Saturday, 02 December 2023 19:38

በአማራ ክልል የተጣለው የኢንተርኔት እገዳ እንዲነሳ ጥሪ ቀረበ

Written by  መታሰቢያ ካሳዬ
Rate this item
(2 votes)

- ከ150 አገራት የተውጣጡ 300 የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች እገዳው እንዲነሳ ጠይቀዋል
  - የእገዳ ተግባሩ ከሌሎች የአፍሪካ አገራት በኢትዮጵያ የከፋ ነው ተብሏል
          
          በአማራ ክልል የተቀሰቀሰውን ግጭት ተከትሎ በመንግስት የተወሰደውን የኢንተርኔት እገዳ እርምጃ በመቃወም መንግስት ያለምንም ቅድመ ሁኔታ እገዳውን እንዲያነሳና መደበኛ የኢንተርኔት አግልግሎት መስጠቱን እንዲቀጥል ከ150 አገራት የተውጣጡ 300 የሚሆኑ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች ጥሪ አቀረቡ። በመንግስት የሚወሰደው የኢንተርኔት እገዳ ተግባሩ ከሌሎች የአፍሪካ አገራት ሁሉ በኢትዮጵያ የከፋ ነው ብለዋል።
የኢንተርኔት እገዳውን በማውገዝ መግለጫ ያወጡትና መንግስት ኢንተርኔት አገልግሎት እገዳውን በአስቸኳይ እንዲያነሳ ጥሪ ያቀረቡት ድርጅቶች በጋራ ባወጡት መግለጫ የአፍሪካ ህብረት ድርጅት መሰረታዊ የሆኑ ሰብአዊ መብቶች በኢትዮጵያ ውስጥ እንዲከበሩና ስራ ላይ እንዲውሉ ግፊት ሊያደርግ ይገባል ብለዋል። ጋዜጠኞች ስራቸውን ያለአንዳች ቁጥጥር ተዘዋውረው እንዲሰሩና ሰብአዊ መብቶቻቸው እንዲከበሩ የአፍሪካ ህብረት ተፅዕኖ ሊያደርግ እንደሚገባም ማህበራቱ በመግለጫቸው አስታውቀዋል።  ከ150 የዓለም አገራት የተውጣጡ 300 ለሰብአዊ መብቶች መከበር የሚሟገቱ አለም አቀፍ ድርጅቶች በጋራ ባወጡት መግለጫ ካለፈው ሀምሌ ወር ጀምሮ እስከአሁን በኢትዮጵያ በአማራ ክልል የኢንተርኔት መስመሮች መዘጋታቸውን አመልክተው ይህ የሚደረገውም በአካባቢው የሚፈፀሙ ወንጀሎች በድምፅና በምስል በማስረጃነት ቀርበው ወንጀለኞቹ ህግ ፊት እንዳይቀርቡ ለማድረግ  እንደሆነም አመልክተዋል።



Read 1336 times