲስ አድማስን መረጃ ይከታተሉ…
Published in
ዜና
Tagged under
Thursday, 31 July 2025 05:08
ኢትዮጵያ ቡናን ለውጭ ገበያ በማቅረብ ከአፍሪካ መሪ ናት - ግብርና ሚ/ር
ዘንድሮ ከቡና የውጭ ገበያ 2.6 ቢሊየን ዶላር ተገኝቷል
የግብርና ሚኒስትሩ ግርማ አመንቴ ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ የቡና ገበያ ላይ ያላትን ድርሻ ለማስጠበቅ ጥራት ያለው ቡናን በስፋት የማምረት ሥራ እየሠራች እንደምትገኝ ተናግረዋል፡፡
ሚኒስትሩ ይህን የተናገሩት የአፍሪካን የቡና እሴት ሰንሰለት ሽግግር ለማሳደግ ያለመ የምክክር መድረክ ላይ መሆኑን ስፑትኒክ ዘግቧል፡፡
በአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብር 8.5 ቢሊዮን የቡና ችግኞች መተከላቸውንም የግብርና ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል፡፡
የግብርና ሚኒስትሩ የቡና ምርታማነትን ለማሳደግ ኢትዮጵያ እያከናወነቻቸው የሚገኙ ተግባራትን ዘርዝረዋል፦
*በስድስት ዓመታት የቡና ምርታማነት ከ500 ሺህ ወደ 1.2 ሚሊየን ሜትሪክ ቶን አድጓል፣
*በዚህ ዓመት ቡናን ለውጭ ገበያ በማቅረብ 2.6 ቢሊየን ዶላር ተገኝቷል፣
*የሄክታር ምርታማነትም ከ0.6 ሜትሪክ ቶን ወደ 0.9 ሜትሪክ ቶን ከፍ ብሏል፣
*ለውጭ ገበያ የሚቀርብ የቡና መጠንም ከ469 ሺህ ሜትሪክ ቶን በላይ ደርሷል፣
ሚኒስትሩ ግርማ አመንቴ፤ ኢትዮጵያ ቡናን ለውጭ ገበያ በማቅረብ ከአፍሪካ መሪ መሆኗንም እንደገለፁ የሀገር ውስጥ ሚዲያ ዘግቧል፡፡
የቴሌግራም ቻናልችንን በመቀላቀል የአዲስ አድማስን መረጃ ይከታተሉ…



Published in
ዜና
Tagged under
Tuesday, 29 July 2025 00:00
ብሔራዊ ቡድኑ ከአሜሪካው ጉዞ በፊት!
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ወደ አሜሪካ ከማምራቱ በፊት የአዲስ አበባ ዝግጅቱን በዛሬው ዕለት አገባዷል።
ብሔራዊ ቡድኑ ዛሬ ከስሪ ፖይንት አካዳሚ ጋር የልምምድ ጨዋታ ያከናወነ ሲሆን፤ በዚህም 1-0 ማሸነፍ ችሏል።
31 አባላትን የያዘው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ልዑክ፣ ዛሬ ምሽት 4:50 ከአዲስ አበባ በመነሳት በሮም በኩል ትራንዚት አድርጎ ረቡዕ በኢትዮጵያ ሰዓት አቆጣጠር ምሽት 1:00 ገደማ አሜሪካ እንደሚደርስ ከኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡
Published in
ስፖርት አድማስ
Tagged under
Tuesday, 29 July 2025 00:00
ሩሲያ በጦርነቱ ሳቢያ ልጆች ለሚወልዱ ማበረታቻ ክፍያ ጀምራለች
የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች ጭምር ልጅ እንዲወልዱ ይበረታታሉ
ለነፍሰጡሮችና ልጅ ለሚያሳድጉ ታዳጊዎች 1260 ዶላር ይከፈላቸዋል
በአገረ ሩሲያ አዲስና አወዛጋቢ የሆነ የስነ-ህዝብ ማስፋፊያ መርሃ ግብር መጀመሩ ተሰምቷል፡፡
ሩሲያ ይህን አዲስ መርሃ ግብር የጀመረችው ከዩክሬን ጋር ከሁለት ዓመት በላይ ባደረገችው ጦርነት ሳቢያ አስደንጋጭ የወሊድ ምጣኔ መቀነስና የህዝብ ብዛት መመናመን ስለገጠማት ነው ተብሏል፡፡
በአዲሱ የሥነ ህዝብ ማስፋፊያ መርሃ ግብር መሰረት ታዲያ ነፍሰጡር ለሆኑና ልጆቻቸውን ለሚያሳድጉ ታዳጊዎች (የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎችን ጨምሮ) 1260 ዶላር ወይም 100,000 ሩብል ክፍያ ጀምራለች ተብሏል - ማበረታቻ መሆኑ ነው፡፡
ይህ ማበረታቻ ባለፉት ጥቂት ወራት ውስጥ በ10 የሩሲያ ግዛቶች ውስጥ መተግበሩ ተነግሯል፡፡
ከዚህ ቀደም ለአዋቂ ሴቶች ብቻ ሲሰጥ የቆየው ይህ ማበረታቻ፣ አሁን የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎችን ሳይቀር ልጅ እንዲወልዱ ለማበረታታት ተብሎ ተዘርግቷል ነው የተባለው።
ጉዳዩ "የሀገር ህልውና" በመሆኑ ሴቶች እስከ ስምንት ልጆች ድረስ እንዲወልዱ እንደሚበረታቱም ተገልጿል።
በሩሲያ ብዙ ልጆች የወለዱ ቤተሰቦች የገንዘብና የግብር እፎይታ ድጋፎች እንደሚደረግላቸውም ታውቋል፡፡
**
የጦርነት ጣጣ ብለን እንለፈው ይሆን?
የቴሌግራም ቻናልችንን በመቀላቀል የአዲስ አድማስን መረጃ ይከታተሉ…
Published in
ዜና
Tagged under





