Sunday, 06 September 2020 00:00

ቢጂአይ ኢትዮጵያ አዲስ ቢራ ለገበያ አቀረበ

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(2 votes)

ቢጂአይ ኢትዮጵያ “ዶፕል” የተሰኘ በቀለሙም ሆነ በአይነቱ የተለየ አዲስ ቢራ ለገበያ ማቅረቡን አስታወቀ፡፡ ኢትዮጵያ በቢራ ምርት የሚገባት ደረጃ ላይ እስክትደርስና ኢትዮጵያዊያን የሚፈልጉትን የቢራ ጣዕም ማማረጥ እስኪችሉ ድረስ ጥናትና ምርምሮችን በማድረግ ብዙ አዳዲስና ዓለም አቀፍ እውቅና ያላቸውን ቢራዎች በሀገር ውስጥ እያስጠመቀ ማቅረቡን ያስታወሰው ኩባንያው፤ ባለ ደማቁ ጣዕምና ባለ ቡናማው ቀለም “ዶፕል” ቢራም የዚሁ የምርምርና የጥራት ውጤት መሆኑን አስታውቋል፡፡
አዲሱ ቢራ የሙከራ ቀመሳ በተደረገበት ወቅት ቀማሾቹ ሙሉ ለሙሉ በጣዕሙ የተስማሙበት መሆኑን የጠቆመው ቢጂአይ፤ ይሄ ሙሉ ኢትዮጵያዊ ጣዕምን የያዘና በኩባንያው የቢራ ሊቃውንት የተመረተ አዲስ ቢራ ለደንበኞቹ አቅርቧል፡፡
ዶፕል እስከ ዛሬ ከሚመረቱትና ወርቃማ ቀለም ካላቸው ቢራዎች የተለየ ደማቅ ጣዕምና ቡናማ ቀለም ያለው የመጀመሪያው ቢራ ሲሆን ጠጪዎች ቀለል ያለ ቢራ እየጠጡ ነገር ግን የተሻለ ለዛ ወዳለው ጠንካራ ቢራ መዞር ለሚፈልጉ እጅግ ትክክለኛ ምርጫ ነው ብሏል - ቢጂአይ፡፡ ዶፕል ቢራ በአሁኑ ወቅት በሁሉም የመጠጥ መሸጫ መደብሮች እንደሚገኝና ለተጠቃሚ መድረስ እንደጀመረም ታውቋል፡፡

Read 2835 times