Friday, 01 September 2023 12:58

‹‹የነፍስ እኩያሞች›› የአጫጭር ልብወለዶች መድበል የፊታችን ማክሰኞ ይመረቃል

Written by 
Rate this item
(0 votes)
በአስራ አንድ ደራሲያን ተፅፎ ለህትመት የበቃው ‹‹የነፍስ እኩያሞች›› የተሰኘ 25 የአጫጭር ልብወለዶች ስብስብ መጽሐፍ፣ የፊታችን ማክሰኞ ነሐሴ 30 ቀን 2015 ዓ.ም በሐገር ፍቅር ቴያትር አዳራሽ ከቀኑ 11:00 ሰዓት ጀምሮ የጥበብ ቤተሰቦች በተገኙበት ይመረቃል፡፡
በመድበሉ ሥራቸው የተካተተላቸው ደራሲያን፡- ሊዲያ ተስፋዬ፣ መንግስቱ መርሐጽዮን ፣ ምርት ባቦ፣ ሮማን ተወልደብርሃን ፣ ቢኒያም አቡራ፣ አበባ የሺጥላ (ዶ/ር)፣ አንለይ ጥላሁን ምትኩ፣ እመቤት ተሾመ፣ ኪሩቤል ዘርፉ፣ ዶዲ ዘመዴ እና ጋሻው የኋላሸት (ዘቢደር) ናቸው።
በምረቃው ሥነሥርዓት ላይ ደራሲ ዓለማየሁ ገላጋይ፣ ደራሲት የዝና ወርቁና መምህር መሠረት አበጀ የክብር እንግዶች ሲሆኑ፤ የመጽሐፍ ዳሰሳ በቴዎድሮስ አጥላው የሚቀርብ ይሆናል ተብሏል፡፡
የመድረኩ መሪ ረድኤት ተረፈ ስትሆን፤ ዶ/ር አበባ የሺጥላ፣ ኪሩቤል ዘርፉና ጋሻው የኋላሸት ግጥም እንደሚያቀርቡ አዘጋጆቹ ለአዲስ አድማስ ገልጸዋል፡፡
የቴሌግራም ቻናልችንን በመቀላቀል የአዲስ አድማስን መረጃ ይከታተሉ…
Read 1031 times