Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62

ሕብረት ባንክ ካለፈው ዓመት በ200 ሚ.ጂ የሚበልጥ ገቢ በማሰባሰብ፤ 300 ሚ.ብር ብር አተረፈ፡፡
በዓለም አቀፍና በአገር ውስጥ የኢኮኖሚ ችግሮች ቢኖሩም የደንበኞችን ፍላጐት በመጠበቅ ዓመቱን በስኬት ማጠናቀቃቸውን የጠቀሱት የዲሬክተሮች ቦርድ ሊቀመንበር፤ አምና የነበረውን 6.1 ቢሊዮን ብር ተቀማጭ ሂሳብ በማሳደግ፣ 6.8 ቢሊዮን ብር እንደደረሰ ተናግረዋል፡፡ በብድር ዘርፍም ከአምናው 3.3 ቢሊዮን ብር በ25 በመቶ የበለጠ 4.1 ቢሊዮን ብር ማበደራቸውን ተናግረዋል፡፡ የምንዛሬ አቅርቦትን ጨምሮ ከዓለም አቀፍ የባንክ አገልግሎት የተገኘው 520ሚ. ብር ከአምናው በ80 ሚ. ብር እንደሚበልጥ ጠቅሰው፤ ከባንኩ አጠቃላይ ገቢ 47 በመቶ በመሸፈን ዋነኛ የባንኩ የገቢ ምንጭ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

በጋና አክራ በተካሄደው 18ኛው የዓለም ጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዝ ጉባኤ የ“ወርልድ ውሜን ትሬድ ፌር አፍሪካ” ዳይሬክተር ወ/ሮ መቅደስ መኩሪያ የክብር ሽልማት የተሸለሙ ሲሆን ኢትዮጵያ 20ኛውን የዓለም ጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዝ ጉባኤ በ2014 ዓ.ም እንድታዘጋጅ ተመርጣለች፡ በጋናው ጉባኤ የመቀሌ ነጋዴ ሴቶች ማህበር ሦስት ተወካዮችና የአባይ ባንክ ፕሬዚዳንት ወ/ሮ መሰንበት ሸንቁጤ ተሳትፈዋል፡፡ የአባይ ባንክ ፕሬዚዳንት በጉባኤ ላይ ባደረጉት ንግግር፤ “ኢትዮጵያ በጥቃቅንና አነስተኛ የት ደርሳለች? ምን ልምድስ አላት?” በሚልና “ባንክና ሴቶች” በተሰኘ ርዕሰ ጉዳይ የአባይ ባንክ ከሴቶች ጋር ያለውን ግንኙነትና የአሰራር ልምድ ለታዳሚዎች አጋርተዋል፡፡ 

ብር ሳይዙ በአዋሽ ካርድ መገበያየት ይቻላል
በግል ባንኮች ምሥረታ ቀዳሚ የሆነው አዋሽ ኢንተርናሽናል ባንክ ባለፈው ዓመት ከታክስ በፊት 531 ሚሊዮን ብር ማትረፉን እንዲሁም 394.4 ሚሊዮን ብር የተጣራ ትርፍ ማግኘቱን አስታወቀ፡፡ የባንኩ ጠቅላላ ገቢ ከ1.1 ቢሊዮን ብር በላይ፣ የባንኩ የተከፈለ ካፒታል ከ912 ሚሊዮን ብር በላይ መድረሱንና ጠቅላላ ሀብቱም ከ19 ቢሊዮን ብር በላይ መሆኑን ገልጿል፡፡
ተደራሽነቱን ለማስፋት ባደረገው እንቅስቃሴ ባለፈው ዓመት 16 አዳዲስ ቅርንጫፎች በመክፈት በአገሪቱ ያሉትን የቅርንጫፎች ብዛት 88 ማድረሱን ጠቅሶ፤ በዚህ ዓመትም 20 አዳዲስ ቅርንጫፎች ለመክፈት ማቀዱን አስታውቋል፡፡

44ኛው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ባራክ ኦባማ በድጋሚ በመመረጣቸው ታዋቂ የሆሊውድ እና የመዝናኛው ኢንዱስትሪ ዝነኞች ተደሰቱ፡፡ በሌላ በኩል የኦባማ ተፎካካሪ የነበሩት ሮምኒ ደጋፊ የሆኑት ዶናልድ ትራምፕ፤ “አብዮት ያስፈልገናል” ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡ ዝነኞች በትዊተር ማስታወሻቸው ላይ ደስታቸውን የሚገልፁ ፅሁፎች ያሰፈሩ ሲሆን ኬቲ ፔሪ “ተሳካ”፤ ኮሜድያን ስቲቭ ማርቲን “የኦባማን ድል መታሰቢያ ያደረገ የሻይ ፓርቲ እደግሳለሁ”፤ ሪኪ ማርቲን “እኩልነት ያወጣል”፤ አንጋፋዋ ድምፃዊ ሼር “አሸነፍን አሸነፍን! ታላቁ አምላክ አሸነፍን፤”  ታዋቂዋ የቲቪ ተዋናይት ኢቫ ሎንጎርያ “እንባዬ መጣ በኦባማ አገሬ ወደፊት ትገሰግሳለች፤”  ሌዲ ጋጋ “ፕሬዝዳንት ባራክ ኦባማ ኮራሁብህ፤ አሜሪካዊነት እጅግ ያኮራል፤ አዎ አዎ አዎ በአሜሪካዊነቴ እኮራለሁ” እያሉ በትዊተር ማስታወሻቸው ፅፈዋል፡፡

በመላው ዓለም መታየት ከጀመረ ሁለት ሳምንት ባለፈው 23ኛው የጀምስ ቦንድ ፊልም “ስካይ ፎልስ” ላይ የተወነው ዳንኤል ክሬግ፤ በትርፋማነቱ “ምርጡ ቦንድ” በሚል ተደነቀ፡፡በ2006 እ.ኤ.አ በተወነው “ካሲኖ ሮያሌ” እና በ2008 እ.ኤ.አ በሰራው “ኳንታም ኦፍ ሶላስ” በተባሉት 21ኛው እና 22ኛው የጀምስ ቦንድ ፊልሞች 1.22 ቢሊዮን ዶላር ገቢ በማስገባት የቦንድን ፊልም ከሰሩ ስድስት ተዋናዮች መካከል ዳንኤል ክሬግ የመሪነት ደረጃውን ሊይዝ በቅቷል፡፡ አዲሱ የቦንድ ፊልም ላይ ተዋናይ “ከት ትሮት ራዘር” የተባለውን ፂም መላጫ በመጠቀም ያሳየው ትወና የምርቱን ገበያ በ405 ፐርሰንት ማሳደጉን የገለፀው ዴይሊ ቴሌግራፍ፤ ከ60 እስከ 300 ዶላር ዋጋ ያለው ፂም መላጫ ተፈላጊነቱ በከፍተኛ ደረጃ ጨምሯል ብሏል፡፡

ሰር ኤልተን ጆን ባለፉት 60 ዓመታት በብሪታኒያ የሙዚቃ ገበያ ውስጥ በነጠላ ዜማ ከፍተኛ ሽያጭ በማስመዝገብ የአንደኝነት ደረጃ አገኘ፡፡ በእንግሊዝ ከሚሊዮን ቅጂዎች በላይ ለመሸጥ የቻሉ 123 ነጠላ ዜማዎች በማወዳደር በወጣው የደረጃ ሰንጠረዥ፣ ሰር ኤልተን “ሰምቲንግ አባውት ዘ ዌይ ዩ ሉክ ቱናይት” በተሰኘ ዘፈኑ የአንደኝነት ደረጃን ተቆጣጥሯል፡፡ ለዌልሷ ልእልት ዲያና መታሰቢያነት በ1997 እ.ኤ.አ የተሰራው ይሄው ነጠላ ዜማ ለአምስት ሳምንት ገበያውን በመምራት 4.9 ሚሊዮን ቅጂዎች ተቸብችቧል፡፡ ሁለተኛ ደረጃ ያገኘው ነጠላ ዜማ በ1984 እ.ኤ.አ በባንድ ኤይድ የተሰራው “ዱ ዘይ ኖው ኢትስ ክሪስማስ” የተሰኘ ዜማ ሲሆን 3.6 ሚሊዮን ቅጂዎች ተሸጧል፡፡ በ1975 እ.ኤ.አ የተለቀቀው የኩዊንስ “ቦሄምያን ራህፕሶዲ” 2.36 ሚሊዮን ቅጂዎች ተሸጦ ሶስተኛ ደረጃን አግኝቷል፡፡ ቢትልሶች 6 ነጠላ ዜማዎቻቸውን በሽያጭ ደረጃ ውስጥ በማካተት ቀዳሚዎቹ ሲሆኑ ጆንትራ ቮልታ፣ ኦሊቪያ ኒውተን ጆን፣ ቦኒ ኤም፣ ሴሌንዲዮንና ስፓስይ ገርልስ ሁለት ሁለት ዜማዎችን ማስመዝገብ ከቻሉት መካከል ይጠቀሳሉ፡፡

Saturday, 10 November 2012 15:50

የሄሊ ቤሪ ትወና ተደነቀ

ወደ ትወና ከገባች በኋላም በሆሊዉድ በአንድ ፊልም እስከ 10 ሚሊዮን ዶላር ከሚከፈላቸው ተዋናዮች አንዷ ለመሆን የበቃች ስኬታማ ተዋናይት ናት፡፡ ሄሊ ቤሪ በ2001 እ.ኤ.አ በሰራችው “ሞንስተርስ ቦል” የተሰኘ ፊልም በምርጥ ተዋናይነት ኦስካር ተሸልማለች፡፡ዘንድሮ ከአዲስ ፍቅረኛዋ ከፈረንሳዊው ኦሊቨር ማርቲኔዝ ጋር  ቀለበት ያሰረችው ሄሊ ቤሪ፤ በዚሁ ዓመት ከዚሁ ፍቅረኛዋ ጋር ትዳር ለመመስረት የነበራት እቅድ ከሽፎባታል፡፡ ምክንያቱ ደግሞ ከሦስተኛ ባሏ ገብሬል አውብሪ ጋር የጀመረችውን የፍርድ ቤት ክርክር ባለማጠናቀቋ እንደሆነ ታውቋል፡፡ በ40ዎቹ እድሜ መጀመሪያ  ላይ የልጅ እናት መሆኗን የወደደችው  ሄሊ ቤሪ፤ ሌላ ልጅ የመውለድ ከፍተኛ ፍላጎት እንዳላት ሰሞኑን ተናግራለች፡፡ “ከአራት ዓመት ልጄ ከናሃላ ጋር ማታ ማታ ሌላ ልጅ እንዲሰጠኝ አምላክን በፀሎት እንማፀናለን” ብላለች -  ለ”ፒፕል” መፅሄት በሰጠችው ቃለ ምልልስ፡፡


200 መቀመጫ ያለው ሲኒማ ቤቱ፤ በወቅቱ የፊልም ቴክኖሎጂ የተደራጀ ነው ተብሏል፡፡ በሌላም በኩል በእስክንድር መርሃጽድቅ የተዘጋጀው “ቀይ ሥሮች እና ሌሎች…”መጽሐፍ ማክሰኞ ፒያሳ በሚገኘው የብሔራዊ ሎተሪ አዳራሽ ይመረቃል፡፡ ከቀኑ 11 ሰዓት የሚመረቀው ባለ 120 ገጽ መጽሐፍ፤ 20 ማህበራዊ ትችቶችና ሌሎች ጉዳዮች ያካተተ ነው፡፡ በቀይሽብር ሰማእታት ቤተመዘክር የሚገኘው “ኢዮሃ ሲኒማ” ነገ ከጠዋቱ 3 ሰዓት እንደሚመረቅ ድርጅቱ ገለፀ፡፡

በአርቲስት ታምሩ ብርሃኑ የተዘጋጀው “ባለሥልጣኑ” የተሰኘው ፊልም ነገ እና ማክሰኞ እንደሚመረቅ አዘጋጆቹ አስታወቁ፡፡ በፊልሙ ላይ ታምሩ ብርሃኑ፣ ሱራፌል ተካ፣ ሃና ዮሐንስ፣ አበበ ተምትም፣ ወለላ አሰፋ፣ ታጠቅ ነጋሽ፣ ፍቅርተ ጌታሁን እና ሌሎችም ተውነዋል፡፡ ፊልሙ ነገ በአዲስ አበባ የግል ሲኒማ ቤቶች እና በመንግስታዊው የስቴርዮ ሲኒማ በዋነኛነት ደግሞ ማክሰኞ ምሽት በኢትዮጵያ ብሔራዊ ትያትር እንደሚመረቅ ተገልጿል፡፡

ወጣትና አንጋፋ ገጣሚያን በሙዚቃ እየታጀቡ ግጥሞች የሚያቀርቡበት “ግጥምን በጃዝ” ፕሮግራም የፊታችን ረቡዕ ከምሽቱ 12 ጀምሮ እንደሚቀርብ አዘጋጆቹ አስታወቁ፡፡ በራስ ሆቴል ትልቁ አዳራሽ በሚቀርበው ዝግጅት ላይ አንጋፋዋ አርቲስት ሙሉአለም ታደሰ የትያትር ቅንጭብ የምታቀርብ ሲሆን አርቲስት አለማየሁ ታደሰ፣ ሜሮን ጌትነት፣ ምንተስኖት ማሞ፣ ምስራቅ ተረፈ፣ ደምሰው መርሻ፣ በኃይሉ ገብረመድህን ደግሞ የግጥም፣ የወግ እና የዲስኩር ሥራዎቻቸውን ለታዳሚዎች ያቀርባሉ፡፡ የዝግጅቱ መግቢያ ዋጋ 50 ብር እንደሆነ ለማወቅ ተችሏል፡፡