Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62

Monday, 05 November 2012 07:48

ፍፅምና

የሞፓሳ ምርጥ አጭር ልብ-ወለድ ናት፡፡
የፅሁፉ ዋና ገፀ-ባህሪ ውብ እና የሚወዳት ሚስት አለችው፡፡ ኑሮዋቸውን የሚደጉመው እየዞረ በሚያሳየው ሠርከሥ ነው፡፡ ችሎታው አንድን ጩቤ ከረዥም ርቀት (5 ሜትር፣ 10ሜትር፣ 15ሜትር …) የተባለው ቦታ ላይ ወርውሮ መሠካት ነው፡፡ ሥቶ አያውቅም፡፡ በፍፁም ስቶ አያውቅም፡፡ ብርቱካኖችን፣ የፖም ፍሬዎችን ከተለመደው ርቀት ጩቤ ወርውሮ ይገምሳቸዋል፡፡ ከብዙ ልምምድ በኋላ የተቀዳጀው ችሎታ ነው፡፡በትርኢቱ ፍፅምናን ተቀዳጀ፡፡ እናም ትዕይንቱን ወደ አስደሳች ግን እጅግ አደገኛ ወደ ሆነ ደረጃ አሳደገው፡፡ እንደ ቀድሞው ኢላማዎቹ የዛፍ ግንዶች፣ ፍራፍሬዎች ወይም ሠሌዳ ላይ የተሣሉ ነጥቦች አይደሉም፡፡ ሠው ነው ኢላማው፡፡ ጩቤውን ወርውሮ ሠው መምታት ግን አይደለም፤ መሣት ነው፡፡

የዝነኛው የሬጌ አቀንቃኝ ቦብ ማርሌይ ባለቤት ማርሌ ለሁለት ሳምንት ጉብኝት ወደ ኢትዮጵያ እንደምትመጣ ተገለፀ፡፡ የጉብኝቷ ዓላማ በኢትዮጵያ መንግስት በሚገነባው የህዳሴ ግድብ አስፈላጊነት በቂ ግንዛቤ ለመፍጠርና የገንዘብ ድጋፍ ለማሰባሰብ ነው ተብሏል፡፡
የቦብ እና ሪታ ማርሌ ፋውንዴሽን ለአዲስ አድማስ በላከው መግለጫ እንዳመለከተው፤ የሬጌ ሙዚቃ ንጉስ ቦብ ኔስታ ማርሌይ በመላው ህይወቱ ስለኢትዮጵያ ብዙ ሃሳብ እንደነበረው ጠቅሶ፤ ምንም እንኳን መንፈሳዊ ምድሬ ወደ የሚላት አገር መጥቶ የህይወቱን የመጨረሻ ዘመናት ለመኖር ባይታደልም ራእዩ ከኢትዮጵያውያን ጋር ዝንተዓለም ይኖራል ብሏል፡፡

Saturday, 03 November 2012 13:22

“ኢህአዴግን እከስሳለሁ”

መግቢያ
በእኔ ላይ ተተርጉሞ አስተውዬዋለሁ ማለት እችላለሁ፡፡ ተወልጄ ያደግኩት ባሻ ወልዴ ችሎት አካባቢ ነው፡፡ ባሻ ወልዴ ችሎት፣ ጉብታ ላይ የተንሰራፋው የምኒሊክ ቤተ - መንግስት ግርጌ ከተኮለኮሉት ጐስቋላ ሠፈሮች አንዷ ነበረች፡፡ ይቺ ሠፈር ነዋሪዎቿን እንደታቀፈች ፖለቲካ ሠራሽ በሆነ በሽታ ወድቃ፣ ቃትታና አጣጥራ የተንከራተተች ውሻ ሞት ስትሞት አብሬአት ነበርኩ፡፡
ወቅታዊው እሳቤዬና ስሜቴ ሁሉ የዚህ ነባራዊ ሁኔታ ውጤት ነው፡፡ ኩሬ ላይ እንደተጣለ ጠጠር የራሷን የማዕበል ሠፌድ ፈጥራ ከሠፈር አካባቢ፣ ከአካባቢ ከተማ፣ ከከተማ አገር አቀፍ ይዘት ትላበስ እንጂ መነሻው አራት ኪሎ ባሻ ወልደ ችሎት ናት፡፡
አገርና ዜግነት…

 

ስድስተኛውን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን ፓትርያርክ ይመርጣል ተብሎ የተጠበቀው የቤተክርስትያኒቱ ቅዱስ ሲኖዶስ የጥቅምት ምልአተ ጉባኤ ምርጫውን ሳያከናውን የተጠናቀቀ ሲሆን ቀጣዩ ፓትርያርክ ከመመረጣቸው በፊት ባለው ሕግ ላይ ተጨማሪ ሕግ ያስፈልጋል በመባሉ ይህንኑ የሚያዘጋጅ የሊቃነ ጳጳሳት ቡድን ተቋቁሟል፡፡ ቡድኑ ሕጉን አርቅቆ ለሕዳር 30 ያቀርባል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ አቃቤ መንበረ ፓትርያርክና የአርሲ ሀገረ ስብከት ሊቀጳጳስ ብፁእ አቡነ ናትናኤል በሚመሩት ቡድን ውስጥ ብፁዕ አቡነ ገብርኤል፣ ብፁእ አቡነ ሳሙኤል፣ ብፁእ አቡነ አብርሃም፣ ብፁእ አቡነ ሉቃስ፣ ብፁእ አቡነ አብርሃም፣ ብፁዕ አቡነ ሉቃስ፣ ብፁእ አቡነ ሕዝቅኤል፣ ብፁእ አቡነ ዳንኤል እና ብፁዕ አቡነ ማቴዎስ የሚገኙበት ሲሆን ቡድኑ ከአቃቤ መንበሩ ጋር እንደ ቋሚ ሲኖዶስ እየሰራ መሆኑ ይታወቃል፡፡

 

የኢትዮጵያ መንግስት ሊያካሂድ ያሰበውን የ1.3 ቢሊዮን ዶላር የቴሌኮሙኒኬሽን ዝርጋታ ፕሮጀክት ሁለት የቻይና ኩባንያዎች ሊቆጣጠሩት እንደሆነ ተገለፀ፡፡ “ዜድቲኢ እና “ሁዋዌይ” የተባሉት ሁለቱ የቻይና የቴሌኮም ኩባንያዎች ለፕሮጀክቱ የተጫረቱ ሲሆን “ሁዋዌይ” 50 በመቶ ድርሻ ማሸነፉን የተለያዩ ድረገፆች ዘግበዋል፡፡ የኢትዮጵያ የኮሙኒኬሽንና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ደብረፅዮን ገብረ ሚካኤል ለብሉምበርግ ኒውስ እንደተናገሩት፤ የኢትዮጵያ መንግስት ከሁለቱ ኩባንያዎች ጋር የሁለት ዓመት ኮንትራት በቀጣዮቹ ሳምንታት ይፈራረማል፡፡

Saturday, 03 November 2012 12:58

ንብ ባንክ 287 ሚ. ብር አተረፈ

ንብ ኢንተርናሽናል ባንክ ባለፈው ዓመት 286.2 ሚሊዮን ብር የተጣራ ትርፍ ማስመዝገቡን ገለፀ፡፡ ባንኩ በላከው መግለጫ፤ የ2003/4 በጀት ዓመት ሪፖርት፣ ካለፈው የበጀት ዓመት ጋር ሲነፃፀር የ16.2 በመቶ ዕድገት ማሳየቱንና በተጠናቀቀው የበጀት ዓመት የባንኩ ጠቅላላ ተቀማጭ ሂሣብ 5.8 ቢሊዮን ብር እንደደረሰ ጠቁሞ የሰጠው ብድርም 3.7 ቢሊዮን ብር ባንኩ ባለፈው ዓመት ስድስት ተጨማሪ ቅርንጫፎችን በመክፈት የቅርንጫፎቹን ቁጥር ወደ 56 ከፍ ማደረጉን የጠቆመው መግለጫው፤ በሁለት የውጪ ምንዛሬ ቢሮዎቹ ዘመናዊ የገንዘብ አከፋፈል ሥርዓቱን ለማሳደግ ከአዋሽ ኢንተርናሽናል ባንክና ከሕብረት ባንክ ጋር ፕሪሜየር ስዊች ሶሉሽን አ.ማ. የተባለ ኩባያ መክፈቱን አመልክቷል፡፡ለባንኩ ትርፋማነትና ተወዳዳሪ መሆን የዳሬክተሮች ቦርድ እንዲሁም፣ የአስተዳደሩና የድርጅቱ ሰራተኞች ትጋት ተጠቃሽ እንደሆነ ባንኩ ገልጿል፡፡

ባለፉት 50 ዓመታት ከ25ሺህ በላይ የእንቅስቃሴ ችግር የነበረባቸውን ሕፃናት መራመድና መሄድ፣ መማርና መሥራት እንዲችሉ ማድረጉን የገለፀው ቸሻየር ሰርቪስስ ኢትዮጵያ፤ የወርቅ ኢዮቤልዩ በዓሉን ዛሬ እንደሚያከብር አስታወቀ፡፡
በመናገሻ ከተማ የሚገኘው ድርጅቱ የመሠረት-ማኅበረሰብ ተሃድሶ አገልግሎት በመጀመር ከ1500 በላይ የአካል፣ የአዕምሮና የስሜት ሕዋሳት የዕድገት ጉድለት እንዲሁም ተደራራቢ ጉዳት ለደረሰባቸው ሕፃናት የቤት ለቤት ተሃድሶ በመስጠት የዕለት ተዕለት የሕይወት ክህሎቻቸውን እንዲያዳብሩ ከማስቻሉም በላይ ዝቅተኛ ገቢ ያላቸውን የአካል ጉዳተኛ ሕፃናት እናቶች ነፃ የተሃድሶ አገልግሎት በመስጠት ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ ችግሮቻቸው ለመቅረፍ ልዩ ድጋፎች ማድረጉን አስረድቷል፡፡

ተፎካካሪዎች እናሸንፋለን እያሉ ነው
ባራክ ኦባማ በዋሺንግተን የድል መድረክ እያዘጋጁ ነው
ሚት ሮምኒ፣ ሚኒስትሮችን የሚመርጥ ቡድን አዋቅረዋል
የ4 አመቷን ሕፃን ያስለቀሰ የምርጫ ዘመቻ
ባራክ ኦባማና ሚት ሮምኒ ሰለቹኝ ብላ ምርር ብላ ታለቅሳለች - ሥማቸውን በሬድዮ ስትሰማ።
በርካታ ሬዲዮ ጣቢያዎችን የሚያካትተው ኤንፒአር ይቅርታ ጠይቋል - እኛም ሰልችቶናል በማለት።
ስልክ ያልተደወለለት የኦሃዮ ነዋሪ የለም ማለት ይቻላል።

Saturday, 15 September 2012 13:07

ድብርትና መዘዙ

የጥርስ በሽታ፣ ጉንፋን፣ የሳንባ በሽታ የድብርት ተጠቂዎች ላይ በስፋት ይታያሉ

ድሮ ድሮ በስልጣኔ ያደጉና የበለፀጉ አገራት ችግር እንደሆነ ይታሰብ የነበረው Depression (ድብርት) ዛሬ ምን በልተን እናድር ይሆን የሚል ሃሳብ ሰቅዞ የያዛቸው ታዳጊ አገራትም አሳሳቢ ችግር ሆኗል፡፡ ችግሩ ከገጠር አካባቢዎች በባሰ መልኩ በከተማ ውስጥ በሚኖሩ ሰዎች ላይ ጐልቶ ይታያል፡፡ በዚህ ዙሪያ የተደረጉ በርካታ ጥናቶች እንደሚያመለክቱትም ስልጣኔና ቴክኖሎጂ የሰው ልጅ በድብርት ችግሮች ለመያዙ ዋነኛ ምክንያቶች እየሆኑ ነው፡፡ የሰው ልጅ ኑሮው ውስብስብ እየሆነ በሄደና በቴክኖሎጂ ባደገ ቁጥር ለውጥረትና ድብርት ችግሮች የመጋለጡ ሁኔታ እየጨመረ ይሄዳል፡፡ ከመጠኑ ያላለፈ ጭንቀት ሰውነትን ለማንቃት እንዲሁም ራስን ለነገሮች ዝግጁ አድርጐ ለማቆየት እንደሚረዳ የሚናገሩት በዘርፉ ጥናት ያደረጉ ባለሙያዎች፤ ጭንቀቱ ከግለሰቡ ሁኔታዎችን የመቆጣጠር አቅም በላይ በሚሆንበት ወቅት ድብርትን በመፍጠር በሽታ ይሆናል ይላሉ፡፡ ድብርት በራሱ በሽታ የመፍጠር ባህርይ ባይኖረውም ለተለያዩ በሽታዎች መከሰት ምቹ ሁኔታዎችን ይፈጥራል፡፡ ድብርት በሰው ልጅ አዕምሮ ላይ በሚፈጠረው ጫናም ሥነልቦናዊ ቀውስ ይከሰታል፡፡

Saturday, 08 September 2012 12:38

የፌጦ ፍትፍትና እንቁጣጣሽ!

የፌጦ ህክምና ሳይንሳዊ ፋይዳ የለውም

የክረምቱ ወራት ተጠናቆ ወርሃ መስከረም ሊከት እነሆ ሁለት ቀናት ብቻ ቀርተውታል፡፡ የአዲስ ዘመን፣ የአዲስ ተስፋ፣ የአዲስ ዓመት መጀመሪያ የሆነውን ወር ሁሉም እንደአቅሙና እንደ ባህሉ ሊቀበለው ጉድ ጉዱን ተያይዞታል፡፡ አዲስ ዓመት ሲመጣ ገላን፣ ህሊናን፣ ልብስን፣ ንፁህ አድርጐ መቀበል ከጥንት የመጣ ኢትዮጵያዊ ባህል ነው፡፡ በአብዛኛው የአገሪቱ ክፍል በተለይም በገጠራማው አካባቢ የጳጉሜ ወር የመታጠቢያና የመጠመቂያ ወር ነው፡፡ በጳጉሜ ወር ወደ ወንዝ ወርዶ ገላ መታጠብ ከሀጢአት ሁሉ እንደመንፃት፣ ሀጢአትን አጥቦ እንደ ማስወገድ ይቆጠራል፡፡ በወረሃ ጳጉሜ በ3ኛው ቀን በዝናብ መታጠብ እንደ ፀበል መጠመቅ፣ እንደ መንፈሳዊ ፈውስም ይታያል፡፡