Saturday, 24 June 2023 20:32

ሐኪም ተከታዩን ማስተማር ግዴታው ነው

Written by  ፀሐይ ተፈረደኝ ከኢሶግ
Rate this item
(1 Vote)

 በኢትዮጵያ 21 ሚሊዮን የሚሆኑ ሴቶች ለመራቢያ አካላት የጤና ችግር ሊጋለጡ በሚችሉበት እድሜ ውስጥ ይገኛሉ፡፡
በ9394 ላይ ደውሎ We care digital health ን ማማከር ለጤና ችግሮች መፍትሔ ለማግኘት ያስችላል፡፡
ዶ/ር በቴል ደረጀ በቅዱስ ጳውሎስ ሚሊኒየም ሜዲካል ኮሌጅ የጽንስና ማህጸን ሕክምና እስፔሻሊስትና የመራቢያ አካላት ካንሰር ሐኪም ናቸው፡፡ ዶ/ር ቤተል የ We care digital health ዋና ስራ አስኪያጅ በመሆንም በማገልገል ላይ ናቸው፡፡ ዶ/ር ቤተል ደረጀ ከዛሬ ሶስት አመት ወዲህ የመራቢያ አካላት ካንሰር ሐኪምም ሲሆኑ በአጠቃላይ በአገሪቱ በዚህ ሙያ ከተሰማሩት 20 ባለሙያዎች አንዱዋ ናቸው፡፡ በአሁኑ ወቅት የመራቢያ አካላት ካንሰር ህክምና ባለሙያ የሆኑ ሴቶችም በቁጥር አምስት ደርሰዋል፡፡ በኢትዮጵያ 21 ሚሊዮን የሚሆኑ ሴቶች ለመራቢያ አካላት ሊጋለጡ በሚችሉበት እድሜ ውስጥ ይገኛሉ፡፡ ከዚህ አንጻር ያለው ባለሙያ ብቁ ነው ባይባልም በፊት ከነበረው ግን የተሻሻለ እና ተስፋ የሚያስቆርጥ አይደለም እንደ ዶ/ር ቤተል አባባል፡፡ ወደፊትም ባለሙያዎች ቁጥራቸው እንደሚጨምር ተስፋ አለ፡፡
ዶ/ር ቤተል ደረጀ የዶ/ር ደረጀ ጉልላት ልጅ ስትሆን አባትዋም በሙያቸው የቀዶ ጥገና ሐኪም እንዲሁም የደረትና የልብ Sub specialist ናቸው፡፡ ዶ/ር ቤቴል በስተመጨረሻ ዶ/ር ያውም የጽንስና ማህጸን ሐኪም ለመሆን የመብቃት ምስጢር የአባታቸው ምኞትና ሀሳብ ጭምር እንደነበር ያስታውሳሉ፡፡ እነሆ ዛሬ በመደበ ኛው ሰአታቸው በቅዱስ ጳውሎስ ሚሊኒየም ሜዲካል ኮሌጅ ከሚሰጡት የህክ ምና አገልግሎት በተጨማሪ የ We care digital health ስራ አስኪያጅ በመሆንም በማገልገል ላይ ናቸው፡፡ ዶ/ር ቤተል በቅዱስ ጳውሎስ ሚሊኒየም ሜዲካል ኮሌጅ በመምህርነትም የሚያገለግሉ ሲሆን ይህንንም ሲገልጹት ‹‹ ሐኪም ያወቀውንና በስራ ላይ ያገኘውን ልምድ ለቀጣዮቹ ማስተላለፍ በምረቃው ወቅት ከሚገባቸው ግዴታዎች ውስጥ አንዱ ነው፡፡  
We care digital health ምን የሚሰራ ድርጅት ነው የሚለው ለዶ/ር ቤተል ደረጀ ያነሳው የመጀመሪያ ጥያቄ ነበር፡፡ እሳቸውም መልሳቸው እንደሚከተለው ነበር፡፡ ‹‹ We care digital health የተባለው ድርጅት የሚሰራው አማራጭ ያጡ ሰዎች ጤናቸውን በሚመለከት ቴክኖሎጂን በመጠቀም አማራጭ የህምና አገልግሎት ማግኘት የሚችሉበት ነው፡፡ አማራጭ ሲባልም አንዳንድ ጊዜ ለህክምና የሚፈለጉ ሐኪሞች የት እንዳሉ የት እንደሚሰሩ አለማወቅና አንዳንድ ጊዜ ደግሞ በጣም የተራዘመ ወረፋ ሊገጥም በሚችልበት ወቅት ተመሳሳይ አገልግሎት የሚሰጡ ሌሎች አማራጭ ሐኪሞችን ለማማከር ቢፈለግ ወይንም ደግሞ መጀመሪያውኑ የሚፈለጉትን ሐኪሞች በክሊኒካቸው ማግኘት ባይቻል እንኩዋን በስልካቸው በሚያማክሩበት ሰአት ወይንም  በ On line-በሚገኙበት ወረፋ ባልሆነበት ሰአት ማግኘት የሚቻልበትን አጋጣሚ መፍጠር ነው፡፡ ይህ ማለት ህብረተሰቡ ጤንነቱን በሚመለከት እንዲያማክረው የሚፈልገውን ሐኪም ማግኘት ሲሳነው  We care digital health በዘረጋው ዘመናዊ የግንኙነት መስመር ካለችግር ሊያገኙ እንዲችሉ የተመ ቻቸ አሰራር ነው፡፡ ታካሚዎች ሐኪማቸውን ማግኘት ሳይችሉ ሲቀሩ ወይም በወረፋ ምክን ያት ያሉበት ሕመም እየባሰ እንደሚሄድና ወቅታዊ መፍትሔ እንዲያገኙ በሚፈልጉበት ወቅት ባሉበት ሆነው ሐኪማቸውን በቀላሉ አግኝተው ስለሕመ ማቸው ምክር እሚያገኙበት ዘዴ ነው፡፡
ሐኪምን ከማማከር ውጪ ድርጅቱ የሚሰጠው አገልግሎትን በሚመለከትም ዶ/ር ቤተል ደረጀ የሚከተለው ብለዋል፡፡
ሰዎች በስልክ ቁጥር 9394 ላይ ደውለው ፡-
የሚፈልጉትን ህክምና የት መታከም እንዳለባቸው፤
የሚፈልጉዋቸው ሐኪሞች የት እንደሚያገኙአቸው፤
የሚፈልጉትን መድሐኒት የት እንደሚያገኙ…..ወዘተ
የተለያዩ ከህክምና ጋር የተያያዙ ጥያቄዎችን ለሚያነሱ ተገልጋዮችም We care digital health መልስ በመስጠት አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል፡፡ ይህ አገልግሎት ታካሚዎች ብቻ ሳይሆኑ ማንኛውም መረጃ የሚፈልግ ሰው በ9394 ላይ ደውሎ የሚፈልገውን ማግኘት ይችላል፡፡
የተለያዩ ጥያቄዎች ከህብረተሰቡ ሲነሳ በ We care digital health በሚገኙ ሐኪሞች ወዲያው መልስ የሚያገኙበት እድል ከሌለ ድርጅቱ እራሱ ባለው መረጃ እና በማፈላለግ ለዚህ ጥያቄ በዚህ አድራሽ እከሌን ወይንም ይህንን የጤና ተቋም ያግኙ የሚል የምክር አገልግሎ ቶች እንሰጣለን ፡፡  
አንዳንድ ጊዜ ታካሚዎች ለሕመማቸው የሚመቸውን ሐኪም  ወይንም የህምና ቦታ ለማግኘት ሶስት አራት ቦታ ይሄዳሉ፡፡ We care digital health የሰጠው አማራጭ ግን በ9394 ደውለው ጉዳዩን ቢያማክሩ ካለምንም ችግር መፍትሔ ያገኛሉ ብለዋል ዶ/ር ቤተል ደረጃ ፡፡
We care digital health ከሚሰጣቸው አገልግሎቶች ውስጥ የቤት ለቤት ሕክምና አገልግ ሎትም ይገኝበታል፡፡ አንዳንድ ጊዜ ሰዎች በህክምና ተቋም መቆየት ሳይኖርባቸው በቤታቸው ሆነው ህክምናቸውን እንዲከታተሉ የሚደረጉበት ሁኔታ ያጋጥማል፡፡ በዚህ ጊዜ በተመላ ላሽነት የህክምና ባለሙያዎች ነርሶች ….ሌሎችም የህክምና ባለሙያዎች በሚፈለጉበት ቦታ ሄደው አገልግሎቱን ለፈላጊዎች እንዲያደርሱ ሁኔታዎችን ያመቻቻል፡፡
 በቤት ውስጥ የህክምና አገልግሎት እንዲያገኙ ሁኔታዎች የተመቻቹላቸው ሰዎች በሁዋላ ወደጤና ተቋም የመሄድ ሀሳብ ቢኖራቸውም ታካሚዎች በቤት ውስጥ ሕክምና በሚያደርጉበት ወቅት የነበራቸውን የህክምና ታሪክ፤ያገኙትን ህክምና፤ የመሳሰሉትን መረጃዎች በማጠናከር ለሚሄዱበት የህክምና ማእከልም በተሟላ ሁኔታ ማስረከብ አንዱ ስራ ነው፡፡  ይህ አገልግሎት ቀደም ባሉ ጊዜያት በእውቅና በመሳሰሉት ካልሆነ በስተቀር የማይገኝ የነበረ ሲሆን እንዲህ እንደልብ በተቋም ደረጃ መገናኘት ግን ከምንም በላይ ለታካሚዎች መፍትሔ መሆኑ አይካድም፡፡  
We care digital health ከሚሰራባቸው ቢሮዎች ተገኝተን የተመለከትነው የጥሪ ማእከሉን ሲሆን በዚያም ባለሙያዎች የሚጠቀሙባቸው በርካት ያሉ ኮምፒዩተሮችን ተመልክተናል፡፡ ይህም ጥያቄ ወይንም አገልግሎት ካላቸው የህብረተሰብ ክፍሎች ጥያቄ ወይም አስተያየት ተቀብለ ውበት መልስ የሚሰጡበት አደረጃጀት ያለው ነው፡፡ ዶ/ር ቤቴል እንደገለጹት እነዚህ ባለሙ ያዎች የጤና ባለሙያዎች ወይንም ዶክተሮች እና አንዳንድ ነርሶች ናቸው፡፡ ዶ/ር እንደሚ ሉት በመደበኛነት በቢሮው ውስጥ ከሚሰሩት በተጨማሪ በበጎ ፈቃደኝነት ለማገ ልገል ወደ (2500)ሁለት ሺህ አምስት መቶ የሚሆኑ የህክምና ባለሙያዎች የተመዘገቡ ሲሆን ካሉበት ቦታ ሆነው በተዘረጋው ቴክኖሎጂ ለሚቀርብላቸው የህክምና አገልግሎት ተገቢውን ምላሽ በመስጠት ላይ ይገኛሉ፡፡ በበጎ ፈቃደኝነት የተመዘገቡት ሐኪሞች ጠቅላላ ሐኪሞች፤Sub Specialiste; ኒውትሪሽኒስቶች፤ፒዚዮቴራፒስቶች ባጠቃላይ በ(38) አይነት የህክምና አገል ግሎት ተመድበው የሚሰሩ ናቸው፡፡ ስለዚህ ይሄንን ህክምና በሚል የተለየ ሳይሆን በሁሉም አይነት የህክምና አገልግሎት ለሚነሱ ፍላጎቶች መልስ የሚሰጥ ነው፡፡   
We care digital health ከጥሪ ማእከሉ በተጨማሪ ሌሎች አገልግሎቶች የሚሰጡበት ተጨማሪ ሁለት ቢሮዎች ያሉት ሲሆን ስራውን ከጀመረ ወደ ሁለት አመት ሆኖታል፡፡ እንደ ዶ/ር ቤቴል ማብራሪያ ይህ አገልግሎት በአዲስ ቴክኖሎጂ እንዲታገዝ በአዲስ መልክ የተጀመረ ነው፡፡ ምንጊዜም አዲስ ነገር ሲጀመር የተጀመረውን አገልግሎት በምን መንገድ እንደሆነ ማስተማርና ከዚያም በላይ አገልግሎቱን ለመጠቀም ፈቃደኛ የሆነ ህብረተሰብ ማግኘት እንደ አንድ ችግር የሚታይ ነው፡፡ ቢሆንም ግን ይህ አገልግሎት 9394 ላይ በመደወልና በዩቲዩብ ቻንል We care digital health በሚለው አገልግሎቱን ለመጠቀም የሚሹ በርካታ ሰዎችን አግኝተናል ብለዋል ዶ//ር ቤቴል፡፡ በሁለት አመት ጊዜ ውስጥ ወደ 23ሺህ የሚደርሱ የስልክ ጥሪዎችን ተቀብለን ጥያቄዎቹን መመለስ ወይንም ከህክምና ባለሙያዎች ጋር ጉዳዮችን በማገናኘት መፍትሔ ማቅረብ ችለናል፡፡ በማህበራዊ ሚድያዎች ጭምር የምናስተ ላልፋቸውን ትምህርቶች የሚከታተሉ ብዙ ደምበኞች አሉን፡፡ ለሕክምና ባለሙያዎችም ስራ ከመፍጠር በተጨማሪ የህክምና ባለሙያዎችን በቀላሉ ለማግኘት የሚያስችል አማራጭ በመፍጠራችን ለውጥ አምጥተናል ብለን እናስባለን፡፡ አከፋፈልን በሚመለከትም ዘመኑ ባፈራቸው የቴክኖሎጂ ውጤ ቶች ማለትም በቴሌብር ወይንም በሞባይል ባንኪንግ በመሳ ሰሉት መጠቀም እንደሚችሉ ዶ/ር ቤተል ደረጀ በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል የመራቢያ አካላት ካንሰር ሕክምና እስፔሻሊስት እና የ We care digital health ዋና ስራ አስኪያጀ አብራርተውልናል፡፡




Read 611 times