Saturday, 02 December 2023 19:15

ሕብረት ባንክ የተመሰረተበትን 25ኛ ዓመት እያከበረ ነው

Written by 
Rate this item
(0 votes)

 የሕብረት ባንክ 25ኛ ዓመት የብር ኢዮቤልዮ ክብረ በዓል ከሕዳር 11 ቀን 2016 ዓ/ም ጀምሮ በተለያዩ ዝግጅቶች እያከበረ ነው። የዚሁ በዓል አካል የሆነው የእውቅናና የድጋፍ መርሀ-ግብርም ተከናውኗል፡፡ባንኩ ከተመሰረተበት ጊዜ ጀምሮ በዳይሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢነት እናበዋና ስራ አስፈጻሚነት ያገለገሉ እንዲሁም አሁን በማገልገል ላይ ያሉ አመራሮች ከእለቱ የክብር እንግዳ አቶ ማሞ እስመለዓለም ምህረቱ የብሔራዊ ባንክ ገዥ እጅ እውቅና እና ሽልማት ተቀብለዋል፡፡ በተመሳሳይ ከ24 አመት እና ከዚያ በላይ በባንኩ ያገለገሉ ሰራተኞች ከባንኩ የዳይሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢ ኢንጂነር ሳምራዊት ጌታመሳይ እጅእውቅናና ሽልማት ተቀብለዋል፡፡ በተጨማሪም ባንኩ ለ10 የበጎ አድራጎት ድርጅቶች ለእያንዳንዳቸው 1.5 ሚሊዮን ብር በድምሩ 15 ሚሊዮን ብር ድጋፍ ተደርጓል፡፡ ድጋፍ የተደረገላቸው የበጎ አድራጎት ድርጅቶች መቄዶንያ የአረጋውያንና የአዕምሮ ህሙማን መርጃ ማዕከል፣ አወልያ እርዳታና ልማት ድርጅት፣ እዝነት የአካል ጉዳተኛ ህጻናትና ወላጆች መርጃ ድርጅት በኢትዮጵያ፣ ቢላሉል ሀበሺ የልማትና መረዳጃ ዕድር፣ ባቡል ኸይር በጎ አድራጎት ድርጅት፣ ይመለከተኛል በጎ አድራጎት ድርጅት፣ በኢትዮጵያ የልብ ህሙማን ህጻናት መርጃ፣ ሳሉ መረዳዳት የዐይነ ስዉራንና አካል ጉዳተኞች ማኅበር፣ የወደቁትን አንሱ የነዳያን መርጃ ማኅበር እና ጌርጌሴኖን የአዕምሮ ህሙማን መርጃ ማኅበር ናቸው፡፡

Read 1102 times