Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62

ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ የ2005/06 ዓ.ም. የመጀመርያውን ውድድር ነገ በጎንደር ከተማ ሊያካሂድ ነው፡፡ የጎንደሩ ውድድር ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ከተመሠረተበት 1993 ዓ.ም. ጀምሮ የተካሔዱትን ውድድሮች 83 ያደርሳል፡፡
በጎንደር ከተማ የሚካሔደው የአምስት ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫ 2,500 ተወዳዳሪዎች ይሳተፉበታል፡፡ የልጆችም ውድድር መዘጋጀቱን ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ አስታውቋል፡፡የታላቁ ሩጫ ውድድር በጎንደር ከተማ የተዘጋጀው ለመጀመርያ ጊዜ ቢሆንም በአማራ ክልል ውድድሩ በባህርዳር፤ ላሊበላ እና ደብረማርቆስ ውስጥ ተካሂዶ ያውቃል፡፡

“ይቅርታ!... ትናንት ያስቀመጥኩልዎትን ጥራዝ አነበቡልኝ ይሆን? ምን አስተያየት እንደሚሰጡኝ ለመስማት ቸኩያለሁ፡፡
…ለመሆኑ ተሰጥዖ አለኝ ብለው ይገምታሉ?”
“አዎ አለህ!” አሉት መምህሩ፡፡ ወጣቱ ግን አሁንም ዝም አላለም፡፡ ውስጡ ተንቀዠቀዠ፡፡ “ገጣሚ ይሆናል ብለው ይገምታሉዋ?” በማለት ጠየቀ፡፡ይህ ወጣት ዓላማው ገጣሚ መሆን ነው፡፡ ሆኖም ስንኝ ስለቋጠረ ወይም ስለተጨበጨበለት ብቻ ገጣሚ ነኝ ብሎ ነጋሪት አላስጎሰመም፡፡ መምህሩ የሚሰጠውን ሃሳብ ጠበቀ፡፡ ከዚህ ወጣት የምንማረው ነገር አለ፤ ፀሀፍት መሆን የሚሹ ሁሉ አዋቂዎች የጻፏቸውን መጽሃፍትና አንባቢዎች የሚለግሱትን ሃሳብ በአንክሮ ሊከታተሉ ይገባል፡፡

Saturday, 12 January 2013 09:49

የቀልድ ጥግ

የ80 ዓመት አዛውንት ለጠቅላላ የጤና ምርመራ (Checkup) ሆስፒታል ይሄዱና ሃኪማቸው “እንዴት ነው ጤንነትዎ?” ሲል ይጠይቃቸዋል፡፡
ሽማግሌውም “በጣም ጤና ነኝ ---እንደውም የ18 ዓመት ኮረዳ አግብቼልህ አርግዛልኛለች----ልጅ ላገኝ ነው --- መታደል ነው አይደል?” ይሉታል - ለሃኪሙ፡፡ ሀኪሙ ነገሩ አልተዋጠለትምና ትንሽ ሲያስብ ከቆየ በኋላ “አንድ ታሪክ አስታወሱኝ” በማለት ይነግራቸዋል፡፡
“አንድ እኔ የማውቀው አደን የሚወድ ሰውዬ ነበር፡፡ በቃ የአደን ነገር ጨርሶ አይሆንለትም፡፡

Saturday, 12 January 2013 09:47

በነገራችን ላይ

ነ.መ.
በነገራችን ላይ ማለት፣ ሁሉን ጐራሽ ሀረግ ሆኗል
ኑ መቃብር እንለካካ፣ ብሎ መጀመር ይቻላል
ኑሮን እንይ ከማለት፣ ሞትን መግለጽ ይቀላል፡፡
በነገራችን ላይ፤
ገዳይ በግፍ ገሎ ሳለ
ሟች ይጠየቅ ከተባለ
ገና ዕዳችን አላለቀም የባሰም ሌላ ግፍ አለ
ከሬሳችን የከበደ፣ ከህሊና የቀለለ!!
በነገራችን ላይ …
ከሟች የተረፈ እንዳለ
ከገዳይም ተራፊ አለ፡፡

ከአንኮራፋህ ብቻህን ትተኛለህ!” - ኖዌል ካዋርድ
የሀገራችን ደራሲና ተርጓሚ የሆነ ፀሐፊ በቅርቡ የስኮትላንዳውያንን ባህሪ አስመልክቶ ባሳተመው ቁም ነገር - አዘል የቀልድ መጽሐፍ የሚከተለው ይገኝበታል
ስኮትላንዳዊው በጣም ተቸግሯል፡፡ የንግድ ሥራው ተሰነካክሎ ከፍተኛ የፋይናንስ ቀውስ ውስጥ ነበር፡
በቀቢፀ - ተስፋ ተውጦ ፈጣሪውን፣
“እባክህን እርዳኝ፤ የመጠጥ ግሮሰሪዬ ተሸጠ፡፡

የኢትዮጵያ ሕዝብ ጨረቃን ከሰማይ አውርዱልን እያለ አይደለም። የኢትዮጵያ ሕዝብ እያለ ያለው ግልጽነትን፣ ቀጥተኝነትን፣ ቅንነትንና ሀቀኝነትን አውርዱልን ነው። ዴሞክራሲን አውርዱልን ነው። ቁሳዊ ልማት ብቻውን አይበቃም፣ ሰብአዊና መንፈሳዊ ልማትንም አውርዱልን ነው።
ዶ/ር ኃይሉ አርአያ
የጌታ ኢየሱስ መንገድ ስል የክርስትና ሃይማኖት ዕምነት ቀኖናውን (ዶግማውን) ሳይሆን ክርስቶስ በዚህ ምድር ላይ ሲያስተምር ያሳየውን የቀናነት፣ የሃቀኝነት፣ የግልጽነት፣ የፍትሓዊነት፣ የእኩልነት፣ የአንድነት፣ የነፃነት፣ የዴሞክራሲያዊነት፣ የመተሳሰብ፣ የመፈቃቀር፣የመከባበር፣ የመተማመን... መንገድ ማለቴ ነው። ይህ መንገድ የክርስትና ሃይማኖት ብቻ ሳይሆን የእስልምና እንዲሁም የሌሎች የዓለም ታላላቅ ሃይማኖቶች መንገድ ነው።

ሙሼ ሰሙ (የኢዴፓ ፕሬዚዳንት)
ላለፉት ስምንት ዓመታት ለመሰረተ ልማት ግንባታ ከፍተኛ ትኩረት የሰጠው የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ልማትንም ሆነ እድገት በማያወላዳ መልኩ ማረጋገጥ አልቻለም፡፡ አወዛጋቢ ቢሆኑም ኢኮኖሚያችን ላለፉት ስምንት ዓመታት ከአምስት ፐርስንት አጠቃላይ ዓመታዊ ምርት እድገት ተነስቶ አሁን ወደ አስር ፐርሰንትና ከዛም በላይ እንዳደገ በርካታ ዋቢዎችን መጥቀስ ይቻላል፡፡
ይህም ሆኖ እድገቱ ያስከተለው ኢኮኖሚያዊ ለውጥ እንደሚወራለት የመሰረተ ልማት፣ የገበያ ትስስርና የምርታማነትን ችግር ፈቶ የኢኮኖሚዊ መዋቅር ሽግግርን በአስተማማኝ ሁኔታ በማረጋገጥ እድገቱ (Growth) በሂደት ወደ ልማት (Development) ተስፋፍቶ የዜጎችን የኑሮ ሁኔታ ማሻሻል የሚችል አስተማማኝ ኢኮኖሚ መሆኑን ማረጋገጥ አለመቻሉ የብዙዎቻችን ጥያቄና የሃገሪቱ ፈተና እንደሆነ መቀጠሉ ግልጽ ነው፡፡

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ አስቸኳይ የምልአተ ጉባኤ ስብሰባውን የፊታችን ሰኞ፣ እንደሚያካሂድ ተገለጸ፡፡ በሲኖዶሱ አቸስኳይ ምልአተ ጉባኤ ስብሰባ፣ በሀገር ውስጥ እና በሰሜን አሜሪካ በስደት በሚገኙት ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት መካከል በተጀመረው የዕርቅና ሰላም ውይይት ቀጣይነት ላይ በመነጋገር ዐቢይ ትርጉም ያለው ውሳኔ ያሳልፋል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
አዲስ አድማስ ከጠቅላይ ቤተክህነቱ ምንጮች እንደተረዳው፤ ሲኖዶሱ በዕርቅና ሰላም ውይይቱ ቀጣይነት ላይ የሚወያየው፣ ከኅዳር 26-30 ቀን 2005 ዓ.ም በዳላስ ቴክሳስ በተካሄደው የዕርቀ ሰላም ጉባኤ የተሳተፈው ልኡክ በሚያቀርበው ሪፖርት ላይ በመመሥረት ነው፡

አንዳንድ ተረቶች ካልተደጋገሙ አይሰሙም፡፡ “ተናገርን ማንም ስለማይሰማ፤ ደግመን እንናገረዋለን” ብሏል አንድ ፀሐፊ፡፡ (We said it; as no one listens, we will say it again) አወጋጉን እንለውጠው እንጂ ወጉ የዱሯችን ነው!
ከዕለታት አንድ ቀን ሁለት ደገኞች ጐረቤታሞች ነበሩ ይባላል፡፡ የኑሮ እሽክርክሪት አልለወጥ ብሏቸዋል፡፡ ያርሳሉ፤ ያርሳሉ፤ ያርሳሉ፡፡ ኑሮ አልገፋ አላቸው፡፡ እንደውም አንዳንዴ እየከፋ፣ እየባሰ ይመጣ ጀምሯል፡፡
ከጥቂት ጊዜ በኋላ አንደኛው ገበሬ በድንገት በልጽጐ ታየ፡፡

ከ31 ዓመታት በኋላ በአፍሪካ ዋንጫ ለመሳተፍ የበቃው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በ29ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ከፍተኛ ድጋፍ በስታድዬም ያገኛሉ ተብለው ከሚጠበቁት ብሔራዊ ቡድኖች አንዱ ሆኗል፡፡ በደቡብ አፍሪካ የሚኖሩ ከ40ሺ በላይ ኢትዮጵያውያን ቡድኑን ለመደገፍ ከፍተኛ እንቅሰቃሴ በማድረግ ላይ መሆናቸው እየተገለፀ ይገኛል፡፡ ይህም ኢትዮጵያ ከደቡብ አፍሪካ፣ ከዛምቢያና ከአንጓላ ቀጥሎ በአፍሪካ ዋንጫው በከፍተኛ ደረጃ ድጋፍ ሊያገኙ ከሚችሉት አገራት ጋር ያሳልፋታል፡፡ የ29ኛው የአፍሪካ ዋንጫ አዘጋጅ ኮሚቴ ከሳምንት በፊት ይፋ ባደረገው መረጃ መሠረት ኢትዮጵያ ለውድድሩ በቀረቡ ትኬቶች ግዢ ሁለተኛ ደረጃ ላይ ናት፡፡

Page 2 of 163