Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Saturday, 17 September 2011 10:34

የየሊጎቹ ሻምፒዮኖች ተተነበ

Written by 
Rate this item
(0 votes)

በአውሮፓ 5 ታላላቅ ሊጎች የውድድር ዘመኑ ከተጀመረ 1 ወር ሲሞላው ሲአይኢኤስÂ ራኒንግ ቦል የተባሉ ሁለት ተቋማት በትብብር ባካሄዱት ጥናት በእንግሊዝ ቼልሲ፤ በስፔን ባርሴሎና፤ በጀርመን ባየር ሙኒክ እንዲሁም በፈረንሳይ ፓሪስ ሴንትዠርመን የሻምፒዮናነት እድል እንዳላቸው ገመቱ፡፡ በተቋማቱ የሚገኙ ተመራማሪዎች ይህን በጥናት ላይ የተመሰረተ ትንበያቸው ለማዘጋጀት በዋናነት ሶስት መስፈርቶችን ተከትለዋል፡፡ የክለቦችና የተጨዋቾች ልምምድና የዝግጅት ብቃት፤ የዓለም አቀፍ ውድድሮች ተሞክሮና የቡድኖች የተረጋጋ ስብስብ ዋና መለኪያቸው ነበሩ፡፡

በአምስቱ ሊጎች ባንድ ውድድር ዘመን በእንግሊዝ 196፤ በስፔን 188፤ በጣሊያን 177፤ በፈረንሳይ 152 እንዲሁም በጀርመን 85 ግጥሚያዎች ሻምፒዮናውን ለመወሰን የሚደረጉ ሲሆኑ ትንበያው የየሊጎቹ ክለቦች በእነዚህ ጨዋታዎች ላይ 98 ክለቦችና ተጨዋቾቻቸው ያሳዩት ብቃትን በመፈተሽም tqÂB…L፡፡ÆlfW አመት ተቋማቱ በሰሩት ጥናታዊ ትንበያ የተፎረሸው በእንግሊዝ ብቻ ሲሆን የሌሎች ሊጎችን ሻምፒዮኖች በመገመት  60 በመቶ túKè§cêL፡፡ አምና በእግርኳስ ኦብዘርቫተሪ ተቋማቱ ሲአይኢኤስ ራኒንግቦል ትብብር የተሰራው ጥናታዊ ትንበያ በፈረንሳይ ሊግ 1፤ በጀርመን ቦንደስ ሊጋ፤ በጣሊያን ሴሪኤ እና በስፔን ላሊጋ ምርጥ ክለቦች ተብለው 1ኛ ደረጃ የተሰጣቸው ሊል፤ ቦርስያ ዶርትመንድ፤ ኤሲ ሚላንና ባርሴሎና እንደቅደም ተከተላቸው የየሊጋቸው ሻምፒዮን ቢሆኑም የእንግሊዝ ምርጥ ክለብ አርሰናል ነው ተብሎ ሻምፒዮን እንደሆነ ቢተነበይም ዋንጫውን ያነሳው በ2ኛ ደረጃ ምርጥ ተብሎ የነበረው ማን ዩናይትድ ሆኗል፡፡በአውሮፓ 5ቱ ታላላቅ ሊጎች የውድድር ዘመኑ አጀማመር በስፔን ላሊጋ እና በጣሊያን ሴሪኤ ከተጨዋቾች ደሞዝና የኮንትራት ስምምነት በተያያዘ በተከሰቱ ውዝግቦች ቢስተጓጎሉም ሰሞኑን የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ሲጀመር በየሊጎቹ ውድድሮች በተረጋጋ በተመጣጣኝ ፉክክር መካሄዳቸውን ቀጥለዋል፡፡
በእንግሊዝ ፕሪሚዬር ሊግ እስከ 4ኛው ሳምንት በተደረጉ ጨዋታዎች ሁሉንም በድል ያደረጉት ሁለቱ የማንችስተር ከተማ ክለቦች ማን ዩናይትድና ማን ሲቲ በግብ ክፍያ በመበላለጥ በ12 ነጥብ 1ኛና 2ኛ ደረጃዎችን ሲይዙ ቼልሲ በ10 ነጥብ የሚከተል ሆኗል፡፡ የኮከብ ግብ አግቢነቱን ደረጃም ሁለቱ የማንችስተር ከተማ ክለቦች አጥቂዎች ሲያያዙበት የማን ዩናይትዱ ሩኒ በ8 ጎሎች ሲመራ የማን ሲቲዎቹ ኤድዊን ዜኮና ሰርጂዮ አጉዌሮ በ6 ጎሎች Yktlù¬L፡፡በጀርመን ቦንደስ ሊጋ በእኩል 12 ነጥብ  መሪነቱን የተናነቁበት ባየር ሙኒክና ዌርደር ብሬመን ሲሆኑ የኮከብ ግብ አግቢነቱን በ8 ጎሎች የሚመራው የባየር ሙኒኩ ማርዮ ጎሜዝ ነው፡፡ በስፔን ላሊጋ የመጀመርያ ሁለት ሳምንት ጨዋታዎች ማሸነፍ የቻሉት ሪያል ማድሪድ ፤ ቫለንሺያና ሪያል ቤቲስ እኩል 6 ነጥብ ይዘው በግብ ክፍያ በመበላለጥ ከ1-3 ያለውን ደረጃ tÃYzWb¬L፡፡ በ4 ጎሎች ኮከብ ግብ አግቢነቱን የሚመራው የማድሪዱ ክርስትያኖ ሮናልዶ ነው፡፡ ከተጀመረ አንድ ሳምንት በሆነው የጣሊያኑ ሴሪ ኤ ጁቬንትስ፤ ናፖሊና ፊዮረንቲና ሙሉ ነጥብ ይዘው በመሪነቱ ተያይዘዋል፡፡
በፈረንሳይ ሊግ 1  ደግሞመሪነቱን በ12 ነጥብ ያለተቀናቃኝ የያዘው ሞንትፕሌየር ነው፡፡በሌላ በኩል ሲአይኢኤስ ይፋ ባደረገው የ2011 የአውሮፓ እግር ኳስ ጥናታዊ ሪፖርት በዘንድሮው የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ የምድብ ፍልሚያ ላይ በተሰለፉ 32 ክለቦች ከ68 አገራት የተሰባሰቡ ፕሮፌሽናል እግር ኳስ ተጨዋቾች እንደሚገኙ ተመልክቷል፡፡ ስፔን በሻምፒዮንስ ሊጉ ተሳታፊ ክለቦች 81 ተጨዋቾችን በማስመዝገብ ግንባር ቀደም ሆናለች ፡፡ ፈረንሳይ በ77፤ ብራዚል በ69፤ ጀርመን በ60፤ አርጀንቲና በ45፤ እንግሊዝ በ42 እንዲሁም ጣሊያን በ41 ተጨዋቾች በመወከል እስከ ሰባት ያለውን ደረጃ አግኝተዋል፡፡ዩ

 

Read 4293 times Last modified on Saturday, 17 September 2011 10:38