Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62

በአያን ፍሌሚን የስለላ ድርሰቶች ላይ ተመስርተው ከተሰረቱት የጄምስ ቦንድ ፊልሞች ሁሉ የላቀ ነው ተብሎ አድናቆት የተቸረው “ስካይፎል”፤ ፊልም ተመልካቾችን ለማርካት በመቻሉ ገበያ ቀንቶታል። በእንግሊዝ የስለላ ተቋም ውስጥ፣ “007” የሚል የሚስጥር ስም የተሰጠው ጄምስ ቦንድን በመወከል ዳንኤል ክሬግ የተወነበት ይሄው ፊልም፤ በአስር ቀናት ውስጥ 670 ሚሊዮን ዶላር በማስገባት ከሌሎቹ የጄምስ ቦንድ ፊልሞች ብልጫ አስመዝግቧል።

በኮንሶ አካባቢ የመሬት አቀማመጥ ላይ ያተኮረው የሁለት ሳምንት ፎቶ አውደርእይ በመጪው ማክሰኞ ይከፈታል አምስት ኪሎ በሚገኘው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቤተመዘክር የሚካሄደውን አውደርእይ በመተባበር ያዘጋጁት የአውሮፓ ሕብረት ኮሚሽን እና የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ናቸው፡፡

አዲስ አበባ ከተማ የተመሰረተችበትን 125ኛ አመት በማስመልከት ተከጋጅቶ በነበረው እየታዩ ያሉ ትያትሮች ውድድር የተመረጡ ትያትሮች ልዩ ሽልማት ተሰጣቸው፡፡ ዋፋ ኮሙኒኬሽን ባስተባበረው ውድድር የተሳተፉት ስምንት ትያትሮች “ምርጥ” በመባል በተለያዩ ዘርፎች ተወዳድረው ተሸልመዋል፡፡በአዲስ አበባ ማዘጋጃ ቤት ከትናንት ወዲያ ማታ በተደረገው የሽልማት ሥነ ሥርዓት በምርጥ የተውኔት ፅሁፍ የኃይሉ ፀጋዬ “ቤተሰቡ” አንደኛ፣ የዘካርያስ ብርሃኑ “የበዓል እንግዶች” ሁለተኛ፣ የአለልኝ መኳንንት “የፍቅር ካቴና” ሦስተኛ ሆነው 125ኛ አመቱን የሚያንፀባርቅ የወርቅ፣ የብርና እና የነሀስ ሜዳሊያ ተሸልመዋል፡፡ በምርጥ አዘጋጅ የዳግማዊ አይሳ ቤተሰቡ፣ የዘውዱ አበጋዝ “የበአል እንግዶች” ሁለተኛ፣ የገነት አጥላው ዝግጅት የሆነው “ጓደኛሞቹ” ሦስተኛ ሆነው ተሸልመዋል፡፡ 

ዘነበ ተስፋዬ (ዲንጐ) ፅፎ ያዘጋጀው “ግራና ቀኝ” ትያትር ዛሬ እንደሚመረቅ ጥሩ አየሁ ፕሮሞሽን እና ጀዋሬ ፕሮዳክሽን አስታወቁ፡፡ ዛሬ ከቀኑ 8 ሰዓት በአዲስ አበባ ማዘጋጃ ቤት ትያትርና ባህል አዳራሽ በሚመረቀው ትያትር ገነት ንጋቱ፣ አስቴር በዳኔ፣ ዘነበ ተስፋዬ፣ ትንሳኤ ብርሃነ፣ ሜሮን ፋንቱ፣ አሳምነው ዘነበ፣ እና ምስራቅ ወርቁ ይተውናሉ፡፡

በአንጋፋው ገጣሚ እና ፀሐፌ ተውኔት አያልነህ ሙላቱ የተዘጋጁትን 2400 ገፆች ያሉዋቸው “ከድጡ ወደ ማጡ” እና “ወይ አንቺ ሐገር” ሁለት የግጥም መፃሕፍት ባለፈው ማክሰኞ ምሽት በሂልተን ተመረቁ፡፡ “ወይ አንቺ ሀገር” ከ1963 እስከ 1967 የተዘጋጁ የግዛተ አፄ ግጥሞች የተካተቱበት ሲሆን “ከድጡ ወደ ማጡ” ከ1967-1983 የተፃፉ የግዛተ ደርግ ግጥሞች ናቸው፡፡ አያልነህ ከግጥም ሥራዎቹ ባሻገር በ”ሾተላይ”፣ “ድሀ አደግ”፣ “በጋሜ መቅረት”፣ “መንታ እናት” እና ሌሎችም ትያትሮቹ እንዲሁም ባሳተማቸው አስር መፃህፍት ይታወቃል፡፡

በአንጋፋው ገጣሚ እና ፀሐፌ ተውኔት አያልነህ ሙላቱ የተዘጋጁትን 2400 ገፆች ያሉዋቸው “ከድጡ ወደ ማጡ” እና “ወይ አንቺ ሐገር” ሁለት የግጥም መፃሕፍት ባለፈው ማክሰኞ ምሽት በሂልተን ተመረቁ፡፡ “ወይ አንቺ ሀገር” ከ1963 እስከ 1967 የተዘጋጁ የግዛተ አፄ ግጥሞች የተካተቱበት ሲሆን “ከድጡ ወደ ማጡ” ከ1967-1983 የተፃፉ የግዛተ ደርግ ግጥሞች ናቸው፡፡ አያልነህ ከግጥም ሥራዎቹ ባሻገር በ”ሾተላይ”፣ “ድሀ አደግ”፣ “በጋሜ መቅረት”፣ “መንታ እናት” እና ሌሎችም ትያትሮቹ እንዲሁም ባሳተማቸው አስር መፃህፍት ይታወቃል፡፡

በአኮርድዮን ዘፈኖቹ የሚታወቀው የእውቁ ድምፃዊ ፍሬው ኃይሉ ልጅ ዳዊት ፍሬው “ጥላ ከለላዬ” በሚል ርእስ ያሳተመውን አልበም የፊታችን ማክሰኞ ከቀኑ 11 ሰአት በሀገር ፍቅር ትያትር ቤት እንደሚያስመርቅ ገለጠ፡፡ በሙዚቃ መሳርያ ብቻ የተቀናበሩት ዜማዎች የጥላሁን ገሠሠን፣ የፍሬው ኃይሉን፣ የማህሙድ አህመድን፣ የምኒሊክ ወስናቸውን ዘፈኖች የያዘው አልበም፤ ለዳዊት ሁለተኛ አልበሙ ነው፡፡ “ጥላ ከለላዬ” ከማክሰኞው ምርቃት በኋላ ለሕዝብ መቅረብ እንደሚጀምር ሙዚቀኛው ለአዲስ አድማስ ተናግሯል፡፡

“ይሳቃል” ኢንተርቴይመንት፣ ሰላም ኢትዮጵያ እና አዲስ አበባ የሚገኘው የስዊድን ኤምባሲ “ሰላም ፌስቲቫል” የተሰኘ የሙዚቃ ድግስ ሊያቀርቡ ነው፡፡ ህዳር 28 እና ህዳር 29 በአዲስ አበባ በሚካሄደው ፌስቲቫል ላይ ታዋቂ ዓለም አቀፍ ሙዚቀኞች እና ኢትዮጵያውያንም ይገኛሉ ተብሏል፡፡ ከትናንት ወዲያ በስዊድን ኤምባሲ ይህንኑ አስመልክቶ በተሰጠ የስዊድን አምባሳደር ጄንስ ኦድላንደር በተገኙበት መግለጫ ተሰጥቷል፡፡ በዚሁ ወቅት አምባሳደሩ የመናገር መብት ከሚገለፅባቸው መንገዶች አንዱ ሙዚቃ ነው ካሉ በኋላ፣ መንግስታቸው በኢትዮጵያ ድህነትን ለመቀነስ ከሚያደርገው እገዛ በተጨማሪ የሙዚቃ ድግስ እገዛው የግሉን ዘርፍ ለማጠንከር ከሚተገብራቸው መርሃ ግብሮች አንዱ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

“አፄ ቴዎድሮስ አጫጭር ታሪኮች” እየተነበበ ነው
የዛሬ 40 ዓመት ሲታተም ከፍተኛ “የሚያቃጥል ፍቅር” ልብወለድ መጽሐፍ እንደገና ታትሞ ለንባብ በቃ፡፡ “እግረ ፀሐይ ከዶክተርነት ወደ ሴተኛ አዳሪነት ለምን ተዛወረች” የሚል ጥያቄ በማንሳት የሚተርከው መፅሐፍ እድሜአቸው ከ18 አመት በታች ላሉ ሕፃናትና ነፍሰ ጡሮች ማንበብ የተከለከለ ሲሆን፣ 212 ገፆች ያሉት መፅሐፍ በ35 ብር እየተሸጠ ነው፡፡ በኃይለስላሴ ደስታ በ1960ዎቹ መጀመርያ የተፃፈው መፅሐፍ የቅጂ መብትን አስመልክቶ ደራሲው ባሰፈሩት ማስታወሻ “ይህ መፅሐፍ ከታተመ ከስድስት ወር በኋላ ማንኛውም ሰው ሳይቀንስ አሳትሞ ቢጠቀም እኔም ሆንኩ ወራሾቼ አንከራከርም” ብለዋል፡፡

Saturday, 24 November 2012 12:04

አርሰናል 3 ፉልሃም 3 ፉልሃም

ምስራቅ በለሳ/ሰሜን ጐንደር/
መቼም ሰው ለስራ ጉዳይ ብሎ የማይገባበት ቦታ የለምና፤ እኔም ለዚሁ እንጀራዬ ብዬ ወደ ሰሜን ጐንደር ካቀናሁ ሶስተኛ ሳምንቴን ያስቆጠርኩ ሲሆን የምስራቅ በለሳ ወረዳ ዋና ከተማ በሆነችው ጉሃላ የስራዬ መደምደሚያ ወረዳ ስትሆን ወረዳዋ ከምእራብ በለሳ ተገንጥላ ራሷን የቻለች ወረዳ እንድትሆን የተደረገው በቅርቡ ሲሆን ወረዳዋ ከተማ ከተማ እንድትሸት መንግስት፤ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች፤ ነጋዴውና ህዝቡ የበኩሉን እየጣረላት የምትገኝ ከተማ ናት፡፡
አንድ ቅዳሜ ቀን የመስክ ስራዬን አጠናቅቄ ሆቴል ውስጥ አረፍ ብዬ መጽሐፍ በማንበብ ላይ ሳለሁ ሁለት እጅግ የተበሳጩ የሚመስሉ የአርሰናል ደጋፊዎች ቡድናቸው አርሰናል ከፉልሃም ጋር 3-3 በመለያየቱ ምክንያት የ90 ደቂቃውን ኳስ እየገመገሙ ሲያወሩ ጆሮዬን ጣል አድርጌ ሰማሁና፣ ከጨዋታቸው ውስጥ ብዙ የሚያዝናኑና የሚያስተምሩ ነገሮች አገኘሁና እስኪ ለአንባቢ ላካፍል ብዬ አሰብኩ፡፡ አንድ መረሳት የሌለበት ነገር ግን የጐንደርኛ ዘዬን ይልቅ ሲሰሙት ይበልጥ ሊያዝናና እንደሚችል ይሰማኛል፡፡

Page 13 of 163