Monday, 06 April 2015 08:51

“ጀግና እንደ ቴዎድሮስ፤ ቆራጥ እንደ ጴጥሮስ” ዛሬ ይመረቃ

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(2 votes)

   አንጋፋዋ ደራሲ ፀሐይ መላኩ ያዘጋጀችውና በብርጋዲየር ጀነራል ታሪኩ አይኔ የውትድርና ህይወት ላይ የሚያጠነጥነው “ጀግና እንደ ቴዎድሮስ፤ ቆራጥ እንደ ጴጥሮስ” የተሰኘው መጽሐፍ ዛሬ ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ጀምሮ በዋቢ ሸበሌ ሆቴል ተመርቆ ለገበያ እንደሚቀርብ ተገለፀ፡፡ በጀነራሉ የልጅነት ታሪክ የሚጀምረው መፅሃፉ፤ በዋናነት ከሚያተኩርበት የውትድርና ህይወት በተጨማሪ የትምህርትና የወጣትነት ዘመናቸውንም ያስቃኛል፡፡ የ1966 አብዮት እንቅስቃሴንና የጀነራሉን ተሳትፎም ይዳስሳል፡፡ በ14 ምዕራፎች ተከፋፍሎ በ260 ገፆች የተቀነበበው መጽሐፉ፤ በ50 ብር ከ80 ሳንቲም ይሸጣል፡፡

Read 3033 times