Saturday, 13 February 2016 10:54

“ከአሜን ባሻገር” - ተስፋ ተስፋ አገኘ!

Written by  አሸናፊ አሰፋ
Rate this item
(10 votes)

     የበዕውቀቱ መፅሀፍ  በግማሽ ቀን ውስጥ ሀያ ሺህ ኮፒ በመሸጥ የመጀመሪያው መፅሀፍ ሆኗል። የመጀመሪያ የሆነው በዚህ ብቻ አይደለም፤ገበያ ላይ ሳይቀርብ፣ ሳይነበብ በፊት የመፅሀፍ ሪቪው የተሰራለት የመጀመሪያው መፅሀፍም ይመስለኛል። (የመጀመሪያው … የምትለዋን ቃል መጠቀም እንደምናበዛ ለመተቸት በዕውቀቱ የፃፋትን ቀልድ አንብቤያለሁ … ‘ለቤተሰቤ ሁለተኛ ልጅ ነኝ ፤ ለቤተሰቤ ሁለተኛ ልጅ በመሆን የመጀመሪያው ነኝ’ ብሎ ነበር ።)
እዚህ አዲስ አድማስ ጋዜጣ የፌስ ቡክ አምድ ላይ ፣ ጥር 14 ቀን 2008 ዓ.ም. ፣ ከቻላቸው ታደሰ ፌስ ቡክ ገጽ የተወሰደ ፣ ‘በዕውቀቱ ስዩም አንደ ናይጄሪያዊው ቤን ኦክሪ’ የሚል ርዕስ ያለው ፅሁፍ እንዲህ ይነበባል፦ “መፅሀፉን ግን “ከአሜን ባሻገር” ብሎ ሲሰይመው ምን ለማለት ፈልጐ ይሆን ? ብለን አሰቀድመን ብንጠይቅ ምንም ችግር የለውም። መቼም ምን አሰቸኮለህ ፣ መፅሀፉ ታትሞ ስታነበው ትደርስበት የለ እንዴ ? የሚል ሰው አይጠፋም። እንዲህ አይነቱ አስተያየት ግን በተፈጥሮው ጥያቄን ገዳቢ ፣ ጥያቄን ፈሪ ነው። እንዲህ አይነት አስተያየት የሚሰጥ ሰው መልሱ ከተገኘ በኋላ ጥያቄ የሚጀምር ሰው መሆን አለበት።” ብሏል ቻላቸው ታደሰ። አስተያየት ከመስጠቱ፣ ሌሎችን መገሰፁ። መቆጣቱ።
ለማንኛውም ለምን የመጽሐፉን ርዕስ “ከአሜን ባሻገር” እንዳለው ጽፏል፡፡ እንዲህ ብሎ ፡- “ከውስጥ ሲያስተጋባ የወንጀል ትዕዛዝ ሥርዓትና ወጉ አሜን ብቻ ሆኗል የመሀይም(ን) ወጉ፡፡”  
የበዕውቀቱ ስዩም በዳዳ-ደስታ-ወየሳን መፅሀፍ አነበብኩት።
የሽፋን ገፁ ያምራል። የገፁ ቀለም የድሮ ፣ ያረጀ ፣ የወየበ የመፅሀፍ የውስጥ ገፅ ይመስላል። የሚገርመው መፅሀፉ ገና ካሁኑ ክላሲክ እንዲሆን የተፈረደበት ይመስላል። ክላሲክ መሆን እጣፈንታው እንደሆነ ያስታውቃል። አይቀርለትም ። Instant Classics አሉ። እጅግ ጥቂት ናቸው እንጂ። አላጋነንኩም ። … ወደ ሽፋን ገፁ እንመለስ … ብስክሌት ቀላል ፣ ውብ ፣ እና ምርጥ መሺን ናት። መፅሀፉ ውሰጥ ያሉትም ሀሳቦች እንዲህ አይነት ናቸው። የድሮና የዘንድሮ መንሰላሰል በምኒልክ ሳንቲምና ከስድሰት አመት በፊት ፦ በ፳፻፪ (2002) ዓ.ም. ወደ ገበያ በገባው የአንድ ብር ሳንቲማችን የብስክሌቱን የፊት እና የኋላ ጎማዎች ሆነው ፣  በቅደምተከተል ተወክለዋል። በዕውቀቱ ሰዩም እራሱ ገፅ 9 ላይ እንዲህ ይላል ፦ “ርግጥ ነው ፤ አንዳንዶች እንደሚያስቡት ታሪክ አሮጌ መጻሕፍት ውስጥ ተጠርዞ የቀረ ነገር አይደለም። ያለፈውን ትተን ወደፊት እንገስግስ የሚለው “ሾላ በድፍን” የሆነ አባባልም ትርጉም የለሽ ነው። ያለፈውን ዘመን ቸል ብንለው ቸል አይለንም። የዛሬው ዘመን ምን ቢታገል ካለፈው ዘመን ተለይቶ ጎጆ መውጣት አይችልም። ያለፈው ዘመንና የዛሬው ዘመን እንዳይፋቱ ሆነው ተቆራኝተዋል። አንዳዴ ሳስበው ፤ “ዘንድሮ” በሚለው ቃል ውስጥ “ድሮ” የሚለው ቃል መገኘቱ ባጋጣሚ አይመስለኝም።”
መግቢያው ላይ ደራሲው የመፅሀፏን ይዘት በአጭር ያስተዋውቃል ፦ “ይህች መጽሐፍ ጉዞ ቀመስ ፣ ፖለቲካ ቀመስና ታሪከ ቀመስ መጣጥፎችን ይዛለች” በማለት። ከመግቢያው ቀጥሎ ያለው ፅሁፍ ፦ ‘የገነት በር’ የሚል ርእስ አለው። አሜሪካ መሄድ አንድ ነገር ነው። ማንም አይክድም። ግን ምነው ይሄን ያህል ? ያስብላል። ናሽናሊስት ገለመሌ ሆኜ አይደለም። እንዲሁ ሳስብ በዕውቀቱ የነሸጠው ቀን ተነስቶ ፣ ሻንጣውን ወይ ፌስታሉን አንከብክቦ ከቤቱ ወጥቶ ፣ ልክ ታክሲ እንደሚያስቆመው አይነት ጣቱን ቀስሮ  ቦይንግ 777 አስቁሞ ፣ ለወያላው 1.50 ዶላር ከፍሎ አሜሪካ መሄድ የሚችል ይመስለኝ ነበር። (ውስጡን አደገኛ አድናቆት ነች ።) እንጂ ይኼን ያህል ‘የገነት በር’ ምናምን የሚል አይመስለኝም ነበር። ልጁ ልሂቅ ነው። ይህ ደረቅ ሀቅ ነው። ጉብዝና ብዙ በሮች እንደሚከፍት አውቃለሁ። አይቻለሁ። የመዝናኛው ኢንዱሰትሪ ውስጥ ላሉት ‘ልጆቻችን’ (ድምፃውያን እና ኮሜድያን) አሜሪካ የውሎ ገብ መንገድ ነው። የአሜሪካ በር ለሱም ሁሌ ክፍት ይመስለኝ ነበር። ጓደኞች አሉ። ወዳጆች አሉ። አድናቂዎች አሉ። ትምህርት አለ። ስራ አለ። ዲቪ አለ። ሾርኒ አለ ። (ለምሳሌ ፦  ከእንግሊዝ ወደ አሜሪካ ማለፍ ። በስነፅሁፍ ውድድር አሸንፎ እንግሊዝ ሄዶ ነበር።) ብዙ ነገሮች አሉ። ሁሉም ተዘጋጅተው የሚጠብቁት ፣ እሱ ግን ችላ ያላቸው ይመስለኝ ነበር።
“አንዳንዴ ሳስበው በዘመናችን አሜሪካ ለመግባት የሚደረገው ውጣ ውረድ አባቶቻችን በአምላክ ፊት ሞገስ ለማግኘት ከነበራቸው መጠመድ ጋር የሚመሳሰል ነው።” ይላል በዕውቀቱ ገጽ 15 ላይ። ቀጥሎም እንዲህ ብሎ ይጠይቃል ፦ “ለመሆኑ ይህ ያስገርማል ?” እጅግ እንጂ በዕውቀቱ። መልስ ከራስህ ነው። እዚያው ገፅ ላይ አንዲህ ብለሀል ፦ “እንደ ብዙዎቹ የዘመን ጓዶቼ የአሜሪካን መስህብ መቋቋም የምችል አይመስለኝም ።” ጥሩ ኮንፌሽን ነው። አሜሪካን መሄድ ገነት መግባት የማይመስላቸው ዘመንተኞች እንዳሉህ አምነሀል።
በዕውቀቱ ፦ “ሴቶች በዋሉበት መዋል” በሚል ፅሁፉ እቴጌ ጣይቱ ፣ ወይዘሮ ላቀች ፣ አዝማሬ ጣዲቄንና ሌሎችንም ሴቶች ጀግኖቻችንን አስታውሷል። የፅሁፉ ማስታወሻነት ለድምጻዊት ንግስት አበበ ይሁን ብሏል ።
እኔም አሜሪካ ስለመሄድ የሚገርም አቋም ያላቸውን በሕይወት ያሉ እናት ላስታውስ። ጎጃም ፣ ባህርዳር እያለሁ የሰማሁዋት እውነተኛ ታሪክ ናት። አኚህ እናት አሜሪካ አምስት ልጆች አሉዋቸው አሉኝ። እሺ አልኩኝ። ሁሉም የአሜሪካ ዜግነት አግኝተው ፣ ምርጥ ኑሮ የሚኖሩ ናቸው። አባት ሞተዋል። ልጆች ወደዚህ ሀገር መምጣት ፣ እናት ወደዚያ ሀገር መሄድ የማይታሰብ ነገር ነው። አይፈልጉም። ወሬው እራሱ ይቀፋቸዋል። የመጀመሪያው ልጃቸው ሊያገባ ሆነ ። ልጆች እዚህ አይመጡም ብለናል ። ሰርጉ አሜሪካ ነው የሚደገሰው። በስንት ልመና ፣ እናት አሜሪካ ሄደው ሰርጉ ላይ ሊገኙ ተስማሙ። ልክ እንደ በዕውቀቱ በአስተርጓሚ ኢንተርቪው ሊሰጡ አሜሪካ ኤምባሲ ሄዱ። ሁሉንም አስፈላጊ ወረቀቶች አሟልተዋል።
ቀረቡ።
“አሜሪካ ሄደው ያውቃሉ ?”
“አላውቅም።”
“ሌላ የት ሐገር ሄደው ያውቃሉ ?”
“የትም ሐገር ሄጄ አላውቅ።”
“አሜሪካ ማ ጋ ነው የሚሄዱት ?”
“ልጄ ጋ ።”
“ለምን ?”
“ለሰርግ ።”
“አሜሪካ ከልጅዎ ሌላ የሚያውቁት ሰው አለ ?”
“ሞልተዋል። ብዙ ናቸው። ልጆቼ ብቻ አምስት ናቸው ።”
ሴትየዋ ጥያቄዎቹ እየደበሯቸው መጡ። አያልቁም እንዴ? እየሰለቻቸው ነው፡፡
“እዚያ ሄደው ቢቀሩስ ?”
“እማማ፣ እዚያ ሄደው ቢቀሩስ እያለዎት ነው ?”
“እኔን ነው ?”
“አዎ ።”
“እኮ እኔ ነኝ የምቀር?”
“እ።”
“እነሱ ሐገር ?”
“እንዲያ ነው ጥያቄው ።”
“በቃ ተወው። እንዲያውም አልሄድም። አታድርቀኝ ፤ አልሄድም ብላሀለች በለው።”
ጀግና።
አሜሪካዊው ተነገረው። ሴትዮዋን አያቸው። የምራቸውን ነው። ወደ ቤታቸው ሊሄዱ ተነስተዋል። እየሳቀ ቪዛውን መታላቸው። ይባላል።
ሲወጡ እንደ በዕውቀቱ ፈላጭ አግኝቶ ፣ የፍንጥር ይፍለጣቸው አይፍለጣቸው አላውቅም። እንዲያ አልተባልኩም። አልተነገረኝም ።
እዚህች ጋ የበዕውቀቱን አንድ አጭር ልቦለድ ማስታወስ ግድ ይላል። የልቦለዱ ርዕስ ፦ “ክንፋም ህልሞች” ነው ። የልቦለዱ ቅርፅ የደብዳቤ መፃፃፍ ነው። እንዲህ ነው ነገርዬው ፦ ማንኩሳ ያለው ሰው ወደ ደብረማርቆስ እንዲወስዱት ደብዳቤ ይፅፋል ። ደብረማርቆስ ያለው ወደ አዲስ አበባ እንዲወስዱት በደብዳቤ ይማፀናል ። ደብረማርቆስ ያለው ወደ ባህርዳር እንዲወስዱት በደብዳቤ ይማፀናል። ባህርዳር ያለው ወደ አዲስ አበባ እንዲወስዱት በደብዳቤ ይለማመጣል። አዲስ አበባ ያለው በበኩሉ ዋሽንግተን መሄድ የቀን ተሌት ህልሙ ነው። እንዲያ ብሎ አሜሪካ ላለው ዘመዱ ደብዳቤ ይፅፋል።  ዋሽንግተን ያለው ደግሞ ወደ ማንኩሳ መመለስ ይናፍቃል። በዕውቀቱ ይህቺን ድንቅ ልቦለድህን ዘነጋኻት ወይ ? ወይስ ፉገራ ነበር ያኔም ? በቃ ዝም ብሎ ልቦለድ ? ብቻ አንተን ይመችህ አቦ!
ደሰታና ቀቢጸ ተስፋ- ዝንባዊነት እና ማቱሳላዊነት
ከ‘የገነት በር’ ቀጥላ መጽሀፉ ላይ የተሰለፈች ፅሁፍ ‘ደሰታና ቀቢጸ ተስፋ’ ትላለች። ግሩም ናት። የዘመናችንን ደስታ ትገመግማለች። በዚህ ፅሁፉ የመሥሪያ ቤቶች ፣ የጫት ቤቶች ፣ የመጠጥ ቤቶች ፣ በየቦታው እንደ ክረምት አግቢ መፍላታቸውን ፅፏል። ምክንያቱንም መርምሯል ።
“የምርምር ማእከሎች ፣ ቤተመዘክሮችና ማተሚያ ቤቶች በግንባታ መስመር ላይ አይታዩም። ከፈጠራ ፣ ከምርምር እና እንቆቅልሽ ከመፍታት የሚገኝ ደስታ ደብዛው የለም። ያለው ሥጋዊ ደስታ ብቻ ነው ።” ብሎ ከገፅ 19 አስከ 20 አማርሯል። እውነት ነው ።
እዚህች ጋ የዶ/ር ፈቃደ አዘዘን ኮስተር ያለች ግጥም ከ “እየሄድኩ አልሄድም” መድበል በክብር እናመጣታለን ፦
ይጮኸል ደራሲ
ይጮኸል አዝማሪ
ይጮኸል ከያኒ ፣
    ግን ማንስ አዳምጦ ?
    ኧረ ማንስ ሰምቶ ?
    ሁሉም እጆሮው ላይ በሆዱ ተኝቶ ።
አንድ ጣሳ አረቄ ፣ አንድ በርሜል ጠላ
ጠጃጠጅ አምቡላ ፤
ከአሥራ-አሥር ክትፎ ጋር ፣ አሥር ኪሎ ስጋ
ቢጐምድ ቢሰለቅጥ ቢቸልስ ቢለጋ
ይመርጣል ዘመኑ ፤
ጥበብ ለእርሱ ምኑ ?
    ድርሰትና ግጥም ፣ ኧረ ምን ለከርሱ ?
    ለበዳ ኅሊናው ለበዳ መንፈሱ ?!

ሰው ፦ ‘ሕይወት አጭርና ከንቱ ናት’ ብሎ ካሰበና በዚህ ስሌትና ስሜት ከተንቀሳቀሰ እጅግ አደገኛ ፍጡር ይሆናል። እድሜያችን አጭር ሲሆን ምንም አይነት ይሁን ደስታን ማሳደድ ላይ እንበረታለን። ስድ እንሆናለን። “Man thinks and lives in the long run. The better the mind the longer the run.”  ብላለች አንዲት ደራሲ። የሰው ልጅ እሩቅ አሳቢ ፣ እሩቅ አዳሪ ነው ፤ ምርጥ አእምሮ ያለው ሰው እጅግ አርቆ ያስባል ፣ ረዥም እርቀትም ይጓዛል ነው ትርጉሙ ።
ጄምስ ዴል ዴቪድሰንና ሎርድ ዊልያም ሪስ-ሞግ (James Dale Davidson & Lord William Rees-Mogg) የተባሉ ልሂቃን Great Reckoning: Protect Yourself from the Coming Depression በሚለው ፣ እ.ኤ.አ. በ1994 ዓ.ም. በታተመና አለም አቀፍ ከፍተኛ ሽያጭ ባስመዘገበ መፅሀፋቸው፤ አሁን ስላለው የሰው እድሜ እርዝመት የሚገርም ክርክር ያቀርባሉ። ሁለት ፅንፎች አቅርበው ልዩነቱን ያስረዳሉ። የሰው ልጅ እድሜው እንደ ዝንብ እድሜ በጣም ቢያጥር ወይም እንደማቱሳላ እድሜ ቢንዘላዘል፣ ሰው አሁን ከምናውቀው ፍፁም የተለየ ባህሪ ያለው ፍጡር ነው የሚሆነው ይላሉ። እድሜያችን እንደ ዝንብ እድሜ ለጉድ አጭር ቢሆን ኖሮ እጅግ አደገኛ ፍጡር እንሆናለን ። ማሰብ ብሎ ነገር የለም። ለነገ መጨነቅ የለም። ዕቅድ ብሎ ነገር የለም። ግብረገብ አይኖርም። የተገኘው ቆሻሻ ላይ ሁሉ እያረፉ የተገኘውን ‘ደስታ’ ሁሉ መሰብሰብ ነው። ቢጤህን ሰው (ዝንብ) መግደል አምሮሀል ? ግደለው። ‘ሀያ አራት ሰዓት’ ለማትሞላ እድሜ ደግሞ። ቤት መገንባት ፣ መማር ፣ ሀብት-ንብረት ማፍራት ፣ ትዳር መመስረት ፣ ልጆች ወልዶ በወጉ አንፆ ማሳደግ … ብሎ ዘፈን የለም። መረጃ ላይ ታች ብሎ አሰባስቦ ፣ ጊዜ ወስዶ አብሰልስሎ ፦ “ከአሜን ባሻገር” ብሎ መፅሀፍ መቸክቸክ አያስፈልግም። እሱን ለማንበብ ጊዜ አይኖርም። ከተወሰኑ ደቂቃዎች በኋላ ለምሞተው አሜን ፣ ቅብርጥስዮ ብሎ ነገር ምንድነው ? ምንም። ቡሌውን ፣ አምቡላውን ፣ ሴሹን ፣ ሀሺሹን ፣ ሺሻውን ፣ ጫቱን ፣ ገረዷን፣ ልጃገረዷን ፣ … ማጧጧፍ ነው ። እና መጨፈር።
“ደንስ ጎበዝ ፣ ደንስ ጀግና
ከረባትህን አውልቅና …
ምንም-ምንም እንዳታስብ ፣ ሁሉን-ሁሉን እንድትረሳ
ደንስ! ካካታው ይነሳ
ጨፍር! ወለሉ እስኪበሳ … ”
እያሉ መጨፈር ነው ።
ዕድሜያችን እንደ ማቱሳላህ እድሜ ቢንዘላዘል ደግሞ ሌላ አይነት ሰው እንሆናለን። ፈሪ እና ደነዝ እንሆናለን። የራሳችንንም ሆነ የሌሎችን ፣ በአጠቃላይ የሰው ልጆችን ህይወት ሊለውጡ የሚችሉ አደገኛ ሙከራዎችን ከማድረግ እንቆጠባለን። አብዛኛዎቹ ፈጠራዎች የሚደረጉት risk ባለበት ሁኔታ ነው። አዲስ ነገር ስንሞከር የገንዘብ ኪሳራ ሊደርስብን ይችላል። ቤተሰባችን ይበተን ይሆናል። ማህበራዊ ህይወታችን ምስቅልቅሉ ሊወጣ ይችላል። የጤና ጉዳይ አለ። ህይወታችን ለአደጋ ይጋለጥ ይሆናል። ከሞትን ብዙ ነገር ነው የምናጣው። በሶስት መቶ አመቴ ባጭር ብቀጭ፣ ስድስት መቶ ምናምን እድሜ ነው የሚቀርብኝ። ከባድ ኪሳራ ነው። ምንም ነገር ከመሞከር አርፎ ህይወትን ማጣጣም ይበጃል ።
ዝንቦቹ ብኩን ናቸው። ማቱሳላና ግብረአበሮቹ ደግሞ ቡከን ናቸው ።
ልከኛና ጣፋጩ የእድሜ እርዝመት አሁን ያለንበት ነው። ያንን ባሣጠርነው መጠን ዝንብ የመሆን እድላችን እየጨመረ ይመጣል። በጣም ከረዘመ ደግሞ እንጀዝባለን ።
“ኢዐማኒ ነኝ ” ተው ባክህ !
በዕውቀቱ ፦ “ከቸርችል ጎዳና ወደ ቸርችል ዳመና” በሚለው ጽሁፉ መግቢያ ገጽ 40 ላይ እንዲህ ብሎ ከትቧል ፦ “የሦስተኛ ዓመት የሳይኮሎጂ ተማሪ እያለሁ The Future of Illusion የተባለውን የሲግመንድ ፍሮይድ መፅሐፍ አነበብኩና ከሀይማኖት ጋር ፍቺ ፈፀምኩ። ይሁን እንጂ አውሮፕላን ላይ በወጣሁ ቁጥር ለአጭር ጊዜ ሃይማኖተኛ እሆናለሁ።”
በዕወቀቱ እርፍና መስሎ ከታየው ኢዐማኒ መሆን መብቱ ነው። ሶስተኛ አመት ደርሶ ይቅርና ፍሬሽ  እያለ Philosophy 101 ወስዶ እግዚአብሔርን ያልተሳፈጠ የለም። አጉል አወቅሁ ባይነት ናት። ጥራዝ ነጠቅነት ናት። ማስታወስ ያለበት ነገር ግን አለ። በጉብዝናችሁ ወራት ጎብኟቸው ያለን የላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናትም ሆኑ የአክሱም ሀውልቶች የተገነቡት በእምነት ሰበብ ነው። ባለም ከተመዘገቡት የሰው ልጆች ሰባት ድንቅ ስራዎች ውስጥ ሶስቱ ፦ ታላቁ የግብፅ ፒራሚድ (The Great Pyramid) ፣ የዙስ ሀውልት  (The Statue of Zeus at Olympia) ፣ እና የአርቲመስ ቤተመቅደስ (Temple of Artemis) የተፀነሱትም የታነፁትም በእምነት ምክንያት ነው። ሀሌሉያ።
አሁን ያለው የሀገራችን ህዝብ እንኳን ፈሪሀ እግዚአብሔርን ከልተህለት እንዲሁም ----- እንኳን ዘንቦበት እንዲያውም ጤዛ ነው። ‘ጤዛነት’ የምትለውን ቃል ያመጣሀት አንተ ነህ። ሰዉ የቅጽበት ባሪያ ሆኗል። ‘ትናንት ? ኖሮ አያውቅም። ዛሬ ? የለም ። ነገ ? መቼም አይመጣም ።’ እንዲሉ ። ቅጽበት ዘላለም ሆናለች። ጤዛነት እና ዝንባዊነት ነግሷል።
ጨው ለራስህ ስትል ጣፍጥ
እምነትን በተመለከተ እንደ ብሌይዝ ፓስካል ቁማር የልብ የምታደርስ የለችም። የፓስካል ቁማር ወይም ፣ ውርርድ (Pascal’s Wager) ትባላለች ። ፓስካል እንዲህ ይላል ፦ እግዚአብሔር ስለመኖር አለመኖሩ እቅጩን ልታውቅ ወይም ማንም ሊነግርህ አይችልም ። ግን ባንዱ በኩል ሆነህ መኖር ፣ መጫወት ፣ ማስያዝ ፣ መቆመር ፣ መወራረድ አለብህ ። እግዚአብሔር የለም ብለህ ኖረህ ፣ ስትሞት ወዳጃችን እዚያ ከጠበቀህ ጉድ ነው ። ቁማሩን ተበልተሀል ። ወደ ሲኦል ትሸኛለህ ። ከሌለስ ? ምንም ጣጣ የለውም ። ዘላለማዊ ጨለማህን የሚወስድብህ የለም ። ዘላለማዊ ጨለማንና ባዶነትን ትወርሳለህ ። እንዲያው ዝም ፣ እንዲያው ዝም ይሆናል ነገርዬው። አልቦ ። Infinte Noting እንዲል ራሱ ፓስካል፡፡
እግዚአብሔር አለ ብለህ አምነህ ፣ ኖረህ ስትሞት ወዳጃችን እዚያ ሲያገኝህስ ? ገድ ቀናችህ ማለት ነው። ብራቮ የኔ ልጅ ብሎ ትከሻህን ቸብ ፣ ቸብ አድርጎህ ዘላለማዊ ሕይወትን ያወርስኸል። ባይኖርስ ? አሁንም አልተሸወድክም ። አሁንም ዘላለማዊ ጨለማህን የሚወስድብህ የለም ። ምንም በምንም ውስጥ እልም ብለህ ትጠፋለህ ። ጭልጥ ።
    የፓስካል ውርርድ ስትጠቃለል እንዲህ የሚሆን ሰንጠረዥ ይወጣታል ፦
አይደለም እግዚአብሔር ሰይጣን እራሱ ያስፈልገናል። እነ ሲግመንድ ፍሮይድ መጥተው ሰበብ መፈለግ ወይም ሰህተትን ሌላ ነገር ላይ ወይም ሰው ላይ ማላከክ (Projection) አንዱ የእምሮአችንን ሚዛን ወይም ጤና መጠበቂያ ነው ብለው ሳያበስሩና ሳያፅናኑን በፊት የሰው ልጅ ስህተቱን ሁሉ በሰይጣን ሲያላክክ ኖሯል። ሰይጣን አሳሳተኝ የዘወትር ቋንቋችን ነው።
አንድ የተሰለቸ አባባል ላስታውስህ ፣ ምናልባት ሲደጋገም ዕውቀት ሆኖ ይረጋ ይሆናል ፦ “If God did not exist, it would be necessary to invent Him” ቮልቴር ነው ። እውነቱን ነው ። እግዚአብሔር ባይኖር እንኳን ልንፈጥረው ግድ ነው ። ጥቅሙ ለኛው ነው ። ፈሪሀ እግዚአብሔር ትልቅ ልጓም ነው ። “ሰው እንኳ ባትፈራ እግዚአብሔርን ፍራ።” ይላሉ ታላላቆቻችን የሰውን ባህሪ መግራት ሲፈልጉ። የዘመን ጓዶቻችን ትልቁ ችግር ሰውንም እግዜርንም አለመፍራት ነው። ሳይኮአናሊስቶች ሳይመጡና በሰዓት ብዙ መቶ ብሮች እየተቀበሉን ጭንቀታችንን ለመስማት ፍቃደኛ ከመሆናቸው በፊት ፣ ጭንቀታችንን ይሰሙ ፣ አእምሮአችንን ያክሙ የነበሩት Father Confessers ነበሩ። የንሰሀ አባት። ለዚያውም በነፃ።
ሦስቱ ኤልሻዳዮች ፦ አራተኛ የለም ወይ ?
በዕውቀቱ ‘ሦስቱ ኤልሻዳዮች’ በሚለው ፅሁፉ ፣ ገፅ 91 ላይ እንዲህ ይላል ፦ “ በታሪካችን ውስጥ አምላክ-አከል ዐቅም የነበራቸው ሦስት ኀይሎች ነበሩ። እነሱም ፤ ግዝት ፤ ጠመንጃና ገንዘብ ናቸው ።” ሌላ የለም ከሶስቱ ሌላ ?
Power : A New Social Analysis የሚል ርዕስ ያለው ፣ በርትረንድ ረስል እ.ኤ.አ. በ1938 ዓ.ም.  ባሳተመው  መፅሀፍ፣ በፊዚክስ ጥናት ኢነርጂ አልፋና ኦሜጋ የሆነውን ያህል ፤ በማህበረሰብ ጥናት ደግም የፓወር ጥናት የኢነርጂ እኩያ ነው ይላል። በዚህ መፅሀፉ አራት ነገሮች ይተነትናል። አንድ ፦ የፓወርን ስሪት ወይም ምንነት ወይም ተፈጥሮ ያብራራል። ሁለት ፦ የፓወርን ቅርፆች ያሳያል። ሦስት ፦ የተቋማትን አወቃቀር ይተነትናል። በመጨረሻም ፦ የፓወር አጠቃቀምን ግብረገብ ይመረምራል። ሶስት አይነት ፓወሮች አሉ ይላል ረስል። እነርሱም ፦ ኢኮኖሚክ ፓወር ፤ የጉልበት ወይም የጡንቻ ፓወር (Naked power) እና ኢንቴሌክቹዋል ፓወር (cultural and civil power) ናቸው። (በረስል በራሱ ብዕር ፦ In … this book I shall be concerned to prove that the fundamental concept in social science is Power, in the same sense in which Energy is the fundamental concept in Physics. Like energy, power has many forms, such as wealth, armaments, civil authority, and influence on opinion. ገፅ 10-11)
በዕውቀቱ ኢንቴሌክቹዋል ፓወርን ረስቷታል። በታሪካችን ወይም በባህላችን ላይ ኢንቴሌክት ድርሻ አልነበረውም ወይ ? ማህሌታይ ያሬድ ታሪካችን ላይ ግዙፍ አሻራ አልተወም ወይ ? አለቃ ገብረሃናስ ? ተዋነይስ ? ሀዲስ አለማየሁ ? ከበደ ሚካኤል ?
ብሔርን በተመለከተ ፦
ብሄርን በተመለከተ ብዙ አልልም። እሰከ ጥግ ድረስ ሄደህበታል። የዚያን የመከረኛውን ምኒልክ ሸክም አራግፈህለታል። ከአሁን በኋላ በሰላም የሚተኛ ይመስለኛል። አሁን አጥንቱ ከተገላበጠ በደስታ ነው የሚሆነው። “ጐሽ የኔ ብላቴና ።” ይልህ ይመስለኛል።  
በበኩሌ የራሱ ስም ደስታ ፤ የአባቱ ስም ሐጎስ ፤ የአያቱ ስም ገመቹ የሚባል ሰው አውቃለሁ። ደስታ ሐጐስ ገመቹ። በጣም አሪፍ ልጅ ነው። በቃ።
እዚያ ያለህበት ሀገር  የነበረ ፣ ሳሙኤል ሀንቲንግተንን የሚባል ልሂቅ የፃፈውን Clash of Civilizations and the Remaking of the New World እስካሁን ሳታነብ የቀረህ አይመስለኝም ። ሳሙኤል ሀንቲንግተን ሁሌም እራሳችንን የምንገልፀው (ማንነታችንን define የምናደርገው) በልዩነቶቻችን ነው ይላል ። ለምሳሌ አንዲት ህግ ያጠናች ሴት ፣ ህግ ካጠኑ ወንዶች ጋር ስትቀላቀል እራሷን የምትገልፀው ፦ “ሴት የህግ ባለሙያ” ብላ ነው። አብረዋት ያሉት ወንዶች ሁሉ ህግ ያጠኑ ናቸው ። ከእነሱ የሚለያት ጾታዋ ነው ። እሱን ታስቀድማለች ። ይህችኑ ሴት የተለያየ ሙያ ካጠኑ ሴቶች ጋር ብትቀላቅላት አሁን የህግ ባለሙያ ትሆናለች ። ምንድነሽ ብትላት በቅድሚያ ፦ “የህግ ባለሙያ ።” ነው የምትለው ።
አሁንም በኛ ሀገር ነገርዬው ኦሮሞ ፣ ትግሬ ፣ አማራ ፣ ብቻ በሚለው አያበቃም።  ከዚያ ፦ የወለጋ ኦሮሞ ፣ የሸዋ ኦሮሞ ፣ የሀረር ኦሮሞ ፣ የአምቦ ኦሮሞ … ወዘተ እያለ ይቀጥላል ። ትግሬውም እንደዛው ፦ የአክሱም ትግሬ ፣ የአድዋ ትግሬ ፣ የሽሬ ትግሬ … እያለ ይቀጥላል። አማራስ ብትል? ተመሳሳይ ነው፡፡
ጆርጅ ኦርዌል ፣ የበርትራንድ ረስልን Power: A New Analysis of Society መጽሃፍ ሪቪው ከአደረገ በኋላ በነዚህ አረፍተ ነገሮች ነው የሚሰናበተው (ኦርዌል አቶ ረስል ያለውን በእውቀቱ በሚል ነው የተካሁት፡፡ ኦርዌል ለበእውቀቱ የፃፈው ነው የሚመስለው።)
በዕውቀቱ በህይወት ካሉ እጅግ ከሚነበቡ ፀሀፍት አንዱ ነው። እንዲህ አይነት ሰው መኖሩን ማወቅ እራሱ ያፅናናል። እሱና እሱን መሳይ ሰዎች መኖራቸውን ስናውቅ አለም ጭርሱኑ አንዳላበደች ይገባናል። ርእሰ ጉዳዮቹን አንጥሮ ማውጣት (ማንጠር) ይችላል። (ምርጥ ርዕሰ ጉዳዮችን መምረጥ ይችላል።) ዋዛ የሚመስሉትንም ሆነ እጅግ ጥልቅ የሆኑ ጉዳዮችን ባሰኘው መንገድ ማቅረብ ይችላል፤ እዚህ መፅሀፍ ላ(የመጨረሻ ክፍል)
-- በህወሓት ጉባኤ ወቅት የተወሰኑ ጄኔራሎች መቐለ አካባቢ ያንዣብቡ ነበር ብለው አንድ ሁለት እዚያ የነበሩ ሰዎች ገለፁልኝ፡፡ ታዲያ ምን አለበት ለራሳቸው ጉዳይ ሄደው ከጉባኤው ጋር ተገጣጥሞ ሊሆን ይችላል ብዬ አልኳቸው። አንደኛው፤ “አይ ማታ ማታ ከፖለቲካ መሪዎች ጋር ይገናኙ ነበር” አለኝ። እኔም የድሮ ጓደኞቻቸውን በአጋጣሚ አግኝተው እየተጫወቱ ይሆናል ስል ግምቴን ተናገርኩ፡፡ “አይ ሰዎች የተለያየ ትርጉም እየሰጡት ነው” አሉኝ። ነገሩ ግራ ገባኝና፤ “በጉባኤዉ ላይ በቀጥታ ተፅእኖ እያሳደሩበት ነው እያላችሁኝ ከሆነ፣ እንዲህ የሚያደርጉ አይመስለኝም፤ህገ መንግስቱን ጠንቅቀው ያዉቁታል፤ በኮርት ማርሻል (ወታደራዊ ፍርድ ቤት) የሚያስቀጣቸዉና በቀጥታ ከሰራዊቱ የሚያባርራቸው መሆኑን በሚገባ ስለሚያውቁት አይሞክሩትም” አልኳቸው፡፡  
 በሌላ በኩል ደግሞ ህወሓት የመከላከያ ጄኔራሎች በፖለቲካው ውስጥ ገብተው እንዲዘባርቁ የምትፈቅድ አይመስለኝም። ፖለቲካዊ ትርጉሙ መሰረታዊ ነው። ብዙ አንፀባራቂ ታሪክ ስርታ እዚህ የደረሰች ድርጅት፣ ይህን ከፈቀደች ሞታለች ወይም አንድ እግሯን ጉድጓድ ውስጥ አስገብታለች ማለት ነው፤ስል ነገርኳቸው። በተጨማሪም የድርጅቱ ሊቀመንበር የጄኔራሎቹን ፖለቲካዊ ጣልቃ ገብነት የሚቀበሉ አይመስለኝም አልኩኝ፡፡ አንደኛው ሰውዬ፤የሊቀመንበሩ አፍቃሪ ስለነበር “ይሄስ እዉነትክን ነው” ብሎኝ ነገሩ ለጊዜው ተቋጨ፡፡
 --- ወይን መፅሄት በ50ኛ እትሙ፣ ህገ መንግስቱን በግላጭ የጣሰና የተፈጠረውን ህዝባዊ እንቅስቃሴ ለማደናቀፍ ኢ-ዴሞክራሲያዊ ሃይሎች ምን ማድረግ እንደሚችሉ የሚያሳይ ደንበኛ ምሳሌ በመሆኑ ሰፋ አድርጌ ለመፈተሽ ተገድጅያለሁ። የወይን ስፖንሰሮች፡- የፌዴራል ሚኒስቴር መስርያ ቤቶች፣ መከላከያ ሚኒስቴር ሳይቀር፣ የአዲስ አበባ ቢሮዎች፣ የዞን ፅህፈት ቤቶች፣ በትግራይም ከክልል ቢሮዎች እስከ ወረዳ ድረስ ያሉ የመንግስት መዋቅሮች ----- ነበሩ፡፡ አሁን ጥያቄው የመንግስት መስርያ ቤቶች የአንድን ፖለቲካዊ ድርጅት ልሳን መፅሄት ስፖንሰር ማድረግ ይችላሉ ወይ? ነው፡፡ የግል ድርጅቶች ተጨምረውበት በማስታወቂያ የታጨቀ ቢሆንም 50ኛ እትሙ መፅሄት በ50 ብር ሲሸጥ ነበር፡፡
 እነዚህ የመንግስት ተቋሞች፣ የአንድ ፖለቲካዊ ድርጅትን ልሳን እንዲደጉሙ ሕገ መንግስቱ ወይም ሌሎች ህጎች ይፈቅዳሉ ወይ? በተለይ በህገ መንግስቱ አንቀፅ 87/5 መሰረት፤ ከፖለቲካዊ ወገናዊነት ነፃ በሆነ መንገድ ስራዉን ማከናወን ያለበት መከላከያ፣ የመጽሄቱ ስፖንሰር ሆኖ ማየት አስገራሚ ነው። ዕብሪት ነው!!! መንግስት ከህግ ዉጪ አንድን ፓርቲ መደጎም የለበትም። አይ… ህገ መንግስቱ አይከለክልም ከተባለም፣ በህጋዊነት ተመዝግበው የሚንቀሳቀሱትን የመድረክ፣ ዓረና እና መኢአድ ልሳኖችን ስፖንሰር ቢያደርጉ የፓርቲዎቹ  የፋይናንስ አቅም ደካማ ከመሆኑ አንጻር፣ ለዴሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታ ድጋፍ እንዳደረጉ በተቆጠረላቸው ነበር። ከዲያስፖራ ጥገኝነትም ያላቅቋቸው ነበር።
  የመፅሄቱን ይዘት በዝርዝር ስመለከት ደግሞ እውነት የህወሓት ልሳን ነው ወይ? የሚል ጥያቄ እንዳነሳ አስገድዶኛል። ከመልካም አስተዳደር ጋር ተያይዞ በኢህአዴግ ውስጥ  መነቃቃት መፈጠሩ ይታወቃል፡፡ የህወሓት ጉባኤ ደግሞ ከሌሎች የግንባሩ ድርጅቶች የሰላ እንደነበር ተነግሯል፡፡ የዚህ የሰላ ጉባኤ ምልክት ተደርገው በህዝቡ ሞገስ ያገኙት ቄስ ገብረገርግስ ገብረማርያም የጉባኤዉን ሂደት ሲገልፁ፤ “ፊት ንፊት ገጢምና እንተወሐደ ንለባም ክርደኦ ገይርና አለና! ቀይናን እዉን ሰንቢዱ አሎ” (ቢያንስ ፊት ለፊት ገጥመን ልባሙን እንዲረዳ አድርገናል! ጠማማው ደግሞ ደንግጥዋል) ነበር ያሉት ከ ዉራይና መፅሄት ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ፡፡ ነባራዊው ሁኔታ እንዲህ ሆኖ ሳለ፣ ትግራይ ውስጥ የተፈጠረውን ማዕበል በተመለከተ ከወይን ምንም አለማግኘቴ ግርምት ፈጥሮብኛል። በኔ አመለካከት ወይን ቁጥር ሃምሳ (ሌሎች እትሞችን ስላላነበብኩ አስተያየት ለመስጠት ያስቸግረኛል) የዴሞክራሲ ማዕበሉ ያስፈራቸው የድርጅቱ አመራር ወይም ከበስተጀርባቸው የሚደጉሟቸው ሃይል ልሳን እንጂ የህወሓትን 12ኛ ጉባኤ መንፈስ የሚያንፀባርቅ አይደለም።  በተለይ የመከላከያ ጉዳይ አሳሳቢ ነው። ታዳጊ አገር እንደመሆናችንና ዴሞክራቲክ ተቋሞቻችን ደካማ በመሆናቸው የታጠቀው ሃይል ወይ ራሱ ንጉስ (King) ወይም አንጋሽና አፍራሽ (King Maker and breaker) የመሆን አደጋ ሊጋረጥብን ይችላል፡፡ አሁን የታየው ምልክት እንዳይሰፋ ከወዲሁ እርምጃ መውሰድ ተገቢ ነው፡፡ የሲቪልያን ቁጥጥሩም ጠበቅ ማለት ይኖርበታል፡፡ ጠንካራ የሃገር መከላከያ፣ የዴሞክራሲያዊ ስርዓታችን ዘብ ቢሆንም፤ ከልክ በላይ ካበጠ ግን የ ኢ-ዴሞክራሲያዊ ሃይሎች መሳርያ ስለሚሆን በዚህ ረገድ የተሰማሩ ምሁራን፤ ወታደራዊ ክፍሉ በዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ወይም ቅልበሳ (democratization and de-democratization) ላይ የሚኖረውን ሚና እንዲያጠኑት መንግስት ሁኔታዎችን ማመቻቸት አለበት፡፡ እኔ በበኩሌ በዚህ ዙርያ ኢትዮጵያን ማእከል አድርጎ የተጠና ጥናት አላገኘሁም።
 ----የመንግስት መገናኛ ብዙኃን ህገ-መንግስቱንና ሌሎች የአገሪቷን ህጎች ከቁብ እንደማይቆጥሩት በተግባር እያሳዩን ነው፡፡ የህወሓት 40ኛ አመት በትግራይ ቴሌቪዥን የወራት ሙሉ ሽፋን እንዲሁም በኢቢሲ (EBC) ላቅ ያለ ሽፋን የተሰጠው ተፎካካሪ ፓርቲዎች ትንፋሽ ለመተንፈስ እንኳ የማትበቃ ጥቂት ደቂቃ በተመደበላቸው የምርጫ ወቅት መሆኑን ስንገነዘብ ደግሞ የመንግስት መገናኛ ብዙኃንን ባህሪና ማንነት የበለጠ መረዳት እንችላለን፡፡ ለመሆኑ ህወሓት በትግራይ ቴሌቪዥንና በEBC ላሰራጨው የወራት ፕሮግራም ክፍያ ፈፅሟል? ቢፈፅምስ ይህ ተገቢ ተግባር ነውን?
 ---- ከመንግስት ውጪ የሆነ የግል የቴሌቪዥን ጣቢያ እስካሁን በአገራችን ላይ አለመኖሩ አስገራሚ ነገር ነው። የዚህ ዋና ምክንያት ምንድን ነው? ብሎ መጠየቅ ተገቢ ነው፡፡ ለመሆኑ  መንግስት፤ ከአብዮታዊ ዴሞክራሲ አስተሳሰብ የተለየ ሃሳብ ለሚያቀነቅኑ ወገኖች የቴሌቪዥን ፍቃድ ለመስጠት ድፍረት ይኖረዋል? ወይስ ለመንግስት የማያጎበድድ ከሆነ ፍቃድ አያገኝም?
  የዚህ ፅሁፍ ፀሃፊ፤ የካቲት 11 መከበር ያለበት፣ በዚህች አገር ታሪክ የዴሞክራሲና የልማት የማዕዘን ድንጋይ የተቀመጠበት ቀን ነው ብሎ ስለሚያምን ነው፡፡ ሆኖም ቀኑ ለርካሽ ጊዜያዊ ፕሮፓጋንዳና ህገ መንግስታዊ ድንጋጌዎችን በመጣስ ሌሎች ተፎካካሪ ፓርቲዎችን ለማፈን መዋል የለበትም ብሎ ያምናል፡፡ የምንወደውና የምናከበርው በዓል፤ ህገ መንግስትን ባከበረና ለዴሞክራሲያዊ ስርኣት ግንባታ አስተዋፅኦ በሚያደርግ መልኩ መከበር አለበት፡፡ የካቲት 11 ሁሌም መከበርና መዘከር ያለበት በዓል ነው። ይህን ስል ግን በሰማእታት ደም እየነገዱ ለመኖር ባለመ ሁኔታ መከበር እንደሌለበትም በማሳሰብ ነው። አንዳንዴ ለበዓሉ የሚወጣውን ገንዘብ ሳስተውል፣ ምናለ ለጥናትና ምርምር ፈሰስ ቢደረግበት እላለሁ፡፡
 በተመሳሳይ መንፈስ ህዳር 11 መከበርና መዘከር ያለበት ታሪካዊ ቀን ነው፤ ነገር ግን የክብረ በዓሉ አጀማመር ልክ የህወሓትን ይመስላል። ጋዜጠኞች ወደ ትግል ቦታ ተወስደዋል፤ በማን በጀት? የክልል ፓርላማ ግልፅ በሆነ መንገድ ከወሰነም፣ የክልሉ መንግስት ይህን ለማድረግ ህገ መንግስቱ ይፈቅድለታል ወይ? በጀቱስ ስንት ነው? ብአዴን በአማራ ክልል ቴሌቪዥንና በ EBC ለሚያሰራጨው ፕሮግራም ይከፍላል ወይ ? አሁንም የበዓሉ አከባበር ህገ መንግስቱንና ሌሎች ህጎችን የተከተለ ነው? እስከ ምን ድረስ አሳታፊ፣ ግልፅና ተጠያቂነትን በሚያረጋግጥ መልኩ እየተሰራ ነው? እስከ ምን ድረስ ሚዛናዊ መረጃስ ለህዝብ ያቀርባል? የሚሉት ጥያቄዎች መመለስ አለባቸው። ይህ ሃቅ ኦህዴድንም ደኢህድንንም የሚመለከት ነው፡፡ በቅርቡ ከኢቢሲ ዜና አንባቢ ጀርባ እናየው የነበረው የኢህአዴግ 10ኛ ጉባኤ መፈክርን ነበር፡፡ ይህ ምን ማለት እንደሆነ ብዙ የሚነግረን ነገር አለ፡፡ ለምሳሌ ዓረና/መድረክ ወይም አብኮ ድርጅታዊ ጉባኤ ቢያካሂዱ ኢቢሲ ተመሳሳይ ሽፋን ይሰጣል? ከእነአካቴውስ በቅጡ ይዘግበዋል? መምቻ ይሆናል ብሎ ካሰበ፣ “አዎ በደንብ ነው እንጂ” ይሆናል መልሱ፡፡ ይህ በግላጭ የሚታይ ፀረ ህገ መንግስትነት በጊዜ መታረም አለበት።
 ---- መሬት ላይ ያለው እውነታ ከላይ እንደተገለፀው ቢሆንም፤ ኢህአዴግ በ1992 ለውይይት ያቀረበው ሰነድ ግን እንደሚከተለው ይላል፡ “ህዝቡ ነፃና ዴሞክራሲያዊ በሆነ መንገድ መወሰንና መሳተፍ አለበት ሲባል ቅንና ሳይንሳዊ የሆኑ ሃሳቦችን ብቻ መስማት አለበት ማለት አይደለም፤ የተሳሳተና ኋላቀር ሃሳብንም በነፃ መስማት አለበት፡፡ ሰምቶ ከተከተለው መከተል ይችላል፡፡ በሂደት በተግባር ከስህተቱ ተምሮ ወደ አብዮታዊ ዴሞክራሲ አስተሳሰብ ይመለሳል፡፡ ካልተቀበለው ደግሞ ይበልጥ በነፃ ፍላጎቱና በሚያስተማምን አግባብ ቅን ወደሆነው ሃሳብ ይገባል፡፡ አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ የአስተሳሰብ ልዕልናውን የሚያረጋግጠው የተሳሳቱ ሃሳቦችን በማፈን አይደለም፡፡ የተሳሳቱ ሃሳቦችን ማፈን ማለት የሚያጋልጣቸውና የሚታገላቸው ሳይኖር ውስጥ ለውስጥ እንዲጎለብቱና እንዲጠነክሩ በር መክፈት ማለት ነው” ይላል በገፅ 65 ላይ፡፡
 ይህ የተጠቀሰው ዶክመንት በገፅ 123 ላይም እንዲህ ይላል፤ “መላውን ህዝብ /አብዛኛው ክፍል/ ለአመታት ለአንድ ፓርቲ አመለካከት በማጋለጥ፣ ሌሎችን በመከላከል የሚደረግ አሰራር መከተል በሃሳቦች መካከል ነፃ ውድድር እንዳይኖር የሚያደርግ ነው፤ የኃይለስላሴና የደርግ መንግስታት ይህን ማድረጋቸው የሚያመላክተው ፀረ-ዴሞክራሲያዊ ባህርያቸውን ነው” (ኢህአዴግ፣ 1992 ዓ.ም ገጽ 123) ። ምን ዋጋ አለው? ሰነድ ሌላ እውነታው ሌላ፡፡
---ሚዲያዎች ተገቢ ሚናቸዉን በተገቢ አዃሃን ከተጫወቱ የዴሞክራታይዜሽን ሃይል ሆነው የላቀ ጥቅም ይኖራቸዋል፤ይህ ሳይሆን ሲቀር ግን አጥፊና የኢ-ዴሞክራታይዜሽን ሃይል መሆናቸው አይቀርም።
  የአንድ ለአምስት ተቋም
 ---- አንድ ለአምስት አደረጃጀትም ለህዝቡ የቀረበና የሚወስዱት እርምጃዎችም ቀጥተኛ ተፅዕኖ የሚፈጥሩ በመሆናቸው ሊጠኑና በጥልቀት ሊዳሰሱ ይገባቸዋል፡፡ ይህ አደረጃጀት እታች ወርዶ የተፈጠረ ተቋም ሲሆን አጠቃላይ ህዝቡን ለልማት አነቃንቆ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ ባህላዊና ፖለቲካዊ በጎ ለውጦችን በማስመዝገብ፣ መዋቅራዊ ለውጥ ለማምጣት ሊያግዝ የሚችል ፈጠራ የታከለበት አደረጃጀት ነው፡፡ በአግባቡ ካልተያዘ ግን የደህንነት ተቋም ተቀጥያ ሊሆን ይችላል፡፡ ለጠባብ የፓርቲ ፖለቲካዊ መሳርያነት ከተጠቀምንበትም ጉዳቱ የከፋ ይሆናል፡፡
በቤተሰብ ውስጥ ስለላንና ጥራጣሬን ሊተክል ይችላል፤ አለን የምንለውን የቆየ ማህበራዊ እሴትንም ድምጥማጡን ሊያጠፋው ይችላል።
 ኢህአዴግ የሚመራው መንግስት ወደ ህዝቡ ወርዶ ለማገልገልና ድህነትን ለመቅረፍ የሚያደርገው ትግል ላቅ ያለ ምስጋና ይገባዋል፡፡ በማዳበርያ፣ በምርጥ ዘር፣ በእርሻ ቴክኖሎጂዎችና አስተምህሮዎች የሚያደርገው ድጋፍ እንዲሁም ውሃ፣ የጤና እና የትራንስፖርት አገልግሎት ወደ ገበሬው ለማድረስ የሚደረገው ጥረትም ይበል የሚያሰኝ  ነው፡፡ በስመ ነፃ ገበያና ሊበራል ዴሞክራሲ ከላይ የተጠቀሱት አገልግሎቶችና ግብአቶች  አይመለከተኝም፣ በገበያ ህግ ይመራ ቢል፣ ምን ሊከሰት እንደሚችል ማሰብ አያዳግትም፡፡
 ሆኖም ይህ ዘላቂ ነውን? ብለን መጠየቅ ተገቢ ነው፡፡ ዘላቂነት የሚረጋገጠው መሰረታዊ የተቋሙን (አንድ ለአምስት) ችግር ሲፈታ ነው፤ መሰረታዊ ችግሩ ደግሞ ሌላ ሳይሆን የዴሞክራሲ እጥረት (democratic deficiency) ነው:: በዚህ ዙርያ ብዙ ነገሮች ይነሳሉ፡፡ ጥልቅ ጥናት የሚፈልግና ከቦታ ቦታ ሊለያይ የሚችል ነገር መሆኑን ሳንዘነጋ ከአጠቃላይ ከባቢው (General environment) እና ከምታዘባቸው ነገሮች ተነስቼ ስለ ጉዳዩ ጥያቄ ማንሳት  ጠቃሚ ይመስለኛል፡፡ በትንሹ የገጠርን እንኳን ብንወስድ ከኢትዮጵያ ህዝብ ከ80% የሚሆነውን ህዝብ የሚያንቀሳቅስ አደረጃጀት መሆኑን ስንገነዘብ፣ በዚህ ጉዳይ ላይ መፃፉ ምን ያህል ጠቃሚ እንደሚሆን እንረዳለን፡፡
 አንድ ለአምስት የሚባለው ተቋም /አደረጃጀት/ ሰዎች በራሳቸው ተነሳሽነት የሚመሰርቱት ተቋም ተደርጎ ሊታይ ይችላል፡፡
የተቋሙ አባላት ለራሳቸው ጥቅም ሲሉ የተደራጁ ናቸው ብንል እንኳ ከውጭ የሚሰጥ አመራርም ቁልፉ ነገር ነው፡፡ ሆኖም ከዴሞክራሲ አኳያ ግን መመለስ ያለብን ጥያቄዎች አሉ፤ መሬት ላይ ያለውን ሃቅን መሰረት አድርገን በመነሳት፡፡
 እውን አሁን ያለን አንድ ለአምስት አደረጃጀት በአባላት በጎ ፍቃድ የተመሰረቱ ናቸው? ፍላጎታቸውን መሰረት አድርገው በነፃነት ራሳቸው ይወስናሉ? የቀረበላቸው ግብአት መርጠው የመቀበልና እምቢ የማለት መብት አላቸው? “ህዝብ ከራሱ ተሞክሮ ይማራል” የሚለው ዴሞክራሲያዊ መፈክር በተግባር ላይ እየዋለ ነው? ግምገማውስ ምን ይመስላል? አንድ ሰው በተለያየ ምክንያት ማዳበርያ ወይም ምርጥ ዘር አልገዛም ቢል ሰውዬው ላይ ምን ይከተላል? ይሄስ እንዴት ነው ሪፖርት የሚደረገው? ባለስልጣናት በቅጣት ሊታጀብ የሚችል ማስገደድን እያከናወኑ አይደለምን? እኔ በጣም አሉታዊና የተፈጠረውን በጎ ውጤት ሊያቀጭጭ ይችላል የሚል ድምዳሜ ነው ያለኝ፡፡ ዘላቂነቱ መረጋገጥ ካለበት የተቋሙ በዲሞክራሲ ዙሪያ የሚታዩ እጥረቶች መታከም መቻል አለባቸው፡፡
ይህ አገር ሙሉ የሚያንቀሳቅስ ተቋም፣ በፀረ ዴሞክራሲ አሰራርና ባህል ከተተበተበ፣ ኢትዮጵያ ላይ የሚያስከትለው ማህበራዊና ፖለቲካዊ ኪሳራ ለመገመት የሚያስቸግር ቀውስ የሚፈጥር ነው፡፡
 ባጭሩ ተቋሙ ቀና ለሆነ ልማታዊና ዴሞክራሲያዊ ተግባር እንዲውል ከተደረገ የዴሞክራታይዜሽን ሂደቱ ዋና መዋቅራዊ መሰረት ይሆናል፤ ምክንያቱም ከ80 ፐርሰንት በላይ የሚሆነው ህዝባችንን የሚያንቀሳቅስ ተቋም በመሆኑ ነው። በተቃራኒው ይህ ተቋም ወይም አደረጃጀት ከታለመለት አላማ አፈትልኮ፣ የጠባብ ፖለቲካዊ ፍላጎትና የቁጥጥርና ስለላ መዋቅር ተቀጥያ ከሆነ ግን የኢ-ዴሞክራታይዜሽን ሃይል ሆኖ ያርፈዋል፡፡
 ከአዘጋጁ፡- ይሄ የመጨረሻው የጽሁፉ ክፍል ለጋዜጣው በሚያመች መልኩ ኤዲት ተደርጎ የቀረበ ሲሆን በቦታ እጥረት ምክንያትም አንዳንድ ሃሳቦች መቀነሳቸውን ለውድ አንባቢያን ልንገልጽ እንወዳለን፡፡
 
ይ አንዳንድ ጉዳዮች የሚገባቸውን ያህል ኮምጨጭ ያለ ትኩረት ነፍጓቸዋል ። መልካም ፣ ሰናይ አእምሮ አለው ። የእእምሮ ወኔ አለው ፤ ይህ ከተራ ብልህነት ይዘላል ፤ የአእምሮ ጀግኖች ጥቂት ናቸው ።
የመውጪያ በር ፦
“ያለፈውን ዘመን ተቀብለን ካለፈው ተምረን የተሻለ የጋራ ቤት መሥራት እንችላለን።” ይላል በዕውቀቱ ሰዩም በዳዳ-ደስታ-ወየሳ።
የአዳም ረታ መረቅ የሚለው ረዥም ልብወለድ ውስጥ አላዛር የተባለው ገፀባህሪ የአስራ ዘጠኝ ሰባዎቹ ፖለቲካ ደብሮት ፦ “Hope is hopeless.” ብሎ ነበር ።
Hope is not hopeless. Hope is hopeful.
GOD BLESS AMERICA!


Read 5698 times