የፍላሚንኮ ጊታር ተጫዋች ሪካርዶ ጋርሺያ፣ አይደጊል ጋርሺያ እና ይስሀቅ ባርቤሮ ከዳንሰኛ መላኩ በላይ ጋር የሙዚቃ ድግስ እንዲያቀርቡ ዝግጅት መደረጉን በኢትዮጵያ የስፔን ኤምባሲ አስታወቀ፡፡ኤምባሲው ለአዲስ አድማስ በኢ-ሜይል በላከው መግለጫ መሰረት፤ የሙዚቃ ድግሱ በመጪው ሐሙስ ከምሽቱ 12 ሰዓት በኢትዮጵያ ብሔራዊ ትያትር የሚቀርብ ሲሆን የዝግጅቱ መግቢያ በነፃ እንደሆነም ማወቅ ተችሏል፡፡