Sunday, 10 December 2023 20:16

ከቫለንሺያ እስከ ፓሪስ 2024 የኦሎምፒክ ማራቶን

Written by  ግሩም ሰይፉ
Rate this item
(0 votes)

 ፓሪስ ለምታስተናግደው 33ኛው ኦሎምፒያድ 230 ቀናት የቀሩ ቢሆንም የኬንያ አትሌቲክስ በሁለቱም ፆታዎች 20 አትሌቶችን በጊዜያዊነት
ለማቶን ቡድኑ ምርጫ መመልመሉን ይፋ አድርጓል፡፡ በሌላ በኩል ባለፈው ሳምንት የተካሄደው የ2023 ቫለንሺያ ማራቶን ኢትዮጵያውያን አትሌቶች
የበላይት ያሳዩበት ሲሆን ለኦሎምፒክ የኢትዮጵያ ማራቶን ቡድን የሚያሳቸው ሆኗል።
          ለዓለም ሪከርድ 1ሚሊዮን ዮሮ
ቫለንሺያ ላይ በኢትዮጵያውያን ተሳትፎ ከፍተኛ እምነት የነበራቸው የአትሌቲክስ ባለሙያ ፓኮ ቦራሮ ይባላሉ። በቫሌንሺያ ማራቶን የውድድር ዲያሬክተር ሆነው ላለፉት 25 ዓመታት የሰሩ ሲሆን፤ ዘንድሮ ከተቻለ የዓለም ሪከርድ ወይንም ፈጣን ሰዓቶች እንዲመዘገቡ ከፍተኛ ጥረት አድርገዋል። ሲሳይ ለማ ከምንጊዜም ፈጣን ሰዓቶች 4ኛውን ማስመዝገቡ፤ በቀነኒሳ በቀለ ከ40 ዓመት በላይ የዓለም ክብረወሰን መገኘቱና በሴቶች ምድብ የኢትዮጵያ አትሌቶች ከ1-3 መውጣታውና በሌሎችም ምርጥ ሰዓቶች መመዝገባቸው አስደስቷቸዋል።ሲሳይ ለማ የቫሌንሺያ ማራቶን ያሸነፈው 2:01:47 በሆነ ሰዓት የቦታው ሪከርድ አስመዝግቦ ነው። ከድሉ በኋላ በሰጠው አስተያየት “ቫሌንሺያ ውስጥ በማሸነፌ ጥሩ ስሜት ይሰማኛል። ውድድሩን ሳጋምሰው በሪከርድ ፍጥነት እየሮጥኩ መሆኔን ተገነዘብኩ። እናም የማሸንፍበት ጥንካሬ እንዳለኝ ተረዳሁ። በቫሌንሺያስሮጥ ለመጀመሪያ ጊዜዬ ነበር። የቦታ ሪከርዱንአስመዝግቤ በማሸነፌ በጣም ደስተኛ ነኝ። በጣምፈጣን የጎዳና ላይ ሩጫ ነው” ብሏል።በሴቶች ምድብ ወርቅነሽ ደገፋ ያሸነፈችውርቀቱን 2፡15፡51 በሆነ ሰዓት በመሸፈን ሲሆንአልማዝ አያናና ሕይወት ገብረኪዳን 2ኛና 3ኛደረጃ አግኝተዋል። “በመጀመሪያ የውድድሩን
ተሳትፎ በማግኘቴ አመሰግናለሁ። በውጤቱም በጣም ደስተኛ ነኝ። ከ30 ኪሎ ሜትር ጀምሮ በራሴፍጥነት ውድድሩን መግፋት ጀመርኩ። ተቀናቃኞቼን
ሳልመለከት ለመሮጥ ወሰንኩ ። አሯሯጮችእንደምጠብቀው አልነበሩም።” በማለት ከውድድሩበኋላ ተናግራለች።ቀነኒሳ በቀለ በቫለንሺያ ማራቶን
ያስመዘገበው ሰዓት 2:04:19 ከ40 ዓመት በላይ የዓለም ማስተርስ ማራቶን ክብረወሰን ሆኖ ተመዝግቧል። የኢትዮጵያ ማራቶን ሪከርድን በ2:01፡
41 በሆነ ሰዓት እንደያዘም ይታወቃል። “በቫለንሺያማራቶን ላይ ያለኝን አቅም ተጠቅሜ በመሮጤናውጤት ስላገኘሁ በትም በጣም ተደስቻለሁ። 2፡04
በሆነ ሰአት 4ኛ ሆኖ ማጠናቀቅ ለወደፊት ሩጫዎችተስፋን ሰጥቶኛል። ያለ ደጋፊዎቼ ይህን ማድረግአይቻልም ነበር። ስፖንሰሬ ANTA ጋር ለሚመጣውጓጉተናል። ቫለንሺያ አስደናቂ ናት። ይህን ያህልደስታ አገኛለሁ ብዬ አስቤ አላውቅም። የመሮጫጓዳናዎቹ በጣም ምቹ ናቸው፤ ወደፊት የአለምሪከርዶችን መስበር የሚቻልበት እድል መኖሩንአጥብቄ አምናለሁ። የዚህ አስደናቂ ጉዞ አካልስለሆናችሁ ሁላችሁንም አመሰግናለሁ። የማይናወጥ
ድጋፋቹ እንድቀጥል ያደርገኛል።” ሲል ከውድድሩበኋላ አስተያየት ሰጥቷል። የቫለንሺያ ማራቶን የበላይጠባቂና ስፖንሰር አድራጊ ጆዋን ሮይግ ከውድድሩ
በፊት በሁለቱም ፆታዎች የዓለም ሪከርድ የሚመዘገብከሆነ 1 ሚሊዮን ዮሮ ለመሸለም ቃል ገብተውነበር። የዓለም ሪከርድ በቀጣይ የውድድር ዘመናት
ሊመዘገብበት እንደሚችል ፖኮ ቦራሮዎ እምነት አላቸው። ያለፉትን 13 ዓመታት ከ304 አባላት በላይያሉትን የዓለም አቀፉ የጎዳና ላይ ሩጫዎች ማህበርAIMS በፕሬዝዳንትነት እየመሩ የሚገኙት ፓኮየዓለም አትሌቲክስ ማህበር የጎዳና ላይ ሩጫዎችኮሚሽን የቦርድ አባልም ናቸው።
      በኦሎምፒክ ማራቶን ሜዳሊያዎችን የመጠቅለል እቅድ በኬንያ
ፓሪስ ለምታስተናግደው 33ኛው ኦሎምፒያድ235 ቀናት ሲቀሩ የኬንያ አትሌቲክስ በሁለቱምፆታዎች 20 አትሌቶችን በጊዜያዊነት ለማራቶንቡድን መመልመሉን ይፋ አድርጓል፡፡ በኬንያአትሌቲክስ የውድድር ዲያሬክተር የሆኑት ሚስተርፓውል ሙታዊ በማራቶን ለኦሎምፒክ ሙሉዝግጅት መጀመሩን ጊዜያዊ ቡድኑን በመዘርዘርሲያስታውቁ፤ የኦሎምፒክ ኮሚቴው ፕሬዝዳንትፖልቴርጋት ፓሪስ ላይ በማራቶን የሜዳልያሰንጠረዥን እንጠቀልለዋለን ብሏል። በሁለቱምፆታዎች የተመለመሉት 20 አትሌቶች ከወር በኋላወደ 10 “ይቀነሳሉ። ኬንያ ባለፈው ኦሎምፒክበሁለቱም ፆታዎች በማሸነፏ አራት አትሌቶችንማሰለፍ ትችላለች። ስምንት ዋና ተወዳዳሪዎች ሁለትተጠባባቂ አትሌቶች በመጨረሻው እንደሚገቡናዝርዝር ልዩ ዝግጅት እንደሚያደርጉ ተገልጿል።የኬንያ አትሌቲክስ በመግለጫው በ2016 ሪዮኦሎምፒክ ላይ እንዲሁም በ2020 ቶኪዮ ኦሎምፒክላይ በሁለቱም ፀታዎችታዎች ማሸነፋቸውን
አስታውሶ። ፓሪስ 2024 ላይ ይህን ከፍተኛ ውጤትለመድገም ተስፋ ማድረጉን አመልክቷል። የማራቶንቡድኑ ወደ ካምፕ በመግባት ወይንም በተናጠል
በየልምምድ ስፍራቸው ዝግጅት እንዲያደርጉምአሳስቧል፡፡ በአትሌቶች ምርጫው የዓመቱ ፈጣንሰዓቶች ደረጃ፤ በትልልቆቹ ማራቶን ማሸነፍ፤ የዓለም
አቀፍ ውድድር የተሳትፎ ፍላጎት እና ለአገር ውጤትበቡድን የመስራት ብቃት መስፈርቶች እንደነበሩምተገልጿል፡፡ በኬንያ የኦለሎምፒክ ማራቶን ጊዜያዊ
ቡድን ከተያዙ 10 አትሌቶች መካከል ኤልዊድ ኪፕቾጌይገኝበታል፡፡ በ2016 ሪዮ ዲጄነሮ እና በ2020 ቶኪዮላይ የኦሎምፒክ ክብሮችን አከታትሎ የወሰደው ኤሊውድ የፓሪስ ተሳትፎን ያገኘው በቀጥታየኦሎምፒክ ሻምፒየን በመሆኑ ነው። አምስተኛውን የኦሎምፒክ ተሳትፎ እንደሚያደርግም ታውቋል።ሌላው በቡድኑ የተያዘው ምርጥ አትሌት በ2023 የለንደንና የቺካጎ ማራቶኖችን ያሸነፈውንና የዓለምክብረወሰንን ያስመዘገበው ኬልቪን ኪፕቱም ነው፡፡የበርሊን ማራቶን አሸናፊው አሞስ ኪፕሮቱ፤ በቺካጎእና በቦስተን ማራቶኖች 3ኛ ደረጃ ያገኘው ቪንሰንትኪፕሞይና ለ3 ጊዜያት የዓለም ግማሽ ማራቶንሻምፒዮን ለመሆን የበቃው ጂዮፍሪ ኪምዎሩርበጊዜያዊው ዝርዝር ተጠቅሰዋል። በሴቶች ምድብደግሞ በኦሎምፒክ ማራቶን ሻምፒዮንነት ክብሯንለማስጠበቅ የምትገባው ሮዝማሪ ዋንጂሩ ናት።የዓለም ግማሽ ማራቶን የወቅቱ ሻምፒዮን ፔሬስጄፕቼሪር፤ የኒውዮርክ ማራቶንን ያሸነፈችው ሄለንኦብሪ እና የዓለም ሪከርድ ባለቤት የነበረችው ብርጊድም ይገኙበታል፡፡
            የኢትዮጵያን የኦሎምፒክ ክብር ፓሪስ ላይ ለመመለስ
የፓሪስ ኦሎምፒክ ዛሬ ላይ ልክ 230 ቀናት ሲቀሩት በኢትዮጵያ የኦሎምፒክ ማራቶን ቡድን
አነማን ይካተታሉ? ብሎ ለማንሳት ይከብዳል፡፡ በቫለንሺያ ማራቶን ኢትዮጵያውያን አትሌቶችካስመዘገቡት ውጤት ጋር ተያይዞ ግን ሁኔታውንመመልከት አስፈላጊ ነው። በተለይም ቀነኒሳለኦሎምፒክ ተሳትፎ የሚያበቃውን ሚኒማ አሳክቷል ይመረጣል ወይ የሚለው አጀንዳ በትልልቅሚዲያዎች መነሳቱም አልቀረም። በኬንያ ያለውንዝግጅት ኢትዮጵያ ላይ መጠበቅ የማይታሰብ ነው፡፡ የዓለም ሻምፒዮና እና ኦሎምፒክ ሲቃረብ በተለይ በማራቶን ቡድን ምርጫ ላይ ውዝግብ የተለመደ ይመስላል፡፡ የ2023 የውድድር ዘመንን የማራቶን ውጤት ከግምት ውስጥ ካስገባን በፓሪስ ኦሎምፒክ2024 ላይ በኢትዮጵያ በድን ለመካተት እድልያላቸውን አንዳንድ መጥቀስ ይቻላል። ታምራት ቶላበኒውዮርክ ማራቶን አሸናፊነቱ እንዲሁም ትግስትአሰፋ በበርሊን ማራቶን አሸናፊነቷ እና የዓለም ማራቶንሪከርድን በማስመዝገቧ የመመረጣቸው ዕድል ሰፊነው፡፡ ከሁለቱ አትሌቶች ባሻገር በሻለንሺያ ማራቶን
የተመዘገበው ውጤት በአትሌቶች ምልመላውላይ ተፅእኖ መፍጠሩ አይቀርም፡፡ ምክንያቱም በቫለንሺያ ሟራቶን የተመዘገቡት ፈጣን ሰዓቶችየዓለም አትሌቲክስ ማህበር በሚያወጣው ደረጃ ላይ የተቀመጡ በመሆናቸው ነው፡፡ የዓለም አትሌቲክስማህበር ላይ በተቀመጠው የዓመቱ የማራቶን ፈጣን
ሰዓቶች ደረጃ መሰረት የቫለንሺያ ማራቶንን ያሸነፈችው ወርቅነሽ ደገፋ በ2፡15፡51 ከዓለም አራተኛ ደረጃ፤በሻለንሺያ ማራቶን ሁለተኛ ደረጃ የነበራት አልማዝ አያና በ2፡16፡22 አምስተኛ ይዘዋል፡፡ በዓመቱ የዓለም የማራቶን ፈጣን ሰዓት ደረጃ ላይ መገርቱ አለሙስምንተኛ፤ ህይወት ገብረኪዳን 11ኛ፤ ሩቲ አጋ 12ኛ፤ መሰረት በለጠ 13ኛ ላይ ይገኛሉ። በወንዶች ምድብ ደግሞ ሲሳይ ለማ በሻለንሽያ ማራቶን ባስመዘገበውሰዓት ከዓለም ሁለተኛ ደረጃ ላይ ሲሆን፤ በበርሊንማራቶን ሶስተኛ ደረጃ ያለው ታደሰ ታከለ 6ኛ ደረጃ፤በሻለንሺያ ማራቶን 2ኛ ደረጃ ያገኘው ዳዊት ወልዴ8ኛ እንዲሁም ቀነኒሳ በቀለ በዓለም የማራቶን ፈጣን ሰዓቶች ደረጃ 13ኛ ላይ የሚገኙ ናቸው፡፡

Read 203 times