Saturday, 28 June 2014 10:19

አንድነት “ወጣትነትና ሰላማዊ ትግል” በሚል ያወያያል

Written by  አበባየሁ ገበያው
Rate this item
(1 Vote)

በአንድነት ፓርቲ የወጣቶች ቋሚ ኮሚቴ አዘጋጅነት “ወጣትነትና ሰላማዊ ትግል” በሚል ርዕስ በነገው ዕለት ከ ጠዋቱ 3 ሰዓት ጀምሮ በፅ/ቤቱ ውይይት እንደሚያካሂድ የጠቆመው ፓርቲው፤ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የፍልስፍና መምህሩ ዶ/ር ዳኛቸው አሰፋ ለውይይት መነሻ የሚሆን ጥናታዊ ፅሁፍ እንደሚያቀርቡ ገልጿል፡፡
የፓርቲው የድርጅት ጉዳይ ሃላፊ አቶ ዳንኤል ተፈራ ለአዲስ አድማስ በሰጡት ማብራሪያ፤ አንድነት በተከታታይ በሚያዘጋጃቸው ውይይቶች የሚነሱ ርዕሰ ጉዳዮች በፓርቲው ውስጥ ያለውን ግልፅነትና ተጠያቂነት ለማጎልበት ያግዛሉ ብለዋል፡፡
በሌላ በኩል የአንድነት ወጣቶች፤ የብሔራዊ ደም ባንክ አገልግሎት ባቀረበላቸው ጥያቄ መሠረት፣ በነገው ዕለት የደም ልገሣ እንደሚያደርጉ ለማወቅ ተችሏል፡፡  

Read 1035 times