የ25 ዓመቷ አቀንቃኝ ሌዲ ጋጋ በትዊተር ገፅዋ ከ20 ሚሊዮን በላይ ተከታዮች በማፍራት አዲስ ክብረወሰን ያዘች፡፡ በሙሉ ስሟ ስቴፋኒ ጀርማኖታ የምትባለው ሌዲ ጋጋ፤ በሶሻል ሚዲያ አጠቃቀሟ ከፍተኛ የገበያ አቅም እየፈጠረች እንደሆነ ታውቋል፡፡ የትዊተር ገጽዋን ከሦስት ዓመት በፊት በመክፈት ከ20 ሚሊዮን በላይ ተከታዮች ያፈራችው ሌዲ ጋጋ፤ በተከታዮች ብዛት ቀዳሚ ሆናለች፡፡ ጀስቲን ቢበር ከ18 ሚሊዮን በላይ ተከታዮች በማፍራት በሁለተኛ ደረጃ ላይ ሲገኝ ኬቲ ፔሪ ከ15 ሚሊዮን በላይ፤ ሻኪራ በተቀራራቢ የተከታዮች ብዛት እስከ አምስተኛ ደረጃ ያለውን ቦታ አግኝተዋል፡፡ የሌዲ ጋጋ የመጨረሻ አልበሟ የሆነው “ቦርን ዚስ ዌይ” በትዊተር ከፍተኛ የማሻሻጥ ስራ ተሰርቶለት 8 ሚሊዮን ቅጂዎች እንደተሸጡ መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡ ከሶሻል ሚዲያ ድረገፆች የዝነኞችን ተወዳጅነትና የተከታዮች ብዛት በመጠቆም ትዊተር ግንባር ቀደም እንደሆነ ይታወቃል፡፡