Saturday, 30 June 2012 12:43

“ፍልስምና ፪” ዛሬ ለንባብ ይበቃል

Written by  መልካሙ ተክሌ (melkamutekele@gmail.com)
Rate this item
(1 Vote)

“መምህሩ” እየተሸጠ ነው

በፀሃፌ ተውኔት፣ ጋዜጠኛና ደራሲ ቴዎድሮስ ተክለአረጋይ የተዘጋጀው “ፍልስምና ፪” ከዛሬ ጀምሮ ለንባብ እንደሚበቃ አዘጋጁ ለአዲስ አድማስ ገለፀ፡፡ዶ/ር ዳኛቸው አሰፋ የአውራምባ ማህበረሰብ መሪ፣ ዙምራ ኑሩ መጋቤ ሃዲስ መምህር እሸቱ፣ አርቲስት ጀማነሽ ሰለሞን፣ አርኪቴክት ሚካኤል ሽፈራውና ሌሎች ባለሙያዎች በመፅሃፉ ቃለ መጠይቅ ውስጥ ተካተዋል፡፡ ቴዎድሮስ ተክለአረጋይ  “ሩብ ጉዳይ”፣ እና “ሰዓት እላፊ” በተሰኙት የመድረክ ተውኔቶቹ እንዲሁም “ቁምነገር” እና “አዲስ ጉዳይ” ላይ በሚሰራቸው ቃለመጠይቆች (Interview) ይበልጥ ይታወቃል፡፡

ከሃይማኖት፣ ከፍልስፍናና ከእውቀት ባለሙያዎች ጋር የተደረጉ ቃለምልልሶችን የያዘው ባለ 139 ገፆች መፅሐፍ ዋጋ 28 ብር ነው፡፡ይህ በዚህ እንዳለ “መምህሩ ዶ/ር ቶማስ” የተሰኘ መፅሐፈ ጨዋታ ባለፈው ሳምንት ገበያ ላይ ውሏል፡፡ በወሲብ፣ በጥበብ፣ በሴት፣ በማንነት፣ በኑሮ እና ምስጢር ላይ የተፃፈው ባለ ሁለት ክፍል የወግና የቀልዶች መፅሐፍ ዋጋ 30 ብር ነው፡፡በተመሳሳይ ዜና በዳኜ አሰፋ (የየውብዳር ልጅ) የተፃፈው ረዥም ልቦለድ መፅሐፍ ለንባብ በቃ፡፡ 234 ገፆች ያሉት መፅሐፍ በሀገር ውስጥ 40 ብር በውጭ ሀገራት 20 ዶላር ነው፡፡ ካሁን ቀደም ደራሲው “የሕይወት ምህዋር”፣ “የአዳም ስሞታ” እና “ሰዓት አልቋል” የተሰኙ መፃሕፍት ለንባብ አብቅቷል፡፡

 

 

 

Read 1815 times Last modified on Saturday, 30 June 2012 12:46