• ሁሉም ሰው ጭምብል እያጠለቀ
ነው። እውነተኛ ህይወት የሚገኘው
በሥነፅሁፍ ውስጥ ነው። በልብወለድ
ጭምብል ውስጥ ነው እውነቱን
መናገር የምትችለው።
ጋኦ ዚንግጂያን
• ከሥነጽሁፍ የምታገኘው መልስ
በምታቀርባቸው ጥያቄዎች ይወሰናል።
ማርጋሬት አትውድ
• የሥነ-ጽሁፍ ዘውድ ሥነ-ግጥም ነው።
ዊሊያም ሶመርሴት ሟም
• የሥነጽሁፍ ማሽቆልቆል የአገርን
ማሽልቆል ያመለክታል፡፡
ጆሃን ዎልፍጋንግ ቮን ገተ
• ቅኔ የላቀ የሥነጽሑፍ ዓይነት ነው።
አልፍሬድ ሂችኮክ
• ሥነፅሁፍ ዜና ሆኖ የሚቆይ ዜና ነው።
ኢዝራ ፓውንድ
• ህይወት ከሥነጽሁፍ ውጭ ገሃነም
ነው።
ቻርለስ ቡኮውስኪ
• የእያንዳንዱ ሰው ትውስታ የግሉ
ሥነጽሁፍ ነው።
አልዶዩስ ሃክስሌይ
• እኔ ሥነፅሁፍ ብቻ ነኝ፤ ሌላ ልሆን
ወይም ለመሆን ፈቃደኛ አይደለሁም።
ፍራንዝ ካፍካ
• ቋንቋ የሰዎች ልብ መክፈቻ ቁልፍ
ነው።
አህመድ ዲዳት
• ሥነፅሁፍ ሞትን ለማሸነፍ ምርጡ
መንገድ ነው።
አይላን ስታቫንስ
• ሥነጽሁፍ የኖረው ዓለም በቂ
ባለመሆኑ ነው።
ፈርናንዶ ፔሶአ
• ሥነፅሁፍ የኒዩክሌር ቦምብ ተቃራኒ
ነው።
አሩንድሃድ ሮይ
• ሥነጽሁፍ የምናባዊ ሰዎች እውነተኛ
ህይወት ነው።
ስቴፋኖስ ሊቮስ
• የሥነፅሁፍ ታሪክ የሰው ልጅ ታሪክ
ነው።
ዊልያም ሂክሊንግ ፕሬስኮት
Published in
ጥበብ