Sunday, 12 November 2023 08:26

የሠላም ድርድሩ ዛሬ ይጠናቀቃል ተብሎ ይጠበቃል

Written by  መታሰቢያ ካሳዬ
Rate this item
(4 votes)

 በድርድሩ የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት ዋና አዛዥ ኩምሣ ድሪባ (ጃል መሮ)ተሳትፏል
                       
       በመንግስትና የኦሮሞ ነፃነት  ሰራዊት (ኦነሰ) መካከል ከማክሰኞ ጀምሮ በታንዛኒያ ዳሬሰላም ሲካሄድ የሰነበተው የሰላም ድርድር ዛሬ ይጠነቃል ተብሎ ይጠናቀቃል። ድርድሩ ሁለቱን ወገኖች ወደ ሰላም በማምጣት አካባቢውን ለማረጋጋት ያስችላል የሚል ተስፋ ተጥሎበታል።
የፌደራል መንግስቱና ኦሮሚያ ክልል መንግስት ከሁለት የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት ከፍተኛ አመራሮች ጋር ለ3 ሳምንታት  የቆየ የፖለቲካ ውይይት ሲያደርጉ መቆየታቸውን የገለፁት ምንጮች፤ የታዛኒያው የሰላም ድርድር የፖለቲካ ውይይቱ ውጤት መሆኑን ጠቁመው በውይይቱ የታየው መግባባትም የሰላም ድርድሩ ስኬታማ ሊሆን እንደሚችል መፍጠሩን ገልጸዋል።
በዚሁ በታንዛኒያ ዳሬሰላም ሲካሄድ በሰነበተው የሠላም ድርድር የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት (ኦነስ) መሪ ኩምሳ ድሪባ (ጀልሮል) የተሳተፈ ሲሆን በዚህ ሂደትም ጀልመሮ ለመጀመሪያ ጊዜ ከፌደራል መንግስቱ ከፍተኛ ወታደራዊ አመራሮች ጋር ፊት ለፊት መገናኘቱም ታውቋል።
በታንዛኒያ ዳሬሰላም በመንግስትና በኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት (ኦነግሸኔ) መካከል ሲካሄድ የሰነበተውን የሰላም ድርድር በማመቻቸት ረገድ አሜሪካ፣ ኢጋድ፣ ኬኒያ እና ኖርዌይ ቁልፍ ሚና የተጫወቱ ሲሆን፤ የኢጋድ ዋና ፀሐፊ ዶ/ር ወርቅነህ ገበየሁ ሁለቱን ወገኖች በማወያየትና በማደራደሩ ጉዳይ ከፍተኛ አስተዋፅኦ እንደነበራቸው ተናግሯል።ዛሬ ይጠናቀቃል ተብሎ በሚጠበቀው በዚሁ የሰላም ድርድር ላይ የፌደራል መንግስቱን ወክለው የመከላከያ ሰራዊት የደህንነት ኃላፊ ጄኔራል ጌታቸው ጉዲና እና በመጀመሪያው ዙር የታንዛኒያው ድርድር ተሳታፊ የነበሩት ምክትላቸው ሜጀር ጄኔራል ደምስ አሜኑ እንደተሳተፉ ታውቋል።
በኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት በኩል የድርጅቱ ዋና አዛዥ ድሪባ ኩምሳን (ጀልመሮን) ጨምሮ ኤፍረስ ኤርጌሳና ጅሬጅ ጉደታ እንደሚገኙበትም ታውቋል።

Read 2253 times