Wednesday, 01 November 2023 00:00

የስኳር ድንች የጤና ጥቅሞች

Written by 
Rate this item
(0 votes)

ስኳር ድንች ገንቢ እና ጣፋጭ አትክልት ሲሆን፤ ብዙ የጤና ጠቀሜታዎችን ሊሰጠን ይችላል።

➡️ በቫይታሚን ኤ የበለጸገ ነው። ይህም ለዓይን ጤና፣ ለበሽታ የመከላከል አቅም እና ለቆዳ ጤንነት አስፈላጊ ነው።

➡️ አንቲ-ኦክሲዳንቶችን (Antioxidants) በውስጡ ይዟል። እንደ:- ካንሰር፣ የስኳር በሽታ እና የልብ ሕመም ካሉ ሥር የሰደዱ በሽታዎች ጋር የተቆራኙትን፤ ኦክሲደቲቭ ስትረስ እና ኢንፍላሜሽንን (Oxidative Stress & Inflammation) የሚከላከሉ አንቲ-ኦክሲዳንቶች (Antioxidants) አሉት።

➡️ ዝቅተኛ የግሊሲሚክ ኢንዴክስ መጠን አለው። ይህም ማለት ምግብ ከተመገቡ በኋላ በደም ውስጥ ያለው የስኳር መጠን በፍጥነት አይጨምርም።

ይህ በደም ውስጥ ያለውን የስኳር መጠን ለመቆጣጠር እና ከስኳር በሽታ ጋር ተያይዘው የሚመጡ ተጓዳኝ የጤና ችግሮችን ለመከላከል ይረዳል።

➡️ በፋይበር ይዘቱ የበለፀገ ነው። ይህም የአንጀት ጤናን ይጠብቃል፣ የኮሌስትሮል መጠንን ይቀንሳል፣ የሆድ ድርቀትን ይከላከላል።

➡️ በተለያዩ የሜታቦሊክ ሂደቶች እና የኢንዛይም ተግባራት ውስጥ የሚሳተፉን:- ማንጋኒዝ፣ ኮፐር እና ፓንታቶኒክ አሲድ (Pentatonic Acid) ምንጭ ነው።

➡️ ፀረ-ካንሰር ባህሪ አለው። አንዳንድ ጥናቶች እንደሚያሳዩት ከሆነ፤ እንደ:- የጡት፣ የአንጀት እና የፕሮስቴት ካንሰር ያሉ አንዳንድ የካንሰር ሕዋሳት እድገትን ሊገታ ይችላል።

➡️ የክብደት መቀነስን ያግዛል። ዝቅተኛ የካሎሪ እና የስብ ይዘት እንዲሁም ከፍተኛ የውሃ እና ፋይበር ይዘት ያለው ሲሆን፤ ይህም የጥጋብ ስሜትን ሊጨምርና የምግብ ፍላጎትን ሊቀንስ ይችላል።

➡️ የአንጎል ሥራን ያሻሽላል። ለማስታወስ፣ ለመማር እና ለግንዛቤ አፈፃፀም አስፈላጊ የሆነውን ኮሊን (Choline) የተባለውን ንጥረ-ነገር በውስጡ ይዟል።

➡️ በሽታ የመከላከል አቅምን ይጨምራል። ነጭ የደም ሴሎችን እና ኢንፌክሽኖችን የሚዋጉ አንቲበዲዎች እንዲፈጠሩ ወይም እንዲመረቱ የሚያደርገውን ቫይታሚን-ሲ በውስጡ ስለያዘ፤ በሽታ የመከላከል አቅምን ከፍ ያደርጋሉ።

➡️ የቆዳ ጤንነትን ያሻሽላል። ቆዳን ከፀሀይ ጉዳት፣ ከእርጅና እና ከብጉር ሊከላከል የሚችል የቫይታሚን-ኤ ጥሬ ዕቃ የሆነው ቤታ ካሮቲን ስላለው፤ የቆዳ ጤንነትን ማሻሻል ይችላል።


Read 553 times