Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን የያዘ ሲሆን ከተለያዩ አገራት ትውልደ ኢትዮጵያዊ ፕሮፌሽናሎችን በመቀላቀልእና ለአቋም መፈተሻ የሚሆኑ የወዳጅነት ጨዋታዎችን በማሳወቅ ለ29ኛው የአፍሪካ ዋንጫ የሚያደርገውን ዝግጅት ቀጥሏል፡፡በአሠልጣኝ ሰውነት ቢሻው በሚመራው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከ2 ሳምንት በፊት በስዊድን የሚጫወተው የሱፍ ሳላህ እና በጀርመን የሚጫወተው ዴቪድ በሻህ አካትቶ ልምምዱን መስራት ከቀጠለ በኋላ በሳምንቱ አጋማሽ ላይ ደግሞ ሶስት ተጨዋቾችን ቀላቅሏል፡፡

ከዚህ ቀደም ስለ ንባብ ጠቃሚነት ብዙ ተብሏል፡፡
ጥሩ ጥሩ መጽሐፍትን ማንበብ ከበሰሉ ሰዎች ጋር ሸንጎ እንደመቀመጥ ይቆጠራል ይባላል፡፡ የአስተሳሰብ አድማስን ስለሚያሰፋ፣ ሁለገብ እውቀት ስለሚያላብስና በራስ መተማመንን ስለሚያጎለብት ማንበብ ሙሉ ሰው ያደርጋል፡፡ ታዋቂው የአሜሪካ ፕሬዝደንት፣ አብርሃም ሊንከን የንባብን ጥቅም አስመልክቶ ሲናገር፣ ‹‹ማወቅ የምፈልጋቸው ነገሮች የሚገኙት መጽሐፍት ውስጥ ነው፡፡ ያላነበብኩትን መጽሐፍ የሚሰጠኝ እርሱ ከጓደኞቼ ሁሉ የተሻለው ነው›› ብሎ ነበር፡፡

Saturday, 22 December 2012 09:48

‘ጭድ’ና ዘመን…

እንዴት ሰነበታችሁሳ!
ስሙኝማ…‘ጄኒዩን’ የሚባል ኦሪጂናሌ ነገር ማግኘት እየከበደ ነው፡፡ ብዙ ነገር አስመስሎ እየተሠራ ግራ እየተጋባን ነው፡፡ ብዙዎቻችን በተለያዩ ነገሮች…አለ አይደል…‘ጦጣ’ ነገር እየተደረግን ነው፡፡
“የፒያሳ ልጅ ነኝ፣ ሌላውን አሞኛለሁ እንጂ አልሞኝም…” “የመርኬ ልጅ ሆኜማ የፈለገ የጨስኩ ብልጥ ነኝ ያለ እኔን አያታልለኝም…” ምናምን ብሎ ፉከራ ዘንድሮ አይሠራም፡፡
የብልጥነት ነገር ካነሳን ይቺን ስሙኝማ…ሰውየው ልጃቸውን ሂሳብ ነገር ሊያስተምሩት ሦስት ማንጎ ጠረዼዛ ላይ ያስቀምጡና ልጁን ምን ብለው ይጠይቁታል…“እነኚህን ሦስት ማንጎዎች ለአራት ሰው እንዴት አድርገህ ታከፋፍላለህ?” ይሉታል፡፡ ልጁ ምን ብሎ መለሰ መሰለችሁ… “ማንጎዎቹን ጁስ አደርጋቸዋለሁ…” አሪፍ አይደል! የዚህን ልጅ አይነት ‘ብልጥነት’ ያብዛልንማ!
ምን ይገርምሀል አትሉኝም…ይሄ የ‘ፎርጀሪ’ ነገር እንዴት እየተሻሻለ እንደሄደ! (በዛ ሰሞን ኪሱ ሞላ ባለ ሰሞን የውስኪ ወዳጅ የሚሆን ወዳጄ ምን አለኝ መሰላችሁ…“በፊት ብራንዲ ከሌላ ጠርሙስ በሲሪንጅ እየተመጠጠ ውስኪ ጠርሙስ ውስጥ እየተከተተ ውስኪው ‘ይወጋ’ ነበር፡፡

‹‹ዕርቀ ሰላሙ ይቅደም›› የሚሉ ጳጳሳት የሲኖዶሱን ውሳኔ አንቀበለውም ብለዋል
የላሊበላው ውዝግብ ወደ አላስፈላጊ ግጭት እንዳያመራ ተሰግቷል
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የስድስተኛውን ፓትርያሪክ ምርጫ ዝግጅት የሚመራና እስከ ጥር መጨረሻ ዕጩዎችን የሚያቀርብ አስመራጭ ኮሚቴ መሠየሙ በቤተ ክርስቲያኒቱ ካህናትና ምእመናን ዘንድ ዓለም አቀፍ ተቃውሞ መቀስቀሱ ተገለጸ። ‹‹የቤተ ክርስቲያን ጉዳይ ያገባኛል›› በሚል መርሕ በዋናነት በማኅበራዊ ሚዲያዎችና ብሎጎች እየተገለጸ ያለው ይኸው ተቃውሞ፤ የቤተ ክርስቲያን ሰላምና አንድነት የሚረጋገጥበት የዕርቁ ጉባኤ ‹‹የአባቶች ጉዳይ ብቻ አይደለም፤ ምእመናኑን ያገለለ ሊኾን አይገባም›› በሚል የካህናቱና ምእመናኑ ድምፅ እንዲደመጥ የሚወተውት ነው፡፡

አራት የተፈረደባቸው የኢትዮጵያ ጋዜጠኞች ተሸለሙ
ከሽብርተኝነት እንቅስቃሴ ጋር በተያያዘ ክስ ተመስርቶበት የ18 ዓመት እስር የተፈረደበት ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ከእስር እንዲፈታ የአውሮፓ ፓርላማ ጠየቀ፡፡ የአውሮፓ ፓርላማ አባላት ለጠ/ሚኒስትር ሐይለማርያም ደሳለኝ በፃፉት ግልፅ ደብዳቤ፤ ጋዜጠኛው በአፋጣኝ ከወህኒ ቤት እንዲለቀቅ ጥያቄ አቅርበዋል።በሌላ በኩል አራት በፍ/ቤት እስር የተፈረደባቸው የኢትዮጵያ ጋዜጠኞች ዝነኛውን የ2012 የሄልማን/ሃሜት ሽልማት ተሸለሙ፡፡ ተሸላሚዎቹ በእስር ላይ የሚገኙት እስክንድር ነጋ፣ ርዮት ዓለሙ፣ ውብሸት ታዬ እንዲሁም በሌለበት የተፈረደበት የቀድሞው የ“አዲስ ነገር” ጋዜጣ አዘጋጅ መስፍን ነጋሽ ሲሆኑ ጋዜጠኞቹ ሽልማቱን ያገኙት በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ሃሳብን በነፃነት የመግለፅ መብትን ለማስጠበቅ ላደረጉት ጥረት ነው ተብሏል፡፡ 

ከምርጫው በፊት ውይይት እንፈልጋለን በሚል በአንድ ላይ የተሰባሰቡ 33 ተቃዋሚ ፓርቲዎች ላቀረቧቸው ጥያቄዎች ምርጫ ቦርድ የሰጠውን ምላሽ ተቃወሙ፡፡ ፓርቲዎቹ ከትላንት በስቲያ በሰጡት መግለጫ፤ “ምርጫ ቦርድ ለዲሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታ የማይጨነቅ ተቋም ነው” ብለዋል። ምርጫ ቦርድ በበኩሉ፤ ፓርቲዎቹ ያቀረቡት ባለ 18 ነጥብ ቅሬታዎች በማስረጃ ያልተደገፉ ናቸው በማለት ሙሉ በሙሉ ውድቅ አድርጓቸዋል። “ተፈጠሩ የተባሉት ችግሮች መቼና የት ቦታ ላይ እንደተከሰቱ በማስረጃ ተደግፎ አልቀረበም” ያለው ቦርዱ፤ “ቅሬታዎቹ ወቅትን ያልጠበቁ፣ አግባብነትና የህግ ድጋፍም የሌላቸው ናቸው›› ሲል ቅሬታቸውን ሳይቀበለው ቀርቷል፡፡

ከ1ሺ በላይ ህገወጥ ኤጀንሲዎች አሉ ተባለ
ባለፈው ሩብ የበጀት ዓመት ከ72 ሺ በላይ ዜጐች ወደ አረብ አገራት እንደተጓዙ ተገለፀ፡፡ 72ሺ 438 ዜጐች ወደ ሳውዲ አረቢያና ኩዌት የተላኩ ሲሆን ከእነዚህ መካከል 68ሺ 474 የሚሆኑት ሴቶች ሲሆኑ 3ሺ 964 የሚደርሱት ደግሞ ወንዶች መሆናቸውን የሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡ በሚኒስትር መ/ቤቱ የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ግርማ ሸለመ ለአዲስ አድማስ እንደገለፁት፤ በመ/ቤቱ ተመዝግበውና ህጋዊ ፈቃድ ወስደው ዜጐችን ወደተለያዩ የአረብ አገራት የሚልኩ ህጋዊ ኤጀንሲዎች ቁጥር 300 ሲደርስ ከ1ሺ በላይ በህገወጥ መንገድ ዜጐችን የሚልኩ ደላሎች አሉ፡፡

የትራንስፖርት ዋጋው ከታክሲ ዋጋ ያነሰ ነው ተብሏል
አሊያንስ ትራንስፖርት ሰርቪስ አክስዮን ማህበር በአዲስ አበባ የግል የከተማ አውቶብስ አገልግሎት መስጠት እንደሚጀምርና ሃያ አምስት አውቶቡሶችን ባለፈው ረቡዕ ወደ አገር ውስጥ እንዳስገባ ተገለፀ፡፡ እያንዳንዳቸው 2 ሚሊዮን ብር ገደማ የተገዙት አውቶቡሶች ባለፈው ታህሣሥ 10 ቀን 2005 ዓ.ም አዲስ አበባ ሲገቡ አቀባበል ተደርጐላቸዋል፡ ሙሉ በሙሉ በአውሮፓ ሞተር የተሰሩትና ቻይና ውስጥ የተገጣጠሙት አውቶቡሶች፤ 100 ሰው የመጫን አቅም እንዳላቸውና ደረጃቸውን የጠበቁ እንደሆኑ አቶ አዲል አብደላ የአሊያንስ ትራንስፖርት ሰርቪስ አክስዮን ማህበር የዳይሬክተሮች ቦርድ ሰብሣቢ ለአዲስ አድማስ ተናግረዋል፡፡ 

መግቢያ፤
የኢትዮጵያ የምድር ባቡር ኩባንያ ባለሥልጣን በገለጹት መሠረት፤ ታሪካዊው፤ የሰማእቱ አቡነ ጳውሎስ ኃውልት፤ ለባቡር መንገድ ግንባታ፤ አሁን ካለበት ለጊዜው ተነስቶ፤ ሥራው ከተጠናቀቀ በኋላ፤ ወደ ስፍራው እንደሚመለስ አስታውቀዋል። ቢሆንም፤ ያልተመለሱ ብዙ ጥያቄዎች አሉ። ይህ ከፍተኛ ጉዳይ በተለይ የሚመለከታቸው ድርጅቶች ለምን ዝም አሉ?! የኢትዮጵያ የሕዝብ ምክር ቤት፤ የሚመለከታቸው የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች፤ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን፤ የኢትዮጵያ አርበኞች ማሕበር፤ የኢትዮጵያ ቅርሶች ጉዳይ ድርጅት፤ የአዲስ አበባ ማዘጋጃ ቤት፤ ወዘተ፤ በጉዳዩ ተመካክረው ወስነዋል? ከሆነስ፤ ድምጻቸው ለምን አልተሰማም፤ ለሕዝብስ በቅድሚያ ለምን በግልጽ አልተነገረም? የሐገር ቅርስ ስለ ሆነው፤ የአቡነ ጴጥሮስ ኃውልት ጉዳይ፤ መናገር ያለበት፤ የባቡር ኩባንያ ነው? ለመሆኑ፤ ኃውልቱ ከቦታው መነሳት ካለበት፤ መቼ ተነስቶ፤ መቼ ይመለሳል?

የፖለቲካ ነገር ጭራና ቀንዱ መግቢያና መውጫው የማይታወቅ፤ በዚህ በኩል ሲይዙት በዚያ የሚያፈተልክ ውስብስብ ጉዳይ የሚመስላቸው ሰዎች ጥቂት አይደሉም - አንዳንዶቹ ውስብስብነቱ ቢማርካቸውም ብዙዎች ይሸሹታል። ግን ከፖለቲካ የሚያመልጥ የለም። በታክስ ጫና ወይም በዋጋ ንረት ኑሯቸው የሚናጋው፤ በ97ቱ አይነት የምርጫ ቀውስ ወይም በሃይማኖትና በብሄረሰብ ግጭት ህይወታቸው አደጋ ላይ የሚወድቀው በፖለቲካ ምክንያት ነው። ሙስናና አድልዎ፣ ፕሮፓጋንዳና አፈና... የፓለቲካ ጉዳይ ናቸው። ከፖለቲካ መሸሽ፣ የትም አያደርስም። ደግሞምኮ ፖለቲካ ውስብስብ አይደለም። በእርግጥ፤ ዋናውን የፖለቲካ ጥያቄ ትተን፣ ቅርንጫፍና ቅጠሉን ዝርዝርና ምንዝሩን እየነካካን ለመምዘዝና ለመተርተር ከሞከርን፤ እዚያው ተተብትበን መቅረታችን አያጠራጥርም።

Page 6 of 163