የእንግሊዝ የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስቴር እንዳስታወቀው፣ ኤርትራ የጥገኝነት ጥያቄያቸው ውድቅ የተደረገባቸውንና በወንጀል የተያዙ ዜጎቿን ዳግም ለመቀበል ፈቃደኛ ባለመሆኗ በሀገሪቱ ዲፕሎማቶች ላይ የእንቅስቃሴና የቪዛ እገዳ ማዕቀብ ጣለች። በዚህም መሠረት በለንደን የሚገኙ የኤርትራ ዲፕሎማቶች ከከተማዋ ከ60 ኪሎ ሜትር በላይ እንዳይንቀሳቀሱ የተገደቡ ሲሆን፣ ለኤርትራ ከፍተኛ ባለሥልጣናት (VIPs) ይሰጡ የነበሩ ፈጣን የቪዛ አገልግሎቶችም ሙሉ በሙሉ መቋረጣቸው ተገልጿል።
የሀገር ውስጥ ሚኒስትሯ ሻባና ማህሙድ፣ ኤርትራ ከእንግሊዝ መንግሥት ጋር ትብብር ማድረግ ካልቻለች ወደ አገሪቱ የሚደረጉ ማንኛውንም የቪዛ አገልግሎቶች ሙሉ በሙሉ የመከልከል እርምጃ ሊወሰድ እንደሚችል አስጠንቅቀዋል። ባለፉት 12 ወራት ውስጥ አደገኛውን የባህር መንገድ አቋርጠው ወደ እንግሊዝ ከገቡ ስደተኞች መካከል ኤርትራውያን 18 በመቶውን ድርሻ እንደሚይዙ የብሪታንያ መረጃዎች ያመለክታሉ።
የቴሌግራም ቻናልችንን በመቀላቀል የአዲስ አድማስን መረጃ ይከታተሉ…
https://t.me/AdissAdmas
Friday, 16 October 2026 06:39
እንግሊዝ በኤርትራ ከፍተኛ ባለሥልጣናትና ዲፕሎማቶች ላይ ጠንካራ ማዕቀብ ጣለች
Written by Administrator
Published in
ዜና
