Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62

Saturday, 17 November 2012 11:59

የግጥም ጥግ

ተወኝ
ላታስታምም አትመመኝ
ላትወስደኝ አታንጠልጥለኝ
ይቅር፣ አንጀቴን ቁረጠኝ
ጋሽዬ፣ አልወድሽም በለኝ፡፡
እጅ እጅ አልበል አታባከነኝ
ባክህ፣ ወንድ ነው ቆራጡ፣ እንትፍ - እርግፍ አርገህ ተወኝ፡፡
አየህ፣ እንዳንተ አባት አለኝ
ሴት በወለድኩ ተዋረድኩሀ፣ ረከስኩ ቀለልኩ እሚለኝ፣
እኔም እንዳንተ እህት አለኝ
ሥጋሽን ሳይሆን ልብሽን ፣ ከፍተሽ ጥለሽ ነው እምትለኝ
እና ተወኝ፣ ባክህ ተወኝ፤
እንዳንተ እኔም አለኝ እናት

Saturday, 17 November 2012 11:36

ስጦታው

አውቶብሱ በሰዎች ጢቅ ብሎ ሞልቷል፡፡ ወጣት፣ ሽማግሌ፣ ወይዛዝርት፣ ባልቴት…በግልም በቡድንም ተሳፍረው እየፈሰሱ ነው - እንደ ዥረት፡፡ የሁሉም መድረሻ ለየቅል ነው - እንደሃሳባቸው፡፡ አውቶብሱ ተሳፋሪዎችን ከወዲህ ወዲያ እያላተመ በልሙጡ አስፋልት ላይ ይከንፋል፡፡ ከአውቶብሱ ተሳፋሪዎች ሁሉ ጐልተው የሚታዩት ሁለቱ ናቸው - የሚያጓጓ የአበባ ዕቅፍ የያዙት ሽማግሌና ዝንጥ ያለችው ድንቡሽቡሽ ወጣት፡፡ ሽማግሌው 60 ዓመት ገደማ ይሆናቸዋል፡፡ ወጣቷ ከ25 ዓመት አይበልጣትም፡፡ አውቶብሱ ላይ ከተሳፈረችበት ቅጽበት አንስቶ ዓይኗን ማዶ የተቀመጡት ሽማግሌ ላይ ጥላለች፡፡ አንዴ ሰውየውን ሌላ ጊዜ ዕቅፍ አበባውን ትክ ብላ ታያለች - በስስት፡፡

ከሠላሣ ስድስት ዓመታት በፊት የኢትዮጵያ ምሥራቃዊ ምድር የሃዘን፣ የሥቃይና የመከራ ምድር ሆኖ ነበር፡፡ ገና በክረምቱ መግቢያ ወቅት የዚያድባሬ መንግስት ወታደሮች በዶሎ፣ በቡሬና በጐዴ ከተሞች ላይ ወረራ አካሄዱ፡፡ ህፃናት፣ ሴቶችንና አቅመ ደካማ አረጋውያንን ሣይቀር እየገደሉ ከተሞቹን ተቆጣጠሯቸው፡፡በምሥራቃዊው የአገሪቱ ክልል አካባቢ ውጥረቱ አየለ፡፡ በሠላም ወጥቶ መግባት የማይታሰብ ሆነ፡፡ በብረት ለበስ መሣሪያዎች፣ በመድፍና በቢኤም 23 ሮኬቶች ተደራጅቶ ለወረራ የመጣውን የሶማሊያ ጦር ለመቋቋም የሚያስችል መሣሪያ ቀርቶ ሮጦ ለማምለጥ አቅም እንኳን ያልነበራቸው ደካማ የጅጅጋና ዙሪያዋ አካባቢ ነዋሪዎች ሐምሌ 12 ቀን 1969 ዓ.ም ማለዳ ላይ መከራ ዘነበባቸው፡፡

Saturday, 17 November 2012 11:04

“የእኛ ሰዎች በየመን”

የመን-የኢትዮጵያውያን ስደተኞች ገሐነም!
አሁን የያዝነው ዘመን የአለማችን ግንባር ቀደም ባለፀጋ ሀገራት ለሚባሉት አውሮፓና አሜሪካ እንኳን የተመቸ አይደለም፡፡ በሚሊዮን ለሚቆጠሩ የአለማችን ህዝቦች የስደትና የመልካም ህይወት ህልም የነበረው ባለፀግነታቸው እክል ገጥሞታል፡፡ እንደ አሜሪካና አውሮፓ አይሁን እንጂ ሌሎች ባለፀጋ የእስያ ሀገራትም የኢኮኖሚ እክሉ ውሽንፍር በሸካራ ምላሱ ልሷቸዋል፡፡ ኢኮኖሚያዊው ችግር በነዋሪዎቹ ወይም በዜጐቹ ላይ የጣለው የፈተና ቀንበር አንድ እጅ ቢሆን በስደተኞች ላይ ግን ሸክሙ በአስር እጥፍ የከበደ ነው፡፡ እናም ይህ የያዝነው ዘመን ለአለም ስደተኞች ከምንጊዜውም ይልቅ እጅግ የከፋና ከእሬት ይልቅ የመረረ ነው፡፡

የአለም ጤና ድርጅት መድሃኒቶችን ለህመምተኞች በሚስማማ መልኩ በተለያየ አይነትና መጠን ተዘጋጅተው በሽታን ለማከም የሚያገለግሉ ኬሚካሎች ናቸው ሲል ይተረጉማቸዋል፡፡ እነዚህ ኬሚካሎች በተለያየ መንገድ ወደ ሰውነታችን ውስጥ ከገቡ በኋላ ለበሽታ ፈውስ ቢያስገኙም የሚያስከትሉት ተያያዥ የጐንዮሽ ጉዳት አላቸው፡፡ የዓለም ጤና ድርጅት ይፋ የሚያደርጋቸው መረጃዎች እንደሚያመለክቱትም፣ ሁሉም መድሃኒቶች የጐንዮሽ ጐጂ ባህርያት አሏቸው፡፡ መድሃኒቶች በጥቅም ላይ በሚውሉበት ወቅትም ይኸው የጐንዮሽ ጐጂ ባህሪያቸው ይጠናል፡፡

 

በተለያዩ በዓላት፣ በህዝባዊ ሰልፎች፣ በስፖርታዊ ውድድሮች፣ በመምህርት ተቋማት፣ በንግድ ማዕከሎች … ወዘተ ተንጠልጥለው ወይም ተሰቅለው የማያቸውን ብዙዎቹን የሰንደቅ ዓላማዎች ከሰንደቅ ዓላማ አዋጁ ድንጋጌዎች አንፃር ስመለከታቸው አዋጁ ስለመኖሩ እንድጠራጠር ያደርገኛል። ላለፈው አንድ ዓመት ሰንደቅ ዓላማችንን በተመለከተ የታዘብኩትን ጥቂት ነገር ላካፍላችሁና ፅሑፌን ልጀምር።
ነሐሴ 2003 ዓ.ም፡- መገናኛ አካባቢ ባለ መንግስታዊ መ/ቤት አጠገብ ሳልፍ ከቅፅር ግቢው ውስጥ በተሰቀለው ሰንደቅ ዓላማ ላይ ዓይኖቼ ተተክለው ቀሩ። ሰንደቁ ላይ የሚውለበለበው የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ ተዘቅዝቆ ነበር።

አንድ የህንዶች ተረት እንዲህ ይላል፡፡
የዱር እንስሳት ተሰብስበው የወቅቱን ችግራቸውን ለመፍታት የወያያሉ አሉ፡፡
በመጀመሪያ ሰስ ተነስታ፤
“ቅጠለ - በል (Herbivore) እንስሳት እኔ ከምመገበው ዛፍ እየበሉ አስቸግረውኛልና አንድ መላ ይበጅልኝ” ስትል አመለከተች፡፡
ለመልሷም፤ ተሟጋቾቿ፤
“ዱር የበቀለ ዛፍ የማንኛችንም ሀብት ነውና የብቻዬ ብላ ልትጠይቅ አይገባም” ተባለች፡፡
ቀጥሎ ጅብ ያነሳው አቤቱታ፤
“እኔ በጭለማ ደፋ ቀና ብዬ ያገኘሁትን አህያ፣ ሌሎች ቀን መንቀሳቀስ የሚችሉ እንስሳት ይቀራመቱኛልና ማዕቀብ ይጣልልኝ” ሲል ጠየቀ፡፡

አንድ የህንዶች ተረት እንዲህ ይላል፡፡
የዱር እንስሳት ተሰብስበው የወቅቱን ችግራቸውን ለመፍታት የወያያሉ አሉ፡፡
በመጀመሪያ ሰስ ተነስታ፤
“ቅጠለ - በል (Herbivore) እንስሳት እኔ ከምመገበው ዛፍ እየበሉ አስቸግረውኛልና አንድ መላ ይበጅልኝ” ስትል አመለከተች፡፡
ለመልሷም፤ ተሟጋቾቿ፤
“ዱር የበቀለ ዛፍ የማንኛችንም ሀብት ነውና የብቻዬ ብላ ልትጠይቅ አይገባም” ተባለች፡፡
ቀጥሎ ጅብ ያነሳው አቤቱታ፤
“እኔ በጭለማ ደፋ ቀና ብዬ ያገኘሁትን አህያ፣ ሌሎች ቀን መንቀሳቀስ የሚችሉ እንስሳት ይቀራመቱኛልና ማዕቀብ ይጣልልኝ” ሲል ጠየቀ፡፡
ሌሎቹ እንስሳትም፤

. ቤተክህነቱ በደብሩ አለቃ የሚፈጸመውን ሙስናና የአስተዳደር በደል መቆጣጠር ተስኖታል
. የውቅር አብያተ መቅደሱ የቱሪስት ገቢ ተቆጣጣሪ የለውም፤ የቅርሶቹ ጉዳት ተባብሷል
. በደብሩ ገንዘብ የተሠሩት የቤተ አብርሃም እና ይምርሐነ ሆቴሎች ባለቤት አይታወቅም
በሰሜን ወሎ ሀገረ ስብከት በሚገኘው የቅዱስ ላሊበላ ደብር የሚያገለግሉ ካህናት እና ምእመናን÷ በደብሩ አስተዳዳር በሚፈጸመው ሙስናና የአስተዳደር በደል መማረራቸውንና አቤቱታቸው ሰሚ አለማግኘቱን ለአዲስ አድማስ ገለጹ፡፡ በሚሊዮን የሚቆጠር የቱሪዝም ገቢ የግል ሀብትን ለማደለብ እየዋለ መኾኑን የጠቆሙት ካህናቱ÷ በቅርሶች ላይ የሚደርሰው ጉዳት በከፍተኛ ደረጃ መባባሱን፣ሙሰኝነትንና የአሠራር ብልሹነትን የሚቃወሙና የሚያጋልጡ ካህናትና ሠራተኞች ለመባረርና ለእስር መዳረጋቸውን ተናግረዋል፡፡

ለመነኰሳቱ የአስቸኳይ ጊዜ የምግብና የአልባሳት እርዳታ ጥሪ ቀርቧል
በሰሜን ጎንደር ሀገረ ስብከት ዓዲ አርቃይ ወረዳ የሚገኘው የጥንታዊው ዋልድባ ደልሽሐ ኪዳነ ምሕረት ማኅበረ ደናግል ገዳም ሴት መነኰሳት ኳሬዳ በተሰኘ ትልና በአካባቢው በብዛት በሚፈላው ምስጥ መቸገራቸውን ለገዳሙ የራስ አገዝ ልማት ርዳታ ለማሰባሰብ የተቋቋመው ኮሚቴ ገለጸ፡፡ ትሉ መነኰሳ ቱ ለዘመናት የኖሩባቸውን ጎጆ ቤቶች /የሣር መክደኛ/ ምቹ መራቢያ እንዳደረገው የተገለጸ ሲሆን ትሉን በምትገበው ኩቱ የተባለች ወፍ በሚራገፍበት ወቅት በመነኰሳቱ ቆዳ ላይ እያረፈ ሰውነታቸውን ያሳብጣል፤ ዕብጠቱ ከሚፈጥረው ሥቃይ ለመዳን መነኰሳቱ ሰውነታቸውን በምላጭ ስለሚበጡት ተጨማሪ ጉዳት እያስከተለባቸው ነው፡፡ በአካባቢው በብዛት የሚፈላው ምስጥ ሌላው የማኅበረ ደናግሉ ፈተና መኾኑ ሲሆን አረጋውያትና ሕሙማን መነኰሳት የሚረዱባቸውን የአልጋ ቆጦችና የቤት ቋሚዎች እየቦረቦረ በመጣል ለጉዳት እየዳረጋቸው መኾኑ ታውቋል፡፡