Sunday, 10 December 2023 20:10

ስለጨቅላሽ በጥቂቱ

Written by  ፀሐይ ተፈረደኝ ከኢሶግ
Rate this item
(1 Vote)

ለለጨቅላሽ በጥቂቱ የሚለውን በርእስነት የተጠቀምንበትን አባባል ያገኘነው ዶ/ር ሙሉአለም ገሰሰ ተሰማ በ2015 ከሳተሙት ባለ 134/
ገጽ መጽሐፍ ላይ ነው፡፡ ዶ/ር ሙሉአለም ገሰሰ የሃምሳ አለቃ ገሰሰ ተሰማ ልጅ ሲሆኑ አባታቸው በደርግ ስርአት ከሱማሌ ጋር በነበረው ጦርነት
ምክንያት በመሰዋታቸው ወደ ኩባ ተልከው ህክምናን አጥንተው የተመለሱ የህጸናት በተለይም ደግሞ የጨቅላ ህጻናት ህክምና እስፔሻሊስት
ናቸው፡፡ዶ/ር ሙሉአለም በአሁኑ ወቅት የሙሉ ጂ ሆስፒታል ባለድርሻ ሲሆኑ የሚጋ ሩትም ከባለቤታቸው ከዶ/ር ገመቺስ ማሞ ጋር ነው፡፡ ሙሉ
ጂ ማለት ሙሉአለምና ገመቺስ ከሚሉት ስሞች የመጀመሪያ ፊደል ተወስዶ የተመሰረተ ነው፡፡ ዶ/ር ሙሉአለም የጻፉት መጽሐፍ ባለ ዘጠኝ ምእራፍ
ሲሆን የዶ/ር ሙሉአለም የህይወት ታሪክ በመግቢያ መልክ ሰፍሮበታል፡፡ ለክፍል አንድ ስራችንእንዲሆነን ያስቀደምነው ወደ ህጻናት ሐኪምነት
እንዴት እንደገቡ እንዲገልጹልን ሲሆን መጽሐፉን ከእጃቸው ተቀብለን ስናገላብጥ መግቢያው ላይየነገሩንን አገኘነው፡፡ እንዲህ ይላል፡፡ ‹‹….እኔ ጨቅላ
የነበርኩ ከጨቅላነቴ ጀምሮ የሆስፒታል ጠረን ያልተለየኝ፤ህጻን ሆኜ ያደኩኝ፤ከልጅነቴ ጀምሮ ህጻን ልጅን የምወድ፤ከእህትና ከወንድሞቼ አንስቶ
ብዙ ልጅ እና የልጅ ልጅ ያሳደኩኝ ነኝ፡፡ ሃኪም ከሆንኩኝ ጀምሮ ላለፉት 37 አመታት እና እስከ አሁንም ድረስ ጊዜዬን ያሳለፍኩትከህጻናት ጋር ሲሆን የኔን ልጆች ጨምሮ እስከልጅ ልጅ ድረስ በመድረስ አሁን ያለሁበት ቦታ ላይ እገኛለሁ፡፡ በ37 አመታት ውስጥ ያከምኳቸውልጆች በተራቸው ልጆች ወልደው፤ ግመሹም ሃኪም ሆ ኖ ግ ማሹም በ ተለያየ ሙ ያ ተ ሰማርቶ በሀገርም ውስጥ ሆነ ከሀገር ውጭ በመሆንሰላምታቸውና ፍቅራቸው ሲደርሰኝ ከመደሰት በላይ እግዚአብሔርን በጣም አመሰ ግናለሁ፡፡ በህይወት ኖሬ ይህን ማየቴንም በጣም እወደዋለሁ፡፡ በጣም በቁጥርም ብዙ የሚሆ ኑት ያከምኳቸው ልጆች በተራቸው ወልደው ልጆቻቸውን እንደገና እያከምኩ እገኛለሁ፡፡ እግ ዚአብሔር የልጅ ፍቅር ሲሰጠኝ ለኔ ከምንም ነገር በላይ ነው፤እንደ ፀጋም አየዋለሁ፡፡ ምክንያ ቱም ልጆች አስመሳዮች አይደሉም፤ንጹሆች ናቸው፤እንዳደረጉአቸው የሚሆኑ ወደ ተቀደደ ላቸው ቱቦ የሚፈሱ
ናቸው፡፡ እ ናም ክ ፋትንና ጭ ካኔን አ ያውቁም፡፡ በዚህ የዋህነታቸው በጣም ያስደስቱኛል፡፡እግዚአብሔርም ለምን እንደሚወዳቸው ይገባኛል፡፡ በጠቅላላው ልጆች ፍቅር ናቸው፡፡ እኔም ምነውህጸን ሆኜ በቀረሁ ብዬ እንድመኝ ያደር ጉኛል፡፡ ሌላው ትንሽ ለየት የሚያደርገኝ የሚመስለኝከልጅነቴ ጀምሮ በአስተዳደጌ እናቴም ሆነች አባቴሰው የሚባለውን ፍጡር የሚወዱና የሚያከብሩ ነበሩ ብለዋል፡፡
 ዶ/ር ሙሉአለም ከጻፉአቸው ውስጥ ያተኮርንበት አንዱ ነገር የሚከተለው ነው፡፡ እንደዚህ ይላል፡፡… አንድ ነገር ሳልናገር ባልፍእግዚአብሔርም ሆነ የኔን መኖር የሚመኝናየሚጸል ይልኝ ሰው ሁሉ ቅር የሚለው ይመስለኛል፡፡ እሱም በህይወቴ በሀገርም ሆነበሰው ሀገር በጣም ለቁጥር በሚሰለች መልኩ ብዙ ጊዜያቶች የቀዶ ጥገናም ሆነ የከባድ የውስጥ ደዌ በሽታን ታክሜ አሳልፌአለሁ፡፡ ብዙዎቹ ከሞት የሚያደርሱ የነበሩና በእግዚአብሔር ተዓምር እና
እሱ በላካቸው አስገራሚ ሃኪሞች ፤እንዲሁም ከቤተሰቤ ጀምሮ የኔን መኖር የሚፈልጉ ሰዎች
ፀሎት ተርፌአለሁ፡፡ግን በዋናነት የሚመስለኝ እና ሰውም የሚመሰክረው የህጻናቱ አምላክ ነው እስከ አሁን ያቆየሽ ይሉኛል፤እኔም አምናለሁ፡፡
የተረፍኩት እግዚአብሔር እንድሰራ ያዘዘኝን ስራ ስላልጨረስኩ ነው ብዬ ስለማምን ትዛዙን ተቀብዬ እንደእርሱ ፈቃድ በሙሉ ጉልበቴ እያገለገልኩ
እገኛለሁ…›› ብለዋል ዶ/ር ሙሉአለም ገሰሰ፡፡ ታሪካቸውን ሲያወጉን ከጠቀሱአቸው አብዛኛዎቹን ….ስለጨቅላሽ በጥቂቱ…በሚልርእስ ጥቅምት 2015/ከታተመው መጽሐፋቸውላይ በመጠኑ ታነቡት ዘንድ አጋርተናችሁዋል፡፡ ዶ/ር ሙሉአለም ገሰሰ በገጠማቸው ሕመምምክንያት በተለይም ለአራት ጊዜ ከሞት እንደተነሱ የሚያስቆጥራቸው ያህል ታመው የነበረ ሲሆን ከእነዚህም ለዘጠና ደቂቃ የልብምት መቋረጥና በኮሮና ምክንያት የገጠማቸው
ከፍተኛ ህ መም ተ ጠቃሽ ና ቸው፡፡ እ ሳቸውም ህጻናቱን በሚመለከት ገና ያልሰራሁዋቸው ብዙነገሮች ስላሉ እግዚአብሔር እንድሞት አልፈቀደም
ብለዋል፡፡ ዶ/ር ሙሉአለም ገሰሰ የህትመት ወጪውን መሸፈን ስላቃታቸው ተጽፎ አልቆ የተቀመጠ መጽሐፍም አሳይተውናል፡፡ ይሄ ሁሉ
ልፋትና ድካም ስለ ጨቅ ላዎች እንዲሁም ህጻናት በተጨማሪም ስለእናትነት እናቶችንና ባለሙያዎችን ለማስ ተማር የሚረዳ እንዲሁም ማንኛውም ሰው የትም ሆኖ ስለህጻናቱ እውቀቱን እንዲ ያዳብር ለመር ዳት ነው፡፡ ዶ/ር ሙሉአለም በኩባ የህክምና ትምህርታቸውን በማጠናቀቅ ላይ እያሉ
በሐገራቸው ጥሪ መሰረት አምስተኛ አመት ላይ ሳይመረቁ አቋርጠው መጥተው በአገራቸው ጥቁርአንበሳ እና የካቲት 12/ሆስፒታል የመጀመሪያውን
ወይም Internship ከጨረሱ በሁዋላ የኩባ አስተማሪ ባሉበት በአገር ውስጥ ለምርቃት የበቁ የጠቅላላ ሐኪም ነበሩ፡፡ በጊዜው ከባለቤታቸው
ጋር በጠቅላላ ሐኪምነት ወደተለ ያዩ አካባዎች በመሄድ ባል(ዶ/ር ገመቺስ) ትልልቅ ሰዎችን ሚስት(ዶ/ር ሙሉአለም) ደግሞ ህጻናትን በማከም
ከፍተኛ አገልግሎት ሰጥተዋል፡፡ ዶ/ር ሙሉአለም ህጻናቱን ስ ለሚወዱ የ ጠቅላላ ሐ ኪም ቢ ሆኑም ምንጊዜም ህክምና የሚሰጡት ለህጻናቱ ነበር፡፡ ያ ልምዳቸው በየካቲት ሆስፒታል ሲመደቡም ቀጥሎአል፡፡ በየካቲት ሆስፒታል ያሉ ጠቅላላ ሐኪሞችበአንድ ቦታ ተወስነው ሳይሆን በመዙዋ ዙዋር
እንዲሰሩ ነበር የሚደረ ገው፡፡እኔ ግን እግዚአብሔር ፈቅዶልኝ በየካቲት 12 ሆስፒ ታል ለአስራ አምስት አመት ስቆይ ለህጻናት ሕክምና እየሰጠሁ ነበር፡፡ በዚያ ቆይታዬ እን ድም ቀን እኔ እራሴን እስፔሻሊስት አ ይደለሁም ብ ዬ አ ስቤ አ ላውቅም ነ በር፡፡ ምክንያቱም የተኙትንም በተመላላሽ ለህክምና የሚቀርቡትንም በቀን እስከ 80/ሰማንያ ህጻናት ድረስ ህ ክምና ስ ሰጥ ም ንም አ ይታክተኝም ነ በር፡፡ ነገር ግን አንድ ቀን ለካስ ጠቅላላ ሐኪም እንጂ የህጻናት ህክምና እስፔሻሊስት አይደለሁም የሚለው ገባኝ፡፡ ግን አላዘንኩም፡፡ መፍትሔውንመፈለግ እንደሚገባኝ አመ ንኩ፡፡ ከባለቤቴ ዶ/ር ገመቺስ ጋር ተነጋገርኩ፡፡ እሱም የወለድ ናቸውን ሁለት ልጆች በኃላ ፊነት ተንከባክቦ እንደሚቆየኝቃል ገብቶልኛ፤ኩባ የተማርኩበት ዩኒቨርሲቲም ፈቅዶልኝ ልጆቼን ለባለቤቴ ትቼ እስፔሻሊስት ሆኜ ለመመለስ ሄድኩ፡፡ እግዚአ ብሔር ይመስገንናየህጻናት ሕክምና በተለይም የጨቅላ ህጻናትሕክምና እስፔሻሊስት ሆኜ ተመለስኩ ብለዋል፡፡እዚህ ላይ ሳንጠቅስ የማናልፈው የባልተቤታቸውንአስተዋጽኦ ነው፡፡ ዶ/ር ገመቺስ ማሞ የውስጥ ደዌ እስፔሻሊስት ለብዙ ባሎች ይህንን በጎ ተግባር እንዲ ያከናውኑ ምሳሌ ይሆናሉ የሚል እምነት አለን፡፡
     ዶ/ር ሙሉአለም ገሰሰ ለእስፔሻሊስትነት ወደ ኩባ ተመልሰው ከመሄዳቸው በፊት ለአመ ታት ህጻናቱን ሲያክሙ ያዩአቸው ጉድለቶች ነበሩ፡፡ በተለይም በጨቅላ ህጻናት ማቆያና ህክምና ዙሪያ፡፡ ከተወሰኑ ጊዜያት በፊት እናቶች ክትትል የሚያስፈልገው ህጻን ሲወልዱ ወደ ጥቁር አንበሳ
ሆስፒታል መሄድ ግድ ነበረባቸው፡፡ ስለዚህ ይህ ለምን ይሆናል በሚል በአገር ውስጥ ያሉ የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር አመራሮችን በማሳመን፤ድጋፍ
የሚያደርጉ አካላ ትን በማስተባበር የጨቅላ ህጻናት ማቆያ እና መንከባከቢያ በአገር አቀፍ ደረጃ እናቶች በሚወልዱ ባቸው ሆስፒታሎች እንዲኖር ለማድረግ ብዙ ሰርተዋል፡፡ ዚህ እ ንዲረዳም በ የሆስፒታሉ ለ ህጻናት ሕክምናው ቅርብ የሆኑትን ነርሶች ከማሰልጠን ጀምሮ የጨቅላዎችን ማቆያ ክፍሎች የማደራጀትን ስራ በሚችሉት ሁሉ ተወጥተውታል፡፡ ዶ/ር ሙሉአለም የሚመሩት መክሊት የሚባል የስልጠና ማእከል አለ፡፡ መክሊት ምንድነው
የሚያሰለጥነው ለሚለው ጥያቄአችን የዶ/ር ሙሉአለም ምላሽ የጀመረው መነሻውን ከማስ ረዳት ነበር፡፡ እናም ከላይ ያስነበብናቸሁ የጨቅላ
ህጻናትን ማቆያ በየሆስፒታሉ እንዲኖር ማስቻል እና በስራው ላይ የሚኖሩ ነርሶችን ማሰልጠን የጀመረው አካሄድ አድጎ መክሊትን ለመመስረት መብቃቱን ነው የተረዳነው፡፡ ጨቅላ ህጻናት ለመሰበር ወይንም ለመጎዳት፤ለማ ለፍ በጣም ቀላል ናቸው እንደ ዶ/ር ሙሉአለም ገለጻ፡፡ በየሆስፒታሉ ጨቅላ ህጻናቱን በሚ መለከት የጎደሉ ነገሮችን እንዲሟሉ ከማድረግና ባለሙያዎችን የማሰልጠን ነገር ከሆስፒታል ደረጃ ዝቅ ብሎ በጤና ጣቢያዎች እንዲዳረስ ለማድረግም ተችሎአል፡፡ የማሰልጠኛ ዶክመንቱም በጤና ጥበቃ ስም እንዲሆን ተደርጎ እንደ መመሪያ በማገልገል ላይ ነው፡፡ እንግዲህ የመክሊት ስልጠናመጀመር ከእነዚህ ጥረቶች በሁዋላ የመጣ ነው፡፡ላደረግሁ ዋቸው እንቅስቃሴዎችም በ2015 የአመቱበጎ ሰው ተብዬ ተሸልሜአለሁ ብለዋል ዶ/ር፡፡
ቀደም ሲ ል በ መንግስት ሆ ስፒታሎች ወ ይንም ጤና ጣቢያዎች ለህክምና የሚቀርቡትን በተለ ይም ቤተሰቦቻቸው አቅም ያልነበራቸውን መከታተል
የሚገኝበት አሰራር ያለ ሲሆን ለካስ በግል ተቋምም እነዚያን አቅም የሌላቸውን ህጻናት መርዳት ይቻላል የሚለውንም የተመለከ ትኩበት እና ስራ
ላይ ያዋልኩትም ስለሆነ በጣም ደስተኛ ነኝ ብለዋል ዶ/ር ሙሉአለም ገሰሰ የህጻናት በተለይም የጨቅላ ህጻናት ሕክምና እስፔሻሊስት፡፡

Read 532 times