መቀመጫውን አሜሪካ ሂዩስተንና ኢትዮጵያ በማድረግ በቴአትር ዘርፍ የሚንቀሳቀሰው ዮሐንስ ቴአትር ፕሮዳክሽን፤ “ደላሎቹ” የተሰኘውን ቴአትር በሚቀጥለው ሳምንት እሁድ ለእይታ ያበቃል፡፡ የምርቃት ስነስርዓቱ በዕለቱ ከምሽቱ 12፡00 ሰዓት በሀዋላ ሴንትራል ሆቴል እንደሚካሄድም ድርጅቱ በላከው መግለጫ አስታውቋል፡፡
በኤርሚያስ ጌታቸው ተደርሶ፣ በህይወት አራጌ በተዘጋጀው በዚህ ቴአትር ላይ ችሮታው ከልካይ፣ ህይወት አራጌ፣ ኤርሚያስ ጌታሁንና ሌሎች አንጋፋና ወጣት ተዋንያን እንደሚሳተፉበት ለማወቅ ተችሏል፡
Published in
ኪነ-ጥበባዊ ዜና