ሪያል ማድሪድ ባለፈው ሳምንት የተጎናፀፈውን 10ኛው የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ዋንጫ እስኪያገኝ ባለፉት 12 የውድድር ዘመናት የነበረው የውጭ እና ሌሎች ሁኔታዎች እንዲህ ናቸው፡፡
ባለፉት 11 የውድድር ዘመናት ክለቡ ከግማሽ ፍፃሜ ማለፍ ተስኖት ነበር፡፡
በዚሁ ጊዜ ከክለቡ የለቀቁ 12 ተጨዋቾች በተለያዩ ክለቦች የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ዋንጫን አንስተዋል፡፡
በአጠቃላይ በ12 ዓመታት እስከ 19.5 ቢሊዮን ብር ወጭ ሆኗል፡፡
ባለፉት 10 ዓመታት በተጨዋቾች የዝውውር ገበያ 3 ጊዜ አዳዲስ ክብረወሰኖችን የሰበረው ክለቡ ከ2002 እኤአ ጀምሮ ዘንድሮ እስከተገኘው አስረኛው የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ዋንጫ ድረስ ሪያል ማድሪድ 62 ተጨዋቾች አስፈርሟል፤ 20 ዎቹ ከእንግሊዝ ፕሪሚዬር ሊግ ናቸው፡፡ በዝውውር ገበያው ወጭ የሆነባቸው ደግሞ 32.74 ቢሊዮን ብር ነው፡፡
በየዓመቱ ለደሞዝ ክፍያ ብቻ የሚያወጣው 2.74 ቢሊዮን ብር የሚደርስ ሲሆን ባለፉት 12 ዓመታት የከፈለው 32.88 ቢሊዮን ብር ነው፡፡
የቡድኑ ዋጋ ግምት 60.45 ቢሊዮን ብር
ተንቀሳቃሽ ትርፉ 3.32 ቢሊዮን ብር
ውዝፍ እዳው 4.49 ቢሊዮን ብር
Saturday, 31 May 2014 14:19
የሪያል ማድሪድ ‘La Decima’
Written by ግሩም ሠይፉ
Published in
ስፖርት አድማስ