Monday, 30 October 2023 20:35

በአድዋ ተራራዎች ላይ የአንባገነኑ መሪ የቤኒቶ ሙሶሊኒ የፊት ቅርፅ ሐውልት ቆሞ እንደነበር.ያውቁ ኖሯል.....?

Written by 
Rate this item
(2 votes)

ይህን ያውቁ ኖሯል.....?

በአድዋ ተራራዎች ላይ የአንባገነኑ መሪ የቤኒቶ ሙሶሊኒ የፊት ቅርፅ ሐውልት ቆሞ እንደነበር......

በ 2ተኛ የኢጣሊያን ወረራ ዘመን በአድዋ በሱሎዳ ተራራ ፊት ለፊት ላይ በፋሺስት ወታደሮች የተገነባው ይህ ሃውልት ቁመቱ 4.80 ሜትር ከፍታ የነበረው ሲሆን ፤ የጣሊያን ወታደሮች በወቅቱ የዚህ ሐውልት በቦታው የመገንባታቸው ዋንኛው ዓላማ እና ለማስተላለፍ የፈለጉት መልዕክት:-

➻ በ 1888 ዓ.ም ላይ የደረሰባቸውን ሽንፈት በውስጣቸው ለነበረው ቁጭት እና እፍረት ማካካሻ ይሆናል ብለው በማሰብ እንዲሁም በሃጉረ አፍሪካ ለነበሩት ለሌሎቹ የቀኝ ገዢዎች የአውሮፓውያን ሃገራት የጠንካራነት ማሳያ የሞራል ማበረታቻ ምልክት ይሆናል በማለት ነበር ከ 40 ዓመት በፊት ሽንፈታቸው ከተጎነጩባት ቦታ ላይ በወርሃ የካቲት 1928 ዓ.ም ላይ ገንብተው ያቆሙት።

ሆኖም ግን አሁን ሐውልቱ በቦታው የለም ሀገራችን ከፋሺስት ጣሊያን ነፃ ከሆነች በኋላ በቦታው ምንም አይነት የሐውልቱ አሻራ እና ፍርስራሽ እንዳይኖር ተደርጎ ሊፈረስ ችሏል።

ክብርና ሞገስ ከወራሪ ነፃ ሀገር ላስረከቡን ጀግኖች አርበኞቻችን

Read 589 times