Saturday, 29 January 2022 00:00

ኤምሬትስ በድጋሚ ወደ ኢትዮጵያ በረራ ሊጀምር ነው

Written by 
Rate this item
(0 votes)

ኤምሬትስ ከነገ ጥር 22 ጀምሮ ከዱባይ ወደ 5 የአፍሪካ ሀገራት በድጋሚ በረራዎችን ማድረግ ሊጀምር መሆኑን አስታወቀ፡፡
ኤምሬትስ ወደ አዲስ አበባ በየቀኑ በረራዎችን ማድረግ የሚጀምር ሲሆን EK 723 ከጠዋቱ 3፡25 ከዱባይ በመነሳት ቀትር 6፡40 አዲስ አበባ የሚደርስ ሲሆን ሌላኛው EK 724 ደግሞ ከሰዓት 9፡05 ከአዲስ አበባ በመነሳት ምሽት 2፡15 ዱባይ የሚደርስ ይሆናል ተብሏል፡፡
ከአፍሪካ ሀገራት ተነስተው በኤምሬትስ በረራ  መዳረሻቸውን ዱባይ የሚያደርጉ ማናቸውም መንገደኞች  በ48 ሰዓት ውስጥ የተደረገ የኮሮና ቫይረስ ምርመራና ፍቃድ ካለው የጤና ተቋም የተሰጠ  ከወረርሽኙ ነፃ (ኔጌቲቭ) መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ሰርተፍኬት እንዲያሳዩ ይጠየቃሉ፡፡ ዱባይ ሲደርሱም በድጋሚ የኮቪድ-19 ምርመራ የሚደረግላቸው ሲሆን ውጤቱ እስኪነገራቸው ድረስ ለብቻቸው የሚቆዩ  (ኳረንቲን)  ይሆናል ተብሏል፡፡
ከአፍሪካ ሀገራት ወደ ዱባይ የሚበሩ ተሳፋሪዎች ሁሉ በመዳረሻቸው የሚጠየቁትን ህግጋት እንዲከተሉና እንዲያከብሩ ይገደዳሉ፤ ብሏል የኤምሬትስ መግለጫ፡፡

Read 2351 times Last modified on Friday, 04 February 2022 05:47