Saturday, 31 May 2014 14:16

ቫንጋል፤ አዲሱ የኦልድትራፎርድ ጌታ

Written by  ግሩም ሠይፉ
Rate this item
(0 votes)

    ሆላንዳዊው የ62 ዓመት ምርጥ አሰልጣኝ ሊውስ ቫንጋል በማንቸስተር ዩናይትድ አሰልጣኝነት ለመስራት  የሶስት ዓመት የኮንትራት ውል ከ3 ሳምንት በፊት ተፈራርመዋል፡፡ በዓመት 6 ሚሊዮን ፓውንድ ደሞዝ የሚሰጣቸው ሲሆን ኦልድትራፎርድ የሚደርሱት በ20ኛው ዓለም ዋንጫ ከሆላንድ ብሄራዊ ቡድን ጋር ተሳትፈው ነው፡፡   የማንችስተር ዩናይትድ ክለብ ሃላፊዎች  በምክትልነት አብሯቸው እንዲሰራ ሪያን ጊግስን ሾመውታል፡፡ ለተጨዋቾች ዝውውር  ገበያ የሚሆን የ200 ሚሊዮን ፓውንድ በጀት አቅርቧል፡፡
በመጀመርያ የውድድር ዘመናቸው የእንግሊዝ ፕሪሚዬር ሊግን ማሸነፍ እንደሚፈልጉ የተናገሩት ሊውስ ቫንጋል በአውሮፓ እግር ኳስ ከ20 ዓመታት በላይ ልምድ አላቸው፡፡ በተለያዩ ሶስት አገራት የሊግ ውድድሮች ሻምፒዮን ሆነዋል፡፡ የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ፤ የአውሮፓ ማህበረሰብ ዋንጫን፤ የኢንተርኮንትኔንታል ካፕ እና የአውሮፓ ሱፕር ካፕ ዋንጫዎችንም ወስደዋል፡፡
ሰሞኑን በወጡ ዘገባዎች እንደተገለፀው የቫንጋል የአሰለጣጠን ፍልስፍና በርካታ ክልከላዎችን በኦልድትራፎርድ ይፈጥራል፡፡ በሊውስ ቫንጋል ጥብቅ መመርያዎች ሊያስቀጡ ከሚችሉ ጥፋቶች መካከል  በመመገቢያ ክፍል በስነስርዓት አለመቀመጥ፤ በግጥሚያ ላይ የኳስ አብዶ ማብዛት፤ በመልበሻ ክፍል ሆነ በማንኛው ቦታ ከአሰልጣኝ ጋር እሰጥ አገባ መግባት፤ ለአንጋፋ ተጨዋቾች ከበሬታ መንፈግ እና ስለደሞዝ እና ዝውውር ጉዳይ በአደባባይ ማውራት የሚሉት ይገኙበታል፡፡

Read 1356 times