Administrator

Administrator

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት በቀድሞ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዝደንት ተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጂ ኡመር ኢድሪስ ህልፈት የተሰማውን ኀዘን ገልጿል፡፡
ምክር ቤቱ ባስተላለፈው የሀዘን መግለጫ፤ የሀገራችን ዋርካ እና የሁሉም አባት የነበሩት ተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጂ ኡመር ኢድሪስ ባጋጠማቸው ህመም በህክምና ሲረዱ ቆይተው ወደ አኼራ ሄደዋል ብሏል::
ሀገራችን ታላቅ አባት አጥታለች ያለው ምክር ቤቱ፤ ሀዘናችን መሪር ቢሆንም የአላህን ውሳኔ ከመቀበል ውጪ አማራጭ የለም ሲል የሀዘን መግለጫ መልእክቱን አስተላልፏል::
ቴሌግራም ቻናልችንን በመቀላቀል የአዲስ አድማስን መረጃ ይከታተሉ…
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት ፕሬዚዳንት የነበሩት ተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጂ ዑመር ኢድሪስ በማረፋቸው ኀዘን ተሰምቶኛል።
ሐጂ ዑመር በአመራር ዘመናቸው የተለያዩ ወገኖች ወደ አንድነት እንዲመጡ እና የእስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት በሕግ ዕውቅና እንዲኖረው ያደረጉትን አስተዋጽዖ ሁሌም እናስታውሰዋለን።
ለቤተሰቦቻቸው እና ለመላ ኢትዮጵያ ሙስሊሞች መጽናናትን እመኛለሁ።
ቴሌግራም ቻናልችንን በመቀላቀል የአዲስ አድማስን መረጃ ይከታተሉ…
ዌልስና ቤልጂየም ባደረጉት የአለም ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታ አንዲት አይጥ ወደ ሜዳዉ ዘልቃ መግባቷ ብዙዎችን አስደምሟል፡፡
ቤልጂየም ዌልስን 4 ለ 2 በሆነ ዉጤት ባሸነፈችበት በዚህ ጨዋታ አይጧ በ65ኛ ደቂቃ ወደ ሜዳ በመግባቷ ጨዋታዉ ለተወሰኑ ደቂቃዎች ተቋርጧል፡፡
የጀርመን ዜግነት ያላቸዉ የእለቱ ዳኛ ዳንኤል ሳይበርት አይጧ ወደ ሜዳዉ ዘልቃ መግባቷን ካረጋገጡ በኋላ ተመልሳ እስከምትወጣ ጨዋታዉን አስቁመዋል፡፡
የዌልስ እና የቶተንሃሙ ተጫዋች ብሬናን ጆንሰን አይጧን ከሜዳ ዉስጥ ለማዉጣት ሲያደርግ የነበረዉ ጥረት በእግር ኳስ ታዳሚዎች ዘንድ ተዝናኖትን ፈጥሯል፡፡
የቤልጂየሙና የሪያል ማድሪድ ግብ ጠባቂዉ ቲቦ ኮተርቶዋንስ በበኩሉ አይጧን በእጅ ይዞ ከሜዳዉ ዉስጥ ለማዉጣት ሲሞክር ከእጁ በማምለጥ አስቸግራዉ እንደነበር ዘ ሰን አስነብቧል፡፡
ለተወሰኑ ደቂቃዎች ያህል የታዳሚዎችም ሆነ የካሜራ አይኖች በአይጧ ላይ ያተኮረ ቢሆንም ከቆይታዎች በኋላ አይጧ በገዛ ፈቃዷ ሜዳዉን ለቃ ወጥታለች፡፡
 
 
 
የማሊ መንግስት የአሜሪካ ዜጎች የቢዝነስ ወይም የጉብኝት ቪዛ ለማግኘት እስከ 10ሺ ዶላር የሚደርስ ተመላሽ የሚሆን ገንዘብ ማስያዝ እንደሚጠበቅባቸው አስታውቋል።
ውሳኔው በቅርቡ ማሊን ጨምሮ በበርካታ የአፍሪካ ሀገራት ላይ ለተጣለው ተመሳሳይ የአሜሪካ ፖሊሲ ቀጥተኛ ምላሽ ነው ተብሏል፡፡
የማሊ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እንደገለጸው፤ እርምጃው የተወሰደው የቪዛ ገደቦችን በተመለከተ ዋሺንግተን በተከተለችው "የአንድ ወገን ውሳኔ" ምክንያት ነው፡፡
.
ይህ በእንዲህ እንዳለ በባማኮ የሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ የራሱን ፖሊሲ አስመልክቶ በሰጠው ምላሽ፣ የገንዘብ ማስያዣው የአሜሪካን ድንበሮችና ብሄራዊ ደህንነት ለመጠበቅ ያለመ ነው ማለቱን ግሬት አፍሪካ ዘግቧል፡፡
2ሺ ፍልስጤማውያን ከእስራኤል እስር ቤት ተለቀቁ
የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ የጋዛን የመሪዎች ጉባኤ ለመምራት ዛሬ ሰኞ የግብፅዋ ከተማ ሻርም ኤል ሼክ መግባታቸው ተዘግቧል፡፡ በጉባኤው ላይ የእንግሊዝና የጀርመን መሪዎችን ጨምሮ ከ20 በላይ የዓለም አገራት መሪዎች እንደሚሳተፉ ታውቋል፡፡ የግብጹ ፕሬዚዳንት አልሲሲ መሪዎቹን እየተቀበሉ መሆኑም ተዘግቧል።
በሌላ በኩል፤ በጋዛ የሰላም ስምምነት መሰረት፣ ከእስራኤል እስር ቤት የተፈቱ ፍልስጤማውያን ወደ ጋዛና ራማላህ ተጉዘው ከቤተሰቦቻቸው መቀላቀላቸውን አልጀ ዚራ ዘግቧል።
እስራኤልና ሃማስ ያደረጉት የተኩስ አቁም ስምምነት መተግበሩን ተከትሎ፣ ሃማስ በህይወት ያሉ 20 እስራኤላውያን ታጋቾችን የለቀቀ ሲሆን፤ እስራኤል በበኩሏ ሁለት ሺህ የሚጠጉ ፍልስጤማውያንን ከእስር ለቃለች ተብሏል፡፡
አዳብና በክስታኔ ዓለም አቀፍ ወጣቶች ማኀበር እና አክራሚ የሴቶች በጎ አድራጎት ማህበር በጥምረት በፌስቲቫል ደረጃ በአዲስ አበባ ወዳጅነት ፓርክ በዛሬው እለት ተከብሯል፡፡
ዘንድሮ ለመጀመሪያ ጊዜ አዳብና በአዲስ አበባ የተከበረ ሲሆን፤ ቀደም ብሎ መስከረም 24 ቀን 2018 ዓ.ም በጉራጌ ዞን በኬላ ከተማ በደማቅ ሁኔታ መከበሩ ተገልጿል፡፡
የአዳብና ባህል የልጃገረዶችና ወጣት ወንዶች ጨዋታና መተጫጫ ስነስርዓት ሲሆን፤ ከ800 ዓመታት በፊት በክስታኔ ቤተ-ጉራጌ አካባቢ ለዘመናት ሲከበር ኖሯል።
ክስታኔ ዓለም አቀፍ ወጣቶች ማህበርና አክራሚ በጎ አድራጎት የሴቶች ማህበር በጋራ ያዘጋጁት ይህ ድንቅ የሆነ የአዳብና ባህል፣ በማይዳሰስ የዓለም ቅርስነት በዩኔስኮ (UNESCO) እንዲመዘገብ ስራዎች እየተሰሩ መሆኑ ተነግሯል።
ቴሌግራም ቻናልችንን በመቀላቀል የአዲስ አድማስን መረጃ ይከታተሉ…
 
 
 
አዳብና በክስታኔ ዓለም አቀፍ ወጣቶች ማኀበር እና አክራሚ የሴቶች በጎ አድራጎት ማህበር በጥምረት በፌስቲቫል ደረጃ በአዲስ አበባ ወዳጅነት ፓርክ ተከብሯል፡፡
በአከባበር ስነ ስርዓቱ ላይ የዞኑ አመራሮች የመንግስት የስራ ሀላፊዎች ሚኒስትሮች እና ተፅኖ ፈጣሪ ሰዎች የጉራጌ ብሄርሰብ ተወላጆች ታድመዋል።
አዳብና ማለት አዳም እና ሄዋን የሚለው ቃል በሂደት ወደ አዳብና መቀየሩ ይነገራል።አዳብና የመስቀል በአልን ተከትሎ እስከ ጥቅምት 1 የሚከበር በአል ነው።
በበአሉ ልዩ ልዩ የጉራጌ ባህላዊ አልባሳት ጭፈራዎች ምግቦች መሰል ቱፊታዊ ክንውኖች ተካሂደዋል።
ሃማስ የሰላም ዕቅዱ አካል የሆነውን የትጥቅ መፍታት አንቀጽ ለመተግበር መስማማቱን የገለጹት የአሜሪካው ፕሬዚዳንት፤ የጋዛ ጦርነት አብቅቷል ሲሉ አውጀዋል፡፡
ትራምፕ በጋዛ የተኩስ አቁም ስምምነት መደረጉን ተከትሎ፣ እስራኤል የገቡ ሲሆን፤ በእስራኤል ፓርላማ ንግግር ያደርጋሉ ተብሏል፡፡
በምክር ቤቱ የእንግዶች ማስታወሻ ደብተር ላይ "ታላቅ ክብር፣ ታላቅና ውብ ቀን" የሚል ማስታወሻ ያስቀመጡት ፕሬዚዳንቱ፤ "ይህ አዲስ ጅማሬ ነው" ሲሉ አክለዋል።
ይህ በዚህ እንዳለ ሃማስ የመጀመሪያ ዙር 5 የእስራኤል ታጋቾችን መልቀቁ ተዘግቧል፡፡
 
 
 
በአዲስ አበባ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ ፋብሪካ ለመገንባት ከአውሮፓ ኩባንያ ጋር ስምምነት መደረሱ ተዘግቧል፡፡
የትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ ሚኒስትር ዴኤታ በረኦ ሐሰን፣ መቀመጫውን አውሮፓ ካደረገው ባትስዋፕ አውቶሞቲቭ ኃላፊዎች ጋር በጉዳዩ ዙሪያ ተወያይተዋል።
ትብብሩ አዲስ አበባ ውስጥ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ ማምረቻ ፋብሪካ መትከል፣ የባትሪ ማምረቻና ጥናትና ምርምር እንዲሁም የአረንጓዴ ትራንስፖርት ዘርፍ ልዩ የኢኮኖሚ ዞን ማቋቋምን ያካትታል።
በ2026 በሚተገበረው የስምምነቱ የመጀመሪያ ምዕራፍ፣ 240 የሙከራ የኤሌክትሪክ ጭነት ተሽከርካሪዎች ሲገነቡ፤ 10 አውቶማቲክ የባትሪ መለዋወጫ ጣቢያዎች በአዲስ አበባ ይዘረጋሉ።
ስምምነቱ ኢትዮጵያ በአፍሪካ የአረንጓዴ እንቅስቃሴ ዘርፍ ቁልፍ ተዋናይ ከመሆን ራዕይዋ ጋር የተጣጣመ ነው መባሉን ስፑትኒክ ዘግቧል፡፡