የደራሲ ቃልኪዳን ሀይሉ ሶስተኛ ስራ የሆነው “አላቲኖስ” ልብለድ መፅሐፍ ለ3ኛ ጊዜ በድጋሚ ታትሞ ለንባብ በቃ፡፡ መንፈሳዊና ታሪክ ቀመስ፣ የፍቅር የሳይንስና የስለላ ታሪክን ያካተተው ይሔው መፅሐፍ በ2010 ዓ.ም ለንባብ በቅቶ ተወዳጅነትን በማግኘቱ ሰሞኑን በድጋሚ ታትሞ ለንባብ መብቃቱን ደራሲው ገልጿል፡፡
በ307 ገፅ የተቀነበበው ይሄው መፅፍ 2010 ዓ.ም ህዳር ወር ላይ በድጋሚ ታትሞ የነበረ ሲሆን አሁን ለሶስተኛ ጊዜ መታተሙም ታውቋል፡፡
ደራሲ ቃልኪዳን ሀይሉ በማህበረሰብ ጤና ከደብረ ብርሃን ዩኒቨርስቲ ዲግሪውን ያገኘ ሲሆን ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ በጋዜጠኝትና ተግባቦት ትምህርት የማስተርስ ዲግሪውን ተቀብሏል፡፡
ደራሲው ከዚህ ቀደም “የነጎድጓድ ልጆች” “ለምን አትቆጣም” “አላቲኖስ” እና “ክብር” የተሰኙ መፅፍትን ለንባብ ያበቃ ሲሆን በ “ዳና” እና “ወላፈን” ተከታታይ የቴሌቪዥን ድራማዎች ደራሲነቱም እናውቀዋለን
Saturday, 07 May 2022 14:52
“አላቲኖስ” በድጋሚ ታትሞ ለንባብ በቃ
Written by ናፍቆት ዩሴፍ
Published in
ኪነ-ጥበባዊ ዜና