የፕሮፌሰር ባሕሩ ዘውዴ “ኅብር ሕይወቴ፤ግለ ታሪክ” መጽሐፍ፣ ዛሬ ከ8:00 ጀምሮ በሃይሌ ግራንድ ሆቴል እንደሚመረቅ ተገለጸ፡፡
በምርቃት ሥነስርዓቱ ላይ ፕ/ር ሰብስቤ ደምሰው፣ ዶ/ር ዘሪሁን መሃመድ፣ ጋዜጠኛ መዓዛ ብሩ፣ ገጣሚ ነቢይ መኮንን፣ ወግ አዋቂ በሃይሉ ገ/መድህን፣ አርቲስት ተፈሪ አለሙና ሌሎችም ታዋቂ ሰዎች ይታደሙበታል ተብሏል፡፡
መርሃግብሩን አርትስ ቴሌቪዥን ከፕሮፌሰሩ አክባሪና ወዳጆች ጋር ያሰናዱት ሲሆን፤ መድረኩን ጋዜጠኛ ሶዶ ለማና ገጣሚ ምሥራቅ ተፈራ እንደሚመሩት ታውቋል፡፡ የምርቃት ሥነስርዓቱን “ያለፈውን መሸኛ የሚመጣውን አዲስ አመት ደግሞ መቀበያ እናደርገዋለን!” ብለዋል፤ አዘጋጆቹ፡
Published in
ኪነ-ጥበባዊ ዜና