Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Saturday, 12 January 2013 10:05

የጀምስ ቦንድን ፊልም የሰራው ኤምጂኤም ከኪሳራ እየወጣ ነው

Written by 
Rate this item
(4 votes)

ከሁለት ዓመት በፊት በኪሳራ የመሸጥ አደጋ አንዣቦበት የነበረው ኤምጂኤም የፊልም ስቱዲዮ ከኪሳራ እያገገመ እንደሆነ “ዘ ሆሊውድ ሪፖርተር” ዘገበ፡፡ ባለፈው የፈረንጆች አመት የመጨረሻ ሶስት ወራት ላይ ለእይታ የበቃውና ከቢሊዮን ዶላር በላይ ያስገባው ሃያ ሶስተኛው የጀምስ ቦንድ ፊልም “ስካይ ፎልስ” የኤምጂኤም ስቱዲዮን ከኪሳራ ለማውጣት ከፍተኛ ሚና እንደነበረው ተገልጿል፡፡

“ዘ ሆቢት፡ አንኤክስፔክትድ ጆርኒ” የተባለው ፊልምም እስከ 800 ሚሊዮን ዶላር ገቢ በማስገኘት ኩባንያውን ከኪሳራ ታድጐታል ተብሏል፡፡ በሙሉ ስሙ ሜትሮ ጎልድዊን ማየር ፒክቸርስ ተብሎ ለሚጠራው ኤምጂኤም ኩባንያ ባንኮች እስከ 650 ሚሊዮን ዶላር ለማበደር ፍላጎት ማሳየታቸውን የጠቆመው “ዘ ሆሊውድ ሪፖርተር”፤ ብድሩ ኤምጂኤምን ከሶኒ እና ከዋርነር ብሮስ ኩባንያዎች እዳው ያላቅቀዋል ብሏል፡፡
ኤምጂኤም ከሁለት ዓመት በፊት በኪሳራ ሲንገታገት እንደ ታይምዋርነር አይነት 16 ትልልቅ የፊልም ኩባንያዎች ስቱዲዮውን ለመግዛት እስከ 3 ቢሊዮን ዶላር ለመክፈል ተዘጋጅተው ነበር ተብሏል፡፡

Read 10854 times