Monday, 03 July 2023 09:33

አፈቅርሻለሁ ነፍሴ፤

Written by 
Rate this item
(5 votes)

አፈቅርሻለሁ ነፍሴ፤
እንደ እራሴ
እንደ አበቦቹ ሽታ፤
እንደ ቢራቢሮ እስክስታ፤
እንደ ጥርኝ ጭቃ፤
ልክ እንደ ስጦታ ዕቃ፤
እወድሻለሁ እኔ፤ እወድሻለሁኝ፡፡
እንደ ፍልስፍና ሃሳብ፤
ሊጠግብ እንዳለ ረሃብ፤
እንደ ህፃን ልጅ ሳቅ፤
እንደ ዘላለማዊ ሃቅ፤
እወድሻለሁ እኔ፤ እወድሻለሁኝ፡፡
እንደ ሎጂክ፤
እንደ ተፈጥሮ ህግ፤
እንደ ቋንቋ፤
ልክ እንደ ሙሉ ጨረቃ፤
እወድሻለሁ እኔ፤ እወድሻለሁኝ፡፡
እንደ ሙዚቃ ቅንጣት፤
እንደ አልጋ ውስጥ ትኩሳት፤
ልክ እንደ እናቴ ስም፤
እንደ ልጅነቴ ህልም፤
እወድሻለሁ እኔ፤ እወድሻለሁኝ፡፡
እንደ ግጥም ስንኝ፤
አንጀሎ እንደጠረበው ቋጥኝ፤
እንደ ጠዋት እንቅልፍ፤
እንደ አየን ራንድ ፅሁፍ፤
እወድሻለሁኝ እኔ፤ እወድሻለሁኝ፡፡
እንደ ብርቱካን ውሃ፤
እንደ ብርሃን ዘሃ፤
እጄ ላይ እንደያዝኩት ሲጋራ፤
እንደ ቀዝቀዛ ቢራ፤
እንደ ሊዮናርዶ ሥራ፤
እወድሻለሁ እኔ፤ እወድሻለሁኝ፡፡
አፈቅርሻለሁ ፍቅር፤
አፈቅርሻለሁ ነፍሴ፤
ልክ እንደ እራሴ፡፡
(አሸናፊ አሰፋ)



Read 1300 times